Fogera woreda communication affairs office

Fogera woreda communication affairs office ወቅታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ

በእስቴ ወረዳ እና በመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የጋራ የፀጥታ ምክክር መድረክ ተካሄደ፤​በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ ወረዳ እና የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅሮች የአካባቢ...
03/06/2026

በእስቴ ወረዳ እና በመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የጋራ የፀጥታ ምክክር መድረክ ተካሄደ፤

​በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ ወረዳ እና የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅሮች የአካባቢውን ዘላቂ ሰላምና የህብረተሰቡን ደህንነት በጋራ ለማስጠበቅ የሚያስችል የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ አስራቴ ባስተላለፉት መልዕክት ሰላም የልማት መሰረት በመሆኑ ሁለቱ የፀጥታ መዋቅሮች በቅንጅትና በትብብር መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አቶ ደስታ አክለውም ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን እንዲያከናውን የፀጥታ ስጋቶችን አስቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

​የ59ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አለሜ በበኩላቸው ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የፀጥታ መዋቅሩ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በቁርጠኝነት የማስቆምና የህግ የበላይነትን የማስከበር ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

​የውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና አባላትም የተሰጣቸውን ተልዕኮ በቅንጅት መፈፀም ውጤታማ እንደሚያደርግ በመጥቀስ፤ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በጋራ በመሙላት የህብረተሰቡን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

መረጃ:- እስቴ_ኮሙኒኬሽን

በ7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የላቀ ተሳትፎ ላደረጉ የዞኑ ነዋሪዎች የደቡብ ጎንደር ዞን  ምስጋና ቀረበ።የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ 7ኛውን ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በነቂስ ወጥቶ ...
03/06/2026

በ7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የላቀ ተሳትፎ ላደረጉ የዞኑ ነዋሪዎች የደቡብ ጎንደር ዞን ምስጋና ቀረበ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ 7ኛውን ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በነቂስ ወጥቶ ለመረጠ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።

በዞኑ 17 የምርጫ ክልሎች እና 1ሽህ 2 መቶ71 ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለፁት ዋና አስዳዳሪው የመንግስትን አስፈላጊነት የተረዳው ማህበረሰባችን ለተወጣው ታሪካዊ ኃላፊነት ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ህዝብ የፈፀመው ተሰልፎ መምረጥ፣ረጃጅም ሰልፎችን ታግሶ ላደረገው ተሳትፎ፣ በምርጫ ካርድ መንግስትን መምረጥ የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን የተረዳው ህዝባችን የምርጫ ማቴሪያል እንዲሟላ ከማድረግ ጀምሮ ላሳየው የላቀ ተሳቶፎ ዋና አስተዳዳሪው አመስግነዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ ከፀጥታውም አኳያ ያሳየው ጨዋነት የተላበሰ ተግባር ድርብ ኃላፊነት እንድንሸከም ያደረገ ኃላፊነት የተቀበልንበት ነው ያሉት አቶ ጥላሁን የተሰጠንን ክብር በሞራል በመስራት ህዝብን ለማገልገ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ህዝቡ በተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋሉት የፀጥታ ችግሮች ሳይበግረው መርጧል፣ ምርጫውን ለማደናቀፍ ሙከራ ያደረጉ ፀረ ሠላም ኃይሎች ያልበገረው ህዝብ መኖሩን በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ተረጋግጧል፣ የመድብለ ፓርቲን ስርዓት መሰረት ያደረገ ምርጫ መሆኑን አውቆ ታላቅ ተሳትፎ ያደረገበትና ከህዝብ ትልቅ ልምድ ያገኘንበት ሂደት ሆኖ አግኝተነዋልም ብለዋል።

መረጃ:- የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ  ምርጫ ማካሄዷንና በአማራ ...
02/06/2026

"በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ አሸንፈዋል" ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ትናንት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷንና በአማራ ክልልም ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ኾኖ መጠናቀቁን ገልጸዋል። በምርጫው ሀገር እና ሕዝብ ማሸነፋቸውን ጠቅሰዋል።

"ከጥንትም ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው የክልላችን ሕዝብ ትናንት ደግሞ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያለውን ቀናዒ ፍላጎት ለዓለም አሳይቷል፤ በአማራ ክልል ምርጫ ማካሄድ ድምጽ ከመስጠት ባሻገር ነው" ብለዋል።

በክልላችን ምርጫ እንዳይካሄድ፤ ዜጎች መብታቸውን እንዳይጠቀሙ፤ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠ መንግሥት እንዳይመሠርት፣ ክልሉ ሁልጊዜ በድህነት እና በግጭት ውስጥ እንዲኖር የሚፈልጉ የውይይት እና የሰላም ተቃራኒ ኃይሎች ብዙ ጥረት ማድረጋቸውንም አንስተዋል። "ይሁን እንጂ በሕዝባችን አስተዋይነት እና በጸጥታ ኃይላችን ጀግንነት እነርሱ የፈለጉት ሳይኾን ሕዝብ የፈለገው ኾኗል" ነው ያሉት።

የክልሉ ሕዝብ ትናንት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያሳየው ተሳትፎ፣ ጽናት እና ትዕግሥት የብልሃት እና የጥበብ ምንጭ መኾኑን ያሰመሰከረበት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ምርጫው ሕዝቡ ለፈተና የማይበገር፤ በዛቻ እና በማስፈራሪያ የማይሰበር፣ ለሰላም እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የትኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል ያሳየበት እንደሆነ አስታውቀዋል። "የክልላችን ሕዝብ በትናንትናው ምርጫ የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በሕዝብ ድምጽ እንጂ በኃይል አለመኾኑን ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈበት ነው" ብለዋል።

የአማራ ክልል ሕዝብ ሰላም ወዳድነቱን፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ፈላጊነቱን፤ በሕግና በሕዝብ ይሁንታ ለሚጸና መንግሥት ቀናዒነቱን በግልጽ እንዳሳየም አብራርተዋል። ለዚህ ደግሞ የከበረ ምስጋናዬን ከጥልቅ አክብሮት ጋር ማቅረብ እወዳለሁ ነው ያሉት።

"ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ምርጫው በክልላችን በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረገው ለሀገር መከለካያ ሠራዊት፣ ለክልላችን የጸጥታ ኃይል፣ በየደረጃው ለሚገኙ የክልላችን አመራሮች እና ለመላው የክልላችንን ሕዝብ በራሴ እና በአማራ ክልል መንግሥት ስም የላቀ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።

ለሀገር እና ለሕዝብ በአንድነት መሥራት ምን አይነት ስኬታማ ውጤት እንደሚያስገኝ ምርጫው ሕያው ምስክር መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በምርጫው ጫፍ ረገጥ አስተሳሰቦች እስከ አደረጃጀቶቻቸው በሕዝብ ደምጽ ከሽፈዋል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሸንፋለች ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት መልእክት።

መረጃ:- አማራ ኮሙዩኒኬሽን

በፎገራ ወረዳና ወረታ ከተማ አስተዳደር የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም ተጠናቋል" የፎገራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤትበደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ  ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ...
02/06/2026

በፎገራ ወረዳና ወረታ ከተማ አስተዳደር የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም ተጠናቋል"
የፎገራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር ከተማው ፈጠነ "በፎገራ 1 እና 2" 7ኛው ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

የጸጥታ አካላት የተናበበና የተቀናጀ ስራ በመሰራቱ ህብረተሰቡ ያለምንም የፀጥታ ስጋት ድምፁን መስጠት ችሏል ያሉት የፖሊስ አዛዡ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ፍጹም ገለልተኛ ሆኖ ህገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን በመወጣቱ ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን ለተወጡት ጥምር የፀጥታ አካላት ፤ለፎገራና ወረታ ከተማ ማህበረሰብ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ገፆቻችን ይጎብኙ
Facebook: https://facebook.com/fogeraworedacommunicationoffice
Telegram: https://t.me/fogeracomm
Twitter: https://x.com/fogeraworeda
YouTube: www.youtube.com/
Tik Tok https://tiktok.com/@.2017055
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም
የፎገራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

🇪🇹🗳️ "በመምረጤ ደስ ብሎኛል" የዕድሜ ባለጸጋዋ እማሆይ ስንታየሁኢትዮጵያውያን ነጋቸውን በካርዳቸው ለመወሰን እየመረጡ ነው።እማሆይ ስንታየሁ ይባላሉ። የ72 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው።በባ...
01/06/2026

🇪🇹🗳️ "በመምረጤ ደስ ብሎኛል" የዕድሜ ባለጸጋዋ እማሆይ ስንታየሁ

ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን በካርዳቸው ለመወሰን እየመረጡ ነው።

እማሆይ ስንታየሁ ይባላሉ። የ72 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው።

በባሕርዳር ከተማ ሕዳሴ የምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሲሰጡ ነው ያገኘናቸው።

በመምረጤ ደስ ብሎኛል፤ መምረጣችን ሰላምን ለማስቀጠል ነው ብለዋል።

ትውልዱ ሀገር ሰላም እንዲኾን መሥራት አለበትም ነው ያሉት። እኛ የምንፈልገው ሀገር ሰላም እንዲኾን፣ በሰላም ሠርተን እንድንኖር ነው ብለዋል።

ከአሁን ቀደምም በነበሩ ምርጫዎች ተሳትፎ እንደነበራቸው ተናግረዋል።
መረጃ:- አሚኮ

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ እና በወገዳ ከተማ አስተዳደር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ነው።የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘ...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ እና በወገዳ ከተማ አስተዳደር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና የስማዳ ምርጫ ክልል 02 የክልል ምክር ቤት እጩ አቶ መሠረት በላይ በስማዳ ተገኝተው ድምፃቸውን ስጥተዋል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የፋርጣ ወረዳ ቁ 01 ምርጫ ክልል የክልል ዕጩ ተወዳዳሪ ወ/ሮ አምሳል ተስፋ በፋርጣ ወረዳ ተገኝ...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!!

የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የፋርጣ ወረዳ ቁ 01 ምርጫ ክልል የክልል ዕጩ ተወዳዳሪ ወ/ሮ አምሳል ተስፋ በፋርጣ ወረዳ ተገኝተው ድምፃቸውን ስጥተዋል።

"ምርጫው የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ነው "የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መንበር ክፈተው የታችጋይንት ወረዳ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ በላይ ጋይን...
01/06/2026

"ምርጫው የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ነው "

የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መንበር ክፈተው የታችጋይንት ወረዳ የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ በላይ ጋይንት ወረዳ ምርጫ ክልል 2 በመገኝት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የእስቴ ወረዳ ምርጫ ክልል 2 የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ደስታ አስራቴ ...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የእስቴ ወረዳ ምርጫ ክልል 2 የክልል ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ደስታ አስራቴ በእስቴ ወረዳ ምርጫ ክልል 2 በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ትመርጣለች! የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ(ዶ.ር) ድምጽ ሰጥተዋል።
01/06/2026

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ(ዶ.ር) ድምጽ ሰጥተዋል።

Address

Fogera
Shashemene
30

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:00
Tuesday 02:30 - 23:00
Wednesday 02:30 - 23:00
Thursday 02:30 - 23:00
Friday 02:30 - 23:00

Telephone

+251584460904

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fogera woreda communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Fogera woreda communication affairs office:

Share