በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት This is the official H/Z Wera Woreda Agri. office page where you can get all the latest info

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ለላይ በደኔ ቀበሌ በፍርሚ አፍሪካ (Farm Africa) ፕሮጀክት አማካኝነት የጤፍ ዘር ድጋፍ ተደረገ ።ነሃሴ 14/18 ዓ.ም የአካባቢው አርሶ አደሮች የዘሩት የበቆሎ...
20/08/2026

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ለላይ በደኔ ቀበሌ በፍርሚ አፍሪካ (Farm Africa) ፕሮጀክት አማካኝነት የጤፍ ዘር ድጋፍ ተደረገ ።

ነሃሴ 14/18 ዓ.ም

የአካባቢው አርሶ አደሮች የዘሩት የበቆሎ ሰብል በወቅታዊ የዝናብ እጥረት ምክንያት መበላሸቱን ተከትሎ ለአርሶ አደሮቹ አስፈላጊውን የጤፍ ዘር እገዛ በማቅረብ የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ።

የምርትና ምርታማነት ማደግና ጥራቱን የጠበቀ ምርጥ የጤፍ ዘር ለአርሶ አደሮች ማቅረብ በሄክታር የሚገኘውን ምርት በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል።

ከዘር ድጋፉ ጎን ለጎን አርሶ አደሮች ዘመናዊ የዘር አዘራርና እንክብካቤ ዘዴዎችን እንዲተገብሩ ያግዛል።

ፍርሚ አፍሪካ በሀገራችን ገጠር አካባቢዎች በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ላይ ትኩረት አድርጎ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ ይህ አይነቱ የአቅም ግንባታና የግብአት ድጋፍ ነው።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በመገኘት በዞኑ በክረምት ወራት የተከናወኑ ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ተግባራት ድጋፍና ክት...
20/08/2026

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በመገኘት በዞኑ በክረምት ወራት የተከናወኑ ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ተግባራት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ዉይይት አደረገ

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ፖሎቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ዴማሞ ሀይሌ፤ የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በመገኘት በዞኑ በክረምት ወራት የተከናወኑ ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ተግባራት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ዉይይት አድርጓል ።

‎የሱፐርቪዥን ቡድን የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ጀማል በተገኘበት ነው ውይይት ያደረጉት።

‎በአጠቃላይ በክረምት ወራት እየተገበሩ ባሉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያደርጉ ሱፐርቪዥን ቡድኑ የጋራ መግባባት በመፍጠር ወደ ወረዳ መዋቅሮች በመገኘት የሱፐርቪዥን ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል።

‎በመድረኩም ላይም የሀላባ ዞን የክረምት በጎ ተግበር አብይ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አመራሮች እና ሌሎች የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል ።
‎ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል

የዌራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የዌራ ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት የህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ኑሮ ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የሚደረግ የጋራ ንቅናቄ መድረክ አካሄዱ...
20/08/2026

የዌራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና የዌራ ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት የህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ኑሮ ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የሚደረግ የጋራ ንቅናቄ መድረክ አካሄዱ

ነሃሴ 14/2018 በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እና ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት የህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ኑሮ ማረጋጋት እና የታክስ ህግ ተገዢነት ለማረጋገጥ የሚደረግ የጋራ ንቅናቄ መድረክ አካሄደዋል ።

በመድረኩ ላይ የገቢ እና የንግድ የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም እና ቀጣይ የ2019 ዕቅድ ዝግጅት በሁለቱም ጽ/ቤት ሀላፊዎች አማካኝነት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ።

መድረኩም የንግድ ሥርዓትን ማስጠበቅ፣ የገበያ ቁጥጥርን ማጠናከርና የገቢ አሰባሰብን ማሻሻል በዋናነት ያለው ዓላማ መሆኑን ተገልጿል።

የውይይት መድረኩን የዌራ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ እና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ያድሶ ዱበላ እና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ሚሀሌ ጋር በጋራ መርተዋል ።

የገቢ አሰባሰብ ከአመት አመት ተስፋ ሰጪ ለውጦችን እያስመዘገበ ነው ያሉት አቶ ያድሶ ዱበላ አሁንም ካለን የልማት ፍላጎት አንጻር የገቢ አሰባሰብ አቅም የበለጠ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በርካታ የልማት ፍላጎቶችን ለመመለስ የገቢ አማራጮች አስፍቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

‎በገቢ ስራ ላይ የቅንጅት ስራን በማጠናከር ካልተሰራ ውጤታማ መሆን ስለማይቻል የቅንጅቱ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም አቶ ያድሶ ያሳሰቡት።

የሕግ ወጥ የንግድ ቁጥጥር፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና የታክስ ህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትኩረት መስራት እንደሚገባ አያይዘው አስገንዝበዋል ።

‎የገቢ አሰባሰብ ስራችን በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ለማድረግ በተለይ እንደ ወረዳ ባሉ የገቢ ማዕከላት ውስጥ ያሉን የገቢ አማራጮችን ለይቶ በማወቅ በወቅቱ ገቢ መሰብሰብ እንዳለበት አቶ ያድሶ ዱበላ አሳሰበዋል።

አቶ ጀማል ሚሀሌ በበኩላቸው በጠንካራ መረጃ የተደገፈ ገቢ አሰባሰብ ሥራ ውጤቱ የላቀ መሆኑን በማንሳት ጠንካራ ስራ መስራት ተገቢ እንደሆነ አንስተዋል።

ጊዜዉ በልማትም ይሁን በሌሎች ተግባራት የዉድድር መሆኑን በመግለፅ ጤናማ እና ዉጤታማ የሆነ ዉድድር በመፍጠር የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ይጠበቃል ነዉ ያሉት።

የኑሮ ውድነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን የሰንበት ገበያ መስፋፋት ፣የገበያ እጥረት መሙላት፣ምርት አቅርቦት፣የንግድ ትስስር መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ጀማል የንግድ ስርዓት በህጋዊ መንገድ ካልተመራ በማህበረሰቡ ላይ የሚያደረሰው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ በህገወጥ ንግድ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የሕግ ወጥ የንግድ ቁጥጥርና የገቢ አሰባሰብ ስራው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም አመራርና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች አስተያየት እና ጥያቄ ተነስተው ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የጋራ ተደርጎ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቅቋል ።

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ፣አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ ፣የወረዳው ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ኑረዲን ሪባቶ፣የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፍ ወ/ሮ አምሪያ ሁሴን፣ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፍ አቶ ሙዜ ሽፋን ጨምሮ ሌሎችም የወረዳው አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

የዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ወቅታዊ የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች ዙሪያ ከቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ ።ነሃሴ 14/18 ዓ.ም የዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ወቅታዊ የተ...
20/08/2026

የዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ወቅታዊ የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች ዙሪያ ከቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ ።

ነሃሴ 14/18 ዓ.ም

የዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ወቅታዊ የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች ዙሪያ ከቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች እና ከSMS ጋር ውይይት አካሄደ ።

ዉይይቱን የዌራ ወረዳ የምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የእርሻ ዘርፊ ኃላፊ አቶ ሀያቱ ደበበ በጋራ መርቷተል።

የዌራ ወረዳ የምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች ጋር ባካሄዱት የውይይት ላይ እንደገለጹት በወረዳው የተያዙ የግብርና ልማት ግቦች በማሳካትና ለአካባቢው አርሶ አደሮች ምርታማነት ማሳደግና ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ግብርና ሥራዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጿል ።

የተቀናጀ የግብርና ልማት ኢኒሼቲቭ፣ የሰብል ልማት፣ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ፣ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን አዋህዶ በመምራት የአርሶ አደሩን ገቢ በዘላቂነት ለማሳደግ የግብርና ባለሙያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል ።

የመኸር አዝመራ ወቅቱ ሰያልፍ ማሳዎች በዘር ማስሻፈን እንዲሁም የሰብል እንክብካቤና የፀረ-ተባይ ቁጥጥር ሥራዎችን በተቀናጀ መንገድ መምራትን እንዳላባቸው አሳስበዋል ።

የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት (FTC/አማማ) ማዕከላቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ በማስገባት ለአርሶ አደሩ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና ልምዶች መቅሰሚያ ማድረግና አርሶ አደሮች አዳዲስ አሰራሮችን የሚያዩበትና የሚማሩበት የከፊል-ገበሬ ማሰልጠኛና የማሳያ ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ መስረት ነው ።

የእንስሳት ምርታማነትን ለማሻሻል የተሻሻሉ የመኖ ዝርያዎችን ማስፋፋትና የመኖ ማከማቸት ባህልን ማሳደግ እንዳለበትም ገልጿል ።

የእንስሳት ክትባት ዘመቻ የእንስሳት ጤናን በመጠበቅ ከአላስፈላጊ እልቂትና በሽታ ለመከላከል የክትባት ሥራዎችን በከላንደሩ መሠረት ማሰራት ይኖርበታል ።

በመጨረሻም የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች ከተሰጣቸው አቅጣጫ አንጻር ከአርሶ አደሩ ጎን በመሆን በቁርጠኝነት እንዲሰሩና የመስክ ክትትላቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

20/08/2026
በወረዳው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ያለውን የስራ አፈጻጸም ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ ነሃሴ 14/2018 በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገል...
20/08/2026

በወረዳው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ያለውን የስራ አፈጻጸም ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ

ነሃሴ 14/2018 በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ያለውን የስራ አፈጻጸም ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

የአፈጻጸም መድረኩን የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ፣አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጀማል አህመድ መርተዋል ።

በወረዳው በሁሉም መስክ የተከናወኑ የክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች አፈጻጸም ይበል የሚያሰኝና አበረታች እንደሆኑ አቶ ጀማል አህመድ አንስተዋል።

በተለይም የአቅመ ደካሞችን ቤት ከመገንባት፣ የመንገድ ከፈታ ሥራዎችን ከመሥራት፣ የክረምት ትምህርት ከመስጠት እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች በርካታ የበጎ ፈቃድ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።

ይህም ማለት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ የሚከናወነው የማህበረሰብ ችግሮችን በጋራ ተሳትፎ ለመፍታት፣ የመረዳዳትና የመተባበር ባህልን ለማጠናከር፣ የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን እና ማህበራዊ ተጠያቂነትን ለማጎልበት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

አቶ ጀማል አህመድ አያይዘው እንደተናገሩት የተጀመሩ ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት በባለቤትነት ስሜት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ብለዋል።

አክለውም የሥራዎቹን ውጤታማነት ለማሳደግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፤ ለዚህም በየዘርፉ የተከፋፈሉ ተግባራትን አቀናጅቶ በማስኬድ በሞዴልነት ማስፈጸም እንደሚገባ አብራርተዋል።

በተጨማሪም በጎነት አብሮነትን ከማጠናከሩ ባሻገር በማህበረሰቡ ውስጥ የተቀራረበ የኑሮ ደረጃ እንዲኖር እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ይህንንም ተግባር የተቀናጀ ርብርብ በማድረግ በሁሉም መስኮች የተያዘው ግብ በላቀ ሁኔታ እንዲፈጸም አሳስበዋል።

በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በየዘርፉ ያሉ ተግባራትን ስኬታማ ለማድረግ የአከባቢውን ወጣቶችና በጎ ፍቃደኞችን በስፋት ማሳተፍ እንደሚያስፈልግ የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱን አጠናቀዋል።

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ኑረዲን ሪባቶን ጨምሮ ሌሎችም የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተገኝተው ተሳትፈዋል ።

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ በወቅታዊ በተቀናጀ ግብርና ስራዎች ከዞን የተሰማራዉ ቲም በመዋቅሮች ያደረገዉን  ድጋፍና ክትትል ግብረ_ መልስ ገመገመ።ነሐሴ:14/12/2018  ዓ/ምየዕለቱን የዉ...
20/08/2026

የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ በወቅታዊ በተቀናጀ ግብርና ስራዎች ከዞን የተሰማራዉ ቲም በመዋቅሮች ያደረገዉን ድጋፍና ክትትል ግብረ_ መልስ ገመገመ።

ነሐሴ:14/12/2018 ዓ/ም

የዕለቱን የዉይይት መድረክ የሀላባ ዞን ም/አስተዳዳሪና የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ ሃጂ ኑሪዬ የመሩት ሲሆን በመድረኩም ላይ የመምሪያዉ ም/ኃላፊዎችና የመኔጅመንት አባላት ተገኝቷል።

"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"ለመሸጋገር በዌራ ወረዳ ለባለድርሻ አካለት የውይይት መድረክ ተካሄደ "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"ለመሸጋገር በዌራ ወረዳ ከባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄ...
20/08/2026

"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"ለመሸጋገር በዌራ ወረዳ ለባለድርሻ አካለት የውይይት መድረክ ተካሄደ

"ከተረጅነት ወደ ምርታማነት"ለመሸጋገር በዌራ ወረዳ ከባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄዷል።

ለመድረኩ የተዘጋጀውን ሰነድ የዌራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ሚሀሌ አቅርበው መድረኩን የዌራ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ያድሶ ዱበላ ጋር በጋራ በመሆን መርተውታል ።

መድረኩ ባለፉት ጊዜያት የነበሩ ስኬቶችንና ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ለጋራ ችግሮች በጋራ መፍትሔ መፈለግ ላይ ያለመ መሆኑን አቶ ያድሶ ዱበላ ገልጿል።

ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው ጉዞ ከፓርቲው ትኩረት አቅጣጫዎችና ኢኒሼቲቮች መካከል ዋነኛው መሆኑንም አቶ ያድሶ ተናግረዋል ።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገውን ሽግግር ለማጠናከርም ሆነ በማህበረሰቡ ዘንድ በየአካባቢው የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ ከወትሮው በላይ በትኩረት መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

አቶ ጀማል ሚሀሌ በበኩላቸው በሀገራችን ስር ሰዶ የቆየውን የተረጂነትና የልመና አስተሳሰብ ለማስወገድ ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ መገኖችን ሁለተናዊ ድጋፍ ማድረግ የሁሉም አካለት ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በቀጣይም ወረዳውን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር በማህበራዊም ሆነ በኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አቶ ጀማል አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና ፖለቲካ ፣አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ኑራዲን ሪባቶ ሌሎችም የወረዳው አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ታች በደኔ ቀበሌ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተገኙበት የቡና ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።ነሀሴ 14/18 ዓ.ም በዌራ ወረዳ ታች በደኔ ቀበሌ የተካሄደው የቡና ...
20/08/2026

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ታች በደኔ ቀበሌ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች በተገኙበት የቡና ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

ነሀሴ 14/18 ዓ.ም

በዌራ ወረዳ ታች በደኔ ቀበሌ የተካሄደው የቡና ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የአካባቢውን የቡና ምርትና ምርታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ እርምጃ ነው። በክልሉ ግብርና ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሰጠውን ግንዛቤ መነሻ በማድረግ አርሶ አደሮች ችግኙን በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲተክሉ ማስቻሉ የስኬቱ አጋዥ ነው።

በዕለቱም ከተከላው ጎን ለጎን የቡና ችግኝ አተካከል፣ ከተከላ በኋላ የሚደረጉ የቴክኒክ እንክብካቤዎችን አስመልክቶ ለተሳታፊዎች ተግባራዊ ግንዛቤ ተሰጥቷል። ይህ መርሃ-ግብር በአካባቢው ጥራት ያለው የቡና ምርት ለማሳደግና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

እንኳን ደስ አላችሁ!​ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የሀላባ ዞን ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት በየዘርፉ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴክተሮችና መዋቅሮች የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት አበር...
19/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!

​ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የሀላባ ዞን ምክር ቤት በ2018 በጀት ዓመት በየዘርፉ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴክተሮችና መዋቅሮች የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።

​በዚህም የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ ባስመዘገበው የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ከዞኑ ኢኮኖሚ ሴክተሮች 1ኛ በመውጣት የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተቀብሏል።

​ይህ አበራታች ውጤት የዞኑ አመራሮች፣የወረዳ አመራሮች፣ከዞን እስከ ቀበሌ ያላችሁ የግብርናው ቤተሰቦች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ መላው አርሶአደረችን፣ ወዳጆችና አጋር አካላት በጋራ ያደረጋችሁት ትጋትና ጥረት ፍሬ ነው።

​ይህ ዕውቅና ለቀጣይ ሥራችን ትልቅ አቅም በመሆኑ፣ እንደ መነሻና ማነቃቂያ በመጠቀም በግብርናው ሴክተር የተጀመሩ የልማት እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ሕዝባችንን ከድህነት ለማውጣት በቁርጠኝነት መትጋት ይገባል።

​እንኳን ደስ አላችሁ!

Address

Alaba K'Ulito
Shewa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share