Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ

Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ Dawuro Zone Health Department supports zonal health system both in preventive and curative approaches.

It is known that prevention is less prodigal than treatment that is 1 dollar to 34 dollars.

አስደሳች ዜና በሀገሊ02  ጤና ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ  እናት በቀዶ ጥገና በሰላም ተገላገለችነሐሴ 28፣ 2018 (ዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ) በዳውሮ  ዞን ኢሰራ ወረዳ ሀገሊ 02  ጤና ጣቢያ ...
03/09/2026

አስደሳች ዜና
በሀገሊ02 ጤና ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ እናት በቀዶ ጥገና በሰላም ተገላገለች

ነሐሴ 28፣ 2018 (ዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ) በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ ሀገሊ 02 ጤና ጣቢያ አንድ እናት ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዶ ጥገና ማዋለጃ አገልግሎት በሰላም መገላገሏ ተገልጿል ፡፡

እናትና በቀዶ ጥገና የተወለዶ ህፃን በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡

የተቀናጀ የድንገተኛ ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት (ISO) አቶ አግኝቸው አምሳሉ እንደገለጹት፣ በሌሎች ጤና ጣቢያና ሆስፒታል ደረጃ በቀዶ ጥገና ማዋለድ የተለመደ ቢሆንም፤ በኢሠራ ወረዳ እና ለእናቶች በአቅራቢ ሌላ አማራጭ ቀዶ ጥገና ማዋለጃ ሆስፒታል ባለመኖሩ ከዚህ ቀደምስል በርካታ እናቶችና ህፃናት በወሊድ ምክንያት ለሞትና ለተዛማች ህመም ስቃይ ስዳረግ በመቆየቱ በዛሬው ዕለት በሀገሊ02 ጤና ጣቢያ አንድ እናት በቀዶ ጥገና በሰላም ማዋለድ መቻሉ የመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑ ጤና ባለሙያዎችንና አከባቢ ማህበረሰብን እንዳስ ደሰታቸው ተገልጿል ።
የቅድሜ ወሊድ ምርመራ እየተደረገላት እንደቆየችና ምጥ ከመጀመሯ በፊት ወደ ጤና ጣቢያ መምጣት እንዳለባት በቂ ግንዛቤ ስለነበረ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ወደ ጤና ጣቢያ መጥተው የሕክምና ክትትል ስር ከቆየች በኃላ በዛሬው ዕለት በቀዶ ጥገና በሰላም መገላገላቸው እንዳስ ደሰታቸው ቤተሰቦቿና ወላድ አባት አቶ ንጉሰ በጋጆ ገልጸዋል።

የጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ማሞ መኩሪያ እንደገለፁት በአሁኑ በጤና ጣቢያ ደረጃ በቀዶ ጥገና የማዋለጃ አገልግሎት ለመስጠት በቂ ዝጅት ተደረጎ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሆነ አብራርቷል።
የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ እና የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ዘላለም ተረፈ እንደገለፁት በጤና ጣቢያው ያልተቋረጠ የቀዶ ጥገና የማለጃ አገልግሎት ሥራ ጎን ለጎን ሁሉ አቀፍ የእናቶችና ህፃናት ህክምና አገልግሎት ትግብራ ለማጠናከር በትኩረት የድጋፍና ክትትል ብሎም የግብዓት አቅርቦት ሥራ እንደሚሰሩ ገልጿል።
ዘገባው : የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ነው።

በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ የሀገሊ 02 ጤና ጣቢያ  የእናቶች ቄዶ ማዋለጃ እና መለስተኛ ቄዶ ህክምና ክፍል (OR) አገልግሎት መስጠት ጀመረ።‎‎ነሐሴ፣21/2018 ዓ.ም ‎‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ...
28/08/2026

በዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ የሀገሊ 02 ጤና ጣቢያ የእናቶች ቄዶ ማዋለጃ እና መለስተኛ ቄዶ ህክምና ክፍል (OR) አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

‎ነሐሴ፣21/2018 ዓ.ም

‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ የሀገሊ 02 ጤና ጣቢያ (OR) ባለሙያዎችንና የተለያዩ ቀሪ ቁሳቁሶችን በማሟላት በዛሬው ዕለት በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

‎በማስጀመሪያ ፕሮግራም ተገኝተው ንግግር ያደረጉ የኢሠራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ተክሌ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረትና የሁለቱ መዋቅር ህብረተሰብ ቀና ትብብር (OR) ወደ ሥራ መገባቱ ትልቅ እፎይታ ያገኘንበት ነው ብሏል።

‎‎አያይዘውም የቀዶ ጥገና ብሎክ ተገንብቶ አገልግሎት እንድሰጥ ብዙ ጥረት መደረጉን አንስቶ ይህ ውጤታማ እንድሆን ድጋፍና ክትትል ያደረጉትን የክልልና የዞን እንድሁም የሁለቱ መዋቅር ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላትን ምስጋና አቀርቧል ።

‎የኢሠራ ባሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢኒጂነር አብነት በጋሻው በበኩላቸው (OR) አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ለሁለቱ መዋቅር የረዥም ዘመናት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት መሆኑ ትልቅ ደስታ ነው ያሉት ከዚህ ቀጥሎ ላለው ድጋፍና ትብብር የተለዬ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል።

‎የኢሠራ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ዘላለም ተረፈ ዛሬ ማስጀመሪያ የተደረገው OR በወረዳውና በባሌ ከተማ አስተዳደር ከሚስተዋሉ ችግሮች አኳያ ትልቅ እፎይታ እንደሚሰጥና የእናቶችና ህጻናት ሞት እንደሚቀንስ አንስተዋል።

አቶ ዘላለም አክለውም ‎የጤና ጣቢያ ቄዶ ጥገና አገልግሎት (OR) በይፋ ሥራ መጀመር በኢሰራ ወረዳ እና በባሌ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል እና ሕብረተሰቡ በአቅራቢያው ጥራት ያለውን ሕክምና እንዲያገኝ የሚያግዝ ጉልህ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።

በቄዶ ጥገና ማዋለጃ የሥራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን ተክሌና በባሌ ከተማ አስተዳደር ካንቲባ በኢንጂነር አብነት በጋሻው የተመራ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር አመራር፣የጤና መዋቅር ባለሙያዎችና ማናጅመንት እንድሁም የአከባቢ ማህበረሰብ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው የቄዶ ጥገና ማዋለጃ ክፍል በይፋ የመደበኛ አገልግሎት እንድጀምር ተደርጓል።

‎ዘገባው፦የኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሜቴ ሊቀመንበር በመሆን ተመረጡ።የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ሊቀመንበርነቱን ከማሊ የጤና እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ኮሎኔል አሳ ...
26/08/2026

ዶ/ር መቅደስ ዳባ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሜቴ ሊቀመንበር በመሆን ተመረጡ።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ሊቀመንበርነቱን ከማሊ የጤና እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ኮሎኔል አሳ ባዲያሎ ቱሬ ተረክበዋል።

በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ ዋና የኮሚቴዉ ሊቀመንበር ዶ/ር መቅደስን ጨምሮ ሁለት የኮሚቴው ምክትል ሊቀ መንበሮችን ሹሟል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር እንዳሻው ሽብሩ መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር በተቀናጀ መልክ  መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።‎‎ታርጫ ነሐሰ 15/2018 ዓ.ም (ዳውሮ  ዞን ጤና መምሪያ)‎‎በዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ   የ2019...
22/08/2026

ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር በተቀናጀ መልክ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ ።

‎ታርጫ ነሐሰ 15/2018 ዓ.ም (ዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ)

‎በዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 በጀት አመት የሐምሌ ወር ሪፖርት ዙሪያ ማናጅመንትና አጠቃላይ ሠራተኞች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ እንደተናገሩት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር በተቀናጀ መልክ በልዩ ሁኔታ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጿል ።

‎አክለውም በጤናው የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በመረጃ አያያዝና ጥራት ላይ የጤና መዋቅር ባለሙያዎችና ባድረሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው መሥራት የጎላ መሆኑን በመረዳት እና ህዝብ ያልተሳተፈ የጤና ሥራ ውጤት አለመኖሩን በመገንዘብ አደረጃጀቶቹን በማጠናከር መተግበር እንዲሁም የተቀመጡ የትኩረት ነጥቦችን ለቅሞ ማሳካት ባለሙያዎች ዲሲፕሊድ በሆነ መንገድ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የጤና መምሪያው ልማት ዕቅድ ዝግጅትና ፋይናንስ አስተዳደር ተወካይ አቶ ዘርሁን ዘነበ በበኩላቸው በዞናችን ከጤና አንፃር ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ከመፍጠር እና ከቤተሰብ ጀምሮ ጤና ኬላዎችን ጤና ጣቢዎችን እንድሁም ወረዳና ዞንን ሞዴል የማድረግ ጉዳይ በቀጣይ ጊዝያት በልዩ ትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎አክለውም በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ከዲጅታል system ጋር በማያያዝ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል።

በ2019 ዓ.ም ሐምሌ ወር የተሰሩ ተግባራት በዝርዝር ከዕቅድ አፈጻጸም አንጻር በታዩ የአፈጻጸም ጉድለቶችና ሳንፈጽማቸው የተቀሩ ተግባራትን በሚገባ በማየት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ጅምር ወር በመሆኑ ቀጣይ ጊዜ በሚደረገው በዞን ወርሃዊ አፈጻጸም ምክክር መድረክ በፊት ስራ ክፍሎች ቀድሞ የየራሳቸውን ተግባራት ከእቅዳቸው መነሻ ገመገሞ የተደራጀ ሪፖርት ማቅረብ በበጀት ዓመት የተሻሌ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ አስገንዝበዋል ።

በስተመጨረሻ በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ተሰጥተው በመምሪያ ኃላፊ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል ።
ዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ
ታርጫ

የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት በማሻሻል ለዘርፉ እድገት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገቡ ተገለጸ የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሶስቱ ጤና ጣቢያ የተ...
20/08/2026

የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት በማሻሻል ለዘርፉ እድገት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገቡ ተገለጸ

የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሶስቱ ጤና ጣቢያ የተከናወኑ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና በ2019 ዕቅድ ዙሪያ የሚደረግ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስፋው ጮራሞ፣ በብልፅግና ፓርቲ የሎማ ቦሳ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስረስ ገቲሶን ጨምሮ ሌሎች የጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የጽ/ቤቱ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስፋው ጮራሞ እንደገለጹት፤ በህክምና ተቋማት የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማሻሻል ተገልጋዩ ህብረተሰብ የተሟላ የጤና አገልግሎት በጥራትና በፍጥነት እንዲያገኝ ለማስቻል በቅንጅትና በተጠያቂነት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ጤና ጣቢያዎች የማህበረሰቡን ጤና ከመጠበቅ አንፃር ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁ አስተዳዳሪው በተቋሙ የሚገኙ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ማህበረሰቡን በታማኝነትና በቁርጠኛነት ማገልገል ይገባቸዋልም ብለዋል።

የዛሬው መድረክም በ2018 በጀት ዓመት በሶስቱ ጤና ጣቢያ የተከናወኑ የስራ አፈጻጸሞችን በጋራ በጥልቀት በመገምገም፣ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለማረም ያለመ እንደሆነም አቶ አስፋው አመላክቷል።

በግምገማው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የነበሩ ስብራቶች፣ የጤና መረጃ አያያዝና አላላክ፣ የመድሀኒት ቁጥጥርና አጠቃቀም፣ አለመቀናጀት እንዲሁም ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ላይ ነጥሮ የወጡ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው ያስገነዘቡት።

የጤና አገልግሎት እርካታን ለማረጋገጥ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተገልጋይን ማዕከል ያደረጉ ፈጣንና ቀልጣፋ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅበት የተናገሩት የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስረስ ገቲሶ ናቸው።

በዚህም የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት በመገምገም፣ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከር እና የታዩ ድክመቶችን በግልጽ ለይቶ ቀጣይ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንደሆነም ኃላፊው ገልጸዋል።

የመድረኩ ዋና ዓላማ የ2018 በጀት ዓመት ጠንካራ አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ውስንነቶችን በማረም ወደ ቀጣዩ ዕቅድ ለማሸጋገር መሆኑን የጠቆሙት የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ኡማ የሚለካና ጠንካራ የጤና ተቋማትና አገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ባለሙያው የሚጠበቅበትን ድርሻ በመለየት ኃላፊነቱን በተገቢው እንዲወጣ ብሎም የጤና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች መፈጸም እንዳለባቸውም በአጽንኦት ተናግረዋል።
ወገባው የሎማ ቦሳ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው።

20/08/2026

Government organisation

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ከዩኒሴፍ (UNICEF) ጋር በመተባበር የተቀናጀ የተለያዩ ማይክሮ ንጥረነገር ዕደላ (MMS) ዙሪያ ለባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነውበዳውሮ ዞን የሎማ ቦሳ ወረዳ ...
18/08/2026

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ከዩኒሴፍ (UNICEF) ጋር በመተባበር የተቀናጀ የተለያዩ ማይክሮ ንጥረነገር ዕደላ (MMS) ዙሪያ ለባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው

በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በዩኒሴፍ (UNICEF) በጀት ድጋፍ የተቀናጀ የተለያዩ ማይክሮ ንጥረነገር ዕደላ (MMS) ዙሪያ ለጤና ኤክስቴንሽን እና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት በብልፅግና ፓርቲ የሎማ ቦሳ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስረስ ገቲሶ እናቶችን ከእርግዝና ጀምሮ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ፣ ክትትል በማድረግ በጤና ተቋም እንዲወልዱ ማድረግ የእናቶችን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር የሚወለዱ ህፃናት በአካል፣ አዕምሮና ሥነ-ልቦና ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የዛሬውም ስልጠና በተለይ የተቀናጀ የተለያዩ ማይክሮ ንጥረነገር ላይ መሠረት ባደረገ መልኩ ሲዘጋጅ በምክንያት መሆኑን አውስተዋል።

ተሳታፊ ባለሙያዎችም ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ተገቢውን ክህሎት እንድትጨብጡ በማለት ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል።

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለማርያም ኡማ በበኩላቸው፣ ነፍሰ ጡር እናቶች የተለያየ ዓይነት ንጥረ ምግቦችን መመገብ የፅንሱን ጤናማ እድገት ለማረጋገጥ፣ የእናትን አካል ኃይል ለመጠበቅ እና እንደ ማህፀን ውስጥ የልጅ የነርቭ ቱቦ ጉድለትን የመሳሰሉ አደጋዎችን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የMMS ተግባራዊ እንዲያደርጉ የጤና ኤክስቴንሽን እና ባለሙያዎች የማያቋርጥ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉም አቶ ኃይለማርያም አሳስበዋል።

የጤና ኤክስቴንሽን እና ጤና ባለሙያዎች የተቀናጀ የተለያዩ ማይክሮ ንጥረነገር ዕደላ (MMS) ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩም በአጽንኦት ተናግረዋል።

በስልጠና መድረኩ የእናቶችና ሕፃናት ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ጌቱ ተክለማርያም እናቶች ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት፦ አስፈላጊ ቫይታሚን፣ ካርቦሀይድሬት፣ ማዕድናትን በበቂ ሁኔታ ማስገኘት የሚችሉ ምግቦችን እንዲያዘጋጁና እንዲመገቡ የማይክሮ ንጥረነገር ማሟያ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የተስተካከለ የነፍሰ ጡር እና አጥቢ እናቶች አመጋገብ ለልጆች ጤናማ እድገት የሚሰጠው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ ጌቱ በአንድ ማዕድ የተለያዩ የምግብ ንጥረ ይዘት ያላቸውን ምግብ መጠቀም እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ነፍሰጡር እናቶችን በመከታተል ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ በጤና ተቋም እንዲወልዱ መድኃኒት በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማድረግ፣ እንደሚገባም አክለዋል ሲል የዘገበው የሎማ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በወረዳው በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆኑ ተገለጸ ።በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ የጤና ፖሊሲውን መሠረት በማድረግ በተሰሩ መደበኛ ተግባራትና የተለያዩ ኢን...
17/08/2026

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በወረዳው በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆኑ ተገለጸ ።

በዳውሮ ዞን ገና ወረዳ የጤና ፖሊሲውን መሠረት በማድረግ በተሰሩ መደበኛ ተግባራትና የተለያዩ ኢንሼቲቭ ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ ውጤት መመዝገቡን የጽ/ቤቱ ኃላፊ ገልጽዋል ።

የጤና ተቋማትን ንፁህ፣ ፅዱ፣ ሳቢና ማራኪ በማድረግ ለማህበረሰቡ ተደራሽና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መሰራቱን የገለጹት የጽ/ቤቱ ኂላፊ አቶ ዘነበ ዳማኮ፣ የተገኘው ውጤት በየግዜው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ ህብረተሰቡ ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻሉን ነው የገለጹት ።

ከዚህ በፊት ስነሳ የነበረው አንዱ ችግር በወረዳው ያለው የጤና ጣቢያው ብዛት አንድ ብቻ ከመሆኑ የተነሳ በርካታ ህብረተሰብ ክፍል የተሻለ አገልግሎት እንዳገኙ ከማድረግ በሻገር የመልካም አሰተዳደር ጥያቄ ሆነው የዘለቀ ስሆን፣በህዝብ ተሳትፎ እና በመንግሥት ድጋፍ በሁለቱ ቀበሌ በባዛ ሾታ እና ዲላሞ ማረቃ ሁሉ አቀፍ ጤና ተቋማት ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ፣ ሌላው ከመድሀኒት እጥረት ጋር ተያይዞ ስነሳ የነበረው ችግር ተፈተው ህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ሰፊው ስራ መሠራቱን እና የወባ በሸታን ለመከላከል በተሰራው ስራ ውጤት መገኘቱን አቶ ዘነበ ይገልጻሉ ።

ሌላው እናቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ የእናቶች ማቆያ በህዝብ ተሳትፎ በመገንባት፣ እህልን፣ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ጨምሮ የተለያዩ አሰፈላጊ ነገሮችን በማዘጋጀት፣በወሊድ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እና እናቶች በጤና ተቋማት መጥተው እንዲወልዱ ለማድረግ የእናቶች ማቆያ ስፍራን ሳቢና ምቹ አድርጎ ማዘጋጀት መቻሉን ተናግሮ ፣ በኢዩ በጀት ድጋፍ በሁለቱ ቀበሌ በባዛ ሾታነ ዲላሞ ማረቃ የተጀመረው ግንባታ ስጠናቀቅ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት መሰጠት እንደሚያስችል ነው ሀሳባቸውን የገለጹት ።

የወልዳሃኔ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ምትኩ ገትሳ በበኩላቸው እንደገለጹት ተቋሙ የጤና ፖሊሲውን መሠራት በማድረግ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመሥጠት በትኩረት መሠራቱን አንስቶ ፣በተላይም የጤና ተቋም ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ንፁህ፣ ፅዱ፣ ሳቢና ማራኪ ለማድረግ በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የተነገረው ።

በተላይ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋራ ተያይዞ ስነሳ የነበረው ችግርን ደረጃ በደረጃ በማየት የተለያዩ ማስተካከያ ማድረጉን የገለጹት አቶ ምትኩ በየግዜው ከሚመለከታቸው አካላትና የቦርድ አባላት ጋር በመመካከርና አቅጣጫ በማስቀመጥ ውጤቶችን በየግዜው እየገመገሙ፣ የሪፖርት ስረዓትን በዲስፕሊን መምራቱ የውጤቱ መነሻ መሆኑን ገልጾ፣ ተቋሙ ከመደበኛ ተግባር በተጨማሪ የተቋማት ማሳን በተለያዩ ምርት መሸፈኑንን ፣ገልጾ የተገኘው ውጤት የባለሙያዎች የአጋር አካላት ቅንጅታዊ ስራ ውጤት መሆኑን ተናግሮ ፣ በተገኘው ውጤት ሳንዘነጋ ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና ከመቸውም ግዜ በላይ ማህበረሰቡን በላቀ ትጋት ለማገልገል በአድሱ በጀት ዓመት መዘጋጀታቸውንም ገልጽዋል ።

ዘገባው የገና ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።

12/08/2026
የሥራ ማስታወቂያ
11/08/2026

የሥራ ማስታወቂያ

Address

Tarch'a Sodo

Telephone

+251912856886

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ:

Shortcuts

Share