Degineh Bogale/ደግነህ ቦጋለ

Degineh Bogale/ደግነህ ቦጋለ ይህ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ደግነህ ቦጋለ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው።
ገፁን በመውደድ ፣ በመከተልና ሀሳብ አስተያየቶን በማጋራት ይወዳጁ።

20/08/2026


‎ሄሎ(Hello'o)

‎ሄሎ አንድነትን እና መተጋገዝን የሚያጠናክር ምርጥ የመድረክ ስራ ነው ።

ምድሪቷ አፍርታለች ኪሶችም በብር ተትረፍርፏል የሚሉ ተጨማሪ ዓሳቦችን ይዟል ።

ድምጻዊ ካሳሁን ለማ

ነሀሴ 14/2018 ዓ.ምየውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የሀገርን ገጽታና ክብር በሚያስጠብቅ መልኩ ሊመራ ይገባል- አቶ ይሁን አሰፋ (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ)
20/08/2026

ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የሀገርን ገጽታና ክብር በሚያስጠብቅ መልኩ ሊመራ ይገባል- አቶ ይሁን አሰፋ (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የስራ እድል ፈጠራ ማዕከል ማድረግ የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት እየተሰራ ነው:-አቶ ይሁን አሰፋ
20/08/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የስራ እድል ፈጠራ ማዕከል ማድረግ የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት እየተሰራ ነው:-አቶ ይሁን አሰፋ

20/08/2026
«የባህልና ቱሪዝም እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ»​የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ግብ ስምምነት...
18/08/2026

«የባህልና ቱሪዝም እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ»

​የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ግብ ስምምነት መድረክ ተካሂዷል።

በ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በጥልቀት ተገምግሟል።

የክልሉን የተፈጥሮ፣ የባህልና የታሪክ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም ለኢኮኖሚ እድገት ለማዋል የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ናቸው ።

“ሀሮሜ”፣ በኦሮሚያ ክልል ለአርሶ አደሮች ምቹና ዘመናዊ መኖሪያን የመፍጠር ሒደትየመደመር መንግሥት ብዙ የመልማት አቅም እያላቸውና ተረስተው የቆዩ የገጠር አካባቢዎችን በማልማት ተጨባጭ ውጤት...
14/08/2026

“ሀሮሜ”፣ በኦሮሚያ ክልል ለአርሶ አደሮች ምቹና ዘመናዊ መኖሪያን የመፍጠር ሒደት

የመደመር መንግሥት ብዙ የመልማት አቅም እያላቸውና ተረስተው የቆዩ የገጠር አካባቢዎችን በማልማት ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡

ለዚህም በከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በገጠር አካባቢዎች በመተግበር የአርሶ አደሮች የኑሮ ዘይቤ እንዲሻሻል እያደረገ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል በዚሁ እሳቤ መሠረት “ሀሮሜ” በሚል ስያሜ በተሰየመ መርሐ ግብር ገጠርን ወደ ዘመናዊነት ለማሸጋገር በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡

ሀሮሜ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ገጠራማ ቀበሌዎችን የለውጥ ማዕከላት ለማድረግ የታቀደ መርሐ ግብር ነው፡፡

ሀሮሜ ፕሮግራም የግንባታ ሥራ ብቻ አይደለም፤ የልማት አስተሳሰብን መቀየርና ገጠርን ወደ አዲስ የልማት ደረጃ ማሸጋገር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

ዘመናዊነት ማለት የልማት መሠረተ ልማቶችን፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶችን፣ የፋይናንስና የፍትሕ ተቋማትን፣ ገበያን እንዲሁም አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን የምርታማነት ማዕከል ለማድረግና ወደ ሕዝቡ ማድረስን ያካትታል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሀሮሜን ሲመሠርት፣ የመንግሥት አገልግሎት፣ መንገድ፣ ውሃ፣ ኃይል፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ጣቢያዎች፣ መድኃኒት ቤቶች፣ ባንኮችና ሌሎች አገልግሎቶችን ወደ አርሶ አደሮች መኖሪያ አካባቢ ለማድረስ ዓላማ አድርጎ ነው፡፡

ሀሮሜ በገጠር፣ በከተማና በመንግሥት መካከል ያለውን ትስስርና ግንኙነት በአዲስ መንገድ ለመገንባት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡

የገጠር ሽግግር ማለት ግብርናን ብቻ ማሻሻል ሳይሆን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወትንም አብሮ ማሸጋገር ይጠይቃል፡፡

ገጠርን የጥሬ ዕቃ ምንጭ ብቻ አድርጎ ከመመልከት በመውጣት፣ የምርታማነት፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ የሙያና የፈጠራ እንዲሁም የብልጽግና ማዕከላት ወደማድረግ መቀየር ያስፈልጋል፡፡

መንግሥት በርካታ የገጠር መኖሪያ አካባቢዎችን ከከፋ ችግር በማውጣት፣ በሀሮሜ አማካይነት የሕዝቡ ኑሮ እንዲለወጥ በቁርጠኝነት እየሠራ ነው፡፡

በገጠር እየተገነቡ ያሉት የሀሮሜ ቤቶች ምቹ ከመሆናቸው በላይ የአርሶ አደሩ ሀብት እየሆኑ መምጣታቸውን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

መርሐ ግብሩ በአንድ በኩል የሕዝቡን ኑሮ በማሻሻል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኢንቨስትመንትና ከተማነትን በተግባር ላይ እያዋለ እንደሚገኝ ነው ያወሱት፡፡

ሀሮሜ የገጠር ሕዝብን ወደ ዘመናዊነት በማቅረብ ሁሉም ገጠራማ አካባቢዎች በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያደርግ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ የተገነቡት የሀሮሜ ማዕከላት ለምረቃ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

ሰዓሊ ጨብሳ መጫ በስነ ጥበቡ ዘርፍ እየሰራክ ላለው ስራ ከልብ እናመሰግናለን ።
13/08/2026

ሰዓሊ ጨብሳ መጫ በስነ ጥበቡ ዘርፍ እየሰራክ ላለው ስራ ከልብ እናመሰግናለን ።

13/08/2026

Address

Saja

Telephone

+251955055747

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Degineh Bogale/ደግነህ ቦጋለ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share