Daniel Bekele

Daniel Bekele Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Daniel Bekele, Addis Ababa.

05/07/2024

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የ5 ዓመት የሥራ ዘመናቸው ማብቂያ ጋር በተገጣጠመው 3ተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ “ኢትዮጵያ ከምትገኝበት የግጭት አዙሪት ዐውድ ለመውጣትና በዚሁ ዐውድ ለደረሱ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በዘላቂነት እልባት ለመስጠት ከሰላማዊ መንገድ፣ ከውይይት፣ ከምክክር እና ከሽግግር ፍትሕ ሂደት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም” ብለዋል። አክለውም የሽግግር ፍትሕ ሂደት ተዓማኒና ቅቡልነት ባለው መንገድ ለመተግበር መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ በሀገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች በሚካሄዱ የትጥቅ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች፣ እንዲሁም የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉም ወገኖች፤ ለሀገራዊ ምክክሩና ለሽግግር ፍትሕ ሂደቱ በቀና መንፈስ ዕድል እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

In his foreword to the 3rd Ethiopia’s Annual Human Rights Situation Report, which coincides with the last year of his five-year term, EHRC Chief Commissioner Dr. Daniel Bekele emphasized that “there is no alternative to peaceful means, dialogue, discussion, and transitional justice processes to end the cycle of recurring conflict in Ethiopia and to achieve a lasting solution to the widespread human rights violations that have occurred in this context.” Underscoring the need to implement the transitional justice process in a credible manner, Dr Daniel also urged all stakeholders —including the government, parties engaged in armed conflicts across various regions in the country, and all stakeholders concerned for the human rights situation in the country — to sincerely support and give a chance to the national dialogue and the transitional justice processes.

🔗 https://ehrc.org/?p=28739

🇪🇹

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ

05/07/2024

የትጥቅ ግጭቶች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዋነኛ ምክንያት ሆነው በመቀጠላቸው ግልጽ፣ አካታች እና ተዓማኒ የሆነ ሰላማዊ መፍትሔ እና የሽግግር ፍትሕ ሂደት አፋጣኝ አስፈላጊነት አመላካች ነው..

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍነውን 3ተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ባለ 132 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ በበጀት ዓመቱ በተሰበሰቡ መረጃ እና ማስረጃዎች መሠረት ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ጠቅለል ባለ መልኩ የሚያሳይ ሲሆን፣ መልካም እመርታዎች፣ አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ምክረ ሐሳቦች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንም በዝርዝር አካቷል።

ዓመታዊ ሪፖርቱ ኢሰመኮ የትኩረት መስክ አድርጎ በለያቸው የሲቪልና የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ፣ የሴቶችና ሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን፣ የስደተኞች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ፍልሰተኞች መብቶች ዘርፎችን የተመለከተ ሲሆን፤ በተጨማሪም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 አተገባበር ጋር ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ፣ በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች እና የታራሚዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን፣ በ4 ክልሎች የተካሄደውን የ6ኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶች ክትትል፣ በኢሰመኮ የተስተናገዱ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ አቤቱታዎች እና አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶች ግዴታዎችን ከመወጣት አንጻር ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታንም በዝርዝር አብራርቷል።

በሪፖርት ዘመኑ ከተመዘገቡ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን ማሻሻል ከሚያስችሉ ቁልፍ ክስተቶች እና እመርታዎች መካከል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መጽደቁ በዋነኝነት የሚጠቀስ መሆኑን አስታውሶ፤ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር የተጀመሩ ሰላምን የማምጣት እንቅስቃሴዎች አበረታች ቢሆኑም ዘላቂ እንዲሆኑ ሂደታቸው ተጎጂዎችን ጨምሮ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተቱ እና ግልጽ ሊሆኑ እንደሚገባ፤ የተጀመረውም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አጠቃላይ ሂደት ተጎጂዎችን ማእከል ያደረገ፣ ተዓማኒ እና ግልጽነት ያለው፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟላ እና የሰብአዊ መብቶች መርሖችን የተከተለ እንዲሆን ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክልሎች የትጥቅ ግጭቶች፣ ጥቃቶች ወይም የጸጥታ መደፍረሶች ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 2016 ዓ.ም. የተመዘገቡ ሲሆን፣ በዚህ ሳቢያ በታጣቂ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርስ የሞት እና የአካል ጉዳት አሳሳቢነት ቀጥሏል። በተለይም በትጥቅ ግጭት ዐውድ ውስጥ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንደቀጠሉ እና እንደተስፋፉ በሪፖርቱ ተመላክቷል። የትጥቅ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በተለይም ሴቶችና ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ለምግብና ለመሠረታዊ ሰብአዊ ድጋፍ እጥረት፣ ለጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች መስተጓጎል ወይም መቋረጥ እንዲሁም ለሌሎች ተጨማሪ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውም ተገልጿል።

በሪፖርት ዘመኑ በትጥቅ ግጭት፣ በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች እንዲሁም ግጭት በሌለበት በአንዳንድ ሁኔታዎች ወቅት ጭምር የሚፈጸም ከሕግ ውጪ የሆኑ የሲቪል ሰዎች ግድያ አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል። በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በሲቪል ሰዎች ላይ በትጥቅ ግጭቱ እንዲሁም በግጭቱ ዐውድ ውስጥ ከሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተጨማሪ ሲቪል ሰዎችን ዒላማ ያደረገ እገታ አሳሳቢነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኢሰመኮ በበጀት ዓመቱ ለ10 ወራት ተፈጻሚ ሆኖ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ አተገባበር ጋር ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ በርካታ ሰዎች መደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች ውስጥ ለተራዘመ እስር መዳረጋቸውን፤ እንዲሁም ለቀናት ወይንም ለሳምንታት ለቆየ ጊዜ ያሉበት ቦታ ሳይገለጽ/ሳይታወቅ በእስር መቆየተቻው ተገልጿል። ኢሰመኮ ሁሉንም መደበኛ ያልሆኑ ቦታዎችን በመጎብኘት ክትትል እና ምርመራ ለማድረግ ያደረገው ጥረት ባይሳካም፣ የደረሱትን አቤቱታዎችና ጥቆማዎች መሠረት በማድረግ ከሚመከለታቸው የክልል እና የፌዴራል የአስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር በመነጋገርና ውትወታ በማድረግ ሲከታተል መቆየቱን፤ እንዲሁም ያሰባሰባቸውን ማስረጃዎች መሠረት በማድረግ በተለያየ ወቅት መግለጫዎችን ይፋ ማድረጉ በሪፖርቱ ተመልክቷል።

ከአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጁ አተገባበር ጋር ተያይዞ ከኮማንድ ፖስቱ ትዕዛዝ ውጪ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በማእከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚዲያ እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን በዚህ ዝርዝር ሪፖርት ተመላክቷል።

በሌላ በኩል “ወቅታዊ ሁኔታ” በሚል ምክንያት ሰዎች ለዘፈቀደ እስር እንዲሁም ለአስገድዶ መሰወር የተዳረጉበት በርካታ ክስተቶች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መመዝገባቸውን፣ የመንቀሳቀስ መብትን በተመለከተ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ሁኔታ ወይም በሚጣሉ ገደቦች ምክንያት በተለይም በየብስ የሚደረግን እንቅስቃሴ አዳጋች ማድረጉ፤ እንዲሁም የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወይም በታጣቂ ቡድኖች ለተከታታይ ቀናት በሚዘጉ መንገዶች ምክንያት የሚደርሱ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች፣ በሸቀጦች ዋጋ እና በገቢ እንዲሁም በጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች ተደራሽነት ላይ የሚደርሱ አሉታዊ ተጽዕኖዎች በዘንድሮ በጀት ዓመትም በተለይ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎችም መቀጠላቸው በዝርዝር ተብራርቷል።

ኢሰመኮ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 306 ፖሊስ ጣቢያዎችን እና 52 ማረሚያ ቤቶችን እንዲሁም አዋሽ አርባን ጨምሮ 15 መደበኛ ያልሆኑ ማቆያ ቦታዎችን ጎብኝቷል። ክትትል በተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች በርካታ መሻሻሎች ተስተውለዋል። ሆኖም በሁሉም ክልሎች ለማለት በሚያስችል ሁኔታ የዘፈቀደ እስር፣ የጅምላ እስር ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ባለማክበር ሰዎችን ይዞ የማቆየት፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች ሰዎችን የመያዝ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።

የተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ በመንግሥት እንዲሁም መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሰብአዊ ድጋፍ በተለይ የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት፤ በተወሰኑ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የተሰባጠረ የተፈናቃዮች የመረጃ አያያዝ ሥርዓት መኖሩ፤ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መብቶችን በተመለከተ የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር በቀል የተራድዖ ድርጅቶች መንግሥት ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚያደርገው ጥበቃ እና ድጋፍ የተሟላ እንዲሆን ድጋፍ የሚያደርጉ መሆኑ በበጀት ዓመቱ ከታዩ መልካም እመርታዎች መካከል ናቸው። ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈናቃዮች ምዝገባ እና ሰነድ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ያለው ክፍተት መቀጠሉ፤ ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እንዳይከናወን አሉታዊ ተጽዕኖ ከማሳደሩ በተጨማሪ ሌሎች የመንቀሳቀስ እና የማኅበራዊ አገልግሎት የማግኘት መብቶቻቸውን ለመጠቀም እንዳይችሉ እንቅፋት መፍጠሩ እንደቀጠለ ነው።

ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ያልተቆራረጠ እንዲሁም ልዩ ፍላጎቶች ያሏቸውን ተፈናቃዮች መሠረት ያደረገ የሰብአዊ ድጋፍ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶች አቅርቦት አለመኖሩ፤ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ በሆኑ ምክያቶች በመፈናቀል ሁኔታ ውስጥ ያሉ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ፤ በትጥቅ ግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አካባቢዎች በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተለይም ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃት መጨመሩ በዓመታዊ ሪፖርቱ ከተነሱ አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል ናቸው።

በመጪው በጀት ዓመት ትኩረት ከሚሹ አንኳር ጉዳዮች መካከል የትጥቅ ግጭቶች በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ ማድረግ፣ የሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕ ሂደት ተዓማኒ አተገባበር ማረጋገጥ፣ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ወይም የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ማድረግ፤ በሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ሕግ እና ፖሊሲዎች ላይ ማሻሻያ ማድረግ፤ በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች እና የታራሚዎች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ማሻሻልና ማረጋገጥ፣ የትጥቅ ግጭቶች በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተጽዕኖ፣ እንዲሁም የመንግሥት የፋይናንስና የበጀት እጥረት በተለይም በጤና እና በትምህርት አገልግሎቶች ላይ ያስከተለው ጉዳት ታሳቢ በማድረግ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ዘርፍ የሚከናወነውን ሥራ ማጠናከርና ማጎልበት የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሥራ ዘመናቸው ማብቃት ጋር በተገጣጠመው በዚህ በ3ተኛው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ባስተላለፉት መልእክት፣ “ኢትዮጵያ ከምትገኝበት የግጭት አዙሪት ዐውድ ለመውጣትና በዚሁ ዐውድ ለደረሱ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በዘላቂነት እልባት ለመስጠት ከሰላማዊ መንገድ፣ ከውይይት፣ ከምክክር እና ከሽግግር ፍትሕ ሂደት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም” ብለዋል። አክለውም የሽግግር ፍትሕ ሂደት ተዓማኒና ቅቡልነት ባለው መንገድ ለመተግበር መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ በሀገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች በሚካሄዱ የትጥቅ ግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች፣ እንዲሁም የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉም ወገኖች፤ ለሀገራዊ ምክክሩና ለሽግግር ፍትሕ ሂደቱ በቀና መንፈስ ዕድል እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሙሉ ሪፖርት 🔗 https://ehrc.org/download/ethiopia-annual-human-rights-report-2/

አንኳር ጉዳዮች 🔗 https://ehrc.org/download/አንኳር-ጉዳዮች-2

English Press Release 🔗 https://ehrc.org/armed-conflicts-still/

የኢሰመኮ የ5 ዓመታት ጉዞ 🔗 https://ehrc.org/download/5-year-summary/

🇪🇹

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ

05/07/2024
05/07/2024

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established by Parliament as the national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.

05/07/2024

The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) is an independent federal state body established by Parliament as the national human rights institution with the mandate for the promotion and protection of human rights.

05/07/2024

ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በ4 ክልሎች የተካሄደው የ6ኛው ዙር ‘‘ቀሪ’’ እና ድጋሚ ምርጫ የሰብአዊ መብቶች ክትትል..

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተሻሻለው መቋቋሚያ አዋጁ አንቀጽ 6 (11) መሠረት የተሰጠውን በምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብቶች ክትትል የማድረግ ሥልጣን እና ኃላፊነት መነሻ በማድረግ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ክልሎች በተደረገው የ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ‘‘ቀሪ’’ እና ድጋሚ ምርጫ ወቅት ያከናወነውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ግኝቶች የያዘ ­የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ክትትል የሚያደርጉ 9 ሴቶች እና 22 ወንዶች በአጠቃላይ 31 ባለሙያዎችን አሰማርቶ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ይፋ የተረደገው ቀዳሚ ሪፖርት በዋናነት ምርጫው በተካሄደባቸው ሁሉም ክልሎች ከተደራጁ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ተብለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ መተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ ሥር የተደራጁትን 5 ልዩ የምርጫ ጣቢያዎችን ጨምሮ በተመረጡ 201 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተከናወነውን የድምጽ አሰጣጥ ሂደት የተመለከተ ነው። በዚህ ሪፖርት ያልተካተቱ ሌሎች የቅደመ ምርጫ፣ የምርጫ ዕለት እና የድኅረ ምርጫ ተግባራትን የተመለከቱ ግኝቶች የማጠናቀሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

የኢሰመኮ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ በዕለቱ ተዘዋውረው የተመለከቷቸውን የምርጫ ጣቢያዎች በመጥቀስ፣ በቀጣይ ምርጫዎች የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኛ፣ ለአረጋውያን እንዲሁም ለሴት መራጮች ይበልጥ ምቹና ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች እንዲቋቋሙ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል። አክለውም የመራጮች መዝገብ ላይ የሚሞሉ እንደ ዕድሜ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ የአካል ጉዳት ዐይነት የመሳሰሉ መረጃዎች የወጣቶች፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞችን የምርጫ ተሳትፎ መብት የተመለከቱ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉ በመሆናቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ለምርጫ አስፈጻሚዎች በመራጮች መረጃ አያያዝ ዙሪያ የሚሰጡ ሥልጠናዎችን እና ለዜጎች የሚሰጡ የመራጮች ትምህርቶችን እንዲያስፋፉ ጥሪ አቅርበዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=28587

🇪🇹

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

05/07/2024

ዓለም ዓቀፉን በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃት ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ..
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከአረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር እና ከሄልፕኤጅ ኢንተርናሽናል (HelpAge International) ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚከበረውን በአረጋውያን ላይ የሚደርስ ጥቃት ግንዛቤ የማስጨበጫ ቀንን በማስመልከት የተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የአረጋውያን ማኅበራት ተወካዮች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።

ውይይቱ የዚህ ዓመት መሪ ቃል በሆነው “ትኩረት በአደጋና አስቸኳይ ሁኔታዎች ውስጥ ለሚገኙ አረጋውያን” ፅንሰ ሐሳብ ላይ ያተኮረ ሲሆን በግጭት እና አሳሳቢ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ውስጥ ያሉ አረጋውያን ላይ በሚደርሱ የጥቃት ዓይነቶች ዙሪያ የውይይት መነሻ ጽሑፎች ቀርበዋል። በተጨማሪም አረጋውያን ላይ በተጨባጭ እየደረሱ የሚገኙ የጥቃት ታሪኮች በዘርፉ ባለሙያዎች ለተሳታፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱ የአረጋውያን ማኅበራት ተወካዮች ድምፃቸው ሊሰማ እንደሚገባ በመግለጽ “በዚህ ረገድ በሀገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች ላይ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ሊደረግ ይገባል” ብለዋል። በአረጋውያን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እና ምልክቶቻቸው ላይ የሚስተዋለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል በማለት ሐሳባቸውን አጋርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር ቦርድ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ክፍሉ በበኩላቸው አረጋውያን መብታቸውን ለማስከበር ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው እና የሚያጋጥሙ የመብት ጥሰቶችን መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መከላከል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም “አረጋውያንን ለጥቃት ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች ለመጠበቅ ሊወሰዱ ከሚገባቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ከተረጂነት ማላቀቅ መሆኑ ታውቆ አረጋውያኑ ገቢ በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ በመንግሥት በኩል ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይገባል” ብለዋል።

የኢሰመኮ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ኢትዮጵያ አረጋውያንን በተመለከተ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ የሌላት መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም ምክንያት በሚፈጸሙ ጥቃቶች ላይ የተቀናጀ ምላሽ ለመስጠት አዳጋች መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም በግጭት እና በተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ለሚደርሱ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎች አረጋውያን በተለየ መልኩ ለጉዳት ተጋላጭ በመሆናቸው አካታች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን የመዘርጋት እና ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን ተጠያቂ በማድረግ ፍትሕ የማስፈን ተግባራት ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተናገረዋል።

🔗 https://ehrc.org/?p=28531

🇪🇹

በነጻ የስልክ መስመራችን 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251115504031

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daniel Bekele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Daniel Bekele:

Share