Wolaita Asaa

Wolaita Asaa Wolaita Asaa official page

ይህ ጎሽ ማንን ይመስላል?
29/05/2026

ይህ ጎሽ ማንን ይመስላል?

ዛሬ የተወዳጇ ዘማሪት ሰላም ደስታ የ29ኛ  ዓመት የልደት ቀኗ ነዉ እንኳን ተወለድሽልን  መልካም የልደት ቀን ይሁንልሽ 🎉🎂🍕🎊
27/05/2026

ዛሬ የተወዳጇ ዘማሪት ሰላም ደስታ የ29ኛ ዓመት የልደት ቀኗ ነዉ እንኳን ተወለድሽልን መልካም የልደት ቀን ይሁንልሽ 🎉🎂🍕🎊

ለአርሴናል ደጋፊዎች ከወላይታ ሶዶ ፖሊስ የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ‼️😮ማሳሰብያ ለአውሮፓ እግር ኳስ ደጋፍዎች በሙሉ አርሴናል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፕዮን መሆኑ ይታወሳል።          ...
23/05/2026

ለአርሴናል ደጋፊዎች ከወላይታ ሶዶ ፖሊስ የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ‼️😮
ማሳሰብያ ለአውሮፓ እግር ኳስ ደጋፍዎች በሙሉ አርሴናል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፕዮን መሆኑ ይታወሳል።

በመሆኑም ነገ የዋንጫ እርክብክብ ስነ-ስራዓት መኖሩን ተከትለው አንድንድ ዲስፕልን ከሌላቸው ደጋፍዎች በአንድንድ ግለሰቦች ላይ ዛቻና መስፈራርያ እየደረሰ እንዳለ ለፖሊስ መረጃዎች እየደረሰ ይገኛል።ስለሆነም ደጋፊ ደስታውን ስገልጽ በደጋፊ ጨዋነት በአግባቡና በልክ መሆን እንዳለበትና የሌላ ክለብ ደጋፍ ስብዕና የምነካ መሆን እንደለለበት የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ያሳስባል። በዕለቱም ከ12:30 ሰዓት ጀምረው ባለ ሁለት እግር ሞቴር ሳይክል በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንም ይገልጻል። በተጨማር የትኛውንም ተሽከርካር ማሰለፍ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ ይገልጻል።አልፈው በምመጡት ላይም ፖሊስ እርምጃ በመውሰድ ሕግ የማስከበር ሥራ የሚሠራ መሆኑን ያሳስባል።

ወንጀልን በጋራ እንከላከል/////
የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ!

19/05/2026

ምን ጉድ ነው 😂
17/05/2026

ምን ጉድ ነው 😂

ሰው ወደ ውሻ ተቀየረ" የተባለው ወሬ ሰደድ እሳት ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እያነጋገረ ይገኛል። 🐕 በሀዋሳ ከተማ የተከሰተው ይሄ አስገራሚ ድርጊት መላውን ከተማ አስደንግጦ ውሏል። "ሰው ወ...
03/05/2026

ሰው ወደ ውሻ ተቀየረ" የተባለው ወሬ ሰደድ እሳት ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እያነጋገረ ይገኛል። 🐕

በሀዋሳ ከተማ የተከሰተው ይሄ አስገራሚ ድርጊት መላውን ከተማ አስደንግጦ ውሏል። "ሰው ወደ ውሻ ተቀየረ" የተባለው ወሬ ሰደድ እሳት ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እያነጋገረ ይገኛል። 😱
​ነገሩ እንዲህ ነው...

እንድ ሀዋሳ ከተማ ናዋሪው ማርቆስ ማቲያስ ገላፃ ይህ የምታዩት ውሻ (ፎቶው ካለህ እዚህ ጋር ትጨምረዋለህ) ከመሞቱ በፊት አበበ የተባለ ሰው እንደነበረና ድንገት ወደ ውሻነት እንደተቀየረ ይናገራል ።

​የተከሰተው ሁኔታ፦ አበበ ወደ ውሻ ሲቀየር ያዩት ሰዎች በድንጋጤ "ጥንቆላ ነው" በሚል ሊገድሉት ሲያሳድዱት፣ ውሻው በሚገርም ሁኔታ "እባካችሁ እኔ አበበ ነኝ፣ አትግደሉኝ!" እያለ በሰው ድምፅ ተማፅኗል ተብሏል።

የመጨረሻው ውጤት፦ ሆኖም ግን ሰዎቹ በድንጋጤና በፍርሃት ተሞልተው ድብደባውን ባለማቆማቸው አበበ ህይወቱ አልፏል።

ለመሆኑ ይሄ ነገር እውነት ሊሆን ይችላል? በቦታው የነበሩ ሰዎች ድርጊቱ እውነት መሆኑን እየመሰከሩ ቢሆንም፣ ብዙዎች ግን "እንዴት ሰው ወደ ውሻ ይለወጣል?" በሚል ጥርጣሬያቸውን እየገለጹ ነው። Via፦ ማርቆስ ማቲያስ ከሀዋሳ

​ እናንተስ ምን ትላላችሁ? በአሁኑ ዘመን እንዲህ ዓይነት የዓይን ምስክሮች ያሉበት "ተአምር" ወይስ "የተራቀቀ የፈጠራ ወሬ"? ሀሳብ አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን እስኪ ?

ግዮን ማለዳ

ቪዲዮ ከስር ባለው ቴሌግራም ይመልከቱ 👇

https://t.me/GhionMaleda

የዎላይታ ሶዶ መናኸሪያ ስውር ደባዎች፤ በተሳፋሪው እንግልት የሚከብሩ "ደላሎች" እና የመንግስት ያለህ ጥሪ!​የዎላይታ ሶዶ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ማዕከልና የንግድ መገናኛ በመሆኗ በቀን በሺ...
03/05/2026

የዎላይታ ሶዶ መናኸሪያ ስውር ደባዎች፤ በተሳፋሪው እንግልት የሚከብሩ "ደላሎች" እና የመንግስት ያለህ ጥሪ!

​የዎላይታ ሶዶ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ማዕከልና የንግድ መገናኛ በመሆኗ በቀን በሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች ያስተናግዳል። ሆኖም ግን፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ መናኸሪያ ውስጥ የሚስተዋሉ የተቀናጁ የሌብነት ሰንሰለቶች የአካባቢውን መልካም ስም ከማጥፋታቸውም በላይ፣ ህዝቡ በገዛ አገሩ ዋስትና እንዲያጣና ለከፍተኛ ምዝበራ እንዲጋለጥ አድርገውታል።

​ከህዝብ ለባካሊያ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በመናኸሪያው ውስጥ የሚፈጸሙት ዋና ዋና የሌብነት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡

​፩. የትኬት ደባ እና የወያላዎች "ንግድ"

​ትኬቶች በቀጥታ ለተሳፋሪው ከመሸጥ ይልቅ፣ ለወያላዎች ተቆጥረው ይሰጣሉ። ወያላዎቹም የራሳቸውን ትርፍ ጨምረው ለተሳፋሪው በውድ ይሸጣሉ። የሚገርመው ግን፣ ተሳፋሪው ትኬቱን በታሪፍ መሰረት ገዝቷል ተብሎ ቢታሰብም፣ መኪና ውስጥ ከገባ በኋላ "ታሪፉ ጨምሯል" በሚል ሌላ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፍል ይገደዳል። ይህ በግልጽ የቀን ዝርፊያ ነው።

​፪. ሆን ተብሎ የሚፈጠር የመኪና እጥረት (ሰው ሰራሽ ቀውስ)

​በመናኸሪያው የተሰለፈው ህዝብ ቁጥር እየታወቀ፣ አስገዳጅ ስምሪት አለመስጠትና መኪናዎችን ደብቆ ማቆየት የተለመደ ስልት ሆኗል። መኪኖቹ ቀኑን ሙሉ ተደብቀው ውለው፣ ምሽት ላይ ተሳፋሪው አማራጭ ሲያጣ ከመናኸሪያ ውጭ ካለ ህግና ታሪፍ በከፍተኛ ዋጋ ሲጭኑ ይስተዋላል።

​፫. ስውር ሴራና የማስፈራራት ተግባር

​የትኬት ቆራጭ ማህበራት ከባለቤቶች ጋር በመሻረክ "የፎርጅድ" ትኬቶችን እስከማተም ደርሰዋል። ትራፊክ ፖሊስ ታሪፍ ሲጠይቅ ተሳፋሪው እውነቱን እንዳይናገር "ሌላ ጊዜ አንጭናችሁም" በሚል ማስፈራራት ይደርስበታል። ይህ ድርጊት ህግን ለማስከበር ሌት ተቀን የሚደክመውን የትራፊክ ፖሊስ ስምና ዝና የሚያጎድፍ፣ በታማኝ ሰራተኞች ስም የሚነግድ ነውር ነው።

​መፍትሄ የሚሹ ነጥቦች (የመፍትሄ አቅጣጫ)

​ይህ አይነቱ ሌብነት በባህሪው የተወሳሰበና በኔትወርክ የተሳሰረ በመሆኑ፣ ተራ ፍተሻ ብቻውን በቂ ላይሆን ይችላል። ስለዚህ፡

​ድብቅ ፍተሻ (Undercover Investigation): የመንግስት የጸጥታ አካላት እንደ ተራ ተሳፋሪ በመሆን የሌብነቱን ሰንሰለት ከውስጥ ሆኖ ማጥናትና እርምጃ መውሰድ አለባቸው።

​የቴክኖሎጂ አጠቃቀም: የትኬት ሽያጭ ስርዓቱን ዲጂታይዝ በማድረግና በየመኪናው ውስጥ የቅሬታ መቀበያ ስልኮችን በግልጽ በመለጠፍ ሌብነቱን መቆጣጠር ይቻላል።

​የማህበራት ተጠያቂነት: በስሙ ትኬት የሚቆረጥበት ማህበርም ሆነ የመኪናው ባለቤት፣ በቅሬታው መሰረት ፍቃዳቸው እስከመሰረዝ የሚደርስ ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል።

​ማጠቃለያ

የዎላይታ ሶዶ ከተማ እንግዳ ተቀባይነትና የህዝቧ ደግነት በእነዚህ ጥቂት ስግብግብ ግለሰቦች ምክንያት መጠልሸት የለበትም። መንግስት የህዝቡን ጩኸት ሰምቶ፣ በመናኸሪያው አካባቢ የተሰገሰጉትን ደላሎችና ሌቦች ለህግ እንዲያቀርብ ባካሊያ ሚዲያ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

​ፍትህ ለተሳፋሪው! ስርአት ለመናኸሪያችን!

በሚስቱ የተቆረጠው የወንድ ብልት በስፌት ተቀጠለ   I በአርሲ ዞን በትዳር አጋራቸው ጥቃት ደርሶባቸው ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ የወደቀው የ42 ዓመት ጎልማሳ ብልት፣ በአሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በተደ...
30/04/2026

በሚስቱ የተቆረጠው የወንድ ብልት በስፌት ተቀጠለ

I በአርሲ ዞን በትዳር አጋራቸው ጥቃት ደርሶባቸው ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ የወደቀው የ42 ዓመት ጎልማሳ ብልት፣ በአሰላ ሪፈራል ሆስፒታል በተደረገ የ3 ሰዓታት ስኬታማ ቀዶ ህክምና ተመልሶ መገጠሙ ተነገረ።

ድርጊቱ የተፈጸመው ከአንድ ወር በፊት ሲሆን፣ በግለሰቡና በባለቤታቸው መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ባለቤታቸው እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ላይ በስለት ሙሉ በሙሉ በመቁረጥ መሬት ላይ ጥለውታል። የ6 ልጆች አባት የሆኑት ተጎጂው፣ የተቆረጠውን ብልታቸውን በፌስታል ጠቅልለው በመያዝ በራሳቸው ጥረት በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መድረሳቸው ታውቋል።

የኩላሊትና የሽንት ቧንቧ ስፔሻሊስት ዶ/ር ፍቃዱ ሀብታሙ እንደገለጹት፣ ህክምናው የተከናወነው ጉዳቱ በደረሰ በ3 ሰዓት ውስጥ ግለሰቡ ሆስፒታል በመድረሳቸው ነው። በጥንቃቄ ለ3 ሰዓታት በተደረገ ስፌት ብልቱ ወደ ቦታው የተመለሰ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ተጎጂው በሽንት ቧንቧቸው በኩል መሽናት መጀመራቸውንና የጤና ሁኔታቸው በመሻሻል ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

እንዲህ ዓይነት ጉዳት ሲያጋጥም በ6 እና በ8 ሰዓታት ውስጥ ሆስፒታል መድረስ ለስኬታማነቱ ወሳኝ ነው ተብሏል። ብልቱ የመቆም እና የግብረ-ሥጋ ግንኙነት የመፈጸም እድሉ ከፍተኛ ቢሆንም፣ እንደ ቀድሞው ሙሉ ጥንካሬ ላይኖረው እንደሚችል ተገልጿል።

የተቆረጠው አካል በንጹህ ፌስታል ተጠቅልሎ ሳይቆሽሽ በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም መወሰድ አለበት።

ተጎጂው በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል ክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ለደህንነታቸውና ለግል ሚስጥራቸው ሲባል ማንነታቸውና ዝርዝር አድራሻቸው እንዳይገለጽ ተደርጓል ሲል ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘግቧል።
ምስል ኤአይ

ግዙፉ ሺንግሻን ኢንዱስትሪ(Tsingshan Industry) በኢትዮጵያ  በብረትና አይረን ምርት ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልግ ተገለፀ።አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21/ 2018 ዓ.ም(ኢ.ኢ.ኮ...
29/04/2026

ግዙፉ ሺንግሻን ኢንዱስትሪ(Tsingshan Industry) በኢትዮጵያ በብረትና አይረን ምርት ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልግ ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21/ 2018 ዓ.ም(ኢ.ኢ.ኮ) ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ከሺንግሻን ኢንዱስትሪ (Tsingshan Industry) ልኡካን ቡድን ጋር ኩባንያው በኢትዮጵያ መዋለ ንዋዩን ማፍሰስ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ከባቢውን ለማሻሻል ተግባራዊ እያደረገች ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ባለሃብቶች የሚያነሱትን ጥያቄ ለመፍታት እንዳስቻለ ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ አክለውም መንግስት ለሺንግሻን ኢንዱስትሪ ስኬታማነት አስፈላጊ የሆኑ እንደ ኤሌክትሪክ ኃይል ያሉ መሰረተ ልማቶችን በበቂ ሁኔታ የሚያቀርብ መሆኑን ጠቅሰው የኢንቨስትመንት ኮሚሽንም ለኩባንያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ መላው አፍሪካ ላይ እንደማፍሰስ እንደሚቆጠር የገለጹት አቶ ዳጋቶ፣ ኩባንያው በድሬዳዋ እና በገዳ የነፃ ንግድ ቀጠናዎች ጨምሮ በሌሎች አማራጮች ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኩባንያው አመራሮች በበኩላቸው በኢትዮጵያ በብረትና አይረን ምርት ዘርፍ መሰማራትና መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንደሚፈልጉ በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል።

ሺንግሻን ኢንዱስትሪ እ.ኤ.አ. በ1992 በቻይና የተመሰረተና በዓለም አቀፍ ደረጃ በብረት፣ በኒኬል እና በሊቲየም ባትሪ ምርት ቀዳሚነቱን የያዘ ግዙፍ ተቋም ሲሆን፤ በአሜሪካ፣ በቻይና፣ በኢንዶኔዥያ፣ በህንድ፣ በዚምባብዌ እና በአርጀንቲና የምርት ማዕከላት አሉት።

ኩባንያው እ.ኤ.አ በ2025 ከ60 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሽያጭ ገቢ ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን፤ በየዓመቱ ከ22 ሚሊዮን ቶን በላይ ብረት (stainless steel) እና 1.5 ሚሊዮን ቶን ኒኬል በማምረት በዘርፉ በስፋት እየሰራ ይገኛል።

Global Giant Tsingshan Industry Expresses Interest in Investing in Ethiopia’s Steel and Iron Sector

Addis Ababa, April 29, 2026 (EIC):

The Deputy Commissioner of the Ethiopian Investment Commission, H.E. Dagato Kumbe, held discussions with a delegation from Tsingshan Industry regarding the company’s potential investment opportunities in Ethiopia.

During the meeting, H.E. Dagato Kumbe stated that the macroeconomic reforms currently being implemented by Ethiopia to improve the investment climate have been instrumental in addressing key questions raised by investors.

The Deputy Commissioner further emphasized that the government is committed to providing essential infrastructure, such as adequate electric power, to ensure the success of Tsingshan Industry's operations. He also reaffirmed that the Investment Commission will provide all necessary support to the company.

 #የወልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኬኒያ ናይሮቢበኬንያ የወላይታ ልማት  ማህበር ቅርንጫፍ ተመሰረተበዛሬዉ ዕለት በኬንያ የሚኖሩ ከ500 በላይ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች በአንድነት ተሰብስበው የወ...
25/04/2026

#የወልማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኬኒያ ናይሮቢ
በኬንያ የወላይታ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ተመሰረተ

በዛሬዉ ዕለት በኬንያ የሚኖሩ ከ500 በላይ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች በአንድነት ተሰብስበው የወላይታ ልማት ማህበር ኬንያ ቅርንጫፍ በይፋ አቋቁመዋል። የቅርጫፉ ምስረታ የተካሄደዉ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሲሆን ቅርንጫፉን ለአንድ ዓመት የሚያስተባብሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል፤ በመተዳደሪያ ደንብ ላይ ዉይይት ተደርጎም ጸድቋል።

በምስረታዉ ስነ-ስርዓት በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ባጫ ደበሌ እና የሚስዮኑ ምክትል መሪ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ተገኝተዉ መድረኩን ከወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አበባየሁ ጋር በጋራ በመሆን መርተዋል፤ ንግግርም አድርገዋል።

በምስረታዉ ስነ-ስርዓት ላይ የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበባዬሁ ቶራ የተገኙ ሲሆን ዶ/ር አበባዬሁ በንግግራቸው የኬንያ ቅርንጫፍ መመስረት በውጭ ሀገር ያሉ ወገኖች በወላይታ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያጠናክር እና ማህበሩ በሚያከናዉናቸዉ በትምህርት፣ በጤና፣ በመሠረተ ልማት እና በማህበራዊ ዘርፎች የሚካሄዱ ተግባራትን ለመደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

Wolaytta Worqaa Mayzzana!

Address

Sodo
WOLAITASODO

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Asaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share