WKU Software Engineering Students-2011 batch

WKU Software Engineering Students-2011 batch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from WKU Software Engineering Students-2011 batch, Library, Wolkite.

Wolkite University Student Union:WKU-PIRDወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል በተወሰደው እርምጃ የተቋረጠውን የ2012 የሁለተኛው ሴሚስተር ትምህርት...
29/09/2020

Wolkite University Student Union:
WKU-PIRD
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል በተወሰደው እርምጃ የተቋረጠውን የ2012 የሁለተኛው ሴሚስተር ትምህርት በቴክኖሎጂ በታገዘ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ለማስቀጠል መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
20/08/2012
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ሐብቴ ዱላ በሰጡት መግለጫ ዓለማችንን እየተፈታተነ ያለው የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል የተቋረጠውን የ2012 ሁለተኛው ሴሚስተር ትምህርት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የዩኒቨርሲቲው የቅድመ-ምረቃና የድህረ- ምረቃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በያሉበት ሆነው በኦንላይን የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ አንዲከታተሉ በማድረግ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠልጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡
በኦንላይን የሚሰጠው ትምህርት በድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ረገድ የሚፈጥረው ችግር ባይኖርም ለቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በገጽ-ለገጽ የሚሰጠውን ትምህርት ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን እንደማይችል ምክትል ፕሬዚደንቱ አመልክተው ይህንን ለማስተካከል እንዲቻል ወረርሽኙ እንደ አገር ሥጋት እንደማይፈጥር ተረጋግጦ ተማሪዎቹ ወደ ቀድሞው የትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ያደረገ የዳሰሳ ትምህርት የሚሰጣቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዚህም መሠረት የመጀመሪያው አመትና ከዚያ በላይ ያሉት የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በወረርሽኙ ምክንያት የተቋረጠው የ2ኛውን ሴሚስተር ትምህርታቸውን በኦንላይን ለመከታተል እንዲችሉ በየትምህርት መስኩ የተዘጋጁ ሞጁሎች፣ ፓወር ፖይንቶችና የማጣቀሻ መጻህፍት የመሳሰሉትን የትምህርት መሳሪያዎች ለትምህርቱ ጉዳይ በተመረጡ ዌብ ሳይቶች እንዲደርሳቸው የሚደረግ መሆኑን በመግለጽ ተማሪዎች ወደ መደበኛው ትምህርታቸው እንዲመለሱ ጥሪ እስኪደረግላቸው ድረስ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ዌብ ሳይቶች ውስጥ

በመግባትና ኢሜይልንና ሌሎችም ፕላትፎርሞችን በመጠቀም እያነበቡ እንዲቆዩ ምክትል ፕሬዚደንቱ ዶክተር ሐብቴ አሳስበዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚደንቱ አክለውም ኮርስ ወስደው የምርምር ሥራዎቻቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በያሉበት ሆነው በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከአማካሪዎቻቸው ጋር እንዲገናኙ ተደርጎ ቀደም ሲል በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሥራዎቻቸውን በትኩረት ለመከታተል የሚያስችል አሰራር ለመፍጠር እየተሰራ በመሆኑ ተማሪዎች ከወዲሁ ከአማካሪዎቻቸው ጋር በስልክ በመገናኘት ተገቢውን መፈጸም አንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡
አንዲሁም ኮርሶችን በምውሰድ ላይ የሚገኙት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ክፍሎቻቸው ጋር በመሆን ከኮርስ መምህራኖቻቸው ጋር ለመገናኘት የሚያስችላቸው ቴክኖሎጂ እየተዘጋጀ በመሆኑ ከወዲሁ ከትምህርት ክፍሎቻቸውና ከመምህራኖቻቸው ጋር ግንኙነት እየፈጠሩ የመማር-ማስተማሩ ሥራ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡በመጨረሻም መላው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በያሉበት የዘመናችን ፈታኝ ከሆነው ኮሮና ቫይረስ ራሳቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውንና አገራቸውን በመጠበቅ የበኩላቸውን ሀላፊነት እየተወጡ በሚከተሉት የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት በተመረጡት ድህረ-ገጾች እየገቡ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ ምክትል ፕሬዚደንቱ ዶክተር ሐብቴ ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል፡፡ እነሱም፡-
1ኛ/ http://ndl.ethernet.edu.et/
የተዘጋጁ የኮርስ ማቴሪያሎችና አጋዥ የትምህርት ተደራሽ የሚሆኑበት ዲጂታል ላይበራሪ
2ኛ/ http://library.techin.et/
በርካታ ይዘቶችን የያዘው የTechin ላይበራሪ
3ኛ/ https://courses.ethernet.edu.et/
የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል የ learning management system የተሰኙት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች በየጊዜው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በያላችሁበት ሠላም ያብዛላችሁ

The National Academic Digital Library of Ethiopia (NADLE) is a project under Ministry of Science and Higher Education, Ethiopia. The objective is to collect and collate metadata and provide full text index from several national and international digital libraries, as well as other relevant sources.....

Address

Wolkite
123456

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WKU Software Engineering Students-2011 batch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category