Gurage zone administration

Gurage zone administration Gurage zone administration is located at Ethiopia federal democratic republic government south nation nationality people regional government.

በመስኖ ልማት ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ነው ፡፡ በኑሬ ረጋሳአርሶአደሩ የዝናብን ወቅት ተጠቅሞ በልግና መህር ያርሳል ከዚህም በተጨማሪ በየአካባቢያቸው ያሉትን የውሃ አማራጮችን ተጠቅመው በመስኖ ...
12/02/2018

በመስኖ ልማት ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ነው ፡፡
በኑሬ ረጋሳ
አርሶአደሩ የዝናብን ወቅት ተጠቅሞ በልግና መህር ያርሳል ከዚህም በተጨማሪ በየአካባቢያቸው ያሉትን የውሃ አማራጮችን ተጠቅመው በመስኖ ልማት ስራ ተሰማርተው ውጤታማ ስራ በመስራት ምርትና ምርታማነታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደጉ ይገኛል፡፡
በቸሀ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በሴቶች እና በወጣቶች ውጤታማ የመስኖ ልማት ስራዎች በባለ ድርሻ አካላቶች ሰሞኑን ተጎብኝተዋል፡፡
አርሶአደሩ በየአመቱ የግብአት አጠቃቀምና የምርትና ምርታማነት እድገት በከፍተኛ ሁኔታ እየለወጠ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
በየአካባቢው ያለውን የውሀ አማራጮች በመጠቀም የተለያዩ አትክልቶችን በማምረት የአርሶአደሩ ህይወትና ኑሮ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን እየለወጡ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
በወረዳው በመስኖ ልማት በየጊዜው ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ሲሆን በዚህም የአርሶደሩ፤የወጣቶች እና የሴቶች የገቢ አቅማቸው እያሳደጉ እንደሆነም የማይዋሽ ሀቅ ነው፡፡
ወጣት ዳንኤል ሽፈታ በቸሀ ወረዳ በወድሮ ቀበሌ ያሚኒ የመስኖ ልማት ማህበር አባል ሲሆን የመጀመሪያው ዲግሪው በሰመራ ዩንቨርሲቲ በሆልቲ ካልቸር ተመርቋል፡፡
ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ እንደወጣ ቲናው የአበባ እርሻ ልማት ማህበር በወር 3 ሺህ ብር እየተከፈለው ለ4 ወራት ያህል ሰርቷል፡፡
መንግስት ለገጠር ወጣቶች ያመቻቸውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቅሞ ከ አራት አባላቶቹ ጋር በመደራጀት በመስኖ ልማት 10 ሄክታር መሬት ከመንግስት ተቀብለው እያለሙ ይገኛሉ፡፡
በማህበር ተደራጅተው መስራት ከጀመሩ በኋላ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ እንደሆነምና ውጤታማ ስራ እየሰሩ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሌሎች ወጣቶች የስራ እድልን መፍጠር መቻላቸው ነግሮናል፡፡
በዚህ ተግባር ሲሰማሩ መነሻ ካፒታላቸው 35 ሺህ ብር እንደነበረ እና በመጀመሪያ አመት ስራቸው 80 ሺህ ብር ትርፍ ማግኘት እንደቻሉም ወጣት ዳንኤል ተናግሯል፡፡
በጉብኝቱ የተገኙት የጉራጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ሀላፊ አቶ አለም ይርጋ ወልደስላሴ እንዳሉት በተያዘው በጀት አመት ሁሉም አርሶአደሮች በመስኖ ልማት ስራ እንዲሳተፉ ለማድረግ ለባለሞያዎችና ለአርሶአደሩ የክህሎት ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡
በዚህም በመጀመሪያው ዙር በመስኖ ልማት 57 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ግብ ተይዞ ወደ ተግባር በመግባት እስካሁኑም ባለው ሂደትም 45 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ተናግረው የአርሶአደሩ የግብአት አጠቃቀም በየጊዜው መሻሻል እየታየበት እንደሆነና በሄክታር ኤንፒኤስ ከአንድ ኩንታል በላይ እንዲሁም ዩሪያ 68 ኪሎ ግራም እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡
ቀደም ሲል በዞኑ መስኖ የሚያለሙ ውስን ወረዳዎች ብቻ እንደነበሩ አስታውሰው በአሁኑ ወቅት ሁሉም አካባቢዎች ቀደም ሲል በመስኖ ተግባር በተሰማሩ በሶዶ ፣ በመስቃን ፣በማረቆ ወረዳዎች ልምድ በመውሰድ በተጠናከረ ሁኔታ እየሰሩበት ይገኛል ብለው በዘርፉም ለውጥ ካመጡበት ወረዳዎች ውስጥ የቸሀ ወረዳ ተጠቃሽ ነው፡፡
በመስኖ ልማት ስራ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ነው ያሉት ሀላፊው በዚህም የሴቶችና የወጣቶች ተጠቃሚነት በስፋት እየተረጋገጠ ይገኛል ብለው ሁሉም ወረዳዎች የተለያዩ የውሀ አማራጮችን ተጠቅመው በበጀት አመቱ የተያዘውን እቅድ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት አየተሰራ ይገኛል፡፡
በዞኑ የመስኖ ልማት ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል የታየበትና የአርሶአደሩም ምርትና ምርታማነት አየተረጋገጠ የመጣበት እንደሆነና ኢኮኖሚያቸው እያሳደጉ ይገኛሉ ያሉት ሀላፊው የሚመረተው ምርት የገበያ ትስስር በመፍጠር በኩል የሚታየውን ውስንነት በዘላቂነት ለመቅረፍ አጽኖት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡
ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር በመጀመሪያው ዙር ያለሙ 12 ሺህ ሄክታር መሬቶች በሁለተኛው ዙር እንደሚለማም አክለው ገልጸውልናል፡፡
የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሰይድ እንዳስታወቁት በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች መስኖ የማልማት ስራ በስፋት እየተሰራበት እንደሆነም ተናግረው በዚህም በርካታ አርሶደሮች፣ ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ወንዝ የሌለባቸው አካባቢዎች ሰፋፊ ኩሬዎችን የመቆፈር ስራ በብዛት ማከናወን የተቻለ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት አመታት በተከናወኑ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ለመስኖ ስራ የሚሆኑ ሰፋፊ ኩሬዎችን በአርሶአደሩ ጉልበት መቆፈር እንደተቻለም፡፡
በዘንድሮ አመት በመስኖ ልማት ስራ የተያዘውን እቅድ ስኬተማ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነም ተናግረው ለዚሁም ተግባር የሚውል ወደ 2 መቶ የሚጠጉ ሞተር ፓንፖች አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረገ እንደሆነና የአርሶአደሩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውስንነት በተገቢው መቅረፍ የሚያስችል ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሩፋኤል ንዥናጋ በበኩላቸው በዘንድሮ አመት በወረዳው ያሉትን የውሀ አማራጮችን በመጠቀም 4 ሺህ 4መቶ 16 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ግብ ተጥሎ እየተሰራ ሲሆን በዚህም 4ሺህ 16 ሄክታር መሬት መሸፈኑም አስታውሰዋል፡፡
የአርሶአደሩ የግብአት አጠቃቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደሆነ ጠቅሰው በአምና ደረጃ በአንድ ሄክታር መሬት ከ60 እስከ 70 ኪሎ ግራም ማዳበሪያ ይጠቀሙ እንደነበር ያስታወሱት ሀለፊው በዘንድሮ አመት 100 ኪሎ ግራም በሄክታር ተጠቅመዋል፡፡
በወረዳው በመስኖ ልማት ሴቶች ወጣቶች እና አርሶ አደሮች በስፋት ተጠቃሚ እየሆኑ ሲሆን በዚህም በወረዳው በዘንድሮ አመት ከተያዘው 10 በመቶ በወጣቶች ፣30 በመቶ በሴቶች እንዲለማ መደረጉም ተናግረው በወረዳው 23 ሺህ አርሶአደሮች በመስኖ እንደሰማሩ ማድረግ ተችሏል፡፡
ወጣቶችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የገበያ ትስስሩ ላይ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ ጠቅሰው ችግሩንም ለመፍታት ፣በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማዎች እንዲሁም ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር የገበያ ትስስር እየተፈጠረ ሲሆን በዚህም አበረታች የሚባል ለውጥ ማምጣት መቻሉም አስረድተዋል፡፡
በመስኖ ተግባር ላይ በማህበር ተደራጅተው የሚሰሩ አንዳንድ ወጣቶችና ሴቶች በሰጡት አስታያየት የውሀ አማራጮችን በመጠቀም ጎመን ፣ካሮት፣ ቲማቲምና ሌሎችም አትክልቶችን በማልማት ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱም ከዞንና ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች ፣ ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ አርሶአደሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ሲቪል ሰርቫንቱ በመሰረታዊ የኮምፒተር እውቀት እንዲታገዝ በማድረግ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዳለበት የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡ለሶስት ተከታታይ ወራት የመሰረታዊ ኮምፒው...
12/02/2018

ሲቪል ሰርቫንቱ በመሰረታዊ የኮምፒተር እውቀት እንዲታገዝ በማድረግ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዳለበት የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡
ለሶስት ተከታታይ ወራት የመሰረታዊ ኮምፒውተር እውቀት ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሰራተኞች ተመረቁ፡፡
በምረቃው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ተወካይ አቶ ሙላት ሸሪፍ እንዳሉት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ሰራተኞች መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡
ተመራቂዎችም በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው በመስራት የህዳሴውን ጉዞ ማስቀጠል እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና የስራ ሂደት የኔትወርክ ዳታ አድሚንስተሬተር አቶ ምትኩ ዳንኤል በበኩላቸው ሲቪል ሰርቫንቱ ያለበትን የኮንፒውተር የክህሎት ውስንነት በተገቢው ለመቅረፍ ጽህፈት ቤቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በአመት አራት ጊዜ ከየሴክተር መስሪያ ቤቶች አንዳንድ ባለሙያ ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ለሶስት ተከታታይ ወራት በመሰረታዊ የኮንፒውተር አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነም አብራርተው ከጥቅምት 5 /2010 እስከ ጥር 5/2010 አመተ ምህረት ድረስ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 14 ሰራተኞች ማስመረቅ መቻሉም አስረድተዋል፡፡
ስልጠናውን የወሰዱ አካላቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፎች የአገልግሎት አሰጣጡን እንዲቀላጠፍ ለማድረግ ስልጠናው ወሳኝ ሲሆን ይህንንም ተግባራዊ የማድረግ ሀላፊነት በመውሰድ በተቋማቸው የተያዘውን እቅድ ስኬታማ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ስልጠና በሚሰጥበት ወቅት አልፎ አልፎ የመብራት መቆራረጥ ይስተዋል የነበረ ሲሆን ይህም በስራቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳሳደረባቸው አስታውሰውዋል፡፡
ስልጠናው ከተከታተሉ ሰልጣኝ ተመራቂ መካከል አቶ አሰበ ፋንቱ በሰጡት አስተያየት በቆይታቸው በቂ እውቀት ማግኘት እንደቻሉና ለተሰማሩበት ስራ አጋዥእንደሆነላቸውም አስረድተዋል፡፡
አክለውም አሰልጣኖች በመሰረታዊ ኮምፒውተር እውቀት በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያደርጉት ጥረት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል

ባለሀብቶች አካባቢያቸውን ለመለወጥና ለማልማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ 150 ሚ...
09/02/2018

ባለሀብቶች አካባቢያቸውን ለመለወጥና ለማልማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ወጣቶችና
ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ 150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡፡
በምረቃው ፕሮግራሙ የተገኙት የኢፌዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስተር ሚኒስቴር አቶ እርስቱ ይርዳ እንዳስታወቁት መንግስት የህዝቡን መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየመለሰ ይገኛል ፡፡
በንጹህ መጠጥ ውሃ ፣በትምህርት ግንባታ በጤና አገልግሎት እና በተለያዩ ዘርፎች የልማት አጋር ድርጅቶች ፣ ባለሀብቶች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም አካባቢን እንዲለማ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡
በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች አርአያነት ያለው ስራ እየሰሩ ሲሆን በወረዳው በአተክልትና ፍራፍሬ ኤክስፖርት ማድረግ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ እንዳለ የተናገሩት ሚኒስተሩ ባለሀብቶች አካባቢያቸውን ለመለወጥ ተባብረው በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የወረዳዎች የመፈጸም አቅም እያደገ መምጣቱን ተናግረው የእዣ ወረዳ ህብረተሰቡን በልማት አነሳስቶ ለዞኑ ሞዴል የሚሆኑ የልማት ስራዎች እያከናወኑ ሲሆን በግብርና ዘርፍ የአርሶአደሩ ህይወት እንዲሻሻልና የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ እየተሰራ ያለውን ስራ አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ኮርንማ በበኩላቸው በወረዳው በመንግስትና በረጂ ድርጅቶች የለሙ ከዳርቻ እስከ ዋቤ የተሰራው መንገድ ፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማት፣ የወሃና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ግንባታዎች ህብረተሰቡ የራሱ መሆኑን ተገንዝቦ በአግባቡ ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡
ባለሀብቶች በግብርና ስራ ፣በውሃ ማኒፋክተሪንግ ፣ ሎጅ በመገንባት እና በተለያዩ ኢንቨስትመንት ላይ በርካታ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ ውጤታማ ስራ እየሰሩ ሲሆን በዘህም ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለም አስረድተዋል፡፡
በዞኑ በማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስቱሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በርካታ ቦታዎች በማዘጋጀት አካባቢያቸውን የንግድ ኢንዱስትሪ ለማድረግ ያለምንም እንግልትና ስቃይ መንግስት ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት የማቅረብ ስራ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
የእዣ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ናስር ሀሰን እንደተናገሩት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመንገድ ፣የቴከኒክና ትምህርት ተቋማት እና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ግንባታዎች ተከናውነዋል፡፡
ለነዚህ ግንባታዎች ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውም ተናግረው የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶች ለወረዳው ልማትና እድገት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸውም አስረድተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡

አርባ አምስት አመት መኪና ስነዳ ምንም አይነት አደጋ አድርሼ አላውቅም፡፡መጀመሪያ ባሮ ድልዲን ከመሀንዲሶች ጋር የቅየሳ ስራ የሰራነው እኛ ነን፡፡( አርአያችን አሽከርካሪ አቶ ሀሰን ሰይድ)በ...
09/02/2018

አርባ አምስት አመት መኪና ስነዳ ምንም አይነት አደጋ አድርሼ አላውቅም፡፡
መጀመሪያ ባሮ ድልዲን ከመሀንዲሶች ጋር የቅየሳ ስራ የሰራነው እኛ ነን፡፡
( አርአያችን አሽከርካሪ አቶ ሀሰን ሰይድ)
በኑሬ ረጋሳ
በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው በመኪና አደጋ ያጣሉ፡፡ ለሰው ልጆች ሞትና ለንብረት ውድመት ብዙ ጊዜ በምክንያትነት የአሽከርካሪው የችሎታ ማነስ፣የተሽከርካሪ ችግር … ወዘተ የሚባሉት አደጋ ከደረሰ በኃላ እንደምክንያት በሰዎች አንደበት ሲነገር ይሰማል፡፡
አሁን አሁን በእኛው ሀገር በመኪና አደጋ የሚሞተው ህዝብ ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም ለዚህም ከመጠን በላይ ማሽከርከር ፣ መንጃ ፍቃድ ሳይኖራቸው በማሽከርከር ፣ተረጋግቶ አለመንዳት፤ለእግረኛ ቅድሚያ ባለመስጠት ስንቱን ምክኒያት ጠቅሼ አልጨርሰውም ለማንኛውም ረጋ ብሎ ማሽከርከር ለራስ ነውና ስናሽከረክር ረጋ ብለን እናሽከርክር፡፡
ዛሬ በዚህ ጹሁፍ ያሁኑን ትውልድ ያስተምራሉ ያልኳቸውን አንጋፋው አሽከርካሪ አቶ ሀሰን ሰይድ በጉራጌ ዞን መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ መኪና አሽከርካሪ ናቸው የእሳቸው የህይወት ተሞክሮን በወፍ በረር ላስቃኛቹሁ ወደድኩ መልካም ንባብ፡፡
አቶ ሀሰን ሰይድ ተወልደው ያደጉት በምስራቅ ሀረርጌ ቀርሳ መንደር ሲሆን በልጅነታቸው ሀረርን ለቀው በመውጣት ደብረብርሀን ከተማ ላይ ከተሙ ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸው ደብረ ብርሀን አጼ ዘረያዕቆብ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ እየሰሩበት ላለው የመኪና ማሽከርከር ሙያ የሚሆን ትምህርት በትርፍ ጊዜያቸው ጋራዥ ውስጥ ሙያ በመማር የመንጃ ፍቃድ ትምህርት ተከታትለዋል፡፡
አቶ ሀሰን ሰይድ የ65 አመት ጎልማሳና የአንድ ወንድ ልጅና የአንድ ሴት ልጅ አባት ሲሆኑ ሁለቱም ልጆች አስተምርው ለወግ ለማዕርግ አብቅተው የልጅ ልጆችም ማየት ችለዋል፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ ወደ መኪና የማሽከርከር ሙያ ስገባ አብራጎዳና ተቀጥሬ ስሰራ ነበር በዚህ ድርጅት ውስጥ ከ20 አመት በላይ ሰርቻለሁ ብለው በመቀጠልም ወደ ገጠር መንገድ ተዘዋውረው መስራታቸው አውስተውኛል ፡፡
በመኪና የማሽከርከር ሙያ 45 አመት እንደሆናቸው እና በዚህ ሙያ ጡረታ ወጥው እንደነበረ ነግረውን የመስራት ወኔያቸው ስራ ስራ ብቻ ስለሚል ጡረታ ወጥቼ ዝም ብዬ መቀመጥ የለብኝም በማለት የዞኑ አስተዳደር መስራት እንደምችልና ጉልበቴ እንዳልዛለ አመልክቼ መኪና እንዲሰጠኝ ጠይቄ በኮንትራት ተቀጥሬ መኪና ተሰጥቶኝ በሰላም ረጋ ብዬ እያሽከረከርኩ ነው በአሁኑ ወቅት ህይወቴን የምመራው፡፡
አርባ አምስት አመት መኪና ስነዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ያላየሁት ሀገርና ያልረገጥኩት ከተማ የለም ማለት ይቻላል የቀረኝ ሰማይ ላይ ብቻ ነው ይላሉ አንጋፋው አሽከርካሪ አቶ ሀሰን፡፡
መጀመሪያ ባሮ ድልድይን ከመሀንዲሶች ጋር የቅየሳ ስራ የሰራነው እኛ ነን ፣ ከጋንቤላ አበቦ መንገድ ስንሰራ በህይወቴ የማልረሳው ትልቅ ገጠመኝ አለኝ እያሽከረከርን እያለ ከፊት ለፊታችን አንድ ዝሆን ከሩቅ አይተን ጡሩንባ ልንነፋ ስንዘጋጅ ከጫካ ውስጥ ብዙ ዝሆኖች ወጡብንና ደነገጥን ከዛም መኪናችን አቁመን አሳለፍናቸው….ይህ በህይወቴ የማልረሳው ልዩ ገጠመኝ ነው ፡፡
እኔ አሁንም ድረስ ይላሉ አቶ ሀሰን ለስራ ያለኝ ፍላጎት ከፍተኛ ሲሆን በተለይ ስራ ይኑረኝም አይኑረኝ ሌሊት አስራ አንድ ሰአት ከእንቅልፌ እነሳለሁ ይህ ደሞ ወግ ሆኖብኛል አሁንም ድረስ ጠዋት ተነስቶ ለስራ መንፈሴን አዘጋጀዋለው ሌሊት ስነሳ መኪና ንዳ ንዳ ይለኛል፡፡
በህይወቴ መኪና ሳሽከረክር ለበርካታ አሽከርካሪዎች ፍጥነት እንዲቀንሱና ረጋ ብለው እንዲያሽከረክሩ የመምከሩ ስራ እሰራለው እኔ አሁንም ድረስ መኪና በምንዳበት ጊዜ ፣ በሰማንያ እና በዘጠና ስፒድ ነው የምነዳው ምክንያቱም የምሄድበት ቦታ እደምደርስ አውቀዋለውና አብሮኝ ያለው ሰው ፍጥነት ጨምር እንኳን ቢለኝ ረጋ ብዬ ነው የምነዳው ብዬ እመልስላቸዋለው፡፡
የአሁን ትውልድ አሽከርካሪዎች በከፍተኛ ፍጥነት በመንዳት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነም ይታወቃል ለዚህም እንደምክኒያት የሚጠቅሱት አሽከርካሪዎች ሰው የሚላቸውን ያለመስማት ፣ ምን ይመጣብኛል ማለት ፣ጭነው ለሚሄዱት ሰው ተገቢውን ክብር ያለመስጠት ፣ የእግረኞች ማቋረጫ ላይ ለሰዎች ቅድሚያ አለመስጠት ፤ፊትለፊታቸው ያለውን ተሸከርካሪ ለመቅደም መሞከር እነዚህና ሌሎችም ምክኒያቶችን አንስተዋል፡፡
ለወጣቶች ቀስ ብላቸሁ ንዱ አሁን አሁን ዘመናዊ መኪኖች እየመጡ ነው እነዚህ ደግሞ ቁልቁለትም ዳገትም እንደፈለጉ ስለሚሮጡ አሽከርካሪዎች አይታወቃቸውም ስለዚህ ቀስ ብለው ነው ማሽከርከር ያለባቸው እኔ በህይወቴ ብዙ አሽከርካሪዎች አደጋ ደርሶባቸውና አደጋ ሲያደርሱም ገጥሞኛል፡፡
አሁን እየሰራሁበት ያለው መስሪያ ቤት ከ20 አመት በላይ አገልግያለው ከህዝቡ ጋር እስማማለው ጥሩ ፍቅር ነው ህዝቡ ለኔ እያሳየኝ ያለው በአጠቃላይ ይወደኛል በጣምም ደስ ይሉኛል በተለይ የወልቂጤ ማህበረሰብ ህዝብ ወዳድና ሰው አክባሪ ህዝብ ያለበት ሀገር ነው የትም አልሄድም ብዬ ወልቂጤ እየኖርኩ ነው፡፡
ማሰልጠኛ ተቋማት ሰልጣኞችን በደንብ ማስተማር አለባቸው እነሱ በደንብ ካላስተማሩ በመኪና አደጋ የሚሞተው ህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት ሊጨምር እንደሚችል ገልጸው የሚደርሰውን አደጋ እንዲቀንስ ማሰልጠኛ ተቋማቶች በትኩረት በማስተማር ብቁና የሰለጠነ አሽከርካሪ መፍጠር ይገባቸዋል፡፤
የሹፍርና ሙያ በጣም እወደዋለው እስክሞት ድረስ ሙያ አልተወውም በፍጥነት የሚያሽከረክሩትም በየጊዜው ከመምከር እና ከማስተማር ወደ ኋላ አልልም፡፡
እኔ ስነዳ ስንት በረሀ አይቻለው ስንት ሀገር ሄጃለው እስከ ዛሬ ድረስ በሰላም ረጋ ብዬ ስለምነዳ ምንም አይነት አደጋ አድርሼም ደርሶብኝም አላውቅም በአሁን ጊዜ አሽከርካሪዎች ላይ የምታየው እሩጫ ነው ሲሮጡ ደግሞ ትርፉ ሞት ብቻ ነው ስለዚህ ጥንቃቄ አድርገው ከነዱ ምንም አደጋ አይደርስባቸውም አያደርሱም ፡፡
ስለ አንጋፋው አሽከርካሪ አቶ ሀሰን ሰይድ ባህሪ ምን እንደሚመስል ያናገርኳቸው የሙያ አጋሮቻቸው እንደሚሉት የእድሜ ጉዳይ ሳይገድባቸው በጠዋት ከማንም ቀድመው ተነስተው በስራቸው ምንም አይነት እንከን ሳይፈጥሩ በታማኝነት በቅንነት የተሰጣቸው ስራቸውን ይሰራሉ ብለውናል፡፡
እኔም የዚህ ጹሁፍ አዘጋጅ አሽከርካሪዎች ተጠንቅቀው ፣ ረጋ ብለው ፣አስተውለው እንዲያስሽከረክሩ እና በመኪና አደጋ የሚሞተው የሰው ልጆች ህይወት መታደግ ይገባል መልዕክቴ ነው፡፡

የቱሪስት ፍሰቱን በማሳደግ የገቢ አቅሙን ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ አስታወቀ፡፡ባለፉት 6 ወራት ከአንድ ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶ...
01/02/2018

የቱሪስት ፍሰቱን በማሳደግ የገቢ አቅሙን ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ አስታወቀ፡፡
ባለፉት 6 ወራት ከአንድ ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ፓርኩን መጎብኘታቸውን ተጠቁሟል፡፡
የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ በጉራጌ ዞን ውስጥ የሚገኝ ብቸኛ ፓርክ ሲሆን ከመዲናችን አዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ሀላፊ አቶ ስኡድ አህመድ እንዳስታወቁት የፐርኩ የገቢ አቅም ለማሳደግ እና የቱሪስት ፍሰቱን እንዲጨምር ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ሀብቶች በተገቢው እንዲጠበቁና እንዲለሙ በማድረግ ለቱሪስት ምቹና አስተማማኝ ስፍራ ለማድረግ ችግሮች የተጋረጡበት ሲሆን ይህንንም ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም አስረድተዋል፡፡
የፓርኩ ማህበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግና የተገልጋዩን እርካታ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ አጽኖት ተሰጥቶት እንደሚሰራም አስታውቀው ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ቁጥር ያላቸው የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ፓርኩን መጎብኘታቸውም ተናግረዋል፡፡
በፓርኩ ውስጥ እየተከናወኑ ባሉ መሰረተ ልማት ግንባታዎችና እና በምርምርና ጥናት ስራዎች ለበርካታ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው አስታውሰዋል፡፡
ባለፉት አመታቶች በፓርኩ ክልል ይፈጸሙ የነበሩ ህገወጥ የከብት በረት ቤት መስራት ለማስቀረት በዚህ ግማሽ አመት በተሰሩ ስራዎች ከሀድያ ዞን በኩል ከሚገቡ ከብቶች በስተቀር ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ፓርኩ የሚገቡ ህገ ወጥ ከብቶች ማስቀረት እንደተቻለም ተናግረው ከሀድያ ዞን በኩል የሚገቡ ህገወጥ ከብቶች ለፓርኩ ደህንነት አስጊ በመሆናቸው ከፓርኩ ክልል ለማስወጣት ከአንድ ወር በፊት ርብርብ ማድረግ መጀመራቸውም ጠቁመዋል፡፡
በፓርኩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ አንዳንድ ግለሰቦች እንደሚሉት ፓርኩ በተገቢው እንዲለማና ለትውልድ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማስቻል ፓርኩ ክልል ያሉ ህገወጥ እርሻ እንቅስቃሴ ማስቀረት እንደሚገባም አስረድተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡

በጉራጌ ዞን በመስኖ ልማት 45 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡በቸሀ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በሴቶች እና በወጣቶች ውጤታማ የመስኖ...
01/02/2018

በጉራጌ ዞን በመስኖ ልማት 45 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
በቸሀ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በሴቶች እና በወጣቶች ውጤታማ የመስኖ ልማት ስራዎች በባለ ድርሻ አካላቶች ሰሞኑን ተጎብኝተዋል፡፡
አርሶአደሩ በየአካባቢው ያለውን የውሀ አማራጮች በመጠቀም የተለያዩ አትክልቶችን በማምረት ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን እየለወጡ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
በጉብኝቱ የተገኙት የጉራጌ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ሀላፊ እንዳሉት በተያዘው በጀት አመት ሁሉም አርሶአደሮች በመስኖ ልማት ስራ እንዲሳተፉ ለማድረግ ለባለሞያዎችና ለአርሶአደሩ የክህሎት ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡
በዚህም በመጀመሪያው ዙር በመስኖ ልማት 57 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ግብ ተይዞ ወደ ተግባር በመግባት እስካሁኑም ባለው ሂደትም 45 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ተናግረው የአርሶአደሩ የግብአት አጠቃቀም በየጊዜው መሻሻል እየታየበት እንደሆነና በሄክታር ኤንፒኤስ ከአንድ ኩንታል በላይ እንዲሁም ዩሪያ 68 ኪሎ ግራም መጠቀማቸውም አስታውሰዋል፡፡
ቀደም ሲል በዞኑ መስኖ የሚያለሙ ውስን ወረዳዎች ብቻ እንደነበሩ አስታውሰው በአሁኑ ወቅት ሁሉም አካባቢዎች ከነዚህ ወረዳዎች ልምድ በመውሰድ በተጠናከረ ሁኔታ እየሰሩበት ይገኛል ብለው በዘርፉም ለውጥ ካመጡበት ወረዳዎች ውስጥ የቸሀ ወረዳ ተጠቃሽ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
በመስኖ ልማት ስራ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ ነው ያሉት ሀላፊው በዚህም የሴቶችና የወጣቶች ተጠቃሚነት በስፋት እየተረጋገጠ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የቸሃ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሰይድ እንዳስታወቁት በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች መስኖ የማልማት ስራ በስፋት እየተሰራበት እንደሆነም ተናግረው በዚህም በርካታ አርሶደሮች፣ ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ ተጠቃሚነታቸው እያረጋገጡ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ወንዝ የሌለባቸው አካባቢዎች ሰፋፊ ኩሬዎችን የመቆፈር ስራ በብዛት ማከናወን የተቻለ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት አመታት በተከናወኑ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ለመስኖ ስራ የሚሆኑ ሰፋፊ ኩሬዎችን በአርሶአደሩ ጉልበት መቆፈር እንደተቻለም፡፡
በዘንድሮ አመት በመስኖ ልማት ስራ የተያዘውን እቅድ ስኬተማ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሆነም ተናግረው ለዚሁም ተግባር የሚውል ወደ 2 መቶ የሚጠጉ ሞተር ፓንፖች አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረገ እንደሆነና የአርሶአደሩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውስንነት በተገቢው መቅረፍ የሚያስችል ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠር ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሩፋኤል ንዥናጋ በበኩላቸው በዘንድሮ አመት በወረዳው ያሉትን የውሀ አማራጮችን በመጠቀም 4 ሺህ 4መቶ 16 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ግብ ተጥሎ እየተሰራ ሲሆን በዚህም 4ሺህ 16 ሄክታር መሬት መሸፈኑም አስታውሰዋል፡፡
የአርሶአደሩ የግብአት አጠቃቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደሆነ ጠቅሰው በአምና ደረጃ በአንድ ሄክታር መሬት ከ60 እስከ 70 ኪሎ ግራም ማዳበሪያ ይጠቀሙ እንደነበር ያስታወሱት ሀለፊው በዘንድሮ አመት 100 ኪሎ ግራም በሄክታር መጠቀም መቻላቸውም አብራርተዋል፡፡
ወጣቶችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የገበያ ትስስሩ ላይ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ ጠቅሰው ችግሩንም ለመፍታት ፣በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማዎች እንዲሁም ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጋር የገበያ ትስስር እየተፈጠረ ሲሆን በዚህም አበረታች የሚባል ለውጥ ማምጣት መቻሉም አስረድተዋል፡፡
በመስኖ ተግባር ላይ በማህበር ተደራጅተው የሚሰሩ አንዳንድ ወጣቶችና ሴቶች በሰጡት አስታያየት የውሀ አማራጮችን በመጠቀም ጎመን ፣ካሮት፣ ቲማቲምና ሌሎችም አትክልቶችን በማልማት ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱም ከዞንና ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች ፣ ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ አርሶአደሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላቶች ተሳታፊ ነበሩ ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው፡፡

የዘመናዊ ትምህርት ፋና ወጊ አባ ፍራንሷ ማርቆስአባፍራንሷ ማርቆስ በቀድሞ አጠራር በምዕራብ ሸዋ አስተዳደር አካባቢ በቸሀ አውራጃ ልዩ ስሙ ናዳነ በተባለው ቦታ በ1902 ዓ.ም ከአባታቸው ከአ...
26/01/2018

የዘመናዊ ትምህርት ፋና ወጊ አባ ፍራንሷ ማርቆስ
አባፍራንሷ ማርቆስ በቀድሞ አጠራር በምዕራብ ሸዋ አስተዳደር አካባቢ በቸሀ አውራጃ ልዩ ስሙ ናዳነ በተባለው ቦታ በ1902 ዓ.ም ከአባታቸው ከአቶ ማርቆስ ኬርሳና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ ማሪያም ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በአሊያንስ ፍራንሲዝ ዘመናዊ ትምህርትን ቀስመዋል፡፡ ከዚያም ወደ ሀረርጌ በመሄድ በፈረንሳዊ አቡነ እንድረያስ ዣሮስ የበላይ ጠባቂነት በጨርጨር አውራጃ ለገሀርባ በተባለው ስፍራና በኋላም በሐረር ከተማ የዘርዓ ክህነት ትምህርታቸውን በጥንቃቄ አገባደው በ1927 በእኚሁ አቡን እጅ የክህነት ማዕረግ ተቀብልዋል፡፡
ከዚህ በኋላም በድሬዳዋ ከተማ ለ2 ዓመታት በርካታ መንፈሳዊና ማህበራዊ ስራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው እምድብር ተመለሱ፡፡
አባ ፍራንሷ መሰረታዊ ተልዕኳቸው መንፈሳዊ ግልጋሎትን ማበርከት ቢሆንም ወደ ሰባት ቤት ጉራጌ ከተመለሱ በኋላ የጉራጌ ህብረተሰብን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሸጋገርና ኋላቀርነቱን ለማስወገድ የሚያስችሉትን የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋሞችን በማስተባበር ለማቋቋም ጥረት በማድረግ ተግባር ላይ ተሰማሩ፡፡
በዚህ መሰረት የእምድብር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የአካባቢው ህዝብ በማስተባበር በአሰባሰቡት ገንዘብ መስርተው የወደፊቱ መሰረታዊ ፍላጎታቸው መግለጫ የሆነውን ተግባር አሀዱ ብለው ጀመሩ፡፡
የእምድብር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መቋቋም ለአካባቢው ህብረተሰብ የትምህርት እድል ማግኘት በር ከፋች ቢሆኑም ረጅም ኪሎ ሜትር አቋርጠው እየመጡ የሚማሩትን ወገኖቻቸውን ድካም ለማስቀረት ተመሳሳይ የትምህርት ተቋማትን በየአካባቢው ማቋቋሙ ተገቢ መሆኑን ተገንዝበው ጥረታቸውን ቀጠሉ፡፡
የጋራ ልማትና እድገት የጋራ ጥረት ማድረግ ልምዱ የሆነው የጉራጌ ህብረተሰብም ለዚህ በጎ አላማቸው ከጎናቸው ተሰልፎ ገንዘቡን ጉልበቱንና እውቀቱን ከማስተባበር ባሻገር ከውጭ ሀገር እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችን የሙያ /ቴክኒክ/ የማቴሪያል የጥሬ ገንዘብ እርዳታ በመጠየቅና በሀገር ውስጥ መንግስትን በማስፈቀድ የግል ርስታቸውን ሳይቀር ስራ ላይ በማዋል ከ1930 ዎቹ ጀምሮ ለዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡
በክልሉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የእሳቸው አሻራ ካሳረፉበት በከፊል
- በቸሃ አውራጃ የቀድሞ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ 1ኛ ደረጃ አሁኑ እምድብር 1ኛ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡፡
- የቀድሞው ልኡል ዘርዓ ያዕቆብ የአሁኑ አባፍራንሷ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ
- የራዘ ስላሴ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
- የደብረትዩ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
- የናደነ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
- በጉመር አውራጃ …የዠምቦሮ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
- የጌቶ ቋንጤ 1ኛ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
- በቀድሞ እዣና ወለኔ አውራጃ የየቅመነ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ት/ቤት
- የምሁር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
- የገራን 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
- የወለኔ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
- በእነሞርና ኤነር አውራጃ የጉንችሬ 1ኛ ደረጃ
- የወሸዋሰር 1ኛ ደረጃ
- የጡማነ ዝግባ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
የአባ ፍራንሷ እድገት ሐዋሪያነት የሚመስክሩ ዘላለማዊ የህዝብ መገልገያ ተቋሞች ናቸው፡፡ ለዘመናዊ ትምህርት ለሐዋሪያት የሚመሰክሩ ለዘላለማዊ የህዝብ መገልገያ ተቋሞች ናቸው፡፡
ለዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ታታሪው አባ ፍራንሷ ማርቆስ ለህዝብ እድገት መሰረት የሆኑት የማህበራዊ ግልጋሎት ሰጪ ተቋማትን በሚያሰሩበት ወቅት ከህዝብ ከመንግስትና ከውጭ ሀገሮች እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ትብብር አልተነፈጋቸውም
በሰባት ቤት ጉራጌ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት የፈጸሙትን ተማሪዎች ሰብስበው አዲስ አበባ በማምጣት በየዘመዱ፣በየወዳጁ ቤትና በየቤተክሪስቲያኑ መጠጊያ ምግብና ልብስ እንዲያገኙ በማድረግ የከፍተኛ ትምህርት እንዲከታተሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ዛሬ ለሀገሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋጾኦ እያደረጉ ናቸው ከነዚህም መካከል ከፍተኛ መኮንኖች የህክምና ባለሙያዎች መሀንዲሶችና ምሁራን ወዘተ ይገኙባቸዋል፡፡
ክቡር አባ ፍራንሷ በወሊድ ምክንያት እናታቸውን ያጡ ህፃናት በመሰብሰብ አሳድገው አስተምረው ለቁም ነገር እንዲደርሱ በጎ ተግባር የሰሩ እኚህ አባት ለወንድ ልጆች እንዳደረጉት ሁሉ ለሴቶች ልጆችም የተለየ ትምህርት ቤት ከፍተው ዘመናዊ ትምህርት እንዲከታተሉ አድርገዋል፡፡
ለትዳር የታጩትን ልጃገረዶች የቀለም የሥነ-ምግባርና የሙያ ትምህርት እንዲያኙ በማድረግ ህብረተሰቡ ዘላቂ የሆነ ትዳር እንዲመሰርት አመቺ ሁኔታን የፈጠሩ አንጋፋ አባት ናቸው ፡፡
ለሀገርና ለወገን በመቆርቆር ሐዋርያዊ ተግባራት የሰሩ እንዲሁም በማህበራዊና ትምህርታዊ ገድል አሁን ላለው ትውልድ አርአያ የሚሆን ተግባር የሰሩ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁሟሉ፡፡
አባ ፍራንሷ ለጉራጌ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የልማትና ኢኮኖሚ እድገት ታላቅ አስተዋጾኦ ያበረከቱ ሰርተው የማይደክሙ ሰፊውን ህዝብ ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሩ ናቸው ፡፡
ስለ ክቡር አባ ፍራንሷ ማርቆስ ትጋት ፣ለሀገርና ለወገን መቆርቆርና ሐዋርያዊ ተግባር በሰፊው አወድሰው ከፃፉት ምሁራን ከፍራንክፈርት ዩንቨርሲቲ ኘሮፌሰር ሀቨርላንድ፣ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ኘሮፌሰር ውልፍ ሌስላው፣ከበርክሌይ ዩንቨርሲቲ ዶ/ር ሻክ፣ከኒው ጀርሲ ዩንቨርሲቲ ኘሮፌሰር ፌሊኘ ለ-ቤል ይገኙባቸዋል፡፡
ለጥናትና ለምርምር ወደ ነበሩበት ክፍል ለመጡ ምሁራን ክቡር አባ ፍራንሷ ማርቆስ መልካም አቀባበል በማድረግ ማረፊያና ምግብ ሰጥተው አስተናግደው ለጥናትና ምርምር ለሚዘዋወሩት ምሁራን ስለ ነበሩበት አካባቢ የህብረተሰብ ባህል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ከውጭ ሀገር የሚመጡ የምርምር ሰዎች በአባ ፍራንሷ ባይረዱ ኖሮ ስለኢትዮጵያ ያደረጉት ጥናትና ምርምር ከግብ የሚደርስ እንዳልነበረ ባዕዳን ሊቃውንት መስክረውላቸዋል፡፡
መሰረታዊ ተልዕኮአቸው መንፈሳዊ ይሁን እንጂ አብያተ ክርስቲያናት ከሰሩባቸው ቦታዎች አጠገብ የቀለምና የተግባረዕድ ትምህርት ቤቶች ማሰራት ዋናው ተግባራቸው ነበር፡፡
ህዝቡ ዘመናዊ ትምህርት ማግኘት ይገባዋል ብለው መንግስትም ከጎናቸው ቆሞአዋል በመቀጠልም የአባ ፍራንሷ ሌላው ተግባራቸው ስለ ቤተሰብ ጤናማ ህይወት የነበራቸው አስተሳሰብ ነበር ኋላቀር ከሆነው ልማዳቸው በመላቀቅ በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ወጣቶች እጮኞቻቸውን እንዲመርጡ፣በጨዋነት እንዲተዋወቁና ትምህርታቸውን ሲጨርሱ እንዲጋቡ አስተምረዋል፡፡ ለዚህም የታጩ ሴቶች ልጆችን በራሳቸው ወጪ እያስተማሩ ለታላቅ ቁም ነገር አድርሰዋል ክቡር ጋብቻን ለማጠናከር ትልቅ መሰረት ጥለዋል፡፡
ሌላው የአባ ፍራንሷ ማህበራዊ ገድል በተፈጥሮ አደጋ በወሊድ ችግሮችና በሌላ ህመም ምክንያት ወላጆቻቸው ያጡ ህፃናት በእንክብካቤ ያድጉ ዘንድ ትልቅ አሻራ ጥለው አልፈዋል
የህብረተሰቡን ሁለተናዊ እድገት የሚወሰነውና ፍሬያማ ውጤትም የሚስገኘው የህዝቡ አመለካከት ተግባራዊ እንቅስቃሴና ጥረት በጋራ ፍላጎትና ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሲገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ ግለሰቦች ችሎታን፣ፍላጎትንና የራስ ሀብትን ለሀገር እድገትና ለከፍኛ ቁም ነገር በማዋል ያበረከቱትን ግንባታ አስተዋጾኦ ካለው በስራቸው ውጤት ምስክርነት በታሪክ ሊታወሱና አርአያነታቸውም ሲዘኪር ይኖራል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ላይ ትልልቅ ስራዎችን የሰሩ አባት ናቸው በቸሀ ወረዳ የፎረ ኽና በሚባለው ቦታ ላይ ሰው ሰራሽ ጥቅጥቅ ደን አስተክለዋል፡፡በሌሎችም የዞኑ አካባቢዎች የደንን ጥቅም ለህብረተሰቡ እያስተማሩ እንዲተክሉ ትልቅ ስራ የሰሩ፡፡
የአርሷደሩ ያስተራረስ ዘዴን ለማዘመን ጥረት ያድርጉ ነበር፡፡የፍራፍሬ ምርጥ ዘሮችን ለህብረተሰቡ ያሰራጩ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በደህና ወጥቶ በደህና እንዲመለስ ሰላሙን በመመኘት የታወቃሉ፡፡
ለ50 አመታት የቃልኪዳን አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የአጣጥ ሆስፒታል መስራች ነበሩ፡፡ ይህ ሆስፒታል ለጉራጌ ፣ ለስልጤ ፣ ለኦሮሚያ እና ሀድያ ከንባታን ማህበረሰቦችን የበለጠ እንዲያገለግል አድርገዋል፡፡
ወደ አካባቢው የሚመጡ ምሁራንን ለአካባቢው የሚጠቅሙ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ያሰሩ ነበር፡፡
ለበርካታ ደራስያን ማለትም ለ ገ/እየሱስ ሀይለማርያም፣ሳህለስላሴ ብርሀነ ማርያም ፣ለነ ጄኔራል ተስፋዮሀብተ ማርያም ፣ለፊታውራሪ ሀ/እየሱስ አበጀ እና ለሀገር ባለውለታ የሆኑ የህክምና ፣የፖለቲካ ፣ የስነጹሁፍ የበርካታ ዲሲፒሊኖች ባለቤት የሆኑ ሀገር ወዳድ ሰው ነበሩ፡፡
አባ ፍራንሷ ማርቆስ ለጉራጌ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለልማትና ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋጾ ያበረከቱ ሰርተው የማይደክሙ ታላቅ ሰው ናቸው ፡፡
እኚህ የህይወት ጊዜያቸው ለህዝብ እድገትና ለውጥ ትልቅ አሻራ ጥለው ያለፉ አባፍራንሷ ማርቆስ ጊዜያቸውን ጉልበታቸውና ገንዘባቸውን ለልማት ያዋሉ ታላቅ ሰው በተወለዱ በ79 ዓመታቸው በ1998 ዓ.ም አረፉ፡፡
ምንጭ
1902-1981 ዓ.ም
የእረፍታቸውን 80ኛ ቀን ለማስታወስ የተዘጋጀ ሰነድ

ጀፎረ /ባህላዊ አውራ መንገድ/በጉራጊኛ የጀፎረ ትርጉም ባህላዊ አውራ መንገድ ማለት ነው፡፡ ይህም አባቶች ምንም አይነት ዘመናዊ የምህንድስና ትምህርት ሳይከታተሉ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅ...
11/01/2018

ጀፎረ /ባህላዊ አውራ መንገድ/
በጉራጊኛ የጀፎረ ትርጉም ባህላዊ አውራ መንገድ ማለት ነው፡፡ ይህም አባቶች ምንም አይነት ዘመናዊ የምህንድስና ትምህርት ሳይከታተሉ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ይመቻቸው ዘንድ የቀየሱት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው የመንገድ አይነት ነው፡፡ ለጉራጌ መንደሮች ትልቅ ውበት መላበስ ምክንያቱ ባህላዊ ጀፎረና የቤት አሰራሩ ነው፡፡ አንድ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች የሚለይበት የራሱ መገለጫ የሆኑ የተለያዩ እሴቶች ይኖሩታል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ህብረተሰቡ ከሚከተለው የህይወት ፍልስፍናና የአኗኗር ዘይቤው መነሻ በማድረግ ነው፡፡ በዚህም የህብረተሰቡ ባህላዊ ስነ-ጥበባት፣ ቁሳዊና ሀይማኖታዊ ክዋኔዎቹ በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡
የጉራጌ ብሔረሰብም ልክ እንደሌሎቹ የአገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ውብና ማራኪ ባህልና ወግ ባለቤት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ብሔረሰቡ በዋነኛነት ከሚታወቅባቸው ሀብቶቹ መካከል የመንደር አመሰራረቱ አንዱ ነው፡፡ የጉራጌ የመንደር አመሰራረትም መሰረት የሚያደርገው ጀፎሮ /ጀፎረ/ ሲሆን ይህም አረንጓዴ ሳር ለብሶ ውብና ማራኪ ገፅታ ያለውና ግርማ ሞገስን ተላብሰው በተገነቡት ባህላዊ ጎጆ ቤቶች ታጅቦ በሁለት መንደሮች መካከል በትይዩ የሚገኝ ከ60 ሜትር በላይ ስፋት ያለው ነው፡፡
የጉራጌ የመንደር አመሰራረት ያኔ በጥንት ዘመን የምህንድስና ጥበብ ባልተስፋፋበት ጊዜ ዛሬ ከደረስንበት ዘመናዊ የምህንድስና ጥበብ የሚቀራረብ ስራ የጉራጌ አባቶች ሲተገብሩ መቆየታቸው ያሳያል፡፡ የጉራጌ አውራጎዳና /ጀፎረ/ አመሰራረት መቼ እንደተጀመረ በውል የተረጋገጠ መረጃ ባይገኝም ከ15ኛው መቶ ክፍለ―ዘመን በፊት እንደተጀመረ አንዳንድ የብሔረሰቡ ተወላጅ የሆኑ የእድሜ ባለፀጋ አባቶች ይናገራሉ፡፡
ጀፎረ ለብሔረሰቡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጠ በርካታ ክፍለ ዘመናት የተሻገረ ሲሆን ስለአጠቃቀሙም ቢሆን የብሔረሰቡ ተወላጅ አባቶች ተሰባስበው በመምከር በባህላዊ መልክ የሚዳኝበትን ህግ አርቅቀው ተግባራዊ በማድረጋቸው ጀፎረ ዛሬ ድረስ ተጠብቆ ሰፊ ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ጀፎረ ባለቤትነቱ የህዝብ አገልግሎቱ ለህዝብ የደህንነቱም ጠባቂ የአካባቢው ህዝብ ነው፡፡
በጉራጌ ታሪክ ጥንት መሬት የሚሸነሸነው በባህሉ በተመረጡ አባቶች /የዥር ዳኘ/ የመሬት ልኬት ዳኞች አማካይነት ስለነበር /ጀፎረ/ ባህላዊ የአውራ መንገድ ልኬት ቅድሚያ ይሰጠው ነበረ፡፡ ጀፎረ በሁለት ትይዩ መንደሮች መሀል የሚያልፍ ወንዝ ገደል ወይም ጥብቅ ደን እስከሌለ ድረስ ሳይቋረጥ የሚቀጥል የመንገድ አይነት ነው፡፡ የጎን ስፋቱ ከ100 እስከ 150 ሜትር ሲሆን መስቀለኛ መንገዶች በሚያልፉበት አካባቢ እስከ 200 ሜትር ተለክቶ ለወል ግልጋሎት ክፍት ይሆናል፡፡ በጉራጌ ባህል ለባህላዊ አውራ መንገድ የተቀየሰ መንገድ አጥሮ ወደ ግል ግቢ መከለል በምንም መንገድ የተወገዘ ተግባር በመሆኑ በብሄረሰቡ ተወላጆች ዘንድ ለህዝብ አገልግሎት የሚውል አውራ መንገድ ማስፋት ባህል ነው፡፡
ጉራጌ /ለጀፎረ/ ለአውራ መንገድ ትልቅ ትኩረት የሚሰጥበት ዋና ምክንያት በብሄረሰቡ የሰርግ የደስታ የሀዘን እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የጋራ መፍትሄ የሚሰጥበት መንገድም መድረክም ስለሆነ ነው፡፡ ለጋራ ወይም ለወል መሬት እንዲሁ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል፡፡
የጉራጌ ጀፎረ በማንም ሳይደፈር ዘመናትን ለማስቆጠሩ ሌላኛውና ትልቁ ምክንያት ጉርዳ የተሰኘው ባህላዊ ቃልኪዳን ነው፡፡ በዚህ ቃል ኪዳን ተከብሮ ዘመን የተሻገረው ጀፎረ ለብሔሰቡ እየሰጣቸው ካሉ አገልግሎቶች መካከል፤- በሰርግ ስነ-ስርዓት የሙሽራውና የሙሽሪት አጀቦችና ወገኖች በዘፈን በግጥም የሚሞጋገሱት፣ ሙሽሮች አጋጌጣቸውና ውበታቸው ጎልቶ የሚወጣበት እንዲሁም በሽማግሌዎች፡ በእናቶችና በአባቶች የሚመረቁበት የተከበረ ተወዳጅ ስፍራ ነው፡፡ ሰው ሲሞት እግረኛና ፈረሰኛ ሙሾ የሚደረድረውና የለቅሶ ስነ-ስርዓት የሚያከናወነውም በዚሁ በጀፎረ ነው፡፡
ሽማግሌዎች ስለ ማህበራዊ ህይወታቸውና አጠቃላይ ኑሯቸው በጋራ የሚመክሩበት፣ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት የሚከናወንበት፣ መንገደኛ ያለአንዳች ችግር የሚጓዝበት ፤ህፃናቶች የሚቦርቁበት ጎረምሶችና ኮረዶች በብሄረሰቡ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው አመታዊ የመስቀልና የአረፋ በአላት ተከትለው የሚመጡ የጉራጊኛ ጭፈራዎች የሚከናወኑበት ፣ወጣቶች ፈረስ ጉግስ የሚለማመዱበት፣ በቅሎና ፈረስ የሚገሩበት፣ ከብቶች የሚጠበቁበትና የመሳሰሉት ተግባራት ከብዙ በጥቂቱ ጆፎረ ለነዋሪው የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ናቸው፡፡
ከዘመናት በፊት ጀምሮ ጉራጌ በጀፎረ ደስታውንና ሀዘኑን ሲገልፆበት እዚህ ደርሷል፡፡ ቂም በቀሉን ይቅርታ ይጠያየቅበታል ፡፡ ስለሰላሙ ይመክርበታል፡፡ ስለህይወቱ ይዘክርበታል፡፡ የተበዳዮችን እንባ ያብስበታል፡፡ ፍትህ ለተነፈጉ ፍትህ ይሰጥበታል፡፡ እምነቱን ይገልፅበታል፡፡ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ይከውንበታል፡፡
ስለዚህም ጀፎረ /አውራ ጎዳና/ ለጉራጌ ህዝብ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንፃር በተገቢው ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ ልናወርሰው ይገባል፡፡ ቅርሳችን እንደመሆኑ መጠን ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት የቱሪስት መስህብ ሊደረግ ይገባል መልዕክታችን ነው፡፡
መነሻ ፅሁፍ ከጉራጌ ባህል እሴቶች መፅሀፍና ከእ/ኤነር ወ/መ/ኮ ማህበራዊ ገፅ

በመንግስትና በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የተጀመረው የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የጉራጌ ዞን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በተገነቡ የቀበሌ ተደራሽ መን...
04/01/2018

በመንግስትና በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የተጀመረው የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የጉራጌ ዞን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
በተገነቡ የቀበሌ ተደራሽ መንገዶች ተጠቅመዉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸው እየጎለበተ መምጣቱን በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገልፀዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ልማት አስተባባሪ አቶ ጀማል አመሌ እንደገለጹት በ2004/2005 29 የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ፕሮጀክቶች ተነድፈዉ 202 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት ታቅዶ እስከ 2009 በጀት አመት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸዉን ተናግረዋል፡፡
በ2006 አመተ ምህረትም 50 የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ፕሮጀክቶች ተነድፈዉ 269 ኪሎ ሜትር ለመገንባት ታቅዶ የዲዛይን ስራቸው በማጠናቀቅ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን የተናገሩት አቶ ጀማል አመሌ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ በተሰራባቸዉ አካባቢዎች አርሶ አደሩ የግብርና ግብዓት ለመጠቀምና የግብርና ምርቱን ወደ ገበያ አውጥቶ በመሸጥ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆን መቻሉ እንዲሁም በትራንስፖርት ችግር እናቶች በእርግዝናና በወልድ ወቅት ይደርስባቸው የነበር ስቃይና የሞት አደጋ እንደቀነሰ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በ2010 በጀት አመት 95 ቀበሌዎችን ከዋናዉ መንገድ የሚያገናን 110 ኪሎ ሜትር መንገድ ለማስገንባት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ኃላፊዉ የዞኑ መንግስትና ህብረተሰብ በመንገድ ልማት ያለዉ የቆየው ልምድ ተጠቅሞ ዉጤታማ ስራ እየሰራ በመሆኑ ቀጣይም አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የእንደጋኝ ወረዳ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው በለጠ በበኩላቸው በባለፈው በጀት አመት ብቻ 40 ነጥብ 75 ኪ.ሜ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ተገንብቶ ለህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎት ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
በወረዳው አጠቃላይ ከተሰሩ መንገዶች 27 ኪሎ ሜትሩ በህብረተሰቡ ተሳትፎ 13 ነጥብ 75ቱ በዩራፕ ፕሮጀክት መገንባቱን የጠቆሙት ኃላፊው የወረዳው ህብረተሰብ በተለይም አርሶ አደሩ የግብርና ቴክኖሎጅዎችን ለመጠቀምና የግብርና ምርት ወደ ገበያ በማውጣት በደላላ ይበዘበዝ የነበረው ገንዘብ በማስቀረት ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረጉንና ለማህበራዊ መስተጋብር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
በእንደጋኝ ወረዳ ወሊቾ ቀበሌ በመንገድ ግንባታ ስራ የበኩላቸዉን እገዛ ሲያደርጉ ካገኘናቸዉ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር ተንሳኤ ሙሉሸዋ እና ጌቱ ክፍሌ ይገኙበታል፡፡ ሁለቱም በሰጡት አስተያየት በመንገዱ መሰራት እጅግ መደሳታቸው ገልፀው የመንገዱ ግንባታ እንዲፋጠን በጉልበታቸዉና በገንዘባቸዉ እየደገፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የመንገዱ መገንባት ተከትሎ ተሸከርካሪዎች እስከ ቀበሌያቸው ድረስ በመግባት የግብርና ምርታቸውን በተገቢው ሽጠው በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉን እንደሚያረጋግጥላቸዉ ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ አስናቀች አተጎ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ የመንገዱ መገንባት ለሴቶች የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው ቀደም ሲል በመንገድ ችግር እናቶች ወደ ጤና ጣቢያ ሄደው ክትትል ለማድረግ ይሁን ለመውለድ ይቸገሩበት የነበረውን እንደሚቀርፍላቸው ተናግረዋል፡፡

በገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታና በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለከታከትና ተግባር ችግር በመፍታት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ...
04/01/2018

በገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታና በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለከታከትና ተግባር ችግር በመፍታት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የጉራጌ ዞን የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አመታዊ ሴክቶሪያል ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ መሀመድ ኮርንማ በጉባኤው ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ሂደት ይታይ የነበር የጥራት መጓደል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመገምገምና እርምጃ በመውሰድ በዞኑ ጥራት ያላቸው መንገዶች እንዲገነቡ መደረጉና በ2006 ለመስራት የተያዙ ፕሮጀክቶች ዲዛይናቸው ተጠናቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነዉ፡፡
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢ አመለካከትና ተግባርን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከትራፊክ አደጋ ነፃ የሆነ አገልግሎት ተገልጋዩ ህብረተሰብ በመስጠት የዞኑን የልማት እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ትራስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍስሃ ዳምጠው በበኩላቸው በሴክተሩ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘሌቄታ ለመፍታት የመልካም አስተዳደርና የልማት እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱንና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመንገድ ግንባታ፣ በትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ችግር ለመፍታት የሴክተሩ አመራርና ባለሙያ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ እንደሚሰሩና ህግና ደንብ በማያከብሩ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳዳራዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀመር አሳስበዋል፡፡
የሴክተሩ ባለድርሻ አካላት በተላይም የትራስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በመንገድ ግንባታ የሚስተዋሉ ተቋራጮችና አማካሪዎች እንዲሁም የሴክተሩ አመራሮች ባለሙያዎች የተጣለባቸው ኋላፊነት ከኪራይ ሰብሳቢነት በፀዳ መልኩ እንደወጡ አቶ ፍስሃ አሳስበዋል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች በስጦታ አስተያየት የሴክተሩ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ተቋሙ ቅንጅታዊ አሰራርና የድጋፍ ክትትል አግባብ መጠናከር እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
አክለው የትራፊክ ፍሰት ጤናና የጠገልጋዩን ህብረተሰብ ፍላጎት በሚያረካ መልኩ አሽከርካሪዎች ህጋዊ አሰራር ተከትለዉ መስራት እንዳለባቸዉት እና በመንገድ ልማት ፕሮግራም ህብረተሰቡ እያደረገው ያለዉ ንቁ ተሳትፎ ውጤት እያመጣ በመሆኑ መንግስትም ለዘርፉ የሰጠዉ ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የተቋሙ የቀጣይ የመልካም አስተዳደር እቅድ እና የልማት ግቦችን ውጤታማ ለማድረግ የታችኛው መዋቅሮዎች ከዞኑ የመንገደና ትራንስፖርት መምሪያ ጋር በጉባኤው ላይ ተፈራርመዋል፡፡

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በጀጀባና ጋሶሬ ቀበሌ ውስጥ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባዉ የላይኛዉ ፈንጣ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዲስ መልክ ተገንብቶ ተመርቀ፡፡ ባለሀብቱና ህበ...
25/12/2017

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በጀጀባና ጋሶሬ ቀበሌ ውስጥ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባዉ የላይኛዉ ፈንጣ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዲስ መልክ ተገንብቶ ተመርቀ፡፡
ባለሀብቱና ህበረተሰቡ ከመንግስት ጎን ተሰልፎ በትምህርት ልማት እድገት ላይ የሚያደርገዉ ንቁ ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ፡፡
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሀሰን አለዊ በምረቃዉ ላይ ተገኝተዉ እንደገለጹት በእለቱ የተመረቀዉ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል መሆኑንና ህብረተሰቡ ግንባታዉን በአግባቡ ይዞ ልጆቹን በማስተማር ዉጤታማ እንዲሆኑ መስራት አለባቸው፡፡
አክለዉም ተማሪዎቹ በንደፈ ሀሳብ የተማሩትን በትግባር በመቀየርና በፈጠራ ስራዎች በመታገዝ ትምህርታቸዉን በትኩረት እንዲማሩ ያሳሰቡት አቶ ሀሰን አለዊ የወረዳዉ ባለሀብትና ህበረተሰብ ከመንግስት ጎን ተሰልፎ በትምህርት ልማት እድገት ላይ የሚያደርገዉ ንቁ ተሳትፎ አርዓያነት ያለው በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ብለዋል፡፡ የዞኑ ትምህርት መምሪያም የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ በመጠቆም፡፡
የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሸመ ንዳ በበኩላቸው ለትምህርት ልማት እድገት የወረዳው ህብረተሰብ በተለይም በጀርመን ሀገር የብሩህ ተስፋ ገብረ-ሰናይ ድርጅት መስራችና ሰብሳቢ አቶ ብዙአየሁ ይገረም በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ትዉልደ ኢትዮጵያንና ተጠቃሚው ህረተሰብ በማስተባበር ሀብት በማሰባሰብ በአበሽጌ ወረዳ ውስጥ እሰሩት ያለዉ በጎ ተግባር ለሌሎች ግለሰብና ድርጅቶች አርዓያነት ያለዉ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ተማሪዎች በስነ ምግባር ታንፀዉ ውጤታማ ሆነው የነገ ሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ለማስቻል መንግስት በሚያደርገው ጥረት የባለሀብቱና የህብረተሰብ ድጋፍ ትልቅ አቅም እንሚፈጠር የተናገሩት አቶ ተሾመ ንዳ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ መሳካት በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት በተለይም ከጀርመን ሀገር ድረስ መጥተው የአንበሳዉን ድርሻ ለተወጡ የብሩህ ተስፋ ገብረ-ሰናይ ድርጅት መስራችና ሰብሳቢ ለሆኑት ለአቶ ብዙአየሁ ይገረም መስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የብሩህ ተስፋ ገብረ-ሰናይ ድርጅት መስራችና ሰብሳቢ አቶ ብዙአየሁ ይገረም የፈንጣ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ግንባታ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በፍጀቱንና በ12 ወራት ውስጥ 12 ክፍሎችን የያዘ 3 ብሎኮች ግንባታቸው ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱን ተናግረዋል፡፡
ከአጠቃላይ ግንባታዉ 80 በመቶው የብሩህ ተስፋ ገብረ-ሰናይ ድርጅት፤ 15 በመቶው ደግሞ በጀጀባና ጃሶሬ ቀበሌ ነዋሪዎች መሸፈኑን የተናገሩት አቶ ብዙአየሁ ይገረም የወረዳዉ ህብረተሰብና መንግስት ለፕሮጀክቱ መሳካት ላደረጉት ቀና ትብብር አመስግነዉ በቀይ በአበሽጌና በእዣ ወረዳዎች የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የትምህርት ቤቱ መገንባት በእጅጉ እንዳስደሰታቸዉና ለተማሪ ልጆቻቸው ወደ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ሲሄዱ የሚያጠፉት ገንዘብና ጉልበት እንደሚታደግላቸውና ተማሪዎች የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡
በጨረሻም በምረቃው ስነ-ስርዓት ለአንዳንድ ቁሳቁስ ሟሟያ በጥሬው ከ25 ሺህ ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ከ100 ሺህ ብር በላይ ደግሞ ቃል ተገብቷል፡፡

የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር መሻሻል የፖለቲካና የትምህርት አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጉራጌ ዞን አስተዳዳደር አስታወቀ፡፡በዞኑ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባ...
25/12/2017

የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር መሻሻል የፖለቲካና የትምህርት አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጉራጌ ዞን አስተዳዳደር አስታወቀ፡፡
በዞኑ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባርን ለማሻሻል መላው ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ልዩ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ኮርንማ የንቅናቄው መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ተማሪዎች ውጤት ዝቅ ማለት እጅግ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ የትምህርት ልማት ስራ ዉጤታማ ለማድረግ የፖለቲካና የትምህርት አመራሮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ የማህበራዊ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ህብረተሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
መንግስት ከፍተኛ ሀብት በመመደብ የትምህርት ተደራሽነት መረጋገጡና ህፃናት በሙሉ ከትምህርት ገበታ እንዳይነጠሉ በማድረግ ውጤታማ ስራ መሰራቱን የገልፀት አቶ መሀመድ በአሁኑ ወቅት ለትምህርት ጥራት መሻሻል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አክለውም የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የትምህርት ልማት ሰራዊቱን በማጠናከር ለትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ግብአት በማሟላት ዞኑን በትኩረት እንደደሚሰራ ጠቁመው ምቹ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይ የዞኑ ህብረተሰብ ደረጃዉን የጠበቀ ት/ቤት ገንብቶ ለመንግስት በማስረከብ እያደረገ ያለዉ ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ በበኩላቸው የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ይዘው እንዲሰሩ ለማስቻል እና ባለው የሰው ሀይል፣ ግብአትና ክህሎት አሟጠው ተጠቅመው ከመስራት ጋር ያለው ክፍተት ሊቀርፉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር መሻሻል ተማሪዎች፣ መምህራን፣ርዕሰ መምህራን፣ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ያለቸው ሚና የጎላ በመሆኑ ተጠናክረውና ተቀናጅተው መስራት ይተበቅባቸዋል፡፡
በዞኑ የተጀመሩ የትምህርት ንቅናቄ እስከታች ቀበሌና ትምህርት ቤት ድረስ የሚዘልቅና በተጨባጭ ለውጥ እንደሚያወጣ ተናግረዋል፡፡
የንቅናቄው ተሳፊዎች በሰጡት አስተያየት በትምህርት ላማት በተለይም በተማሪዎች ውጤት መሻሳልና በስነ-ግምባር መታነጽ ላይ የሚሰሩት ስራ ክፍተት ያለበት መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ውጤታማና በስነ መግባር የታነፀ ትውልድ ለመፍጠር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የዞኑን የትምህርት ልማት ስራ ዉጤታማ ለማድረግ በቁርጠኝነትና በተነሳሽነት በተጣለባቸዉ ትልቅ ኃላፊነት መሰረት ትኩረት ሰጥተዉ እንደሚሰሩ ባወጡት ባለ12 ነጠብ የቋም መግለጫ ተስማምተዋል፡፡

Address

Irish Building
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage zone administration posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage zone administration:

Share