Bayra Koysha Woreda Government Communication/የባይራ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Bayra Koysha Woreda Government Communication/የባይራ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን

Bayra Koysha Woreda Government Communication/የባይራ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bayra Koysha Woreda Government Communication/የባይራ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን, Public & Government Service, Bayra koysha woreda, Sodo.

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ የቅድመ መደበኛ የት/ቤቶች ግንባታ በተመለከተ ለክልል ተቋማት ተልዕኮ በመስጠት ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀመጡ   ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበይነ መ...
28/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ የቅድመ መደበኛ የት/ቤቶች ግንባታ በተመለከተ ለክልል ተቋማት ተልዕኮ በመስጠት ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀመጡ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት በክልሉ በሁሉም ዞኖች የሚገነቡ የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች ግንባታ በተመለከተ ለክልሉ ተቋማት ተልዕኮ በመስጠት ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።

በስብሰባው በክልሉ በፌዴራል፤ በክልሉ መንግስት እና በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች በጣምራ የሚገነቡ የ140 የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም ቀጣይ ተልዕኮ የተመለከተ በክልሉ ትምህርብ ቢሮ በኩል ዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፤ መንግስት ለማህበራዊ ብልፅግና ትልም ስኬት ቁልፍ ለሆነው ለትውልድ የትምህርት ዘርፍ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይ እንደ ሀገር ያጋጠመን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በመደረግ ላይ ባለው ጥረት በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ህብረተሰቡን ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ለዘርፉ ውጤታማነት መሰረት የጣሉ ውጤቶች በመገኘት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዚሁ ጥረት አካል በተለይ ለታችኛው ዕርከን የትምህርት ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት በአሁኑ ወቅት የ140 የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች ግንባታን በፌዴራል መንግስት፤ በክልሉ መንግስት እና በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች በጣምራ ገንብቶ በማጠናቀቅ ለ2019 የት/ዘመን ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት በመሰራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶቹ በክልሉ በሁሉም ዞኖች የሚገነቡ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለዚህም የቦታ ርክክብ፤ የተቋራጭ ውለታ እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን እና ከክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ጋር በማስተሳሰር ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል፡፡

በግንባታው ረገድ እሰካሁን የ82 ት/ቤቶች ግንባታን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ አበረታች ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለትምህርት ቤት ግንባታዎች አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ባለቤት ፈጥሮ ፈጠራና ፍጥነት በተካለበት አግባብ ግንባታዎችን ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የተያዘው ግብ የትምህርት ዘመኑ ትምህረት መስከረም 5 በይፋ ሲጀመር፤ በግንባታ ላይ ያሉ ት/ቤቶችን አጠናቆ ስራ እንዲጀምሩ ማስቻል መሆኑንም ጠቅሰው፤ ለዚህ የክልል ቢሮዎችና ተጠሪ ተቋማት ከዞኖች እና ወረዳዎች ጋር ተቀናጅተው ግንባታዎችን በባለቤትነት ክትትል በማድረግ ከዳር ማድረስ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የት/ቤቶች ግንባታ ሲጠናቀቅም ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ለትምህርት ቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ በማህበረሰብ ተሳትፎ የትምህረት ቤት ምገባን ለማስጀመር መስራት የሚገባ መሆኑንም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

ለተያዘው ግብ ስኬት በየደረጃው ያለው አመራር በከፍተኛ ኃላፊነትና የባለቤትነት ስሜት ፕሮጀክቶቹን መከታተልና መደገፍ፣ እስከታችኛው መዋቅር ባለቤት ፈጥሮ መስራት፣ ብቃት ያለው የፕሮጀክት ክትትል በማድረግ መፈፀም እና ማስፈፀም እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ግንባታው ከፍተኛ አቅም እና ድጋፍ የሚፈልግ በመሆኑ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጠናከር፣ የግንባታ ግባዓቶችን ባለሀብቱን አስተባብሮ አስቀድሞ ዝግጁ ማድረግ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ብቁ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ለማሟላት መስራት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለግንባታው ውለታ

ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ በሆነና የሰዎችን ነጻነትና ክቡር በሚገፋ መልኩ መጠቀም የሚያስከትለው ተጠያቂነት ላይ ትኩረት ያደረገ የንቃተ ህግ ትምህርት ንቅናቄ መካሄድ በመካሄድ ...
28/08/2026

ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ በሆነና የሰዎችን ነጻነትና ክቡር በሚገፋ መልኩ መጠቀም የሚያስከትለው ተጠያቂነት ላይ ትኩረት ያደረገ የንቃተ ህግ ትምህርት ንቅናቄ መካሄድ በመካሄድ ላይ ነው

በቅሎ ሰኞ፤ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ በሆነና የሰዎችን ነጻነትና ክቡር በሚገፋ መልኩ መጠቀም የሚያስከትለው ተጠያቂነት ላይ ትኩረት ያደረገ የንቃተ ህግ ትምህርት ንቅናቄ መካሄድ በመካሄድ ላይ ነው።

በንቅናቄው የወላይታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጤናዬ ትርንጎ እንደተናገሩት ማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የሌሎችን ነጻነት፣ ክብርና መልካም ስም ማክበር ያለው አስፈላጊነት ላይ ትኩረት እየተሰጠ ሲሆን፣ ህገወጥ የሆኑ ይዘቶችን ማሰራጨት፣ የሰዎችን ክብርና መብት መጣስ እንዲሁም ሌሎችን ሊጎዱ የሚችሉ መረጃዎችን ያለአግባብ ማሰራጨት የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት እንዳለ ማወቅቅ ያስፈልጋል ስሉ ተናግሯል።

በተጨማሪም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መብታቸውን ከመጠቀም ጋር ተያይዞ ያለባቸውን ህጋዊና ማህበራዊ ኃላፊነት እንዲገነዘቡ በማድረግ፣ ዲጂታል መድረኮችን ለጠቃሚ መረጃ፣ ለግንዛቤ ማስጨበጫና ለማህበራዊ በጎ አስተዋፅኦ እንዲውሉ ማበረታታት የንቅናቄው ዋና ዓላማ መሆኑ ገልጿል።

የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ በበኩላቸው ወጣቱ መብትና ግዴታውን ለይቶ በማወቅ የወንጀል ድርጊት እንዳይፈጸም የሚያግዝ መሆኑን ተረድቶ የግንዛቤ ስልጠናውን በተገቢው እንዲከታተሉ ገልፆል።

የንቃተ ህግ ትምህርት ንቅናቄው ማህበራዊ ሚዲያን በነጻነት ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሌሎችን መብትና ክብር ሳይጎዳ በኃላፊነት መጠቀም የሚገባ መሆኑን በማስገንዘብ፣ የህግ ጥሰቶችን ከመፈጸም በፊት ግንዛቤን በማሳደግ የህግ ተጠያቂነትን ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑ ታምኖበታል ብሏል።

የባይራ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች  የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ በቅሎ ሰኞ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር ለአ...
28/08/2026

የባይራ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

በቅሎ ሰኞ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

መንግስት ለትምህርት የሰጠው ትኩረት በሁሉንም ማህበረሰብ ክፍሎች ተቀባይነት እንዲያገኝና ውጤታማ እንዲሆን በዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ ተናግሯል።

በአቅም ውስንነት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ የሚሆኑ ልጆችን በመደገፍና በመርዳት ከሌሎች ጋር እኩል እንዲማሩና ለማድረግ ታልሞ እንደሚሰራ ተናግሯል።

በቀጣይም ጥራትን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆንና የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ዘላቂ ድጋፍ ይደረጋል ብሏል።

የወላይታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጤናዬ ትርንጎ በበኩላቸው በአቅም ውስንነት ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ያልቻሉ ልጆችን ለመደገፍ ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መቆየቱን ገልጿል።

ልጆች በአቅም ውስንነት ምክንያት ከቤተሰብ ተለይቶ ወደ ጎዳና እንዳይወጡና ከትምህርት እንዳይርቁ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ በመግለፅ ልጆችና ቤተሰቦች በቀጣይ የተሻለ ኑሮ ለመምራት ካገኙት ነገር መቆጠብና የራሳቸውን ለማደራጀት መጣር አለባቸው ብሏል።

‎የዲምቱ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ሥልጠና እየሰጠ ነው።‎‎በቅሎ ሰኞ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ‎‎ሥልጠናው...
28/08/2026

‎የዲምቱ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ሥልጠና እየሰጠ ነው።

‎በቅሎ ሰኞ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

‎ሥልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የዲምቱ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ እሸቱ እማሞ እንደተናገሩት በአሁኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ማህበራዊ ሚዲያ መረጃን በፍጥነት ለማግኘት፣ እውቀትን ለማስፋፋትና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ትልቅ እድል ይዞልን መጥቷል።

‎አያይዘውም ይህንን መልካም አጋጣሚ በኃላፊነት ስሜት ካልተጠቀምንበት፤ በተለይም የጥላቻ ንግግሮች እና ሐሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ የማህበረሰባችንን ሰላምና ሀገራዊ አንድነት የሚፈታተኑ ትልልቅ ተግዳሮቶች እንደሚሆኑ ሁላችንም የምንገነዘበው ሐቅ ነው ብለዋል።

‎​መንግስት እነዚህን አደጋዎች ለመከላከልና የመግለጽ ነፃነት በሌሎች ሰዎች መብትና ሰላም ላይ አደጋ እንዳያደርስ ለማድረግ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 በስራ ላይ መዋሉን አንስተው ይህም ሕግ አላማ ያደረገው የዜጎችን ሐሳብ የመግለጽ ነፃነት ማፈን ሳይሆን፣ መቻቻልን፣ መከባበርንና ኃላፊነት የተሞላበት የመረጃ አጠቃቀምን ማጎልበት ነው ሲሉ የተናገሩት።
‎​
‎​የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ኃላፊነት በተሞላበት አካሄድ ሰላማዊና መከባበር በሰፈነበት እንዲሁም ህግን ባከበረ መንገድ መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

‎የዲምቱ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ክላስተር አስተባባረ አቶ በረከት ሊሬ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ታስቦ ሥልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ከማስተላለፍ ይልቅ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

‎በሥልጠና መድረኩ የወላይታ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ በረከት ወርቁ፣
‎የዲምቱ ከተማ አስተባባሪዮች፣የዘርፍ አመራሮች የፖሊስ እና ጸጥታ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ቡሳጆ (BUSAJO) የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት የበቅሎ ሰኞ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምልከታ በማድረግ የመጽሐፍ ድጋፍ አደረጉ በቅሎ ሰኞ፤ ነሐሴ 19/2018ዓ.ም ቡሳጆ (BUSAJO) ...
25/08/2026

ቡሳጆ (BUSAJO) የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት የበቅሎ ሰኞ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምልከታ በማድረግ የመጽሐፍ ድጋፍ አደረጉ

በቅሎ ሰኞ፤ ነሐሴ 19/2018ዓ.ም ቡሳጆ (BUSAJO) የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የበቅሎ ሰኞ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምልከታ በማድረግ የትምህርት ጥራት ለማጠናከር 1ሺህ የመጽሐፍ በገንዘብ ከ2.7 ሚሊየን ብር በላይ የምገመት የመጽሐፍ ድጋፍ አድርጓል።

በመር-ሃግብሩ ላይ የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ባስተላለፉት መልእክት፣ ትምህርት የአንድ ሀገር የዕድገትና የብልፅግና መሠረት በመሆኑ ለትምህርት ዘርፍ የሚደረጉ ድጋፎች የወደፊቱን ትውልድ ለመገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ድጋፉ የተማሪዎችን የንባብ ባህል ለማሳደግ፣ የመማሪያ ሀብታቸውን ለማስፋት እና የትምህርት ጥራታቸውን ለማጠናከር ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ቡሳጆ(BUSAJO) ለተማሪዎች ያደረገውን የመጽሐፍት ድጋፍ በማድነቅ፣ ይህ ዓይነቱ በጎ ተግባር የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ከማሳደጉ ባሻገር የትምህርት ቤቶችን የመማሪያ ሁኔታ ለማሻሻል ጉልህ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

ቡሳጆ (BUSAJO) በኢትዮጵያ ደረጃ በሁሉም አከባቢ ላይ እያደረጉ ያለው ትምህርትን በመደገፍ የትውልዱን የትምህርት ዕድል ለማስፋት የሚያግዙ የበጎ አድራጎት ተግባራት አስፈላጊነትንም ያሳያል ስሉ አክለዋል።

በተጨማሪም ለተማሪዎች የሚደረግ የመጽሐፍትና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በተቋማት፣ በግል ዘርፍና ማህበረሰቡ በጋራ በመረባረብ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።

የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ በበኩላቸው ቡሳጆ (BUSAJO) ለበቅሎ ሰኞ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላደረገው የመጽሐፍት ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፉ ተማሪዎች በንባብ የበለጠ እንዲተጉና በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ትልቅ አበረታች ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ቡሳጆ (BUSAJO) በጎ ተግባር የትምህርት ተቋማትን በመደገፍ የተማሪዎችን የመማር ዕድል ለማስፋት የሚደረገው የጋራ ጥረት አንድ አካል ሲሆን፣ ተመሳሳይ ድጋፎች እንዲበረቱ ትልቅ አብነት ይሆናል ስሉ ተናግሯል።

በባይራ ኮይሻ ወረዳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ የቤት ቁሳቁስ (ኪት) አሰባሰብ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው በቅሎ ሰኞ፤ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞ...
25/08/2026

በባይራ ኮይሻ ወረዳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ የቤት ቁሳቁስ (ኪት) አሰባሰብ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

በቅሎ ሰኞ፤ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ የቤት ቁሳቁስ ከ600 መቶ በላይ (ኪት) በገንዘብ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተሰበሰበ።

በብታው የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ እንደተናገሩት ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት ዙሪያ ተቋማዊ አሠራርን መትከል፣ አደረጃጀቶችን በመጠቀም፣ በየማህበራዊ መሠረት ህዝቡን ማሳተፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጡ ጠቁሟል።

ተረጂነት አንገት የሚያስደፋ፣ የሚያዋርድ ብሎም የሀገር ሉአላዊነትን የሚያስደፍር ተግባር በመሆኑ በአስተሳሰብም ሆነ በተግባር ለመዋጋት እና የስራ ባህልን ለመቀየር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከተረጂነት አስተሳሰብ በመውጣት ፈተናዎችን በራስ አቅም የመቻል ጉዳይ ላይ በማተኮር ሀገራዊ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጽኖኦት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁሟል።

የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ለህብረተሰባችን ቀልጣፋ፣ግልጽና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መድረክ ነው ተባለ፦ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስበቅሎ ሰኞ፤ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም የወላይ...
25/08/2026

የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ለህብረተሰባችን ቀልጣፋ፣ግልጽና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መድረክ ነው ተባለ፦ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ

በቅሎ ሰኞ፤ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ ከባይራ ኮይሻ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በጋራ አዘጋጅነት "ሕግን ማወቅ ለአካባቢ ሰላም፣ለተፋጠነ ልማትና ለአስተማማኝ ፍትሕ!"በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የንቃተ-ህግ ትምህርት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።

በመድረኩ የወረደው ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ እንደተናገሩት በፍትህ ሥርዓታችን ውስጥ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት፣የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ለህብረተሰባችን ቀልጣፋ፣ግልጽና ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ሀሳቦችን በመለዋወጥ ወሳኝ መድረክ ነው ብሏል።

በቀጣይም በልዩ ዘመቻ በሚሠሩ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዙሪያ እስከ ታች በሚወረዱ መድረኮች የህግ ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ለማድርግ ያለመ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ የሚያበረክት መድረክ እንደሆነም ገልጿል።

አክለውም ዶ/ር አሸናፊ ‎ሕግን ማወቅ ማለት የሕግ አንቀጾችን በቃል መያዝ ብቻ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ዜጎች መብታቸው ምን እንደሆነ፣ግዴታቸው ምን እንደሆነ፣መብታቸው ሲጣስ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስዱበት መንገድ ምን እንደሆነና የሌሎችንም መብት ማክበር የጋራ ኃላፊነት መሆኑን መረዳት አሰፈላጊ መሆኑንም አክለዋል።

‎የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል ጋዳቦ በበኩላቸው የሕግ እውቀት በሕዝቡ ዘንድ ሲስፋፋ ግጭቶችን በሕጋዊ መንገድ የመፍታት ባህል ይጠናከራል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የሕግ ጥሰትን መከላከል ይቻላል፣ዜጎችም በፍትሕ ተቋማት ላይ ያላቸው ግንዛቤና እምነት እንደሚጨምርም አብራርቷል።

‎የፍትሕ ንቃተ ህግ ማሳደግ ለመንግሥት እንደ አንድ ተጨማሪ ሥራ ሳይሆን እንደ መሠረታዊ የአስተዳደር ኃላፊነት መታየት የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም አስምረውበታል።

‎የመንግሥት ተቋማት ሕግን በመከተል፣በግልጽነት በመሥራት፣ለዜጎች ተጠያቂ በመሆንና የሕግ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ለሕግ የበላይነት ተጨባጭ ምሳሌ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

‎በመድረኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ፣ የወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አየለ መንታ ፣ የወረዳው አሰተባባሪ አካላትና አጠቃላይ መካከለኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የኃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጉባኤው እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መላው እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 501ኛውን የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰ፦ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስየባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዶ...
25/08/2026

መላው እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 501ኛውን የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰ፦ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ

የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ መላው እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 501ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል።

የመውሊድ በዓል የሰላም መልዕክቶች የሚተላለፍበት፣ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የአብሮነትና የአንድነት መገለጫ ነው።

ከእምነቱ አስተምህሮ የምንማረው እውነትንና ታማኝነትን፤ ትህትንና መልካም ስነ-ምግባርን ነው። በጎነትንና ትግስትን፣ ፍትሕንና እኩልነትን ነው።

በዓሉ ተራርቀው የቆዩ የሚገናኙበት ፈጣሪያቸውን በጋራ የሚያመሰግኑበት በመሆኑ ማሕበራዊ ግንኙነትን በማጠናከር አንድነትንና ወንድማማችነትን ያጸናል።

መውሊድ የመቻቻል፣ የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶች ጎልተው የሚታዩበት በዓል ነው። እነዚህን ኃይማኖታዊ እሴቶች ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ በጋራ መስራት ይኖርብናል።

ስለሆነም ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር የተቸገሩ ወገኖቻችንን በማሰብና በመደገፍ እንዲሁም ሰላምን በመጠበቅ እና አንድነትን በማጠናከር ሊሆን ይገባል።

በወረዳችን የምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዞ
በወረዳችን የተጀመረችውን የልማትና የሰላም ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንድሞች እና እህቶች ጋር ጠንክራችሁ እንድታስቀጥሉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

በድጋሚ ለመላው ሕዝበ ሙስሊም፣ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁን!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ዒድ ሙባረክ!
ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ
የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ 1501ኛውን የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት "ለእስል...
25/08/2026

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ 1501ኛውን የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

"ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በሰላም (መውሊድ) አደረሳችሁ!

መውሊድ መተባበርና አብሮነት፣ መተዛዘንና መፈቃቀድ በተግባር የሚገለጽበት ነው። ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ ማኅበራዊ ትሥሥር የሚጠናከርበትና በአንድነት አብሮ የሚያሳልፉት ታላቅ በዓል ነው።

ይህ በዓል ለሌሎች መልካም ሥራ በመሥራት የሂሊና ዕረፍት የምናገኝበት፣ በሌሎች ደስታ የምንደሰትበት በአጠቃላይ በነቢዩ አስተምህሮ መሠረት ፍቅርን የምንጋራበት ድንቅ እሴቶች ያሉት በዓል ነው።

በዓሉን ስናከብር በነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ መሠረት የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ፣ በፍቅር እና በአብሮነት፣ በሰላም፣ በመተሳሰብ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት ሊሆን ይገባል።

በሙስሊሙ ዘንድ ያለው መተሳሰብ እና አንድነት ለሀገር አንድነት ወሳኝ በመሆኑ ከእምነቱ ተከታዮች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌላውም ጋር የተለመደ ወዳጅነት፣ ፍቅር እና አንድነት እየጎመራ ሊሄድ የሚገባ ነው።

በበዓል ጊዜ የሚታየው አንድነት በዘላቂነት በህዝቦች እና በአማኒያን መካከል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፣ ይህም ለአገር ግንባታ ሥራችን ወሰኝ ነው የሚል እምነት አለኝ። በመሆኑም በበዓሉ ጊዜ የሚታየው መተሳሰብ፣ መተባበር፣ አንድነትና ፍቅር ሁሌም ጎልቶ ሊቀጥል ይገባል።

በድጋሚ እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ!"

ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ነሐሴ/2018 ዓ.ም

"ኢትዮጵያ አሸንፋለች!
23/08/2026

"ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

Address

Bayra Koysha Woreda
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bayra Koysha Woreda Government Communication/የባይራ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share