Wolaita Sodo City Land Administration Department

Wolaita Sodo City Land Administration Department Striving to to Build Vibrant Digital City!! Striving to Build Vibrant Digital City

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ህብረት አባላት "ጠንካራ አደረጃጀት ለተሳካ ምርጫ" በሚል መሪ ሃሳብ ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ተካሂዷል ወላይታ ሶዶ፦ግንቦት 3/2018 ዓ.ም የ...
11/05/2026

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ህብረት አባላት "ጠንካራ አደረጃጀት ለተሳካ ምርጫ" በሚል መሪ ሃሳብ ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ተካሂዷል

ወላይታ ሶዶ፦ግንቦት 3/2018 ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ህብረት አባላት "ጠንካራ አደረጃጀት ለተሳካ ምርጫ" በሚል መሪ ሃሳብ ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ተካሂዷል ።

መድረኩ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ መንትያ ግቦች በማሳካት እንዲጠናቀቅ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል ።

"ምርጫ የዴሞክራሲ መገለጫና የህዝብ ድምጽ ማረጋገጫ መሆኑን የገለፁት የብልፅግና ህብረት አባላት ምርጫው ሰላማዊና ቅቡልነት ባለው መንገድ እንዲጠናቀቅ ከመስራት ባለፈ በፓርቲው አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጿል ።

ፓርቲው በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ የገለጹት የብልፅግና ህብረት አባላት አደረጃጅቶችና አባላት የተሰሩ ስራዎችን በአግባቡ ማሳወቅ እንዳለበትም ገልጸዋል።

በከተማ ከ150 ሺህ በላይ መራጮች የምርጫ ካርድ ማውጣታቸው የህዝቡን ከፍተኛ ተሳትፎና የዴሞክራሲ ግንዛቤ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማ በሁሉም አካባቢዎች በተካሄዱ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፎች የታየው ህዝባዊ ተሳትፎም ህብረተሰቡ ለፓርቲያችን ያለውን አለኝታነት በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።

በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት የታየው ህዝባዊ ተሳትፎ ከምርጫው ሂደት እስከ ድህረ ምርጫው ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ጠንካራ አደረጃጅት ጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስትና ሀገረ መንግስት ለመገንባት ፋይዳው ጉልህ መሆኑን የገለፁት የብልፅግና ህብረት አባላት ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ምቹ አውድ በመፍጠር ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አካሒዶ ምረጫውን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ አደረጃጅቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በከተማችን ፣ በክልላችንና እንደ ሀገር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ ፓርቲ መሆኑንም አንስተዋል።

ክፍል 1የአመራር ዘይቤዎችን መረዳት፡ በጥበብ እና በተለዋዋጭነት የመምራት ኃይልአመራር ለሁሉም የሚስማማ ኃላፊነት አይደለም። እያንዳንዱ መሪ በባህሪ፣ ራዕይ፣ ልምድ፣ አካባቢ እና በሚያገለግሉ...
11/05/2026

ክፍል 1
የአመራር ዘይቤዎችን መረዳት፡ በጥበብ እና በተለዋዋጭነት የመምራት ኃይል

አመራር ለሁሉም የሚስማማ ኃላፊነት አይደለም። እያንዳንዱ መሪ በባህሪ፣ ራዕይ፣ ልምድ፣ አካባቢ እና በሚያገለግሉት ሰዎች ፍላጎት የተነካ ልዩ አቀራረብ አለው። ከላይ ያለው ምስል ድርጅቶችን፣ ማህበረሰቦችን፣ መንግስታትን፣ ንግዶችን፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ እንቅስቃሴዎችን የሚቀርጹ በርካታ ዋና ዋና የአመራር ዘይቤዎችን ያጎላል።
አንድ ታላቅ መሪ ውጤታማ አመራር ሰዎችን ስለመቆጣጠር ሳይሆን ስለ ተጽዕኖ ማሳደር፣ ስለማብቃት፣ ስለመምራት እና ትርጉም ያለው ውጤት ስለማምጣት እንደሆነ ይረዳል። የተለያዩ ሁኔታዎች የተለያዩ የአመራር ዘይቤዎችን ይፈልጋሉ፣ እና አስተዋይ መሪዎች መቼ መላመድ እንዳለባቸው ያውቃሉ።
1. ባለራዕይ አመራር

ባለራዕይ መሪዎች ስለወደፊቱ ጊዜ ያተኩራሉ። ሰዎች ወዴት እየሄዱ እንደሆነ እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ግልጽ በሆነ ምስል ያነሳሱ። እነዚህ መሪዎች ከአሁኑ ገደቦች በላይ ባሉ እድሎች እንዲያምኑ የሚያበረታቱ የህልም ገንቢዎች ናቸው።

ባለራዕይ አመራር ኃይለኛ ነው ምክንያቱም አቅጣጫ፣ ዓላማ እና ተስፋ ስለሚፈጥር። ሰዎች በተፈጥሯቸው ወዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁ መሪዎችን ይከተላሉ።

ሆኖም፣ ባለራዕይ መሪዎችም ተግባራዊ ሆነው መቆየት አለባቸው። ያለተግባር ራዕይ ምናባዊ ብቻ ይሆናል።
2. የቡድን አመራር

በቡድን ላይ ያተኮሩ መሪዎች በትብብር እና በአንድነት ያምናሉ። ስኬት ብቻውን እምብዛም እንደማይገኝ ይገነዘባሉ። የግለሰብን ክብር ከማበረታታት ይልቅ በጋራ ስኬት ላይ ያተኩራሉ።

ይህ የአመራር ዘይቤ ግንኙነትን፣ መተማመንን፣ ትብብርን እና የጋራ ኃላፊነትን ያበረታታል። የቡድን መሪዎች ሰዎች ዋጋ እንዳላቸው እና እንደተካተቱ የሚሰማቸውን አካባቢዎች ይፈጥራሉ።

ጠንካራ ቡድኖች ብዙውን ጊዜ ተገልለው የሚሰሩ ተሰጥኦ ያላቸውን ግለሰቦች በተሻለ ሁኔታ ይቆጣጠራሉ።
3. ዴሞክራሲያዊ አመራር

ዴሞክራሲያዊ መሪዎች ሌሎችን በውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ ያሳትፋሉ። ሀሳቦችን ያዳምጣሉ፣ ተሳትፎን ያበረታታሉ እና ከቡድን አባላት የሚሰጡ አስተያየቶችን ከፍ ያደርጋሉ።

ይህ አካሄድ ሰዎች ሰምተው እና ተከብረው ስለሚሰማቸው ታማኝነትን እና ባለቤትነትን ይገነባል። ዴሞክራሲያዊ አመራር ፈጠራ እና ትብብር አስፈላጊ በሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ይሰራል።

ሆኖም፣ ከመጠን በላይ ምክክር አንዳንድ ጊዜ በአስቸኳይ ሁኔታዎች ውስጥ የውሳኔ አሰጣጥን ሊያዘገይ ይችላል።
4. ስትራቴጂካዊ አመራር

ስትራቴጂካዊ መሪዎች ስለ ረጅም ጊዜ ግቦች፣ አደጋዎች፣ እድሎች እና ዘላቂነት በጥንቃቄ ያስባሉ። እርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ሁኔታዎችን በጥልቀት ይተነትናሉ።

እነዚህ መሪዎች እቅድ አውጪዎች ናቸው። አመራር ስለ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ስለ ነገም ስለመዘጋጀት ጭምር እንደሆነ ይገነዘባሉ።

ስትራቴጂካዊ አመራር በንግድ፣ በፖለቲካ፣ በተቋማት እና ፈጣን ለውጥ ወይም ውድድር በሚገጥማቸው ድርጅቶች ውስጥ አስፈላጊ ነው።
5. የትራንስፎርሜሽን አመራር

የትራንስፎርሜሽን መሪዎች ጥልቅ ለውጥን ያነሳሳሉ። ሰዎች ከመካከለኛ ደረጃ በላይ እንዲያድጉ፣ እንዲሻሻሉ እና እንዲነሱ ይፈታተናሉ።

ስርዓቶችን ከማስተዳደር ይልቅ፣ የትራንስፎርሜሽን መሪዎች የአስተሳሰብ፣ የባህል እና የህይወት ለውጥ ያደርጋሉ። ፍቅርን፣ ፈጠራን፣ ዲሲፕሊን እና የግል እድገትን ያቀጣጥላሉ።

ብዙ ተደማጭነት ያላቸው የዓለም ለዋጮች እና የተሃድሶ አራማጆች በትራንስፎርሜሽን አመራር በኩል ይንቀሳቀሳሉ ምክንያቱም ከውስጥ ሰዎችን በመቀየር ላይ ያተኮሩ ናቸው።

"ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት  ቅንጅት ወሳኝ ነው።" አቶ ሙሉቀን ታደሰየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ለዞንና ሬጂኦ ፖሊሲ ከተማ ...
11/05/2026

"ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው።" አቶ ሙሉቀን ታደሰ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ለዞንና ሬጂኦ ፖሊሲ ከተማ ፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች፣ ለምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ለባለድርሻ አካላት በምርጫ ህጎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ ነው።

ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (ወዞመኮአ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ለዞንና ሬጂኦ ፖሊሲ ከተማ ፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች፣ ለምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ለባለድርሻ አካላት በምርጫ ህጎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ መስጠት ጀምሯል።

ሥልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ እንደተናገሩት ምርጫው ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው።

ፍርድ ቤትና ዐቃቤ ህግ በምርጫ ዙሪያ የሚቀርቡ የፍትህ ጥያቄዎች በፍፁም ገለልተኝነት ውሳኔ ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤት በተቀመጡ አሠራሮች መሠረት የሚፈጠሩ ችግሮችን በምክክር መፍታት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፍትህ ሴክተር የሚቀርቡ ከምርጫ ጋር የሚያያዙ ጉዳዮችን ፍትህ ለመስጠት በዕውቀት ለመምራት የሚሰጠው ሥልጠና አቅም የሚሰጥ እንደሆነም ተናግረዋል።

11/05/2026
11/05/2026

ሚዲያዎች የእውነት ምንጭ እና የሀገር መንፈስ መሆን አለባቸው - ብልፅግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚዲያዎች ሙቀት ሳይሆን ብርሃን መፍጠር ላይ ማተኮር፤ ጫጫታ ላይ ሳይሆን የእውነት ምንጭ እና የሀገር መንፈስ መሆን አለባቸው አለ ብልፅግና ፓርቲ።

ፓርቲው “ሚዲያ የሀገር መንፈስ ነው” በሚል መሪ ሐሳብ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

ዓለም አቀፍ የሚዲያ ቀንን ምክንያት በማድረግ “የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በተከታታይ ሳምንታት ሲካሄዱ የቆዩ ሚዲያ ላይ ያተኮሩ መድረኮች በዘርፉ የታዩት ስኬቶችንና በቀጣይ የሚጠበቁ ቁልፍ ተግባራትን በማመላከት በስኬት ተጠናቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ደማቅ የማጠቃለያ መድረክ ላይ ጥልቅ የሚዲያ ዕይታዎችና ዕሳቤዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፤ ለዘርፉ ተዋንያንና ለመላው ህዝብም መልዕክቶች ተላልፈውበታል፡፡

ከዕሳቤዎቹና መልዕክቶቹ መካከል ሚዲያ የሀገር መንፈስ መሆኑን የሚገልጽ ይገኝበታል፡፡ ይህ መንፈስ ሲታወክ ሀገር ትታወካለች፤ ሲረጋጋ ደግሞ ሀገር ታድጋለች፣ ትበልጽጋለች፡፡ በዚህ መሠረት ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከፈተው የዴሞክራሲ ምህዳር በዋናነት የተሰጠን ነፃነት ብቻ ሳይሆን ኃላፊነትም ጭምር ነው። የሚዲያ ጉዞው እንከን አልባ ባይሆንም የተመዘገቡት ስኬቶች እጅግ ግን ተስፋ ሰጪ ናቸው። በተለይ የሚዲያ ምህዳሩን በዴሞክራሲያዊ አውድ ለመዋጀት የተወሰዱ እርምጃዎች ለሀገር ግንባታ ጠንካራ መሠረት ጥለዋል። ዛሬ ላይ ሚዲያዎቻችን ከጥላቻ ትርክት እና ከዋልታ ረገጥነት ወጥተው በእውነት ላይ የተመሰረተ ትረካ መገንባት የሚጠበቅባቸው ወቅት ላይ ናቸው።

ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባው ተመሳሳይ ሀሳቦችን በማስተጋባት ብቻ ሳይሆን ተቃራኒ ሀሳቦችንም በማስተናገድ ነው። ስለሆነም የሚዲያ አውታረ-መረቦቻችን የራስን ሀሳብ ብቻ ከመጫን ወጥተው ልዩነቶች በሰላም የሚስተናገዱበት መድረክ መሆን ይኖርባቸዋል። ባለፉት ዓመታት የታዩት ከፍተቶችም ትምህርት ሊሆኑን ይገባል። እውነተኛ የሚዲያ እመርታ የሚለካው በተለያዩ ሀሳቦች መካከል ድልድይ በመሆን እና ለብሔራዊ መግባባት በሚሰሩ ሥራዎች ነው። ሚዛናዊነትን የጠበቀ፣ ለህዝብ ቅርብ የሆነ እና ከተጽዕኖ ነፃ የሆነ አጠቃላይ የሚዲያ አውድ መፍጠር የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታችን መሠረት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ዓለም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ትግል ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት ሚዲያዎቻችን በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥልቅ ትንተና ማቅረብ ለነገ የማይባል የቤት ሥራ ነው፡፡ መንግስት የገነባው ብሔራዊ የመረጃ ቋት "National Cloud" የቴክኖሎጂ መሠረት ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነታችን እና የመረጃ ደህንነታችን መከታ ነው። ይህንን መሰረት በመጠቀም በማህበራዊ ሚዲያ የሚነዙ የሀሰት መረጃዎችን በመመከት እና የድህረ-እውነት ዘመን የሚያመጣውን የስነ-ልቦና ጦርነት በመጋፈጥ ረገድ ሚዲያው ግንባር ቀደም መሆን አለበት። ቴክኖሎጂን የታጠቀ፣ በጥናት የተደገፈ እና ለሀገር አዎንታዊ ገጽታ ለመገንባት የማይሳቀቅ ሚዲያ ለኢትዮጵያ የማይተካ አቅም ነው።

ሚዲያዎች ሙቀት ላይ ሳይሆን ብርሃን መፍጠር ላይ ማተኮር፤ ጫጫታ ላይ ሳይሆን የእውነት ምንጭ እና የሀገር መንፈስ መሆን አለባቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት “ሙቀት የሚፈጥሩ ሚዲያዎች ብርሃን መሆን አይችሉም”ና የሚዲያ አውታሮቻችን ከጊዜያዊ ገጽታ ግንባታና ቁንጽል ሀሳብ ሽያጭ ይልቅ ለሀገራዊ አጀንዳዎች እና የወል ትርክት ትኩረት በመሥጠት የብልፅግና መንገድ ጠራጊ እንዲሆኑ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

11/05/2026

የሀገራዊ ምክክር ዋጋ ስንት ነው?

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሃሳብ ልዩነቶች ምክንያት የገባችባቸውን አስከፊ ግጭቶች ስንመለከት እንደ ሀገር የደረሰብን ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ኪሳራዎች እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በዘመናት ለተፈጠሩ ቅራኔዎች እና ቁርሾዎች መፍትሔ ለማፈላለግ የተሄደባቸው የተለያዩ የግጭት መፍቻ መንገዶችንም ስንመለከት ለተለያዩ የሙዓለ-ነዋይ ወጪዎች እንደዳረጉን ተመልክተናል፡፡

ለመሆኑ ከሌሎች የግጭት መፍቻ መንገዶች ጋር በትይዩ ሀገራዊ ምክክር ምን ያህል ወጪ ሊያስወጣ እንደሚችል ገምተው ያውቃሉ? የሀገራዊ ምክክር የመጨረሻው ግብ የሰው ልጆችን እልቂት አስቀርቶ መግባባትን ዕውን ማድረግ በመሆኑና ይህም በገንዘብ የማይተመን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሂደቱ የተለያዩ ወጪዎችን ሊያስከትል እንደሚችል ይታወቃል፡፡

በእርግጥ ሀገራዊ ምክክር ከበርካታ የግጭት መፍቻ መንገዶች ጋር ሲነፃፀር በተለያዩ ረገዶች አነስተኛ ሊባል የሚችል ወጪን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሂደቱን ለማከናወን መሰረታዊ የሎጂስቲክስ፣ የጊዜ እና ተያያዥ ጉዳዮች በራሳቸው በሙዓለ-ነዋይነት የሚያዙ ቢሆንም ሀገራዊ ምክክር በዋነኛነት የሚጠይቃቸው ወጪዎች ተፈጥሮ ግን ከሌሎች የግጭት መፍቻ መንገዶች ይለያል፡፡ እነዚህ ወጪዎች የተመካካሪዎችን ሥነ-ልቦና ማዕከል ያደረጉ ሲሆን በአመዛኙ ሰብዓዊነት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ የሚከተሉት ሃሳቦች ሀገራዊ ምክክር ከሌሎች የግጭት መፍቻ መንገዶች ጋር ሲነፃፀር የሚጠይቀውን ዋጋ ከብዙው በጥቂቱ ያብራራሉ፡፡

👉ስምምነት ላይ ለመድረስ መስዋዕትነትን መክፈል
በአንዳንድ ሀገራት በተደረጉ የምክክር ሂደቶች ያለፉ የፖለቲካ ኃይሎች መግባባትን ዋነኛ ዓላማቸው አድርገው ወደ ሂደቱ በመግባታቸው ሁሉም በየበኩላቸው እጅግ ከባድ ሊባሉ የሚችሉ የመርህ እና የአቋም ማስተካከያዎችን አድርገዋል፡፡ ይህም ከራስ በላይ ሀገርን በማስቀደም የጊዜ፣ የዕውቀት፣ የጉልበት፣ የሥነ-ልቦና እና የስሜት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆንን እንደሚጠይቅ ያስገነዝበናል፡፡

👉ከፉክክር መንፈስ ይልቅ በሰብዓዊነት የሌሎችን ችግር ለማድመጥ መዘጋጀት
ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እርስ በእርሳቸው በሰብዓዊነት እና በርህራሄ አንዱ የሌላውን ችግር እንዲያዳምጡ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ ከፉክክር እና ክርክር መንፈስ ይልቅ ሌላውን በእውነት ለመረዳት በር ከፋች ነው፡፡ ይህም በተለያየ ደረጃ ሊገለፁ የሚችሉ የሞራል እና የሥነ-ልቦና ጥንካሬ እንደሚጠይቅ መመልከት ይቻላል፡፡

👉 ለዘመናት የያዝናቸውን አቋሞች ለመቀየር መፍቀድ
በሀገራዊ ምክክር ውስጥ ተሳትፎን ስናደርግ አንዳችን ሌላችንን በአግባቡ ሳንረዳ የተለያዩ አስተሳሰቦችን እና የገነገኑ አመለካከቶችን አዳብረን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ ሂደት ሁሉም ባለድርሻ አካል የራሱን ሰብዓዊ እውነታ ይዞ የሚቀርብበት በመሆኑ ከአንዳንድ አቋሞች ጀርባ ያሉ ፍላጎቶችን እና እውነታዎችን እንድንገነዘብ ምክንያት ይሆነናል፡፡ ይህም ተመካካረዎች አንዳንድ እውነታዎችን በሚገነዘቡበት ወቅት አቋሞቻቸውን እንዲለውጡ እና የእኔ ብለው የያዙትን ‘እውነታ’ ዳግም እንዲያጤኑት ያደርጋል፡፡

👉ትዕግስት እና ፅናትን ማጎልበት
የሀገራዊ ምክክር ሂደት የአንድ ቀን ወይም የአንድ ወቅት ክስተት እንደማይሆን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሂደቱ ባልተግባባንባቸው ጉዳዮች ላይ ምንአልባትም ለአመታት ለመነጋገር ፍቃደኝነታችን የሚጠይቅ እንደሚሆን ማወቁ ጠቃሚ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ የማንግባባቸው ጉዳዮች መኖራቸው ለግጭት መንስኤ እንዳይሆኑ ተስማምተን በምክክር በይደር እያቆየን ለመፍታት መወሰን በራሱ የሥነ-ልቦና፣ የስሜት እና የጊዜ መስዋዕትነትን ያስከፍላል፡፡
በመሆኑም ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ራሳችንን በታማኝነት ፈትሸን በሃሳብ ልዮነቶች ላይ ለመነጋገር መፍቀዳችንን የሚጠይቅ ሂደት እንደመሆኑ በቁጥር የማይተመኑ ረቂቅ የሆኑ ዋጋዎች ይኖሩታል፡፡ ይህም ውድ የሆነውን የሰው ልጆችን ህይወት ከሚቀጥፈው ጦርነት ጋር ሲነፃፀር ምክክር አዋጭ የመግባቢያ መንገድ እንደሆነ መገንዘብ ያስችላል፡፡

ሀገራዊ ምክክር ለሀገራዊ መግባባት!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡ አስደናቂ ስኬቶች********************ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ የተቀናጁ የልማት ሥራዎች 96 ሺህ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር የተቻለ ሲሆን...
11/05/2026

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡ አስደናቂ ስኬቶች
********************

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ የተቀናጁ የልማት ሥራዎች 96 ሺህ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም 2.1 ትሪሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማስመዝገብ ችለዋል።

የማምረቻ ዘርፉ የገበያ ድርሻ ከ25 በመቶ ወደ 46 በመቶ በማደግ ከፍተኛ እመርታ የታየበት ሲሆን፣ በወርቅ ኤክስፖርት ረገድም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

እነዚህ አሃዛዊ እውነታዎች የሀገራችን የኢኮኖሚ ጉዞ በጠንካራ መሠረት ላይ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው።

11/05/2026
ከጂኦግራፊያዊ እስረኝነት ወደ ቀጣናዊ መሪነትኢትዮጵያ በታሪክ ማኅደር ስሟ ከቀይ ባሕርና ከዓለም አቀፍ የንግድ መተላለፊያ መስመሮች ጋር ተሳስሮ የቆየ ሀገር ናት። ይሁን እንጂ ባለፉት ሦስት ...
11/05/2026

ከጂኦግራፊያዊ እስረኝነት ወደ ቀጣናዊ መሪነት

ኢትዮጵያ በታሪክ ማኅደር ስሟ ከቀይ ባሕርና ከዓለም አቀፍ የንግድ መተላለፊያ መስመሮች ጋር ተሳስሮ የቆየ ሀገር ናት። ይሁን እንጂ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ "የየብስ እስረኛ" (Landlocked) ሆና እንድትቆይ መደረጓ፥ በልማቷ፣ በደኅንነቷና በሉዓላዊነቷ ላይ ትልቅ አደጋ ደቅኖ ቆይቷል። ዛሬ ላይ የባሕር በር ጥያቄ የፍላጎት ጉዳይ ሳይሆን የ130 ሚሊዮን ሕዝብ የህልውና እና የብሔራዊ ጥቅም ማረጋገጫ ሆኖ ብቅ ብሏል።

ኢትዮጵያ የታሪክ እና የሞራል ልዕልና ባለቤት ናት፤ ኢትዮጵያ የባሕር በር የነበራት ሀገር መሆኑ የታሪክ ድንገቴ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀቅ ነው። ከአክሱም ስልጣኔ ጀምሮ የአዱሊስ ወደብ የዓለም የንግድ ማዕከል እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያረጋግጣሉ። የባሕር በር ማጣት በሂደት የተከሰተ የታሪክ ስብራት እንጂ የሕግ ውጤት አይደለም።

በ1993ቱ የኤርትራ መገንጠል ሰበበ-ምክንያት፥ ኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ እንድትሆን የተደረገው በወቅቱ በነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች ስምምነት እንጂ፥ በሕዝብ ውሳኔ (Referendum) የታገዘ አልነበረም። ይህም ጥያቄው ዛሬም ድረስ የሞራል እና የታሪክ መሠረት እንዲኖረው አድርጎታል።

የኢኮኖሚ ደም ሥር እና የንግድ ተወዳዳሪነት

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን እድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት አንዷ ብትሆንም የባሕር በር ማጣት የኢኮኖሚዋን "ደም ሥር" እንደመቁረጥ ይቆጠራል። በሀገሪቷ ውስጥ ያለውን ፈጣን እድገት ተከትሎ፥ ለወደብ ኪራይና አገልግሎ በየዓመቱ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የምትከፍለው ክፍያ ለታዳጊ ኢኮኖሚ ትልቅ ሸክም ነው።

የንግድ መጠን በአሁኑ ወቅት በዓመት የምታንቀሳቅሰው 20 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጭነት በ2030 ወደ 35 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ያድጋል ተብሎ ይገመታል። የራስ የባሕር በር አለመኖር የዋጋ ግሽበትን ከመጨመሩም በላይ፥ የውጭ ንግድ ተወዳዳሪነትን (Export Competitiveness) በእጅጉ ይጎዳል።

ጂኦ-ፖለቲካዊ እና ቀጣናዊ ደኅንነት

ቀይ ባሕር በዓመት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የንግድ ልውውጥ የሚያልፍበት ስትራቴጂካዊ መስመር ነው። እንዲህ ያለ ግዙፍ የሕዝብ ቁጥርና ወታደራዊ አቅም ያላት ሀገር ከዚህ ቀጠና መገለሏ ለቀጠናው ሰላም ዋስትና አይሆንም።

ኢትዮጵያ ካለችበት የጂኦ-ፖለቲካዊ እና ቀጣናዊ ደኅንነት አኳያ የባሕር ኃይል አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም፤ የቀይ ባሕር ቀጠና ለባሕር ላይ ወንበዴነት፣ ለሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ለሽብርተኝነት የተጋለጠ ነው። ኢትዮጵያ ጠንካራ የባሕር ኃይል ኖሯት በንቁ ተሳትፎ መገኘቷ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችን ደኅንነት ለመጠበቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ከዚህ በተጓዳኝ በቀጠናው የጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win Solution) እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ በስፍራው መገኘት ለውሳኔ የሚቀርብ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ጥያቄ የሌላውን ሉዓላዊነት በመጋፋት ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፥ በልማት ሽርክና (Port-for-Equity) ወይም በሊዝ ስምምነት ላይ ያተኮረ ነው። ይህም ለጎረቤት ሀገራትም ትልቅ የኢኮኖሚ ዕድል ይፈጥራል፡፡

የሕግ እና የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ አግባብ የኢትዮጵያን ፍላጎት በጽኑ የደገፈ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባሕር ሕግ (UNCLOS) የየብስ እስረኛ ሀገራት ወደ ባሕር የመድረስ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል። ኢትዮጵያ ይህንን መብቷን በሰላማዊ መንገድና በዲፕሎማሲያዊ ድርድር ለማስከበር የምታደርገው ጥረት ከዓለም አቀፍ መርሆዎች ጋር የተጣጣመ ነው።

በሁለት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ያውቃሉ? ************** 1) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ - ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ድምፅ ሲሰጡ በሀገር አቀፍ ...
11/05/2026

በሁለት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ላይ ድምፅ እንደሚሰጥ ያውቃሉ?
**************

1) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ - ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ድምፅ ሲሰጡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወክልዎን ተወካይ ይመርጣሉ።

2) ለክልል ምክር ቤት ምርጫ - ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ድምፅ ሲሰጡ በክልል ደረጃ የሚወክልዎን ተወካይ ይመርጣሉ።

#በምርጫብቻ

Address

Frew Altaye Avenue
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Sodo City Land Administration Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share