የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Silt'e
  • የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን
Warabe City Administration Youth's Federation

25/08/2026
25/08/2026
24/08/2026
በትግራይ ክልል አሁንም ያጠላው የጦርነት ስጋት የወጣቶችን ህልም አጨልሟል - የሲዳማ ክልል ወጣቶች++++++++++++++++ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአገራችን የተቀሰቀሰው ጦርነት በትግራይ ክል...
24/08/2026

በትግራይ ክልል አሁንም ያጠላው የጦርነት ስጋት የወጣቶችን ህልም አጨልሟል - የሲዳማ ክልል ወጣቶች
++++++++++++++++
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአገራችን የተቀሰቀሰው ጦርነት በትግራይ ክልል የብዙ ወጣቶችን ሕልም ቀጭቷል። አሁንም በአካባቢው የስጋት ጥላውን ያጠላው የጦርነት ዳመና በወጣቶች ሕይወት ላይ እያሳደረ ያለው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም።

የሲዳማ ክልል ወጣቶች ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ጦርነት አሸናፊ የለውም፤ አገርንም ሆነ ወጣቶችን ያደኸያል። በኃይል የሚመጣ ሥልጣንም ሆነ የሚገኝ ድል የሰላምን ያህል ዘላቂነት የለውም። አሁን ላይ ወጣቶች የሚያስፈልጋቸው የመሣሪያ አፈሙዝ ሳይሆን የትምህርት፣ የሥራና የሰላም ዕድል እንደሆነ ገልጸዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችና በወቅቱ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ወጣት መክሊት መንግሥቱ፣ ያሳለፈችው የመከራ ጊዜ አሁንም ትኩስ ጠባሳ ሆኖ እንደሚሰማት ተናግራለች።

“በጦርነት ዕድል አለ ብዬ አላስብም፤ በጦርነት ድልና ማሸነፍ የለም” የምትለው ወጣት መክሊት፤ ሰውን መጥቀምና ሕይወትን ማዳን እንጂ መጠፋፋት እንደማያስፈልግ ትናገራለች። ጦርነት ከገንዘብና ቁሳዊ ውድመት በላይ የሰውን ትልቁን ሀብት ተስፋን እንደሚያሳጣ ገልጻለች።

የራሷን የግል ሥራ እያከናወነች የምትገኝ አሠልጣኝና ገለልተኛ አማካሪዋ መክሊት፤ “ተስፋ ያጣ ሰው መኖሩም መሞቱም አንድ ነው፤ ወጣቶች ለሰዎች ተስፋ፣ የሰላም ድምፅ የሚሆኑበትን መንገድ መከተል አለባቸው” ስትል ታሳስባለች።

የሲዳማ ክልል የወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ጋማርሳ ዲዳ በበኩሉ፤ ሰላም የሚጀምረው ከራሱ ከግለሰቡ አስተሳሰብ መሆኑን ይናገራል። በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ የሰውና የአገር ኪሳራ መድረሱንና አሁንም በችግሩ ምክንያት በርካታ የትግራይ ወጣቶች ያለፍላጎታቸው ለጦርነት ማገዶ እየሆኑ ይገኛሉ ሲል በትካዜ ገልጿል።

በአካባቢው ያለው ወጣት “ከዚህ ቀደም ከነበረው ጦርነት ምን አተረፍን? አሁንስ ማንንስ ገድለን ነው ድላችንን የምናበስረው?” የሚሉትን ጥያቄዎች በሰከነ መንፈስ ማስላት እንዳለበት ያመላከተው ወጣት ጋማርሳ፤ ከጦርነት ቀጣና የተፈናቀሉና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች በሥራና በተለያዩ ማኅበራዊ ድጋፎች ሊያቅፏቸው እንደሚገባ ገልጿል።

ከጦርነቱ አምልጠው የመጡትም የጦርነቱን አሰቃቂነት ለዓለም በማሳወቅ የእንቅስቃሴው አካል መሆን እንዳለባቸው የጠቆመው ወጣቱ፤ “በትግራይ ክልል ያሉት አብረውን የተማሩ በጎና መልካም አስተሳሰብ ያላቸው ጓደኞቻችን በተለያየ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል፤ እኛ በሰላማዊ አካባቢ ያለነው ወጣቶች የእነሱን ችግር በመካፈል ድምፅ ልንሆናቸው ይገባል” ሲል አሳስቧል።

ደራሲና የሲዳማ ክልል ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ምንተስኖት መኩሪያ በበኩሉ፤ አገራችን ከትናንት ስህተቷ ተምራ ነገን ከመፍጠር ይልቅ በድግግሞሽ አዙሪት ውስጥ መክረሟ ከፍተኛ ቁጭት እንደፈጠረበት ይናገራል።

“በጦርነት አትራፊ የለም፤ የጋራ ሽንፈት እንጂ ዕድገት አላየንም” የሚለው ወጣት ምንተስኖት፤ አሁን ያለው ሁኔታ በተለይ በትግራይ ክልል ወጣቶች ላይ ትልቅ የትውልድ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋቱን ገልጿል።

በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የምንገኝ ወጣቶች በትምህርትና በዕውቀት ወደፊት ስንራመድ፣ የትግራይ ወጣቶች በጥቂት ነውጠኞች ከሁሉ ነገር ወደኋላ ቀርተው ተስፋ ቢስ የሚሆኑበት ዕድል ያሳዝናልም ያሳፍራልም” ብሏል።

የሰሜኑ ሕመም የሙሉ አገሪቱ ሕመም በመሆኑ ወጣቶች በእጃቸው ያለውን ቴክኖሎጂና ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን በመጠቀም የሰላም ጥሪዎችን እንዲያስተላልፉና በትግራይ ክልል የጦርነት አባዜ የተጠናወታቸውን አካላት እንዲቃወሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በመጨረሻም ወጣቶቹ፣ የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያ ለማዳንና የወጣቶችን ተስፋ ላለማጨለም የሕወሓት ቡድን አመራሮች ከጦርነት አዙሪት ወጥተው ለንግግርና ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በሔርሞን ፍቃዱ
-

#ሕወሓት #ትግራይ #ኢፕድ #ኢትዮጵያ
Mintesinot Mekuria Gamarsa Dida Dimato 👌👌

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ያሰማራው ሱፐርቪዥን ቡድን በስልጤ ዞን በመገኘት በክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል።ነሐሴ ...
24/08/2026

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ያሰማራው ሱፐርቪዥን ቡድን በስልጤ ዞን በመገኘት በክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል።

ነሐሴ 18 /2018 | በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የሴቶች ክንፍ ምክትል ኃላፊ በወ/ሮ አሰለፈች ታደሰ የተመራው ይህ የሱፐርቪዥን ቡድን በዞኑ የ2018 የክረምት በጎ ተግባር አፈጻጸምን የመደገፍና የመከታተል ሥራውን ጀምሯል።

ብልፅግና ፓርቲ ከመሰረቱም ቢሆን ሰውን ማዕከል ያደረጉና የህዝቡን የዕለት ተዕለት የአኗኗር ዘይቤ በጥራት የሚያሻሽሉ ዘላቂ የልማት ተግባራትን የማስቀጠል ፅኑ መርህ ያለው በመሆኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን በተለየ ትኩረትና ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም የዚሁ የመስክ ምልከታና ግምገማ ዋና ዓላማ ይፋ የተደረጉት የበጎ አድራጎት ስራዎች በተግባር መሬት ወርደው የህብረተሰቡን ህይወት በውል መለወጣቸውን ማረጋገጥና ተጠቃሚው የህብረተሰብ ክፍል በተከናወኑት ስራዎች ላይ ያለው የእርካታ ምን ያህል እንደሆነ በቅርበት ለመገምገም እንደሆነ ገልፀዋል።

በተለይም ደግሞ ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ የሚገኘውን ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞችና በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች የመኖሪያ ቤት ግንባታና እድሳት ሥራ ያለበትን ደረጃ በቅርበት የመስክ ምልከታ በማድረግ፣ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከርና ያሉ ማነቆዎችን በመለየት በቀጣይ የሚሰሩ ተግባራትን ይበልጥ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር በውይይቱ ላይ እንደገለጹት የዘንድሮው የክረምት በጎ ተግባር እንቅስቃሴ በተደራጀ፣ በተቀናጀና በተጠናከረ የአመራር ቁርጠኝነት እየተመራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በሁሉም የተግባር መስኮች ከፍተኛ የዕቅድ አፈጻጸም መመዝገቡን የገለፁት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ እየተከናወኑ የሚገኙት አጠቃላይ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የፓርቲውን እውነተኛ ሰው ተኮርነትና ለህዝብ ጥቅም የቆመ መሆኑን በተግባር ያረጋገጡ እንደሆኑ ገልጸዋል።

አክለውም ለዚህ ስኬት መመዝገብ የሁሉንም አደረጃጀቶች አቅም በአግባቡ ከመጠቀም ባሻገር በተለይም የአቢይ ኮሚቴውንና የቴክኒክ ኮሚቴውን ጠንካራ ስምሪት እና የመስክ ክትትል ሂደቱ የጠበቀ በመሆኑ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወናቸውን ገልፀዋል።

በተለየ መልኩ ተስፋቸው ተመናምኖ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እምባቸውን አብሰን በርካታ ስራዎችን መስራት ችለናል ሲሉ ገልፀዋሉ።

በሂደቱም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ማሳተፍ የተቻለ ሲሆን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ኮሌጆች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና የሃይማኖት ተቋማት በተግባሩ በቅንጅት እንዲሳተፉ መደረጉ ከተጠበቀው በላይ የተሻለና የጎላ ስራ እንድንሰራ አስችሎናል ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በየተቋማቱ የሚከናወኑ የክረምት በጎ ተግባራት በየሳምንቱ በቴክኒክ ኮሚቴው አማካኝነት በጥብቅ ሁኔታ እየተገመገሙ እንደሚገኙና ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ የተዋቀሩ ቡድኖች በመሬት ላይ ያለውን እውነተኛ የአፈጻጸም ሁኔታ በየጊዜው በመከታተል የስራዎቹን ጥራትና የተጠናቀቁበትን ደረጃ በትክክል እያረጋገጡ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም ከበጎ ተግባሩ ተጠቃሚዎች መካከል የአረጋውያን ልየታ በተገቢውና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ተከናውኖ ስራው ከመጀመሪያው እስከ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ድረስ ልዩ ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም በዚህ በጎ እንቅስቃሴ ውስጥ የወጣቶች፣ የሴቶችና የአጠቃላይ ማኅበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በሂደቱም ለተለያዩ ድጋፎች የሚውሉ ቁሳቁሶችንም የማሰባሰብ ስራ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተለየ መልኩ እንደ ዞን በዕቅዳችን ከጨመርናቸው መስኮች መካከል የቁጠባ ቤቶችን ለመስራት በተያዘው እቅድ መሰረት እስከ አሁን ስምንት የቁጠባ ቤቶችን ገንብቶ ማጠናቀቅ መቻሉን ክብርት ነኢማ ገልጸዋል።

አክለውም የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በነዚህ የበጎ ተግባር እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጉ ስራው ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ አቅም መፍጠሩን የጠቆሙ ሲሆን በተለይም ሁሉም ተቋማት ከእቅድ ዝግጅት እስከ ሪፖርት ማቀረብ ባለው ሂደት በቅንጅት "አንድ እቅድ፣ አንድ ሪፖርት" በሚል መርህ ተናበው መስራታቸው ለተግባሩ ስኬት ዋናው መሳሪያ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የባለሀብቶች ተሳትፎ ለስራው ውጤታማነት አወንታዊ ሚና እንደነበረው ገልጸው፣ የበጎ ተግባር እንቅስቃሴው ወሰን ተሻጋሪ በመሆኑም ስራው ከወረዳ እስከ ወረዳ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ዞኑ ወደ ሌሎች አጎራባች ዞኖች በመሄድ ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አብራርተዋል።

የስልጤ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ዋና ኃላፊ አቶ ፈቱ ኪንባዶ በበጎ ፍቃድ እንቅስቃሴው የተከናወኑ አጠቃላይ ተግባራትን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሂደቱም ስራው ከመጀመሪያው አንስቶ በተቀናጀ፣ በተናበበና በተደራጀ አመራር ስለተመራ አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ነሐሴ 18 /2018
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
__________________________________________

23/08/2026
👉የ2018 የወራቤ ከተማ የክረምት የጤና የእግር ኳስ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ውጤት   ◻️      ቅዳሜ 16/12/18               4:00 🔴ስልጤ ዞን ፓሊስ 5_2  ማዘጋጃ🔵⭐የ...
22/08/2026

👉የ2018 የወራቤ ከተማ የክረምት የጤና የእግር ኳስ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ውጤት

◻️ ቅዳሜ 16/12/18
4:00

🔴ስልጤ ዞን ፓሊስ 5_2 ማዘጋጃ🔵

⭐የጨዋታው ኮከብ መሀመድ ከፖሊስ

🏟️ ሀይረንዚ ሜዳ


◻️ ቅዳሜ 16/12/18
9:00

🔴ሶጃት 0_1 ሰንዳቦ🔵

⭐የጨዋታው ኮከብ ተውፊቅ ከሰንዳቦ

🏟️ ሀይረንዚ ሜዳ

የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትራፊክ ደህንነት ላይ ያተኮረ የመንገድ ዜብራ ቀለም የመቀባት ስራ ተከናወነ !ነሀሴ /2018 4በወራቤ ከተማ አሰተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ...
22/08/2026

የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በትራፊክ ደህንነት ላይ ያተኮረ የመንገድ ዜብራ ቀለም የመቀባት ስራ ተከናወነ !

ነሀሴ /2018 4

በወራቤ ከተማ አሰተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ና ከወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር በመቀናጀት የክረምት በጎ ተግባር መርሃ-ግብር አካል የሆነው የመንገድ ላይ የትራፊክ ምልክትና የዜብራ ቀለም የመቀባት ስራ በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

የክልሉ የበጎ ተግባር ሱፐርቪዥን ቡድን በወራቤ ከተማ የበጎ ሥራዎች ላይ የድጋፍና ክትትል ሥራ አከናወነ!~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ነሐሴ 15፣ 2018የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበ...
21/08/2026

የክልሉ የበጎ ተግባር ሱፐርቪዥን ቡድን በወራቤ ከተማ የበጎ ሥራዎች ላይ የድጋፍና ክትትል ሥራ አከናወነ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ነሐሴ 15፣ 2018
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበጎ አገልግሎት ተግባር ሱፐርቪዥን ቡድን በወራቤ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ተግባራት አፈጻጸምን የድጋፍና ክትትል ሥራ አከናወነ።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራትን በመመልከት የተግባራቱን አፈጻጸም በመገምገም እና አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት ክትትል አድርጓል።

በክትትሉ ወቅት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ አጠቃላይ የክረምት በጎ ተግባራት፣ በተለይም ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞች የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች ያሉበት ደረጃ የተመለከተ ሲሆን ቀሪ ሥራዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የክረምት በጎ ተግባር አፈጻጸሙን ይበልጥ ስኬታማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቧል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በከተማዋ በሁሉም መዋቅሮች የታዩ ጠንካራ ተግባራትን አድንቆ በቀጣይም የተፈጠረውን አደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓት በማጠናከር የበጎ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁሟል።

የድጋፍና ክትትል ሥራውን ካጠናቀቀ በኋላም የሱፐርቪዥን ቡድኑ ለወራቤ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ግብረ-መልስ በመስጠት የታዩ ጥንካሬዎችንና ቀሪ ሥራዎችን በማመላከት ቀጣይ አቅጣጫ ሰጥቷል።

በአጠቃላይ የሱፐርቪዥን ሥራው በወራቤ ከተማ የክረምት በጎ ተግባራትን በተደራጀና ቀጣይነት ባለው አሠራር በማጠናከር ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅና የበጎ ተግባራትን ውጤት በማሳደግ ረገድ የጋራ ትኩረት እንዲደረግ አቅጣጫ ሰጥቷል።

በድጋፍና ክትትሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልባር ኡስማን፣ የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባር ትምህርትና ሥልጠና አውታሮች ማስተባበሪያ ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ኑር ከድር፣ የክልሉ ትምህርትና ሥልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ታየች ሞላ እንዲሁም የወራቤ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

[ወራቤ ኮሙኒኬሽን]

Address

Werabe
Silt'e

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን:

Shortcuts

Share