የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ/ CERS Women & Children affairs Bureau

  • Home
  • Ethiopia
  • Werabie
  • የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ/ CERS Women & Children affairs Bureau

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና  ህፃናት ጉዳይ ቢሮ/ CERS Women & Children affairs Bureau ይህ ትክክለኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የፌስቡክ ገፅ ነው! ገፃችን Like Follow Share በማድረግ ቤተሰብ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ጽ/ቤት በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የህግ ማዕቀፎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።ወራቤ፣ ነሃሴ 28/2018 የማዕከላዊ ኢትዮ...
03/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ጽ/ቤት በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የህግ ማዕቀፎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።

ወራቤ፣ ነሃሴ 28/2018 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ጽ/ቤት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የህግ ማዕቀፎች ላይ ለሴቶች ሴክተርና አደረጃጀት ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

የስልጠና መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር ከመሬት አጠቃቀም አዋጅ ጋር በተያያዘ አዋጅ ቁጥር 36/2016 የተሰኘ አዲስ አዋጅ መኖሩን አንስተው ከዚያ ጋር ተያይዞ ሰፊ የግንዛቤና የመሬት ሀብት አጠቃቀም ውስንነት እንዳለ ጠቁመዋል።

በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች ፍትሃዊ ያልሆነ በመሬት ገንዘብ ተበድሮ ሙሉውን የመመለስ ልምድ እንደነበር ያመለከቱት ሀላፊዋ በአዲሱ አዋጅ መሬትን አሲዞ የመበደር እና ስራ እድል መፍጠር ላይ የነበረ ክፍተት እንደሚዘጋ አስታውቀዋል።

የሴቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ የሚወጡ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና እቅዶች ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባና ለዚህም መሰል የስልጠና መድረኮች ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳላቸው አመላክተዋል።

ለዚህም በቢሮው በኩል አስፈላጊው ድጋፍና ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ ዘቢባ አረጋግጠዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ጽ/ቤት ፕሬዚደንት ወ/ሮ ፎዚያ መሐመድ በበኩላቸው የሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ተሳትፎ፣ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሴት አደረጃጀቶች ሚና የጎላ መሆኑን አስታውሰዋል።

የሴቶች ማህበር ጽ/ቤት ከእነዚህ አደረጃጀቶች አንዱ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ፎዚያ ጽ/ቤቱ ዓላማውን እና ተልዕኮውን ለመወጣት ባለፉ ጊዜያት በየተቋሙ የሚገኙ የሴት አመራሮችን፣ ባለሙያዎችንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እንዳከናወነ አስረድተዋል።

ከሴቶች ተጠቃሚነት አንጻር ጉድለት ካለባቸው ዘርፎች አንዱ የገጠር መሬት መሆኑን በማስታወስ ሴቶች የመሬት ባለሀብት፣ ባለመብት እና አጠቃቀም አዋጅ ላይ ግንዛቤ ኖሯቸው መሬታቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙ በቤተሰብ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበረሰብ ደረጃም ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጡ አብራርተዋል።

በዚህም የሴቶች የኢኮኖሚ ነፃነታቸው እንደሚጨምር፣ በመሬቱ በማምረት፣ በንግድ እና በሌሎች ምርታማ ሥራዎች በመጠቀም ገቢያቸውን እንደሚያሳድጉ አስታውቀዋል።

በቀጣይ ጊዜያት ጉድለቶችን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎችን በትኩረት በቅንጅት፣ በመተባበርና በኃላፊነት ስሜት እንዲሰራ ሀላፊዋ አሳስበዋል።

የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ቢሮ  የስርዓተ ፆታ ሞዴል ቤተሰብ እና የስርዓተ ምግብ ተኮር የግብርና መንደር የምስረታ ተግባራት ያለበት ደረጃ ድጋፍና ክትትል አደረገ፡፡የ...
03/09/2026

የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ቢሮ የስርዓተ ፆታ ሞዴል ቤተሰብ እና የስርዓተ ምግብ ተኮር የግብርና መንደር የምስረታ ተግባራት ያለበት ደረጃ ድጋፍና ክትትል አደረገ፡፡

የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ቢሮ ከክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ጋር በመቀናጀት የስርዓተ ፆታ ሞዴል ቤተሰብ እና የስርዓተ ምግብ ተኮር የግብርና መንደር የምስረታ ተግባራት ያለበት ደረጃ ድጋፍና ክትትል በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፉቻሬ ቀበሌ ላይ አካሂዷል፡፡

የቢሮው ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በወረዳው ፉቻሬ ቀበሌ ያደረገውን የድጋፍ እና ክትትል ስራ ማጠቃለያ ግብረ መልስ ሰጥቷል፡፡

የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ምክትል እና የሴቶች ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ነጂሚያ ራህመቶ የስርዓተ ምግብ ኢንሼንቲቮችን ተደራሽ ለማድረግ በተሰራው ስራ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡

ለሴቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ በማድረግ የሴቶችን ጊዜ እና ጉልበት መቆጠብ ይገባል ያሉት ወ/ሮ ነጂሚያ የስርዓተ ምግብ ተኮር ሞዴል መንደር ለመፍጠር የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ሱልጣን በርጋ በሴቶች የሚወርዱ ስልጠናዎችን በአግባቡ ተደራሽ በማድረግ ሴቶች ውሳኔ ሰጭነታቸውን ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የምግብ ሰርቶ ማሳያ እና የአመጋገብ ባህሪያትን ከማሻሻል በተጨማሪ ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችን ማስወገድ ላይ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የወረዳው የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሱልጣን አሳውቀዋል፡፡

በድጋፍ እና ክትትሉ ወቅት የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ሱልጣን በርጋ የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ ምክትል እና የሴቶች ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ነጂሚያ ራህመቶ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የስርዓተ ጾታ እና ስርዓተ ምግብ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ግዛቸው ዮሀንስ የምግብ እና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ብዙነሽ ሰማ የክልሉ ሴቶች ንቅናቄ እና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ሰብለወንጌል ጥላሁን የወረዳው ሴቶች እና ህጻናት ጉዳዮች ሃላፊ ወ/ሮ ሽኩሪያ ጀማል የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል እና የእርሻ ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብራር አክመልን ጨምሮ ሌሎች አካላት ተገኝተዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር የተለያዩ የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራትን አከናወነ ።ከክልሉ ግብርና ቢሮ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በገጠር መሬት...
03/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር የተለያዩ የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራትን አከናወነ ።

ከክልሉ ግብርና ቢሮ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በገጠር መሬት አጠቃቀም ህግ ማዕቀፍ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በወራቤ ከተማ እየተደረገ ይገኛል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሐመድናስር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ፎዚያ መሐመድ እና ሌሎች የተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ከመድረኩ አስቀድሞ የከተማ ማፅዳት ፣የችግኝ ተከላና ለወራቤ መቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከል ድጋፍ በማድረግ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትን አከናውነዋል።

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እና ከክልሉ ግብርና ቢሮ በጋራ በመሆና የሞዴል ቤተሰብ በስርዓታ ፆታ ከFSR ጋር በመተባበር  የተሰሩ ስራዎችን  የመስክ ምልከታ ተደረ...
03/09/2026

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እና ከክልሉ ግብርና ቢሮ በጋራ በመሆና የሞዴል ቤተሰብ በስርዓታ ፆታ ከFSR ጋር በመተባበር የተሰሩ ስራዎችን የመስክ ምልከታ ተደረገ!

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ እና ከክልሉ ግብርና ቢሮ በጋራ በመሆና የሞዴል ቤተሰብ በስርዓታ ፆታ ከFSRP ጋር በመተባበር የተሰሩ ስራዎችን የመስክ ምልከታ በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በዱና ቀበሌ ገበሬ ማህበር ተደረገ

የማዕከላዊ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትልና ሴቶች ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራመቶ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የስርዓታ ፆታና የስርዓታ ምግብ ከፍተኛ በለሙያ፣ የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ዋና ሀላፊ አቶ መሀመድ ሺፋ ፣ የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅህፈት ቤት ዋና ሀላፊ ወ/ሮ ፈሪዳ የሲን እናም የክልልና የወረዳው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ክትትልና ድጋፍ ምልከታ ተደርጓል።

በዘሬው እለት በዱና ቀበሌ ገበሬ ማህበር ላይ በገጭም ሴጦ ጎጥ FSRP ከስርዓታ ፆታ ጋር በመተባበር በሞዴል ቤተሰብ በጓሮ አታክልት ና ሌሎች የተቀናጁ የግብርና ስራዎች እንዲሁም የሞዴል ቤተሰቡ አደረጃጀት የተሰሩ ስራዎች የመስክ ምልከታ ተደርጓዋል።

የማዕከላዊ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትልና ሴቶች ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራመቶ እንደገለጹት የሴቶችን የስራ ጫናን ለመቀነስና የሴቶችን እኩልነትን ለማረገጋጥ እና ሴቶች በሀገር ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሰትፎዋቸው ለማረገገጥ ስርዓታ ፆታ ወሳኝ ሚና እንደለው በመግለፅ የተሰሩ ሰራዎች አበርታችና አካታች መሆናቸውን መመልከታቸውና ይበልጥ ውጤቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ሁለቱ ሴክተሮች ተቀናጅተው አደርጃጀቶችን በማጠናከር ተሞክሮው ለሌሎች ለማስፋት በሚቻል መልኩ መጠናከር እንዳለበት ቲሙ ከሰዓት ቡሃለ በተቋም ደረጃ ግብረ መልስ በመስጠት መርሃግብሩ መጠናቀቁን ከወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት የገኘነው መረጃ ያመላክታል

የህፃናት ፓርላማ ለማጠናከርና አቅመ ደካማ ተማሪዎችን ለማገዝ የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ ከ"ሆፕ ፎር ጀስቲስ" ለክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ተሰጠ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሴቶችና ...
02/09/2026

የህፃናት ፓርላማ ለማጠናከርና አቅመ ደካማ ተማሪዎችን ለማገዝ የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ ከ"ሆፕ ፎር ጀስቲስ" ለክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ተሰጠ

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆፕ ፎር ጀስቲስ ጋር በመተባበር የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር በማለም ለሁለት ተከታተይ ቀናት በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ለክልሉ ህፃናት ፓርላማ ማጠናከሪያና ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ከ"ሆፕ ፎር ጀስቲስ" ለክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ተሰጥቷል።

ድጋፉን የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር እና የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ ተቀብለዋል።

በድጋፉ ርክክብ ወቅት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድናስር እንዳሉት የህፃናት ፓርላማን በየደረጃው ማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

ሆፕ ፎር ጀስቲስም በተለያዩ ጊዜያት ስልጠናና ልዩ ልዩ ድጋፎችን በመስጠት አጋዥ የሆነ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በዛሬው እለት ላደረገው ድጋፍ በክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ስም ከልብ አመስግነዋል።

በስልጠናው መድረክ ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ እንደ ቢሮ የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ሰፋፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል።

የህፃናት ፓርላማ አደረጃጀት ዋናኛ አላማ የህፃናትን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ያሉት ወ/ሮ አምሪያ የህፃናት ፓርላማን ከክልል ጀምሮ በየደረጃው እንዲደረጅና ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ፓርላማውን ከማደራጀት በተጨማሪ አጠቃላይ ከፓርላማው በሚከናወኑ ስራዎችና ልዩ ልዩ ርዕሶች ላይ የአባላቱን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና በተቋሙና ከአጋዥ አካላት ጋር በመሆን በየወቅቱ እየተሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለተከታታይ ቀናት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆፕ ፎር ጀስቲስ ጋር በመተባበር የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር በማለም የተሰጠው ስልጠናም የዚሁ አካል እንደሆነ ገልፀው አባላቱ ከስልጠናው በገኙት ግንዛቤ ተግዘው የሚጠበቅባቸውን መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የህፃናት ፓርላማ አባላት በስነምግባራቸው በትምህርታቸውና በስራቸው ለሌሎች ህፃናት አርአያ መሆን እንዳለባቸውም መክረዋል።

በየደረጃው በህፃናት ፓርላማ በክረምት የበጎ ፍቃድ እና በሌሎችም ዘርፎች እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸውም አክለዋል።

የሆፕ ፎር ጀስቲስ ካንትሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሶስና ይርጋ እንደገለፁት ድርጅቱ በየደረጃው የሚገኙ የህፃናት ፓርላማዎችን ለማጠናከር ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን የመስጠትና የቁሳቁስ ድጋፎች እየተደረጉ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም ባለፉት ተከታታይ አመታት የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር የሚያስችል ድጋፍ መደረጉን የገለፁት ዳይሬክተሯ በዘንድሮው አመትም ህፃናት ትምህርታቸውን በተገቢው መከታተል እንዲችሉ በማሰብ ለ150 ልጆች የሚሆን የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

ህፃናትና ወጣቶችን ከዘመናዊ ባርነትና ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተጋላጭነት በመቀነስ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በማሰብ ድጋፉ እንደተደረገ አስገንዝበዋል።

የህፃናት ፓርላማ አባላት የህፃናትና የወጣቶችን ዘመናዊ ባርነትና ህገወጥ ዝውውር ተጋላጭነትን ለመከላከል በስልጠናው በገኙት ግንዛቤ መሰረት ስራቸውን መስራት እንዳለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር በልዩ ልዩ ርዕሶች ላይ የተዘጋጀው ስልጠና በቢሮው የሴቶችና ህፃናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ በሆኑት በወ/ሮ ሰላማዊት ተሰማ እና የሆፕ ፎር ጀስቲስ ፕሮግራም ማናጀር አቶ እንድሪያስ መጣሙ ተሰጥቷል።

ሆፕ ፎር ጀስቲስ የክልሉ መንግስት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን ስራ በማገዝ ላደረገው ጉልህ አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

በጠምባሮ ልዩ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሁሉም ቀበሌ በሴቶች አደረጃጀች የጋራ ፎረም አማካይነት ''እኔ የሰላም እናት ነኝ'' በሚል መሪ ቃል በቅንጅትና ንቅናቄ የሚሰሩ ሥራዎች የአንድ...
02/09/2026

በጠምባሮ ልዩ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሁሉም ቀበሌ በሴቶች አደረጃጀች የጋራ ፎረም አማካይነት ''እኔ የሰላም እናት ነኝ'' በሚል መሪ ቃል በቅንጅትና ንቅናቄ የሚሰሩ ሥራዎች የአንድ ሳምንት መርሃ-ግብር እና የማስፈጸሚያ ስልት ዘመቻን አስመልክቶ ልዩ መድረክ ተካሂዷል።

በዘመቻው መድረክም አንድነትንና ቤተሰባዊ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችል የመላው ኢትዮጵያውያን ልዩ መለያ የሆነው ''ቡና ጠጡ'' መርሃ-ግብርም እንደተካሄደም የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ደሳለች ማቴዎስ ገልጸዋል።

ኃላፊዋ እንዳሉት የሴቶች አንድነትና በጋራ መቆም ለሀገራዊ ሰላም ግንባታ የጎላ ሚና ያለው በመሆኑ ሴቶች ከቤታቸው ተርፎ ለጎረቤትና ለማህበረሰቡ እንድሁም ለሀገር ሰላማዊ ተምሣሌትነታቸውን ልያጠናክሩ እንደሚገባም ማቅረባቸውን ከልዩ ወረዳው የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ የገኘነው መረጃ ያመላክታል።

‎የሀላባ ዞን የሴቶች ህጻናት ጉዳይ መምሪያ የክረምት በጎ ተግባር አካል በሆነው ስለ ሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያተኮረ "ቡና ለሰላም! እኛ ሴቶች፣ የሰላም ባለቤቶች ነን! እኔ የሰላም እናት ...
02/09/2026

‎የሀላባ ዞን የሴቶች ህጻናት ጉዳይ መምሪያ የክረምት በጎ ተግባር አካል በሆነው ስለ ሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያተኮረ "ቡና ለሰላም! እኛ ሴቶች፣ የሰላም ባለቤቶች ነን! እኔ የሰላም እናት ነኝ!›" በሚል መሪ ቃል የዉይይት መድረክ መካሄዱ ተገለፀ

‎በመድረኩ ላይ የክረምት በጎ ተግባር የቴክኒክ ኮሚቴ የሴቶች አባላት እና የሀላባ ዞን የሴት የፐብሊክ ሳርቨንት አባለት የተገኙ ሲሆን፥ በባህላዊ የቡና ስነ-ስርዓት የታጀበው ይህ ውይይት በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን የሰላም፣ የፍቅር እና የሁለንተናዊ አብሮነት እሴት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል ።

‎የሀላባ ዞን ሴቶች እና ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊነት ወ/ሮ እመቤት ጀማል እንደገለፁት ሴቶች በቤተሰብ እና በማህበረሰብ ደረጃ ሰላምን በመገንባት፣ ዘላቂ መረጋጋትን በማስፈን እና ግጭቶችን በውይይት በመፍታት ረገድ የመሪነት ሚና እንዳላቸው በአትኩሮት ተነግሯል ።

‎የቡና ስነ-ስርዓት እንደ ባህላዊ የሰላም መድረክ፡ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል እውቀቶች እና ባህሎች ውስጥ የቡና ስነ-ስርዓት የውይይት፣ የምክክር እና የእርቅ መድረክ በመሆኑ ይህንን እሴት በመጠቀም ህዝባዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ ጭምር ወ/ሮ እመቤት ገልጸዋል ።

‎ሴትች ከህብረተሰብ መሪዎች ጋር በመቀናጀት የሴቶችን አቅም ለበጎ ተግባር እና ለሰላም ማስጠበቅ ስራ ላይ እንዲያውሉ የሚያስችሉ ግንዛቤዎችን በመድረኩ አንስተው ወ/ሮ እመቤት በሰፊው አብራርተዋል ።

‎​"እኛ ሴቶች የሰላም ባለቤቶች ነን፤ የሰላም እናትነት ሚናችንን በመወጣት በክረምቱ በጎ ተግባራችን ለዞናችን እና ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፏል ።

‎በመጨረሻም ሰላም እናት በመለየት በዞኑ በየልማት ህብረቱ ዉይይት አጀንዳው ተጠናከሮ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ማካሄድ እንዳለበት ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ዉይይቱን መጠናቀቁን ከዞኑ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ የደረሰን መረጃ ያመላክታል

02/09/2026
የህፃናት ፓርላማን በየደረጃው በማጠናከር የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል:- ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆፕ ፎር ጀስቲስ ...
01/09/2026

የህፃናት ፓርላማን በየደረጃው በማጠናከር የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል:- ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆፕ ፎር ጀስቲስ ጋር በመተባበር የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር የሚያስችል ስልጠና በሆሳዕና ከተማ እየሰጠ ነው ።

በስልጠናው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከነዚህም መካከል ህፃናት ሁለንተናዊ አቅማቸውን የሚያሳድጉበትና ተሳትፎአቸውን የሚያጎለብቱበትን የህፃናት ፓርላማ ከክልል ጀምሮ በየደረጃው እንዲደረጅና ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚሰራው ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚቻል ባለመሆኑ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበት አመላክተዋል።

ለህፃናት ጠቃሚ የሆኑ ስራዎችን በትኩረት በመስራት ከሚደርስባቸው ጥቃት እንዲጠበቁ ተከታታይነት ያለውን ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

የህፃናት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለጉዳት የሚያጋልጥ እንዳይሆን ወላጆችና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ወ/ሮ አምሪያ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በየወቅቱ የሚሰጡ ስልጠናዎች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ሁሉም የህፃናት ፓርላማ አባላት የሚሰጣቸውን ስልጠና እንደግብኣትነት በመጠቀም ውጤታማ ስራ እንዲሰሩም አሳስበዋል።

ወ/ሮ አምሪያ አክለውም ሆፕ ፎር ጀስቲስ በቢሮው የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እያደረጉት ላለው ድጋፍ በቢሮው ስም አመስግነዋል።

የሆፕ ፎር ጀስቲስ ካንትሪ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሶስና ይርጋ ባስተላለፉት መልዕክት ሆፕ ፎር ጀስቲስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

የወጣቶች ንና የህፃናትን ዘመናዊ ባርነትና ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና የፓርላማ አባላቱ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመከላከል አንፃር ጥሩ ግንዛቤ አግኝተው በየደረጃው በትኩረት እንዲሰሩ ለማስቻል እንደሆነም አመላክተዋል።

ሁሉም የህፃናት ፓርላማ አባላት በሰለጠኑት ስልጠና መሰረት በተገቢው በማስተማር የህፃናትና የወጣቶችን ተጋላጭነት መቀነስ እንዳለባቸውም ወ/ሮ ሶስና መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የህፃናት ፓርላማን ለማጠናከር በልዩ ልዩ ርዕሶች ላይ የተዘጋጀው ስልጠና በቢሮው የሴቶችና ህፃናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ በሆኑት በወ/ሮ ሰላማዊት ተሰማ እና የሆፕ ፎር ጀስቲስ ፕሮግራም ማናጀር አቶ እንድሪያስ መጣሙ ተሰጥቷል።

በስልጠና መድረኩ የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅና የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የሆፕ ፎር ጀስቲስ ኃላፊዎች፣ የክልል የዞንና የልዩ ወረዳ የህፃናት ፓርላማ አመራሮችና የሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ አስተባበሪዎች ተሳትፈዋል።

Address

Central Ethiopia Region Women And Children Affairs Bureau
Werabie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ/ CERS Women & Children affairs Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share