Tocha Communications

Tocha Communications This is an official page of Tocha Woreda Government Communication Affairs Office posting any social, economic, cultural and political events of this woreda.

በወረዳዉ እንደ ሀገር "ተስፋ እንትከል"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር በሁሉም ቀበሌዎች በየ ማህበራዊ መሰረት እየቀጠለ ይገኛል።‎‎ቶጫ ኮሙኒኬሽን !!!‎
03/08/2026

በወረዳዉ እንደ ሀገር "ተስፋ እንትከል"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር በሁሉም ቀበሌዎች በየ ማህበራዊ መሰረት እየቀጠለ ይገኛል።

‎ቶጫ ኮሙኒኬሽን !!!

03/08/2026
‎"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የወደፊት ተስፋችን ነዉ አቶ ታምራት ታደሰ የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ !!!‎‎«ተስፋ እንትከል» በሚል መሪ ቃል በቶጫ ወረዳ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ያሳተፈ...
03/08/2026

‎"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የወደፊት ተስፋችን ነዉ አቶ ታምራት ታደሰ የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ !!!

‎«ተስፋ እንትከል» በሚል መሪ ቃል በቶጫ ወረዳ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ያሳተፈ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ግብራ ቀበሌ ተካሄደ ።

‎«ተስፋ እንትከል» በሚል መሪ ቃል ሀገራዊ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቶጫ ወረዳ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ባሳተፈ መልኩ በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።

‎በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የወረዳው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በነቃ ተሳትፎ ተሳታፊ ሆነዋል።

‎የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ታደሰ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት፦ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የወደፊት ተስፋችንን የምንገነባበት፣ የአካባቢያችንን ስነ-ምህዳር የምንጠብቅበት እና ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴና የተመቻቸች ሀገር ለማስረከብ የምናደርገው ታሪካዊ ባለአደራነት ነው፤ እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል ያሳየው ተሳትፎም የዚህ ተስፋ ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

‎የቶጫ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት ቡንጉዶ በበኩላቸው፡የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎቻችን በላይ የህዝባችንን አንድነት እና የጋራ ልማት የሚያጠናክር ትልቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ነው፤ ይህን ተስፋችንን የመትከል ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን" ሲሉ ገልጸዋል።

‎የቶጫ ወረዳ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ እና ህብረት ስራ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰይፌሚካኤል ኡሸቾ እንደጠቆሙት፦የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁና ለተፈለገው ዓላማ እንዲበቁ ከዛሬው ተከላ ባልተናነሰ ሁላችንም አስፈላጊውን እንክብካቤ እና ጥበቃ ልናደርግላቸው እንደሚገባ በማንሳት በጽ/ቤታቸዉ በኩል አስፈላግዉን የሙያ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደረጉ አብራርተዋል ።

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶችም የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ የማስቀመጥ ስራ አካባቢያቸውን ለመጠበቅና የተስፋን ዘር ለመትከል ትልቅ አቅም እንደሆናቸው በመግለጽ፣ የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል ።

‎ዘገባዉ የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።

የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በዳውሮ ዞን ተጀመረ‎‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ አሩሲ አንገላ ቀበሌ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የአ...
03/08/2026

የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በዳውሮ ዞን ተጀመረ

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ኢሰራ ወረዳ አሩሲ አንገላ ቀበሌ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ዞናዊ ተከላ መርሐ-ግብር በይፋ ተጀምሯል።

‎የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በቦታው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ከተጀመረበት ወቅት አንስቶ በፓርቲም ሆነ በመንግሥት ዘንድ ቅቡልነት እያገኘ የመጣ መሆኑን ገልፀዋል።

‎አክለውም በዞኑ አጠቃላይ በአንድ ጀንበር 8.62 ሚሊየን ችግኞች ከ5 መቶ ሺ በላይ ዜጎችን ባሳተፈ መልኩ እንደሚከናወን ጠቅሰው፤ የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አኳያ ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ ህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

‎የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ለምነት ቁልፍ ሚና ይጫወታል ያሉት የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ ረ/ፕርፌሰር በተላ በየነ፤ የአንድ ጀንበር ተከላው የመሬት መሸርሸርን በመከላከልና ለምነትን ከማስጠበቅ ረገድ ወሳኝ ነው ብለዋል።

‎ባለፉት 7 አመታት የነበረውን ተሞክሮ ለማስቀጠል እንደ ዞን በበልግ፣ በመኸር እና በአንድ ጀንበር 82 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ያሳወቁት ኃላፊው ለአርሶአደሩ የገቢ ምንጭ እየሆነ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

‎የኢሰራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ተክሌ ዛፍ ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚ እንደሚተከል ታሳቢ በማድረግ የሰው ልጆችን ፍላጎት ሊያሟሉና የገቢ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ የፍራፍሬ፣ የአትክልት፣ የቅመማቅመም እዲሁም የመኖ ችግኞች እንደሚተከሉ ነው የተናገሩት።

‎ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገበበት ያለው አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በመጀመሩ የስራ ዕድሎች እየተፈጠሩና ጤናማ አካባቢ እንዲኖር አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የጠቆሙት የዞኑ ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና የተፈጥሮ፣ ደንና አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ ለይኩን ናቸው።

‎የዞኑ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ እርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተካልኝ በቀለ በበኩላቸው በዋናነት ለኢንዱስትሪ፣ ለኢኮኖሚና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች በተለይም በአቮካዶና በቡና ምርት ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

‎ኃላፊዎቹ ህብረተሰቡ መትከል ላይ ብቻ ሳይሆን ችግኞቹ እንዲፀድቁ መንከባከብ ላይም ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የዘገበው SWMN ነው።

አረንጓዴ አሻራ ከአየር ንብረት ጥበቃ ባለፈ ለምግብ ዋስትናም ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነ...
03/08/2026

አረንጓዴ አሻራ ከአየር ንብረት ጥበቃ ባለፈ ለምግብ ዋስትናም ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ጌሊት ቀበሌ የ2018 ዓ.ም የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላን በይፋ አስጀምረዋል

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት፣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር ደረጃ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም፣ የአፈር ጥበቃና ለምነት ማሻሻል እንዲሁም ለምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

በክልሉ ባለፉት ዓመታት በልዩ ትኩረት ሲከናወን መቆየቱን ነው ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የተናገሩት።

አረንጓዴ አሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም፣ ለአፈር መሸርሸር መከላከል፣ አፈር ለምነት መጠበቅ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት
በዘንድሮው “በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ 800 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።

ከዚህ ውስጥ 25 ሚሊዮን ችግኞች የክልሉ ድርሻ መሆናቸውን ጠቁመው የተተከሉ ችግኞች ለቀጣይ ትውልድ ዘላቂ ጥቅም እንዲያመጡ በአግባቡ መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መስፍን መንገሻ በበኩላቸው እንደሀገር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር ከተጀመረ ጀምሮ በዞኑ በተከናወነው ሥራ ለአየር ንብረት ለውጥ ከመቋቋም ባለፈ ለምግብ ዋስትና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

በ2018 ዓ.ም በደቡብ ቤንች ወረዳ በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ 1.5 ሚሊዮን የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል።

በችግኝ ተከለው የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአከባቢው ማሕበረሰብ ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ እየተከለች ነዉ!!
03/08/2026

ኢትዮጵያ እየተከለች ነዉ!!

ተስፋን የመትከል የህልውና ዘመቻ፡ 800 ሚሊዮን ዐሻራዎች በአንድ ጀምበር(የዕለቱ መልዕክት)ዛሬ ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ እና ደማቅ የታሪክ ገጽ እየጻፈች ነው። ሀገራችን በአንድ ጀምበር 800...
03/08/2026

ተስፋን የመትከል የህልውና ዘመቻ፡ 800 ሚሊዮን ዐሻራዎች በአንድ ጀምበር

(የዕለቱ መልዕክት)

ዛሬ ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ እና ደማቅ የታሪክ ገጽ እየጻፈች ነው። ሀገራችን በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የሕይወት እስትንፋሶችን ወደ ምድር ማህፀን በማስገባት ከነገው ትውልድ ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን እየገባች ትገኛለች።

ዛሬ እጃችንን አፈር ስናስነካ፣ ለሀገር ህያው ተስፋ እየሰጠን ነው። የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ ግንድና ቅጠል ብቻ ሳይሆን ልጆቻችን ተማምነው የሚኖሩባት ሀገር መሠረት ነው። ይህ ተግባር በቃላት ከሚገለጸው በላይ ጥልቅ ትርጉም ያለው ሀገራዊ ኃላፊነት ነው።

የዛሬው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የቅንጦት ወይም የውበት ጉዳይ ሳይሆን፣ የህልውናችን መሠረት እና የመጻኢ ዘመናችን ዋስትና ነው።

የተራቆተችና የደረቀች ምድር የነገ ልጆቿን አቅፋ ልታሳድግ፣ ልትመግብና ሕይወት ልትሰጥ አትችልም። የአካባቢ መራቆትና የደን መመናመን የሚያመጣውን አሳሳቢ ፈተና ለመቀልበስ፣ ተፈጥሮ በለመለመ እቅፏ ያወረሰችንን ድንቅ ምድር ጠብቆ ማቆየት የግድ ይላል።

ሀገራችን በገዛ እጃችን የተፈጥሮ ውበቷና ጸጋዋ እንዳይደበዝዝ ከፊታችን የተደቀነውን ታላቅ አደራ የምንወጣበት፣ ምድራችንንም ዳግም የምናክምበት ዕለት ዛሬ ነው።

ይህ የተቀናጀ ርብርብ የዘመናችን «ዓድዋ» ነው። ትናንት አባቶቻችን በዓድዋ ተራሮች ላይ ልዩነቶቻቸውን አክስመው፣ በአንድነትና በጽናት ለነጻነት እንደቆሙት ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ የትናንቱን የነፃነት አርበኝነታችንን በተፈጥሮ ጥበቃ የምንደግምበት የጀግንነት ቀን ነው።

ጀግንነት ጦር ሜዳ ላይ ጠላትን በማንበርከክ ብቻ ሳይሆን፣ ድህነትንና የተፈጥሮ መራቆትን በማሸነፍም ይገለጻል። በመሆኑም የዛሬው ትውልድ ዕውቀቱን፣ ጉልበቱንና ፍቅሩን አስተባብሮ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እያለበሳት ይገኛል።

በዛሬው ዕለት አብረን በጋራ የምናፈሰው ላብ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ የሚያለመልም፣ በሀገራዊ ልማት ራዕይ ሕዝባችንን ከዳር እስከ ዳር የሚያስተሳስር የወል ታሪክ ነው።

የአረንጓዴ ዐሻራ ተግባራችን ሀገራችን የምግብ ዋስትናዋ በዘላቂነት የተረጋገጠ፣ በግብርናው ዘርፍ ምርታማነቷ የጨመረ እንዲሁም የአየር ንብረት መዛባት የማይበግራት ጽኑ ሀገር እንድትሆን ያደርጋታል።

እያንዳንዷ በየቤታችን ደጃፍ፣ በየተራራው፣ በየሸለቆውና በወል መሬት ላይ የምንተክላት ችግኝ ነገ ተያይዛ ታላቅ ደን፣ የሀገራዊ ኢኮኖሚ ታላቅ ኃይል ትሆናለች። ይህ የዛሬው ተግባራችን ከሀገራዊ ፋይዳው አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚረዳን ለዓለም ማኅበረሰብ የምናበረክተው የማያረጅ ሕያው ውርስ ነው። ኢትዮጵያም ለዓለም አረንጓዴ ልማት ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የምታሳይበት ታላቅ ሁነት ነው።

ነገ በታሪክና በትውልድ ፊት እንዳናፍር፣ የለመለመችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ዛሬውኑ እንነሳ። የዛሬው አረንጓዴ ዐሻራችን፣ የነገው ትውልድ ብሩህ ተስፋችን ነው እና አቅሙ የሚፈቅድለት አንድም ሰው በቤቱ መቅረት የለበትም። ዛሬ አንዲት ችግኝ በመትከል የሕይወት፣ የሰላምና የብልጽግና ተስፋን እንትከል! የተስፋችን ምድር ዳግም ትለምልም፤ ለሁላችንም መልካም የልማትና የተስፋ ተከላ ወቅት ይሁንልን!

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረበአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ የሚጻፍበት ሀገራዊ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን...
03/08/2026

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ የሚጻፍበት ሀገራዊ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ አብሥረዋል።

ሚኒስትሯ መርሐ ግብሩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ መላው ኢትዮጵያውያን የተጎሳቀለችውን ምድር ለማዳን እና እንደተለመደው ታሪክ ለመሥራት በአንድነት መነሣታቸውን ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለመሬት አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች" በማለትም የሕዝቡን አኩሪ ባህል እና የምድሪቱን ፀጋ አወድሰዋል።

በመደመር መርሕ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በአንድነት ወጥቶ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ ዐሻራውን እንዲያሳርፍና "ኑ ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ ደማቅ ተሳትፎ እንዲያደርግ ሚኒስትሯ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

800 ሚሊዮን ችግኞች፣ በተግባር እና በሐሳብ አንድነት በመደመር ዕሳቤ እናሳካለንም ብለዋል።

ይህ ታሪካዊ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በመላው ሀገራችን በሚገኙ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ይሆናል።

በወረዳዉ በአንድ ጀምበር ከ1 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ-ቡዙ ጥቅም ያላቸዉ ችግኞች መዘጋጀቱ ተገለጸ።‎‎በዳዉሮ ዞን ቶጫ ወረዳ "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ...
31/07/2026

በወረዳዉ በአንድ ጀምበር ከ1 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ-ቡዙ ጥቅም ያላቸዉ ችግኞች መዘጋጀቱ ተገለጸ።

‎በዳዉሮ ዞን ቶጫ ወረዳ "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የወረዳ ግ/አከ/ጥ/ህ/ስ/ል/ጽ/ቤት አስታወቀ ።

‎የቶጫ ወረዳ ግብርና አከ/ጥ/ህ/ስ/ል/ጽ/ቤት ም/ኃ አቶ አንዷለም አባቴ እንዳስተወቁ "ተስፋን እንትከል "በሚል መሪ ቃል ለሚከናወነው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ- ግብር እንደ ወረዳችን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

‎አያይዘውም በወረዳው ወስጥ በሚገኙ የችግኝ ጣቢያዎች ላይ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ፍራፍሬ ፣የደንና አግሮፎረስተር እንዲሁም ቡና፣ ለመኖነት የሚውሉ ችግኞች በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

‎የቶጫ ወረዳ ግ/አከ/ጥ/ህ/ሰ/ል/ጽ/ቤት የተፈጥር ጥበቃ ቡድን አስተባባሪ አቶ አታሮ አይዛ በበኩላቸዉ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር 1115288 ደንና ዘረፌ ብዙ ጥቅም የምሰጡ ችግኞች በ251 ሄ/ር ለመሸፈን ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል ።

‎በአረንጓዴ አሻራ የሚተከሉ ችግኞች የደን ሽፋንን ከማስጠበቅ ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አቶ አታሮ ገልጸዋል።

‎በመጨረሻም ጽ/ቤቱ ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ሁሉም ማህበረሰብ ክፍል በዕለቱ በነቂስ በመዉጣት ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል።

‎"ተስፋን እንትከል "

‎ዘገባው፦ የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

‎በቶጫ ወረዳ በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል ዕርስ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ተግባር ቀጥሏል።‎‎ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም በዳዉሮ ዞን ቶጫ ወረዳ የክረምት ወራት ወጣቶች በ...
31/07/2026

‎በቶጫ ወረዳ በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል ዕርስ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ተግባር ቀጥሏል።

‎ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም በዳዉሮ ዞን ቶጫ ወረዳ የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ተግባር በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

‎በዛሬው ዕለት በቶጫ ከተማ ወጣቶች ወጥተው የተበላሹ መንገዶችን የመጠገን ስራ በመስራት በቀጣይ አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና ሌሎች በጎ ስራ ላይ እንደሚሳተፉ ቃል ገብተዋል።

‎ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"🇪🇹

‎ቶጫ ኮሙኒኬሽን !

Address

Tocha
Toamasina

Telephone

+251911418197

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tocha Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Tocha Communications:

Shortcuts

Share