16/08/2026
አደገኛ መጤ አረም ምንድን ነው?
አደገኛና መጤ አረም ማለት በተፈጥሮ ባልነበሩበት /ባልኖሩበት/ ሥፍራ በከፍተኛ ደረጃ በመስፋፋት ነባር ዝርያን የሚፈታተኑ ዝርያዎች ማለት ነዉ፡፡ ይኸዉም በቀጥታ በመሻማት፤ በሽታ አስተላላፊ ወይም ጥገኛ በመሆንና የነባር ዝርያዎችን ሥነ-ምህዳር በመለወጥ እሰከ መጨረሻዉ እንዲጠፉ በማድረግ አካባቢዉ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረግ ነው፡፡ አደገኛ የሆኑ በመሬትና ውሃ አካላት ላይ ተስፋፊ እፅዋት ሆነው ከትናንሽ የውሃ ላይ ተንሳፋፊ እስከ ትላልቅ ዛፍ የሚያካትት ነው፡፡
አደገኛና መጤ አረሞች በብዙ አካባቢዎች በሰው ጤና ፣ በግብርና ሥራዎች ፣ በመዝናኛ ቦታዎች ፣ በዱር እንስሳት ፣ በደኖች ወዘተ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ተብለው የተለዩ አረሞች ማለት ነው፡፡
በክልል ደረጃ አንድ አረም አንድ ጊዜ በአደገኛ አረምነት ከተለየ በኋላ የሚመለከተው የተቆጣጣሪ መ/ቤት ባለስልጣን አረሙ ከቦታ ቦታ እንዳይዛመት የውስጥና የውጭ ቁጥጥር ተግባራትን በአረሙ ላይ ይፈፅማል፡፡ አረሙን ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት የተለያዩ እርምጃዎችን ይወስዳል አረሞችም ከአካባቢው ጋር የመላመድ ችሎታ ስላላቸውና በአጠቃቀም ጉድለት የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ራሳቸውን በማስፋፋት ይታወቃሉ፡፡
ልዩ ባህሪያቸው ምንድን ነው፡-
በፍጥነት የማደግ ፣በፍጥነት የመራባት ፣ዘራቸው በርቀት የመሰራጨት ፣ራሳቸውን ከአካባቢው በቀላሉ የማላመድና የመራባት ችሎታ ወ.ዘ.ተ አላቸው፡፡
አደገኛና መጤ አረም የሚያስከትለው ጉዳት
1. በብዝሃህይወት፤ በእርሻ፤ በዉሃ ሀብትና በሰው ልጅ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላሉ፡፡
2. የተፈጥሮ ሚዛንን በማዛበት የስነ-ምህዳር ሂደቶችን ያራቁታል
3. ነባር ዝርያዎችን በየትኛውም ስነ ምህዳር በመላ አለም ዙሪያ በመስፋፋት በተለያየ መንገድ በመሻማትና ጥገኛ በመሆን አሉታዊ ተፅዕኖ በመፍጠር ያጠፋሉ፡፡
4. በተለያዩ የመሬት ይዞታዎች ፣ በእርሻ ማሳ ፣ በግጦሽ መሬት ወ.ዘ.ተ በመስፋፋት የሰብል ምርትና ምርታማነትን ይቀንሳል፡፡
5. የመኖ ዝርያን በማጥፋት ከእንስሳት የሚገኘውን ምርት ይቀንሳል፡፡
6. በውሃ አካላትና ጥብቅ ስፍራዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡
7. የእንስሳት መኖና ተዋፅኦ ጣዕም ማበላሸትና የተዋፅኦ ጥራቱን መቀነስ /የወተትና የማር ጣዕም መቀየር/
8. ለሌሎች ተባዮች መጠጊያ መሆን
9. በሰብል ላይ ጥገኛ መሆንና ጉዳት ማድረስ
10. በመስኖ ቦታዎችና ቦዮች ላይ ችግር በመፍጠርና የውኃውን ፍሰት መዝጋት
በቅርቡ በተካሄደ ጥናት በአገራችን 35 መጤና ወራሪ የሆኑ አረሞች ተለይተው የታወቁ ሲሆን ከነኝህም መካከል ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ/Prosopis juliflora, ፓርቲኒየም/Parthenium hysterophorus), እንቦጭ/Water hyacinth (Eichhornia crassipes), የወፍ ቆሎ/Lantana camara, የተለያዩ የግራር ዝርያዎች/Acacia species, እና ኦሮባንቼ/Orobanche የተባሉት ዝርያዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በአማራ ክልል ጉዳት እያደረሱ ያሉ መጤ ወራሪ ዕፅዋቶች …
1.ቅንጨ /Parthenium hysterophorus/
2.Eichhornia crassipe
3. የወፍ ቆሎ/Lantana camara/
4. ነጭ ለባሽ/ /የአህያ ሾህ /Argemone ochroleuca/
5.በግድ ዘመድ/ደርግ /Xanthium strumarium
6. አሚኬላ /Hygrophila auriculata/
7. ፕርፕሮሶፒስ /ወያኔ ዛፍ/ Prosopis juliflora/
8. ሰርክ አበባ /Senna didymobotrya /
9. ቦረን /Chrysanthium segetem/
10. አቀንጭራ
ዳይመረጭ/የጅብ ራስ /Orobanche spp/
12. ኑግ አንበሳ /Cuscuta spp/
13.እንቦጭ Eichhomiae crossipe
ማን ይሥራው ?
• ኅ/ሰቡንና ሌሎች አጋር አካላት
• በሰው ጉልበት በራሱ የልማት መሣሪያዎች
• በቀበሌዎች የክትትልና የአስወጋጅ ግብረ ኃይል ማቋቋም
• የት/ቤት ማኅበረሰብን ከአካባቢው ኅብረተሰብ ጋር አቀናጅቶ ማንቀሳቀስ
የመጤ ተስፋፊ ዕፅዋት/አረም አያያዝ ፕሮገራም ጥቅል ስልቶች
መከላከል-ተስፋፊ መጤ ዕፅዋት አዲስ መሬት እንዳይወሩ ማድረግ(የዘር ንፅህናን መጠበቅ፣ አረሞችን ዘር ከመፍጠራቸው በፊት ማስወገድ፣ ዘሮችንና ሌሎች የመራቢያ አካላት ስርጭት መከላከል፣የዘር ኝፅህናን የሚያስከብሩ ህጎችን ማውጣት)
መቆጣጠር- ተስፋፊ መጤ ወራሪ ዕፅዋቱ በምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ ተፅዕኖ መቀነስ
ማስወገድ- ከተወረረው አካባቢ ሁሉንም የተስፋፊ መጤ ወራሪ ዕፅዋቶችና የመራቢያ አካላት ማስወገድን ይጨምራል
ምንጭ ፡-ባ/ዳር ብዛሂዎት
nvasive alien plant species in Ethiopia: ecological impacts on biodiversity a review paper