በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን

  • Casa
  • Italia
  • Tora
  • በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን

በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ !

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ  ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በወራቤ ከተማ የተገነባውን የአቅመ ደካማ እናት ቤት መርቀው ቁልፍ አስረከቡ ሆሳዕና፣ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ምበማዕከላ...
10/09/2026

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በወራቤ ከተማ የተገነባውን የአቅመ ደካማ እናት ቤት መርቀው ቁልፍ አስረከቡ

ሆሳዕና፣ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት ተገንብቶ የተጠናቀቀው የአቅመ ደካማ እናት መኖሪያ ቤት የቁልፍ ማስረከብ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል ።
በመርሃ ግብሩ የፍራፍሬና የውበት ችግኝ ተከላ ተከናውኗል ።

በጦራ ከተማ አስተዳደር በ2018 በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ አዳዲስ ቤቶችን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የማስመረቅ መርሃግብር ተከናወነ !____...
07/09/2026

በጦራ ከተማ አስተዳደር በ2018 በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ አዳዲስ ቤቶችን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የማስመረቅ መርሃግብር ተከናወነ !
_________________________________

ጳጉሜ 2 / 2018 :- በስልጤ ዞን በጦራ ከተማ አስተዳደር በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአረጋውያንና ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶችን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የማስመረቅ ተግባር ተከናውኗል ።

በከተማ አስተዳደሩ በክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለተለያዩ አረጋዊያን፣ አቅመ ደካሞችና የመከላከያ ቤተሰቦች ቤት በመገንባት የተጠናቀቁ የምስኪን ቤተሰብ ቤቶች በዛሬው ዕለት ለምርቃት በቅተዋል ።

07/09/2026
07/09/2026
የስልጤ ዞን የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የነሃሴ ወር አፈፃፀም በበየነ መረብ ገመገማ ነሀሴ 23/2018 [የብኢስኮ]                           ...
29/08/2026

የስልጤ ዞን የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የነሃሴ ወር አፈፃፀም በበየነ መረብ ገመገማ

ነሀሴ 23/2018 [የብኢስኮ]

​የስልጤ ዞን የብልፅግና የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በዛሬዉ ዕለት ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር በዝርዝር ገመገማ::
​በመድረኩ የኮሚሽኑ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ሽኩር ጀማል፣ ምክትል ሃላፊ አቶ ሀያቱ ሙክታር ፣ እንዲሁም የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት ዋናና ምክትል ሃላፊዎች ተገኝተዉ በቼክ-ሊስት የተደገፈ እንዲሁም በዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

• ​የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም:-በ2019 በጀት ዓመት «አንድ እቅድ፣ አንድ ሪፖርት፣ አንድ ምዘና» መርህን መሰረት በማድረግ የታቀደው እቅድ ላይ ለአመራሮች፣ አባላትና ባለድርሻ አካላት ኦሪንቴሽን በመስጠት ጠንካራ የፈጻሚ ዝግጅት መደረጉ እና አንድ ደረጃ ዝቅ ካሉ አደረጃጀቶች ጋር የግብ ስምምነት መፈራረም መቻሉ ተገምግሟል።

• ​የተቋም አቅም ግንባታ፡-የ2018 ስኬቶችን በማስፋትና ክፍተቶችን በማረም የ2019 እቅድ አፈጻጸም የበለጠ ማላቅ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን፣ ቅ/ጽ/ቤቶችን በግብዓትና በጠንካራ የአመራር ስምሪት ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።

• ​የአሰራር ሥርዓትና ክትትል የኮሚሽኑን አሰራሮች በዲሲፕሊን በመፈጸም ተቋማዊ አቅምን መገንባት፣ እንዲሁም ተልዕኮን በጥራት ለመወጣት ተከታታይነት ያለው የድጋፍ፣ የክትትልና የግብረ-መልስ ስርዓት በመዘርጋት መስራት እንደሚያስፈልግ ተሰምሮበታል።

• ​የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ትኩረት በብቁ ዝግጅት ላይ የተመሰረተ የ2019 አንደኛ ሩብ ዓመት ኢንስፔክሽን በአራቱ የትኩረት መስኮች ላይ በማካሄድ፣ ግኝቶችን ከምክረ-ሃሳብ ጋር በማቅረብ ለፓርቲው እሴት ለመጨመር በቁርጠኝነት መተግበር እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል::
​ኮሚሽኑ የዉስጥ አሰራሩን በማጠናከር ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ የበኩሉን ሚና ለመወጣት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በመግባባት መድረኩ ተጠናቋል::

"ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ"

29/08/2026
28/08/2026

Indirizzo

Tora

Telefono

+251916573025

Sito Web

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Contatta L'organizzazione

Invia un messaggio a በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን:

Scelte rapide

Condividi