30/08/2026
የቦንጋ መናሀሪያ ህጋዊ የታሪፍ ማሳወቂያ!!
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ከ ትራፊክ ፖሊስ ማስተባበሪያ ጋር በመቀናጀት ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከልና ተሳፋሪዎችን ከብዝበዛ ለመታደግ የጉዞ ታሪፍ ማሳወቂያ ባነር በመናሀሪያው መውጫ መቁረጫ ቢሮ ግድግዳ ላይ በግልጽ እንዲለጠፍ አድርጓል።
:-
#ግልጽነት:-ተሳፋሪዎች ከመሳፈራቸው በፊት ህጋዊውን ታሪፍ ማወቅ እንዲችሉ ማድረግ።
:- ከአሽከርካሪዎችና ደላሎች የሚደርሰውን ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪ በዘላቂነት መግታት።
:- የትራፊክ ፖሊሶችና ተቆጣጣሪዎች ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር።
#የተላለፈ-ጥሪ:-
#ለተሳፋሪዎች-በመናሀሪያው የተለጠፈውን ባነር በማየት ትክክለኛውን ህጋዊ ክፍያ ብቻ ይክፈሉ፤ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ የሚጠይቁ አካላት ሲያጋጥሙዎት ወዲያውኑ ለትራፊክ ፖሊስ ወይም ለመናሀሪያው አስተዳደር ጥቆማ ይስጡ።
#ለአሽከርካሪዎች:-ከህጋዊው ታሪፍ ውጪ ትርፍ ገንዘብ ማስከፈል በጥብቅ የተከለከለ ነው። መመሪያውን ጥሰው በሚገኙ አካላት ላይ ተሽከርካሪን እስከ ማገድና ከባድ የገንዘብ ቅጣት የሚጣል መሆኑን እንገልፃለን።
የሚመለከቷቸው ዋና ዋና መስመሮች: ጌሻ፣ አዲዮ፣ ጠሎ፣ ጨታ፣ ዴቻ፣ ጨና፣ ሺሺንዳ፣ ቢጣ፣ ቴፒ፣ ጂማ፣ ሚዛን እና ሌሎች አከባቢዎች መሆናቸውም ተጠቅሷል።