Posetivity is prefer To all things.

Posetivity is prefer To all things. ለሰውና ለሀገር የሚጠቅም ነገር ለመስራት ግዜ አያስፈልግም። ማህበራዊ ሚዲያ ግዜን በተገቢው ይፈልጋል። እውነት ለሀገር ግንባታ እንስራ ለዚህም ግዴታ አመራር መሆን አይጠበቅም። በዚህ ገጽ ትውልድ ስለ ሀገር ያለው ሚናና እውነተኛ መረጃ የሚለቀቅበት ነው።

ጠቃሚ ሀገራዊ ወቅታዊ መረጃዎች በገጹ መልቀቅ

11/04/2026
ምርጫችን ብልጽግና ነውምልክታችን የስንዴ ነዶ ነውመልእክታችን ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገርመንገዳችን  መደመር
11/04/2026

ምርጫችን ብልጽግና ነው

ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው

መልእክታችን ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር

መንገዳችን መደመር

...የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጥ...
11/04/2026

...የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጥልቁ ጨለማ ጠፍተን እንድንቀር አሥረው ለመያዝ የሚሞክሩ ወጥመዶች ብዙ ናቸው። ወደ ተስፋ ምድር እንዳንሻገር የሚጎትቱ ሰበቦች ሞልተዋል። ዳሩ ግን ከሕማማቱ ወዲያ ትንሣኤ፣ ከዕንቅፋቱ ባሻገር ስኬት እንደሚጠብቀን አምነን እንታገላለን። ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )

‎​"ከሀገራችን አልፎ ለአፍሪካና ለሌሎችም ሀገራት ጭምር ሞዴል በሆነ ተቋም ውስጥ ህዝብና መንግስትን ማገልገል መቻል ትልቅ ዕድል ነው" ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው‎፠፠፠፠፠...
31/03/2026

‎​"ከሀገራችን አልፎ ለአፍሪካና ለሌሎችም ሀገራት ጭምር ሞዴል በሆነ ተቋም ውስጥ ህዝብና መንግስትን ማገልገል መቻል ትልቅ ዕድል ነው" ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው
‎፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው ከሀገራችን አልፎ ለአፍሪካና ለሌሎች ሀገራት ጭምር ሞዴል በሆነ ተቋም ውስጥ ሕዝብና መንግስትን ማገልገል መቻል ትልቅ ዕድል ነው ያሉት በጠቅላይ መምሪያው በተዘጋጀ የአቀባበልና የትውውቅ መርሃ-ግብር ላይ ነው።

‎​ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሀገራችን የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ሪፎርም ውስጥ ግንባር ቀደም የሆነ ለውጥና ዕድገት በማስመዝገብ ዘመኑን የዋጀ የፖሊስ አገልግሎት በመስጠት የሀገር ኩራትና መከታ፤ የህዝባችን የክብር መገለጫ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

‎​ተቋሙ በልዩ ሁኔታ በተግባሩና በአስተሳሰቡ የገዘፈ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ፣ ሙያዊ ተልዕኮውን በሚገባ ያወቀና የተረዳ፣ ዜጎች በአለኝታነት የሚተማመኑበት ተወዳዳሪ ተቋም መሆኑን አንስተዋል። በተለይም በሰብዓዊ መብት አያያዙ በዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር የተመሰከረለት መሆኑንም ተናግረው ውጤቱም የአመራሩና የመላው ሠራዊት ሀገርን የማገልገል ከፍተኛ ቁርጠኝነት ውጤት እንደሆነም ገልፀዋል።

‎​ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዕድገትና ለውጥ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ የተመዘገበው ስኬት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ በዲስፕሊንና በሙያዊ ክህሎቱ የተመሰገነ እና ከሀገር የተሻገረ ዕውቀት ያለው ሠራዊት ለመገንባት ከፍተኛ አመራሩ በበለጠ በጋራና በትብብር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎​የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሊሳ አብዲሳ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሰባት የሪፎርም ዓመታት በተሰራው ጠንካራ ሥራ በወንጀል ምርመራ ላይ ይቀርብ የነበረውን ከፍተኛ ቅሬታ በመቅረፍ ተጠያቂነት ያለው አሠራር መዘርጋቱን ጠቅሰው፤ ሕግን አክብሮ የሚያስከብር ፕሮፌሽናል የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠትና የተመዘገበውን ዕድገት ለማስቀጠል ከፍተኛ አመራሩ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

‎​በመርሃ ግብሩ ላይ የጠቅላይ መምሪያው ተጠሪ ምክትል ዋና መምሪያዎችና መምሪያዎች የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
መረጃው የፌደራል ፓሊስ ነው።

10/11/2025
28/10/2025
 #ኢትዮጵያ  #ኦሮሚያ ምዕራብ አርሲ ዞን
20/09/2025

#ኢትዮጵያ
#ኦሮሚያ ምዕራብ አርሲ ዞን

16/09/2025

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Posetivity is prefer To all things. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Posetivity is prefer To all things.:

Share