Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office

Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office, Wolkite.

ስፖርትን ለአንድነትና ለከተማ ልማት ልንጠቀምበት ይገባል—አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደርወልቂጤ፣ ጳጉሜ 1/ 2018 ዓ.ምስፖርት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሰባሰብ ለአንድ...
06/09/2026

ስፖርትን ለአንድነትና ለከተማ ልማት ልንጠቀምበት ይገባል—አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

ወልቂጤ፣ ጳጉሜ 1/ 2018 ዓ.ም

ስፖርት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሰባሰብ ለአንድነት፣ ለማህበራዊ ትስስርና ለአካባቢ ልማት የሚያግዝ ትልቅ መሳሪያ በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት እንደሚገባ አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገለጹ።

በወልቂጤ ከተማ የሚገኘው የወልቂጤ ጤና እግር ኳስ ቡድን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለጹት፣ ስፖርት ልዩነቶችን በማጥበብ ህብረተሰቡን በአንድ ዓላማ ዙሪያ ለማሰባሰብ የሚያስችል ኃይል በመሆኑ ይህንን አቅም ለከተማዋ አንድነትና ልማት ማዋል ይገባል።

ከእግር ኳስ ውድድር ባለፈም የቡድኑ አባላት በከተማው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ ለአካባቢያዊ ልማት አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ ከንቲባው አስገንዝበዋል።

የጤና ቡድኑ የማህበራዊ መስተጋብርንናg የህብረተሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ ተግባራትን አጠናክሮ በመቀጠል፣ ወጣቶችን በማፍራትና ከሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚካሄዱ የወዳጅነት ጨዋታዎችንና የልምድ ልውውጦችን በማጠናከር የወልቂጤን ከተማ ባህል፣ እሴትና ልምድ ማስተዋወቅ እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቶፊቅ ጀማል በበኩላቸው፣ የወልቂጤ ጤና ቡድን ከእግር ኳስ ቡድንነት ባለፈ ማህበራዊ ትስስርን እየፈጠረ የሚገኝ ቡድን መሆኑን ገልጸዋል።

ቡድኑ ወጣቶች በስፖርት ልምድና ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ ጤናቸውን እንዲጠብቁና ትርፍ ጊዜያቸውን በአምራች ተግባር እንዲያሳልፉ የሚያግዝ መሆኑን የገለጹት አቶ ቶፊቅ፣ በቀጣይም ይህንን ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የወልቂጤ ጤና ቡድን መስራችና ዋና አሰልጣኝ አቶ አብድልሀኒ ተሰማ እንደገለጹት፣ ቡድኑ ከተመሰረተ ስድስት ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን ከ35 እስከ 40 የሚደርሱ አባላትን በማካተት እየሰራ ይገኛል።

ቡድኑ ከስፖርት ተግባሩ በተጨማሪ በተለያዩ በጎ ተግባራት በመሳተፍ ለህብረተሰቡ አርአያ ለመሆን እየሰራ መሆኑንም አሰልጣኙ አብራርተዋል።

በተጠናቀቀው ዓመት ቡድኑ አረጋውያንን በመርዳትና በመደገፍ፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን በዩኒፎርምና በትምህርት ቁሳቁስ በማገዝ፣ በችግኝ ተከላና በከተማው የጽዳት ሥራዎች ላይ በንቃት መሳተፉን ገልጸዋል።

የቡድኑ አባላትም እንደገለጹት፣ ስፖርት ጤናን ከመጠበቅና ውድድርን ከማካሄድ ባለፈ ለማህበረሰብ ጠቀሜታ ያለውን በጎ ተግባር ለማከናወን ዕድል ይፈጥራል።

በመሆኑም ቡድኑ በቀጣይ በስፖርት እንቅስቃሴው ላይ በመቀጠል በከተማውና በሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ያለውን ተሳትፎ ሊያጠናክር ይገባል።

አባላቱ ከወርሃዊ መዋጮ በተጨማሪ የቡድኑን የገቢ አቅም ለማሳደግ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን በማከናወን የቡድኑን ዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።

በዚህም የወልቂጤ ጤና ቡድን ስፖርትን ከጤናና ከውድድር ባለፈ ለማህበራዊ ትስስር፣ ለወጣቶች አቅም ግንባታ፣ ለከተማዋ ዕድገትና ለበጎ ተግባራት ማጠናከሪያ ለማዋል ያለውን ቁርጠኝነት በጉባኤው አረጋግጧል።

በወልቂጤ ከተማ ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን “እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ተከበረጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም | ወልቂጤበጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን “እምርታ ለዘላቂ ከ...
06/09/2026

በወልቂጤ ከተማ ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን “እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ተከበረ

ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም | ወልቂጤ

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን “እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በግብርና ዘርፍ የተመዘገቡ የምርትና ምርታማነት ስኬቶችን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን እና ሊስፋፉ የሚችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመስክ በመጎብኘት ተከበረ።

በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በተካሄደው የእምርታ ቀን የግብርና ሥራ ጉብኝት ዋና ዓላማም “እምርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ የምርትና ምርታማነት ዕድገትን ማበረታታት፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስፋፋትና በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን የበለጠ ማበረታታት ነው።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የእለቱ የመስክ ምልከታ በዋናነት በምርትና ምርታማነት ዕድገት ላይ ልዩ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ መነሳሳትን ለመፍጠርና ተሞክሮን ለማስፋፋት ያለመ ነው።

ከንቲባው አክለውም በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመስክ ማየት፣ የልምድ ልውውጥን ማጠናከርና ሊሰፉ የሚችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስፋፋት በዘርፉ የህብረተሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ ከንቲባው ገለጻ፣ ሀገራችን በኢኮኖሚው እያስመዘገበች ባለው ዕድገት ከተሞች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ሁሉም የከተማው ማህበረሰብ በግብርና ዘርፍ ያለውን ዕድል ተገንዝቦ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይገባዋል።

በተለይም በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ባለሀብቶችና ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን እምቅ አቅምና ሀብት ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር ምርታማ እንዲሆኑና የትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጀምሮ ያለው ድጋፍና ክትትል መጠናከር እንዳለበትም አቶ ሙራድ አስገንዝበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ በቀለ በበኩላቸው፣ ብልጽግና “መንገዳችን መደመር፣ መዳረሻችን ብልጽግና ነው” የሚል መሪ ሀሳብ ሰንቆ በሁሉም መስክ በተግባር የተረጋገጡና በተጨባጭ የሚታዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በግብርናው ዘርፍም በተለይ በከብት እርባታ ላይ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተለያዩ ንዑስ ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አቶ ታደለ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የግሉ ባለሀብቶችና ኢንተርፕራይዞች እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ፣ ከተረጂነት ተላቀው ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ መደገፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ወልደማሪያም ዘሬ በበኩላቸው፣ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚቻለው ጠንካራና ችግር ፈቺ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ሲኖር መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በከተማው ባለፈው በጀት ዓመት ከ420 ሺህ በላይ የአንድ ቀን ጫጩቶች፣ ከ378 ሺህ በላይ የ48 ቀን ጫጩቶች፣ ከ560 ቶን በላይ ወተት እንዲሁም በሰብል ልማት ዘርፍ ከ28 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን ዶክተር ወልደማሪያም ገልጸዋል።

እንደ ዶክተር ወልደማሪያም ገለጻ፣ ብልጽግና መጪውን ዘመን የሚዋጅ ምግባር ባለቤት መሆኑን ካስመሰከሩ ተግባራት መካከል የአረንጓዴ አሻራ፣ የስንዴ አብዮት፣ በሌማት ትሩፍት እና ሌሎች የግብርና ሥራዎች ይገኙበታል፤ በእነዚህም የእምርታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

በእለቱ ከተጎበኙት የግብርና ሥራዎች መካከል የበርደፈር የአንድ ቀን ጫጩትና የእንቁላል ጣይ ዶሮ ማርባት ማህበር ይገኝበታል።

ማህበሩ ለ12 ሰዎች፣ ለ8 ሴቶችና ለ4 ወንዶች፣ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን የማህበሩ ካፒታልም 4 ሚሊዮን ብር መድረሱን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጠሀ ሳሊም ጠቁመዋል።

አቶ ጠሀ ሳሊም ቀደም ሲል የመንግስት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን፣ አሁን ከ3,000 በላይ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን እያረቡ ይገኛሉ።

በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ብድር ተጠቃሚ በመሆን የወሰዱትን ብድር በወቅቱ በመመለስ ተጨማሪ ብድር ወስደው ሥራቸውን እያስፋፉ መሆኑን ገልጸዋል።

ሆኖም በእርባታ ሥራው ያጋጠማቸው ዋነኛ ችግር የእርባታ ቦታ እጥረት መሆኑን አቶ ጠሀ ጠቁመዋል።

ሌላው የጉብኝቱ አካል የግል ባለሀብቷ ወይዘሮ እልፍነሽ ፋርም ሲሆን፣ በዚህ ፋርም ዘመናዊ ባልትና፣ የወተት ሀብት ልማት፣ የከብት ማደለብ እና የመኖ ሀብት ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በፋርሙ የሚመረተው መኖ በዘመናዊ ማሽን ተቀነባብሮ ለከብቶች የሚቀርብ ሲሆን፣ የወተት ማለብ ሥራም በዘመናዊ ማሽን ይከናወናል።

ይህም የምርት ጥራትን ከማሻሻል ባለፈ ብክነትንና የጊዜ ኪሳራን በመቀነስ ፋርሙን የበለጠ ትርፋማ እንዲሆን እያገዘው ይገኛል።

ፋርሙ ከ133 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በቋሚና በጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠሩንና አሁን ያለው ጠቅላላ ካፒታል ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን የድርጅቱ ባለቤት ወይዘሮ እልፍነሽ ጠቁመዋል።

ይህ ፋርም ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከግብርና ሥራ ጋር በማጣመር ምርታማነትን፣ የምርት ጥራትንና የሥራ ዕድል ፈጠራን በአንድ ላይ ያሳየ የእምርታ ተሞክሮ ሆኖ ተመልክቷል።

በቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ግቢ የሚከናወነው የተቀናጀ ግብርና ሥራ
ሌላው በእለቱ የተጎበኘው የግብርና ሥራ በአርሴማ በቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተቋም ግቢ እየተከናወነ ያለው የተቀናጀ የግብርና ሥራ ነው።

ተቋሙ የተቀናጀ የግብርና መተግበሪያና ማሳያ ማዕከል በመሆን የወተት ሀብት ልማት፣ የንብ ሀብት ልማት፣ የጓሮ አትክልት ልማት እንዲሁም ከ4 ሄክታር በላይ የበቆሎ ልማት እያከናወነ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ ገነተ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ/ን አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ መዝገቡ ገልጸዋል።

ይህም የሃይማኖት ተቋማት ከመንፈሳዊ ተልዕኮአቸው ባሻገር በምርታማነት፣ በምግብ ራስን መቻልና በልማት ሥራዎች ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ሚና የሚያሳይ ተሞክሮ ነው።

የፊደል የወተት ሀብት ልማት ማህበር
በጉብኝቱ መጨረሻ የተጎበኘው የፊደል የወተት ሀብት ልማት ማህበር ሲሆን፣ ማህበሩ ለ7 ያህል ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንና አሁናዊ ካፒታሉ ወደ 3 ሚሊዮን ብር መድረሱን የማህበሩ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜሮን መራዊ ተናግረዋል።

ወይዘሮ ሜሮን መራዊ በ2 ሚሊዮን ብር ካፒታል የጀመሩትን የከብት ማደለብና የወተት ሀብት ልማት ሥራ እያስፋፉ የሚገኙ ሲሆን፣ ከገጠሟቸው ችግሮች መካከል የመኖ ቦታ እጥረት ዋነኛው መሆኑን ጠቁመዋል።

በእለቱ በተደረገው የእምርታ ቀን የመስክ ጉብኝት የወተት ምርት፣ የከብት ማደለብ፣ የንብ ሀብት ልማት፣የበቆሎ ማሳ፣ የጓሮ አትክልት፣ የባልትና ውጤቶች ምርት እንዲሁም ሌሎች ጅምር የግብርና ሥራዎች ተጎብኝተዋል።

በአጠቃላይ የእምርታ ቀን በወልቂጤ ከተማ በግብርና ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማየት ብቻ ሳይሆን፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማጠናከር፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከግብርና ጋር ለማቀናጀትና ሊሰፉ የሚችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማስተላለፍ ያለመ የእምርታ መልዕክትን ያጎላ ሆኖ ተከብሯል።

በበዓል ዋዜማ የምርት አቅርቦትና የዋጋ መረጋጋት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየቸሰራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ!ወልቂጤ፤ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ምበበዓል ዋዜማ ...
06/09/2026

በበዓል ዋዜማ የምርት አቅርቦትና የዋጋ መረጋጋት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየቸሰራ እንደሚገኝ የወልቂጤ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ!

ወልቂጤ፤ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም

በበዓል ዋዜማ የሸማቾችን ፍላጎት ለማርካት፣ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች አቅርቦትን ለማረጋገጥና ከተገቢው ያለፈ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅትና የቁጥጥር ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በበዓል ወቅት ሊከሰት የሚችል የምርት እጥረትና የዋጋ ንረትን ለመከላከል ከአምራች ማህበራትና ከተለያዩ የገበያ ተዋናዮች ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማከናወኑን አስታውቋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ግርማ ንቅበሽዋ እንደገለጹት፣ በዓላት በሚያመጡት የገበያ ፍላጎት መጨመር ምክንያት ሸማቾች በተገቢው ዋጋ ምርቶችን እንዲያገኙ ከአምራች ማህበራት ጋር የተቀናጀ ሥራ ተሠርቷል።

በተለይም የሰንበት ገበያ ስፍራዎችን በማመቻቸት አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ ለሸማቾች እንዲያቀርቡ ዕድል ተፈጥሯል።

ይህም በአምራችና በሸማች መካከል ያለውን የገበያ ሰንሰለት በማሳጠር ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ እያስቻለ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በበዓል ወቅት ሸማቾችን በመጠቀም ሕገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ፣ ምርትን በመደበቅ እጥረት ለመፍጠር የሚሞክሩ ወይም የንግድ ሕጉን ተከትለው የማይሠሩ ነጋዴዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም አቶ ግርማ አስረድተዋል።

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓትን ለማስፈን የሚያግዙ ተግባራትም በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

ኃላፊው ሕጋዊና ፍትሐዊ የገበያ ሥርዓት እንዲጠናከር የሸማቾች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዋጋ ጭማሪ፣ በምርት እጥረት ወይም በሌሎች ሕገ-ወጥ የገበያ አሠራሮች ላይ ሕብረተሰቡ በ9348 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል፣ በከተማዋ በተመቻቹ የሰንበት ገበያ ስፍራዎች ምርታቸውን እያቀረቡ ያሉ አምራች ማህበራት፣ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ምርቶችን በበቂ መጠንና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾች ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በገበያ ስፍራዎቹ ያገኘናቸው ሸማቾችም ለበዓሉ የሚያስፈልጓቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዙ እንደሚገኙ ገልጸው፣ አምራችና ሸማችን በቀጥታ የሚያገናኘው የሰንበት ገበያ አሠራር በቀጣይም እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

በመሆኑም የበዓሉን ደስታ የሚያደበዝዝ የምርት እጥረትና ከተገቢው ያለፈ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት፣ አቅርቦትን የማረጋገጥ፣ ገበያን የመቆጣጠርና ሸማቾችን የመጠበቅ ሥራዎች በበዓሉ ዋዜማም ሆነ በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

 #የሳምንቱ ዓበይት ዜናዎች በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደህንነት ካሜራ በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።‎‎በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደ...
06/09/2026

#የሳምንቱ ዓበይት ዜናዎች

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደህንነት ካሜራ በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።

‎በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በ2018 ዓ.ም. የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተጀመሩ የተለያዩ በጎ ተግባራት በሁሉም ዘርፎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።
‎።
‎በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ህንጻ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ የመስክ ጉብኝት በማካሄድ ተገመገመ።

‎የተቋም ግንባታ ስራ እውን ለማድረግ በሚያስችል መልኩ በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የተጀመሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለፀ


‎በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የአረንጓዴ አሻራና የከተማ መሬትን ከሕገ-ወጥ ወረራ የመጠበቅ ሥራዎች በመስክ ተጎብኝተው ተገምግመዋል።

‎ጉህራልድ ከፊንላንድ ኢምባሲ ጋር በመተባበር በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 21 የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናቶች የተሀድሶ ህክምና በአዲስ አበባ በኪዩር ኢትዮጵያ የልጆች ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እንዲጀምሩ መደረጉን ተገለፀ።


‎የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ከየም ዞን እና ከቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶች የ2018 ዓ.ም ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ ሥራ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የተለያዩ የበጎ ተግባራትን አከናውነዋል።

‎በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ፣ ከጥራት ደረጃ በታች የተመረተ እና ለሸማቾች ጤና ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ምርት ወደ ገበያ እንዳይገባ የሚደረገው የቁጥጥርና የኢንስፔክሽን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።



‎ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችንv ለማግኘት ከታች የተቀመጡ ሊኮች በመጫን የተቋማችን ሌሎች የሚዲያ አማራጮችን ይጠቀሙ፡-👇

‎👉Our city portal:- https://admin.wolkitegurageportal.gov.et
‎👉 Our website፦ http://www.wolkitecityadministration.gov.et
‎👉Our guragugna page
https://www.facebook.com/profile.php?id=61582165524047
‎👉Our page https://www.facebook.com/profile.php?id=100071941941290

‎👉 ዩቲዩብ ፦https://youtube.com/.c?si=rqFMyMVDSkYdKny1

‎👉 Our Telegram Channal፦ https://t.me/wcagca

‎👉 Our tiktok Account tiktok.com/.city.gov
‎👉Our Instagram Account::https://www.instagram.com/wolkite_city_gov.tcommun/profilecard/?igsh=MW1uMW43ZTl5MHAwNg==

‎👉Our X Account :-https://x.com/WolkiteA67?t=hnyplUuDhg31lig5TCpw1w&s=09

‎👉ኢ_ሜይል፦ [email protected]" rel="ugc" target="_blank">[email protected] ይጎብኙ
‎👉 ስልክ፦ +251113659879


ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደህንነት ካሜራ ተመርቆ ሥራ ጀመረወልቂጤ፤ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ...
05/09/2026

ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደህንነት ካሜራ ተመርቆ ሥራ ጀመረ

ወልቂጤ፤ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደህንነት ካሜራ በይፋ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።

የደህንነት ካሜራው በከተማዋ የሚከሰቱ የወንጀል ተግባራትን አስቀድሞ ለመከላከል፣ ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝም የምርመራ ሥራን ለማጠናከርና ወንጀል ፈጻሚዎችን በሕግ አግባብ ለማስጠየቅ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በሥራ ላይ ማዋል ወሳኝ ነው።

በተለይም በባጃጅ ላይ የሚፈጸም ዝርፊያ፣ በተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ዝርፊያዎችና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶችን ከመከላከል አንጻር የደህንነት ካሜራዎች ጠቀሜታቸው ከፍተኛ መሆኑን ከንቲባው ጠቁመዋል።

የደህንነት ካሜራዎቹ በስማርት ፖል ቴክኖሎጂ በመታገዝ በተመረጡ የከተማዋ አካባቢዎች መተከላቸው፣ የወንጀል ተግባራትን በቅድሚያ ለመከላከልና የተፈጸመ ወንጀልን በፍጥነት ለመመርመር የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም፣ ከተሞች እያደጉና የነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ሊከሰቱ የሚችሉ የወንጀል አፈጻጸሞችን በብቃት ለመከላከል ዘመኑን የሚመጥን ቴክኖሎጂን መጠቀም እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የደህንነት ካሜራዎችን በከተማዋ በተመረጡ ስፍራዎች በማስፋፋት ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል፣ የፖሊስን የሥራ ጫና መቀነስና የምርመራ ሥራን በመረጃ ማጠናከር የሚያስችሉ ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚከናወኑም አስታውቀዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ በቀለ በበኩላቸው፣ የደህንነት ካሜራ የስማርት ሲቲ አንዱ መለኪያ መሆኑን ገልጸው፣ ፖሊስ ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም በአግባቡ በመጠቀም ለማኅበረሰቡ በሰላምና ደህንነት ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

አቶ ታደለ አክለውም ከተሞችን ከስማራት ሲቲ እሳቤ ጋር በማስተሳሰር ከማዘመን እና ዘመኑ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ አኳያ የደህንነት ካሜራዎች የትራፊክ ቁጥጥር፣ የፀጥታ ስራዎችን፣ ወንጀሎችን ለመከላከል ያግዛል ብለዋል።

በወልቂጤ ከተማ ማኅበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ስልት ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ፖሊስ ከነዋሪው ሕዝብ ጋር በመደጋገፍ ባከናወናቸው ተግባራት ከተማዋ ለነዋሪዎቿም ሆነ ለሚጎበኟት እንግዶች ሰላማዊና ምቹ ከተማ እንድትሆን አስተዋጽኦ ማድረጉን አቶ ታደለ ገልጸዋል።

የወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ መንዚላ አህመድ በበኩላቸው፣ የደህንነት ካሜራው የከተማዋን የሰላምና ደህንነት ሥራ ከማጠናከር ባሻገር በተቋማት ውስጥ የሚሰጠውን አገልግሎት ግልጽ፣ ተጠያቂነት ያለውና ቀልጣፋ ለማድረግ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

አፈ ጉባኤዋ አክለውም፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሕዝብን ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ ተቋማት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተገቢው ሁኔታ እንዲወጡ የሚያግዝ የቁጥጥርና የተጠያቂነት መሣሪያ መሆኑን ጠቁመው፣ ቴክኖሎጂው ከሕግና ከሥነ ምግባር መርሆች ጋር ተጣጥሞ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል ተቋማት በኃላፊነት ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ይታገሱ ደሳለኝ እንደገለጹት፣ በከተማው የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ሕንፃ ላይ የደህንነት ካሜራ ተተክሎ የተቋሙን ደህንነት ከመቆጣጠር ባሻገር በመደበኛ የሥራ ሰዓት ሠራተኞች ለአገልግሎት ፈላጊዎች በራቸውን ክፍት አድርገው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ለመከታተልም እያገለገለ ነው።

የደህንነት ካሜራው በፖሊስ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የሚከናወኑ የሥራ እንቅስቃሴዎችንና የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ለመከታተል እንዲሁም የተቋሙን ንብረትና ሕንፃ ደህንነት ለመጠበቅ ጠቀሜታ እያለው መሆኑን አዛዡ ገልጸዋል።

የተገጠሙት የደህንነት ካሜራዎች ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ዜጎች ደህንነት ተሰምቷቸው እንዲኖሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በከተማዋ በሁሉም አካባቢዎች በፖሊስና በሕዝብ ትብብር አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የገለጹት አዛዡ፣ ማኅበረሰቡ ከፖሊስ ጎን በመቆም በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ የሚያደርገውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በአጠቃላይ፣ የደህንነት ካሜራው በወልቂጤ ከተማ የሰላምና ደህንነት ሥራን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ወንጀልን በቅድሚያ ለመከላከል፣ የምርመራ ሥራን ለማጠናከር፣ የፖሊስን የሥራ ጫና ለመቀነስና ከተማዋን የበለጠ ሰላማዊ፣ ደህንነቷ የተጠበቀና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የሚያግዝ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የከተማ የፊት አመራሮች፣ የካቢኔ አካላት፣ የከተማ የፀጥታ የዘርፍ አመራሮች፣ ተሳትፈዋል።

የከተማን ውበትና የመንገድ ደህንነት ለማሳደግ የዚብራ መስመሮች በበጎ ፈቃደኞች ተቀብቷልወልቂጤ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት አካል የሆነው የከተማዋ...
05/09/2026

የከተማን ውበትና የመንገድ ደህንነት ለማሳደግ የዚብራ መስመሮች በበጎ ፈቃደኞች ተቀብቷል

ወልቂጤ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት አካል የሆነው የከተማዋን የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገዶች የዚብራ መስመሮችን የመቀባት ሥራ ተከናወነ።

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ተስፋ በጎ አድራጎት ክበብ ከከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እንዲሁም ከከተማዋ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ይህን በጎ ተግባር አከናውኗል።

የዚብራ መስመሮችን በግልጽና በተገቢው ሁኔታ መቀባት ለከተማዋ ውበት ከሚያበረክተው ጥቅም ባሻገር፣ እግረኛ ተጠቃሚዎች መንገድ በሚሻገሩበት ወቅት ተገቢውን የትራፊክ ጥንቃቄ እንዲያገኙ እና የመንገድ ተጠቃሚዎችም የእግረኞችን የመሻገሪያ ቦታ በግልጽ እንዲለዩ ያግዛል።

በተለይም በከተማ መሃል በሰውና በተሽከርካሪ ፍሰት የበዛባቸው መንገዶች ላይ የዚብራ መስመሮች ግልጽነት የእግረኞችን የመንገድ መሻገሪያ ሥፍራ በማመላከት ለትራፊክ ደህንነት የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል።

የአዲስ ተስፋ በጎ አድራጎት ክበብ ያከናወነው ተግባርም በጎ ፈቃድ ማለት በገንዘብ ወይም በቁሳቁስ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን፣ የራስን ጊዜ፣ ጉልበትና አቅም ለማህበረሰብ ጥቅም በነፃ ማዋል መሆኑን ያሳያል።

በጎ ፈቃደኞች በሚኖሩበት አካባቢ የሚታዩ የማህበረሰብ ችግሮችን በመለየት በተግባር መፍትሔ ለማምጣት መሳተፋቸው የዜጎችን የከተማ ባለቤትነት ስሜት ከማጠናከር ባለፈ፣ የመንግስትና የማህበረሰብ ተቋማት በጋራ ሲሰሩ የሚፈጠረውን ውጤታማ ትብብርም ያሳያል።

የዚህ ዓይነቱ በጎ ተግባር በከተማዋ የንፅህና፣ የውበትና የደህንነት ሥራዎች ላይ ህብረተሰቡ በቀጣይነት እንዲሳተፍ የሚያነሳሳ ሲሆን፣ ወጣቶችም በአካባቢያቸው ልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ ሚና እንዲወጡ የሚያበረታታ ነው።

የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትም በከተማዋ በተለያዩ ዘርፎች የሚከናወኑ የበጎ ተግባራትን በማስተባበር የዜጎችን ተሳትፎ እያሳደገ ይገኛል።

በጎ ፈቃድ የሚጀምረው ከራስ ጊዜና ጉልበት ሲሆን፣ ውጤቱ ግን ለመላው ማህበረሰብ ስለሆነ ተሳትፏችን አጠናክረን እንቀጥል።

ወሄም ሳረነም! ወሄም ሳረነም! እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን! የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ልዩ ተሸላሚ ሆነወልቂጤ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከ...
05/09/2026

ወሄም ሳረነም! ወሄም ሳረነም!
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን!

የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ልዩ ተሸላሚ ሆነ

ወልቂጤ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው አመርቂ የሥራ አፈጻጸም በዞኑ ከሚገኙ መዋቅሮች መካከል ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነ።

ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ የልማት ሥራዎችን በዕቅድና በትጋት በማከናወን፣ ለከተማው ነዋሪዎች የሚጠቅሙ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማስፋፋት እንዲሁም ቀልጣፋና ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል።

የተገኘው እውቅናም ጽ/ቤቱ በልማት ሥራዎችና በአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ያሳየውን ተግባራዊ አፈጻጸም ከፍ ብሎ የሚያሳይ ሲሆን፣ ውጤቱ የከተማው አመራሮች፣ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የማኅበረሰቡ የተቀናጀ ጥረት ውጤት መሆኑ ተመላክቷል።

ለጽ/ቤቱ በተሰጠው እውቅና መላው የወልቂጤ ከተማ አመራርና ማኅበረሰብ ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ይህ ስኬት በቀጣይ የበለጠ ለመሥራት ተጨማሪ ማበረታቻ እንደሚሆን ተገልጿል።

ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤቱም የተጀመሩ የልማትና የአገልግሎት ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል፣ የከተማውን ነዋሪ ተጠቃሚነት ይበልጥ በማረጋገጥና ከዚህ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ የላቀ የአገልግሎት ተሞክሮን ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጧል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! 🏆👏

የወልቂጤ ከተማ ስኬት ይቀጥላል!

የጉራጌ ዞን ከተማ ተርማሞትም ኮንስትራክሽን መምሪያ የ2018 በጀት ዘበር የᎈጅᎄ የሴክቶሪያል ጉባይ አትነት የጥዳት፣ የትቦት አገግሮት፣ ውሳኔ የተርማᎀት ቢብር አንፍ ወባጀ በወርቕጥየ ከተማ...
05/09/2026

የጉራጌ ዞን ከተማ ተርማሞትም ኮንስትራክሽን መምሪያ የ2018 በጀት ዘበር የᎈጅᎄ የሴክቶሪያል ጉባይ አትነት የጥዳት፣ የትቦት አገግሮት፣ ውሳኔ የተርማᎀት ቢብር አንፍ ወባጀ በወርቕጥየ ከተማ ቲያሜ ይትረከብ።

ናሴ 30/2018 ዘበር (ወርቕጥየ)

የጉራጌ ዞን ከተማ ተርማሞትም ኮንስትራክሽን መምሪያ አላፊ እመዌቸ ትብለጥ እስጢፋኖስ ጭዋዳ ቲከፍተማ በ2018 ዘበር ኸልቅዌ በጥሬ ፍራንክ፣ በጉልበት፣ በግብር ተ722 ሚሊየን ብር በረን እጐዠ ዋሚየታ ነሰማም።

ተዝም በᎈር በበጀት ዘበርዌ 70 ኪሎ ሜትር ይምር ኤማ ሽኳቸም 149 ተኪየ 7 ኪሎ ሜትር ቶክፍት በረን፣ 62 ተኪየ 57 የማብራት ወዝራጋ፣ 77 ተኪየ 4 ይሀ መስመር ወትዝራጋታ ኦደማም።

በሔተነዌ ዙር ያት ከተማ ኣት ፕሮጀክት ተርሰሶት 28 ፕሮጅክት ቦᎈጅ ያገግሮት ወክፍት ኸረም።

ከተማዌ ይረብሮዌ ይሽርም ይሸብ የቄጥ የርብረት በተርሰሶት ይትመችኸማ ዮዋሚ የቈነሽዮ የተርማሞት ሜናዌ አጥናኰርም ወቕጥር ይትጐባው የባሮ።

ቦባጀ መድረክዌ የጉራጌ ዞን ሔተነ ያትዳድሮ አበቃጥ አበራ ወንድሙ፣ የጉራጌ ዞን የመንግስት የጉዣ ይጠኖ አበቃጥ ደሳለኝ ፈቀደ፣ የዞንዌ ወባጀ ቤት የኢኮኖሚ ዘፈር ቋሚ ኮሚቴ ይስበስብ እመዌቸ ወይዘሮ ጠጄ ደነቀ፣ የዞን የቤሮም ኮንስትራክሽ መምሪያ ኣላፊዌ እመችዌ ትብለጥ እስጢፋኖስ፣ ዮረዳም የከተማ አተድር ያትየድሮዌ፣ ከንቲባዌም የጥፈት ቤት ኣላፊዌ፣ የማዘጋጃ ቤት ሜና ያቾቶ፣ የመምሪያዌ የኸልቅ ክንፍ አካል የመምሪያዌ ማኔጅመንትም ሜነነ ተረከቦም።

ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ በወልቂጤ ከተማ ተካሄደወልቂጤ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሳምንታዊ የጋራ...
05/09/2026

ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ

ወልቂጤ፣ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሳምንታዊ የጋራ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ።

በዘመቻው የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑን ጨምሮ የከተማው አስተባባሪ አካላት፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የሴፍቲኔት ሰሪ ሀይሎች፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በንቃት ተሳትፈዋል።

ምክትል ከንቲባና ጤና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ በጽዳት ዘመቻው ላይ በመሳተፍ የጽዳት ሥራ የከተማ መንግሥት ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የእያንዳንዱ ነዋሪ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አመላክተዋል።

ከተማዋን ንጹህ፣ ማራኪና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚከናወኑ የጽዳት ሥራዎች በዘመቻ ጊዜ ብቻ ሳይወሰኑ የዕለት ተዕለት ባህል እንዲሆኑ የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

የጽዳት ዘመቻው ዋና ዓላማም የከተማዋን ንጽህናና ውበት ማስጠበቅ፣ ከቆሻሻ አወጋገድ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን መቀነስ እና ነዋሪዎች በጋራ ኃላፊነት የሚሳተፉበትን የንጽህና ባህል ማጠናከር መሆኑ ጠቁመዋል።

በተለይም የከተማ አስተዳደሩ ከነዋሪዎች፣ ከወጣቶች፣ ከመንግሥት ተቋማትና ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር የሚያካሂደው የጋራ የጽዳት ዘመቻ የከተማዋን ንጽህና ከማስጠበቅ ባለፈ የህብረተሰቡን የጋራ ተሳትፎ ለማጠናከር አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ገልጸዋል።

በዘመቻው ላይም የዕለት ተዕለት የጽዳት ሥራዎችን እንዲሁም በየሳምንቱ የሚካሄደውን የጋራ የጽዳት ዘመቻ ከወትሮው በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ንጹህ ከተማ የጋራ ኃላፊነት፣ የጋራ ጥረትና የጋራ ባለቤትነት ውጤት ናት” የሚለውን መርህ በተግባር ለማስረጽ፣ ሳምንታዊ የወልቂጤ ከተማ የጽዳት እንቅስቃሴዎች በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ተጠቁሟል።

ወሄም ሳረነም! ወሄም ሳረነም! እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን! በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው የትምህርት ጉባኤ ላይ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰ...
04/09/2026

ወሄም ሳረነም! ወሄም ሳረነም!
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው የትምህርት ጉባኤ ላይ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መካከል፣ ከአዳሪ ትምህርት ቤቶች ውጪ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዘርፍ፣ የዋልቡርግ ትምህርት ቤት ተማሪ አብድልሀፊዝ ሙሰማ የ568.17 ውጤት በማስመዝገብ በክልሉ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የታብሌትና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል።

ይህ ድንቅ ውጤት የተማሪውን ትጋት፣ ትምህርት ላይ ያለውን ቁርጠኝነትና የላቀ የትምህርት ውጤት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ የዋልቡርግ ትምህርት ቤትና የወልቂጤ ከተማ በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን አበረታች ውጤት የሚያረጋግጥ ታላቅ ስኬት ነው።

በመድረኩም የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ዞኖች መካከል 1ኛ ደረጃን በመያዝ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ መሆኑ የድሉን ደስታ የበለጠ አጠናክሮታል።

ይህ ድል የአንድ ተማሪ ስኬት ብቻ አይደለም፤ የተማሪዎች፣ የወላጆች፣ የመምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮችና የመላው የጉራጌ ዞን ህዝብ የጋራ ድል ነው!

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን!

ለተማሪው አብድልሀፊዝ ሙሰማ፣ ለወላጆቹ፣ ለመምህራን፣ ለዋልቡርግ ትምህርት ቤት አመራር፣ ለጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ እና ለመላው የዞናችን ህዝብ እንኳን ደስ አለን!
የዛሬ ስኬት የነገ ታላቅ ስኬት መነሻ ይሁን!

ወሄም ሳረነም!
ወሄም ሳረነም!

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share