05/09/2026
የወጣቱን አሰቃቂ ግድያ በጽኑ እናወግዛለን!
ግድያና ዝርፊያ ሥርዓታዊ እንጂ ተናጠላዊ ጥቃት እንዳልኾነ ሕዝቡ ሊረዳ ይገባል!
ወጣት ተገኝ ባልቻ(ኦሮሮ) እጅግ ሰው አክባሪና በአካባቢው ማኅበረሰብ ተወዳጅ፣ በሥራው ትጉሕ ነበር ይላሉ የቅርብ የሚያውቁት። ያ ተስፈኛና ሽመናው ላይ አቀርቅሮ ሩቅ ዓላሚ፣ ለተቸገሩ ደራሽ "ኮሪደር ልማት" የሚል የዳቦ ስም የተሰጠው የማገለያና ነጥሎ አውዳሚ ትግበራ የዚኽ የብዙኃን ተስፋ ሕልም ተጨናገፈ። መሥሪያው ፈረሰ፣ ምትክም ስጡኝ ሲል በቀል አዝሎ የሚዞረው ሥርዓት ፊቱን ኦዞረበት፣ ሕልሙን ተነጠቀ። ከዚያ በኋላ ለሰዎች የሚደርስ ሳይኾን ለእሱ ከንፈር የሚመጠጥለት ኾነ ይላሉ የቅርብ ወዳጆቹ። በመጨረሻም ትናንት ሕልሙን ያጨናገፈው ሥርዓት ሕይወቱን ቀጠፈው። ለየት የሚያደርገው መሸፋፈንና ጨለማ መጠበቅ ሳያስፈልግ በአደባባይ በጠራራ ፀሐይ መፈጸሙ ብቻ ነው።
ትብብራችን ይኼ ታሪክ የአንድ ወጣት ተገኝ ብቻ ሊመስል ይችላል እንጂ ጥቃቱም ግፉም በመላው አዲስ አበባ ወጣት ላይ የተሰነዘረ ነው ብሎ ያምናል። ልዩነቱ የዓይነትና የቀናት ብቻ ነው። ብልጽግናም አንድ ቀን በስልጣን እስካለ ድረስ ይኽ መራራ እውነት ገሃድ ኾኖ፣ ሥጋ ለብሶ ይቀጥላል።
ትብብራችን የግፍ ግድያውን በጹኑ እያወገዘ የወጣቱን ነብስ ይማር፤ ለቤተሰቡና ለመላው የአዲስ አበባ ነዋሪ መጽናናትን ይመኛል።
ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ግንቦት ፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
***
👍 ገጾቻችንን ይወዳጁ👍
https://www.facebook.com/share/1JwwMKYDV1/
👍👍
https://t.me/tibibir_2018
👍👍
https://vt.tiktok.com/ZSuj3572y