24/06/2022
ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ
አዲስ አበባ
ሰኔ 17 /2014 ዓ.ም
“ህገ ወጥ ሰነዶችን ለመከላከል ከሚመለከታው ተቋማት ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ”
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ የሰነድ ማጭበርብርን እና ህገወጦችን ለመከላከል በጋራ እየሰሩ መሆኑን የገለፀው ኤጀንሲው ተቋማቱ አጠቃላይ የሚሰጡት አገልግሎቶች በጋራ መስራት አስፈላጊ ነው ተብሏል ፡፡
በዚህም መሰረት ዉጭ ላይ ለሚሰሩ የሰነድ ማጭበርብር ( የፎርጀሪ) ስራ በስፋት በኤጀንሲዎቹ ላይ ችግር እየፈጠረ ያለ በመሆኑ ይህንን ተግባር ለመከላከል በጋራ የአሰራር ስርዓቶችን በመንደፍ አጠቃላይ እየታዩ ያሉትን የፎርጀሪ ስራ የሚያስቀር አሰራርን ዘርግቶ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
በዛሬዉ እለትም ከሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ ኮሚቴዎች በተገኙበት ውይይት አድርገው በቀጣይ አሁን ባለዉ የቴክሎጂ ግብዓት ተጠቅሞና የሲስተም ስርዓት ዘርግቶ አብሮ ለመስራት ተግባብተዋል ፡፡