Gishe wereda Government Communication Affairs Office-የግሼ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Shewa
  • Gishe wereda Government Communication Affairs Office-የግሼ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን

Gishe wereda Government Communication Affairs Office-የግሼ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የግሼ ወረዳ በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን ውስጥ ይገኛል፡፡

ክረምቱ ዘግይቶ ቢገባም፤ በወረዳችን ወፍለቅ ቀበሌ የስንዴና የባቄላ ሰብል ይህን ይመስላል።👇
01/09/2026

ክረምቱ ዘግይቶ ቢገባም፤ በወረዳችን ወፍለቅ ቀበሌ የስንዴና የባቄላ ሰብል ይህን ይመስላል።👇

በግሼ ወረዳ የአረጋውን ማህበር ምስረታና የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄዴ። በወረዳው ሴ/ወ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት እና በወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት "ታሪክ አለን የአረጋውያን ...
31/08/2026

በግሼ ወረዳ የአረጋውን ማህበር ምስረታና የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄዴ።
በወረዳው ሴ/ወ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት እና በወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት "ታሪክ አለን የአረጋውያን መረዳጃ ማህበር" ተመስርቶ የማህበሩ አመራሮችም ተመርጠው በጠቅላላ ጉባኤው ፀድቋል።
የወረዳም ምክትል አስተዳዳሪና ንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ የሺጥላ ተፈሪ አረጋዊያኑን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ፤ ማህበሩ እንዴት መጠናከር እንዳለበትና መረዳዳት በሚቻልባቸው መንገዶች ውይይትም ተደርጓል።
በመቀጠልም የማእድ መጋራት ተካሂዷል።
በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ቅን ልብ ያላቸው ወገኖችም እነዚህን አረጋውያን በማህበሩ በኩል እንዲደግፉም ጥሪ የቀረበ ሲሆን የማህበሩን የባንክ አካውንት ተቋማችን( የመንግስት ኮሙኒኬሽን) በቅርቡ በገፃችን የሚያሳውቅ ይሆናል።

🙏🙏በጎነት በተግባር ሲገለፅ እንዲህ ነው!!!!🙏🙏 የፈ/ቤት ጤና ጣቢያ ሀኪሞች ወደ ጤና ጣቢያው መምጣት ለማይችሉ እና የመታከሚያ ገንዘብ ለሌላቸው ወገኖቻችን እንዲህ ቤት ለቤት አየዞሩ ህክም...
28/08/2026

🙏🙏በጎነት በተግባር ሲገለፅ እንዲህ ነው!!!!🙏🙏
የፈ/ቤት ጤና ጣቢያ ሀኪሞች ወደ ጤና ጣቢያው መምጣት ለማይችሉ እና የመታከሚያ ገንዘብ ለሌላቸው ወገኖቻችን እንዲህ ቤት ለቤት አየዞሩ ህክምና እየሰጡ ነው። 🙏🙏🙏ክብር ይገባቸዋል 🙏🙏🙏🙏

ውይይቱ ቀጥሏል።  "የውጭ ወረራ ስጋትን እና የውስጥ ፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሠላምና  ልማትን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ሃሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ፤ ከአሽከርካሪዎች እና ጫኝና አ...
27/08/2026

ውይይቱ ቀጥሏል። "የውጭ ወረራ ስጋትን እና የውስጥ ፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሠላምና ልማትን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ሃሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ፤ ከአሽከርካሪዎች እና ጫኝና አውራጅ ማህበሮች ጋር ውይይት ተደርጓል።

🌟 የምስራች ለግሼ ወረዳ ነዋሪዎች በሙሉ❤  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሀን ዲስትሪክትየ1.5 ቢሊየን ብር በጀት ሰፊ የብድር አገልግሎቶችን አመቻቸ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃ...
27/08/2026

🌟 የምስራች ለግሼ ወረዳ ነዋሪዎች በሙሉ❤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሀን ዲስትሪክት
የ1.5 ቢሊየን ብር በጀት ሰፊ የብድር አገልግሎቶችን አመቻቸ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ብርሃን ዲስትሪክት የህብረተሰቡን የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላትና የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ራቤል ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ በየነ በሪሁን እንዳስታወቁት፤ ዲስትሪክቱ ለመላው የሰሜን ሸዋ ዞን የላቀ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ባለፉት 3 ወራት ውስጥ ብቻ የ1.5 ቢሊየን ብር በጀት መድቦ ወደ ስራ ገብቷል።
በተመደበው በጀትም ለአገር ውስጥ ንግድ፣ ለግብርና እና አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ለአዳዲስ አልሚ ባለሀብቶች የሚውል በቂ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የብድር አቅርቦት ተዘጋጅቷል።
በተጨማሪም ባንኩ ለሚከተሉት ዘርፎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ማራኪ የብድር አማራጮችን አቅርቧል፦
👉1. ያለምንም ዋስትና ለሚሰጥ የሰራተኞች ብድር፣ ለመንግስትና ለግል ድርጅት ቋሚ ሰራተኞች ደመወዛቸውን በንግድ ባንክ ሲከፈሉ በዲጂታል አማራጭ የቀረበ ሲሆን፤ ሰራተኞች ያለምንም ዋስትና እስከ 150 ሺህ ብር ማግኘት የሚችሉበት ልዩ የብድር አይነት ተመቻችቷል!
👉 2. ለንግዱ ማህበረሰብ፣ ለሁሉም የንግዱ ዘርፍ አባላት ስራቸውን እንዲያሰፉ የተመቻቹ ብድሮች።
👉 3. ለቤትና መኪና ግዢ፣ ቁጠባን መሰረት ያደረጉና ህልምዎን እውን የሚያደርጉ የብድር አማራጮች።
👉 4. ለስራ እድል ፈጠራ፣ አዳዲስ ስራ ፈጣሪዎችን እና ወጣቶችን የሚያበረታቱ ብድሮች።
👉 5. ለግብርናው ዘርፍ፣ በዘርፉ ለተሰማሩ አምራቾች ምርታማነትን የሚያሳድጉ ብድሮች።የዲስትሪክቱ ዳይሬክቶሬት እንዳሳሰበው፣ ደንበኞች እነዚህን ልዩ የብድር አማራጮች በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ ማናቸውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ ማብራሪያ መውሰድና አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

ሀሳብዎን ወደ ተግባር ለመቀየር ባንካችን ሁሌም ከጎንዎ ነው!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ! ✨

26/08/2026
በኢፊዲሪ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ያላቸው በ45ኛ ዙር ፅናት ኮርስ የተመረቁ ኮማንዶ የመከላከያ አባላት በግሼ ወረዳ ሰላም እያስከበረ ያለውን 105ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።ዛሬ ነሃሴ ...
26/08/2026

በኢፊዲሪ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ያላቸው በ45ኛ ዙር ፅናት ኮርስ የተመረቁ ኮማንዶ የመከላከያ አባላት በግሼ ወረዳ ሰላም እያስከበረ ያለውን 105ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።
ዛሬ ነሃሴ 20/2018 ዓ.ም በማለዳው ወደ ወረዳችን ሲገቡ በአጠቃላይ የወረዳው አመራሮችና ልዩ ልዩ የህሰ/ብ ክፍሎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

26/08/2026
26/08/2026
የክረምቱ ጨለማ አልፎ ብሩህ ሰማይ ለማየት ዋዜማው ላይ እያለን የ2019 በጀት አመት በዓላት መጀመሪያ የሆነውን የደብረ ታቦር/ቡሄ/ በዓልን በወረዳችን ግሼ በራቤል ከተማ ከወረዳው አመራሮች፤...
20/08/2026

የክረምቱ ጨለማ አልፎ ብሩህ ሰማይ ለማየት ዋዜማው ላይ እያለን የ2019 በጀት አመት በዓላት መጀመሪያ የሆነውን የደብረ ታቦር/ቡሄ/ በዓልን በወረዳችን ግሼ በራቤል ከተማ ከወረዳው አመራሮች፤ ከልጅ እያሱ አማተር ክበብ አባልት፤ ከራቤል ቀበሌ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው ልዩልዩ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ባህላዊና ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በአይሲቲ አዳራሽ ‹‹ ባህላችን ድልድያችን አንድነት መዳረሻ›› በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል፡፡
የደብረ ታቦር በዓል አከባበር መነሻ "እየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮት ለሀዋሪያት በደብረ ታቦር የገለፀበት ቀን እንደሆነ ሀይማኖታዊ መሰረቱ ያስተምራል፡፡
ደብር ማለት ተራራ፣ ታቦር ማለት ደግሞ የተራራ ስም እንደሆነ ይገለጻል፡፡ የቃሉ ስያሜም ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህ ምድር ላይ በሚያስተምርበት ጊዜ ዘጠኙን ሀዋሪያት ከተራራው ጥግ ትቶ ሶስቱን ማለትም ጴጥሮስን፣ዮህንስንና፣ ያዕቆብን መርጦና አስከትሎ በደብረ ታቦር ከተራራው አናት ላይ በመውጣት ማስተማሩንና የተለያየ ታዓምራትን መፈፀሙን ለመግለፅ ሲሆን ከተራራው ሲወርዱም ያዩትን ና የሰሙትን እስከ ትንሳኤው ድረስ ለማንም እንዳይናገሩ ስለ ማዘዙ የሚነገር ታሪክ ነው፡፡
ቡሄ ማለት፣ በግዕዝ ቋንቋ ብራ፣ብርሃን ፣ገላጣ ወይም መላጣ ማለት ሲሆን በኢትዮጲያ በየ አመቱ ነሃሴ 13 ቀን የሚከበር ሲሆን በቡሄ ክብረ በዓል ዉስጥ ጅራፍ ፣ችቦና ሙልሙል ዳቦ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡

Address

Amhara Region North Shewa
Shewa
251

Telephone

+251033 811 99 93

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gishe wereda Government Communication Affairs Office-የግሼ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gishe wereda Government Communication Affairs Office-የግሼ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን:

Shortcuts

Share