Dillibbo

Dillibbo የተሻልክ ሠው ሆነህ መገኘት ያለብህ ከሌሎች ሠዎች ሳይሆን ከ? Qanxaffele Qafar Xisaanama

21/03/2025

መንግስት ሰላምን ያስቀደመ መሆን አለበት"

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (ሰላም ሚኒስቴር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፓርላማ በመገኘት በፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት መንግስት ሰላምን ያስቀደመ፣ ሰላምን በይፋ የሚናገርና ለሰላም የሚተጋ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

"ሰላምን የሚያደፈርስ ነገር ሲኖር ግልጽ መመዘኛዎች ያስፈልጉታል ያሉ ሲሆን መንግስት በብቸኝነት ሀይል የመጠቀም ስልጣን ያለው በመሆኑ ዘላቂ ሰላምንና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ወደ ግጭት ሊገባ ይችላል" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በኢትዮጵያ የመጣው ችግር ፍረጃ ነው። የጠላትና የወዳጅ ፍረጃ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ለሰላማዊ ድርድር ቦታ አይሰጥም። ስለሆነም በኃይል ስልጣን የመያዝ አባዜን አምጥቷል። በምርጫ የተመረጠን መንግስት በኃይል ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። እነዚህ አካላት የሚያሰቃዩት እንታገልልሃለን የሚሉትን ህዝብ ነው” ብለዋል፡፡

መንግስት ለሰላም እጁ የተዘረጋ ነው፡፡ በድርድር እና በሰለጠነ መንገድ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ሁሌም ቢሆን ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

17/03/2025
10/03/2025
27/02/2025

Address

Dubti
Welo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dillibbo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dillibbo:

Share

Category