የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region

  • Home
  • Ethiopia
  • Kebele 13
  • የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region ራዕያችን በአገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የሆነ ፍርድ ቤት መገንባት ነው ! / Our vision is excelling to become a model judiciary in Ethiopia !

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ፀደይ ባንክ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙአዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 /2018 ዓ.ም (የአማራ  ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት) በዛሬው...
12/05/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና ፀደይ ባንክ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 /2018 ዓ.ም (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት)

በዛሬው ዕለት በፀደይ ባንክ ዋናው መ/ቤት በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና በፀደይ ባንክ መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፣ ይህም በአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ ፍ/ቤቶች ዳኞችና የአስተዳደር ሠራተኞችን በሥራ ላይ ማቆየት የሚቻልባቸው ጉዳዮችን የሚመለከት ነው።

ስምምነቱን የፈረሙት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘዳንት አለምአንተ አግደው፣ ፀደይ ባንክ የፍ/ቤት መጠናከር ለአገር ያለውን ፋይዳ በመረዳት በጋር ለመስራት የወሰደውን እርምጃ ያደነቁ ሲሆን፣ የፀደይ ባንክ ፕሬዘዳንት ዮሃንስ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ባንኩ ዘመናዊና በቴክኖሎጅ የተደገፉ አዳዲስ የአሰራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት ላይ ያለ እና ለሕዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሁሉአቀፍ የለውጥ ሥራ ውስጥ ከሚገኘው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ጋር በጋራ ለመሥራት በመስማማታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከተለያዩ የህግ ተቋማት ለተወጣጡ ባለሙያዎች በካፒታል ገበያ አሰራርና ህጎች  ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀባህርዳር፣ ግንቦት 01/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)የአማራ ክ...
09/05/2026

ከተለያዩ የህግ ተቋማት ለተወጣጡ ባለሙያዎች በካፒታል ገበያ አሰራርና ህጎች ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

ባህርዳር፣ ግንቦት 01/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ከተለመደ አሰራር በማላቀቅ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ተገማች እና አመኔታን ያተረፈ ለማድረግ በሁሉ አቀፍ የለውጥና ማሻሻያ ሂደት ላይ ይገኛል።

ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠር እና የዘመናዊ ዳኝነት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶችን በሁሉም የክልሉ ፍርድ ቤቶች በመገንባት ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፣ የተቋም ግንባታውን ሙሉ ለማድረግ የሚዘረጉ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል የሚችል አመራር፣ ዳኛ እና ሰራተኛ ለመፍጠር የአጭር እና የረጅም ጊዜ የስልጠና አማራጮችን በመጠቀም አቅማቸውን በመገንባት ላይ ነው።

የዚህ አቅም ግንባታ ፈጠራ አካል የሆነ የትብብር ስምምነት ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ጋር የተፈራረመው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የክልሉ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህጎችና ሌሎች የሕግ አካላት ለሀገራችን አዲስ በሆነው የካፒታል ገበያ አሰራሮች እና የህግ ማእቀፎች ላይ ከሀሙስ ሚያዚያ 29/ 2018 ዓ.ም እስከ ቅዳሜ ግንቦት 01/2018 ዓ. ም ለሶስት ቀናት የቆየ ስልጠና ሰጧል።

የዳኝነት እና የፍትህ አካላት በካፒታል ገበያ ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮችን ለመፍታት ተመሳሳይ የህግ አተረጓጎም እንዲኖር ለማስቻል በህግ ማዕቀፉ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታሳቢ በማድረግ የተሰጠው ስልጠናው ፣ እንደ ሀገር እየተዋወቀ የሚገኘው የካፒታል ገበያ ስርዓት በህብረተሰቡ፣ በባለአክሲዎኖች፣ በአልሚዎች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት አመኔታን በማትረፍ ለሀገር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ማስቻል ነው።

ስልጠናው፣ ጥልቀት ያለው ካፒታል ገበያ የሕግ ማእቀፍ፣ የጋርዮሽ ኢንቨስትመንት ፈንድ፣ የኢንቨስተሮች ጥበቃ፣ የተከለከሉ ተግባራት እና በገበያው ሊከተሉት ስለሚገባው ስነምግባር እንዲሁም በአክሲዮን ግብይት ሂደቶች እና በሌሎች ርእሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ዳኞች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ጠበቆችና ሌሎች የህግ ባለሙያዎች ተሰጧል።

ስልጠናውን የወሰዱ፣ ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከክልሉ የፍትሕና ህግ ኢኒስቲትዩት፣ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ እና ከርእሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የተወጣጡ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህጎች እና የህግ ባለሙያዎች፣ ካፒታል ገበያን በተመለከቱ መመሪያዎች ፣ አዋጆች እና አሰራሮች ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳገኙ ተናግረዋል።

የኢትዮጲያ የካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ስልጠናውን በቋሚነት መስጠት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች መደበኛ  ሙያዊ ውይይታቸውን አካሄዱ ባህርዳር ፣ ሚያዚያ 30/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወራቶች የተጀ...
08/05/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች መደበኛ ሙያዊ ውይይታቸውን አካሄዱ

ባህርዳር ፣ ሚያዚያ 30/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወራቶች የተጀመረው የክልሉ ዳኞች መደበኛ ሙያዊ የህግ ውይይት በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች በየ 15 ቀኑ መካሄዱን ቀጥሏል።

እስካሁን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች በሁሉም የክልሉ ፍርድ ቤቶች የተካሄዱ ውይይቶች፣ ዳኞች በጉዳዮቹ ላይ ተቀራራቢ አረዳድና ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል ሲሆን፣ ተገማች እና ጥራት ያለው ውሳኔ ሰጭነትን የሚያሳድግ ነው።

ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በንብረት ማስከበር እና እግድ አሰጣጥ ህጎች ላይ በተነሱ ነጥቦች ተወያይተው የነበሩት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች፣ ዛሬም በዚህ ርእሰ ጉዳይ መነሻነት በባለፈው ሳምንት ያልተዳሰሱ ቀሪ የውይይት ነጥቦች ላይ ተወያይተዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ የሆኑት ክቡር ዳኛ አቶ ግርማ እውነቱ፣ ባለፈው ካነሱት የንብረት ማስከበርና እግድ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ቀሪ የመወያያ ርእሰ አቅርበው ዳኞች በጉዳዩ ላይ የራሳቸውን ሀሳብ እና ሙያዊ አረዳድ በማቅረብ ለሌሎች ተሳታፊ ዳኞች ግንዛቤ የሚፈጥር ሀሳብ አስተያይታቸውን አጋርተውበታል።

በየደረጃው ባሉ የክልሉ ፍርድ ቤቶች በየ 15 ቀኑ በመደበኛነት የሚካሄደው የዳኞች ሙያዊ የውይይት መድረክ፣ በተለያዩ ይዘቶችና የአቀራርብ ማሻሻያዎች በቀጣይነት የሚካሄድ ይሆናል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙባህርዳር፣ ሚያዚያ 29/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላ...
07/05/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ባህርዳር፣ ሚያዚያ 29/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉን የዳኝነት እና የፍትሕ አገልግሎት በሚታይ መልኩ ለማሻሻል ተጨባጭ የለውጥ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በሁሉ አቀፍ ዘላቂ የተቋም ግንባታ ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የሁሉም መሰረቱ ብቃት ያለው አመራር፣ ዳኛ እና ሰራተኛ ነው በሚል መርህ፣ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶች አመራሮችን፣ ዳኞችን እና ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ስነስርዓት፣ የዚህ አቅም ግንባታ ፈጠራ ፕሮግራም አካል ሲሆን፤ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህጎች እና ሌሎች የህግ አካላት ከካፒታል ገበያ ጋር የተገናኙ ሀገር እና አለምአቀፍ ህጎች ላይ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ነው።

የስምምነት ሰነዱን፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው እና የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ አብነት ዘርፉ ተፈራርመዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ካሁን በፊት በሰሩባቸው ከፍተኛ ተቋማት ያካበቱት ልምድ፣ አርቆ አሳቢነት እና አዳዲስ ሀሳቦችን ለማስረጽ ያላቸው ቁርጠኝነት ለሀገራችን አዲስ በሆነው የካፒታል ገበያ ላይ የክልሉ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህጎችና ሌሎች የህግ ባለሙያዎች በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ያላቸው ብርቱ ፍላጎት ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጋር በትብብር እንድንሰራ አድርጎናል ያሉት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ አብነት ዘርፉ፣ ስምምነቱ የክልሉ የህግ አካላት ሀገር አቀፍ እና አለምአቀፍ የካፒታል ገበያ ህጎችን ጠንቅቀው እንዲያውቁ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የካፒታል ገበያ ሀብት ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ክልል፣ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ ያስችላል ያሉት አቶ አብነት፣ ስምምነቱ ይሄንን ሀብት በአግባቡ የሚመራ የሰው ሀይል ለማፍራት ያስችላል ብለዋል።

አብረናችሁ እንድንሰራ እድሉን ስለጣችሁን እናመሰግናለን ያሉት ሰብሳቢ ዳኛው፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጋር ያደረግነው ስምምነት እና በስምምነቱ መሰረት ለክልሉ ዳኞች፣ አቃቢያነ ህጎችና ሌሎች የህግ አካላት የምንሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሌሎች ክልሎችም አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤታችን ስምምነቱን ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ጋር ያደረገው የክልሉን ዳኞችና የህግ ባለሙያዎች በካፒታል ገበያ እና ሌሎች ህጎች ላይ አቅማቸውን ለመገንባት ነው ያሉት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው፣ በምጣኔ ሀብት እና በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ላለች ሀገር፣ ስምምነቱ በእነዚህ መስኮች ላይ የተጀመሩ የማሻሻያ ስራዎችን መሬት ለማውረድ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የህግ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ ሆነው በመስራት የባላክሲዎኖች እና ባለሀብቶችን መብት በማስጠበቅ የካፒታል ገበያው ለሀገር ምጣኔ ሀብት እድገት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ዘርፉን የተመለከቱ ሀገር እና አለምአቀፍ ህጎችን አውቆ መገኘት ያስፈልጋል ያሉት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፣ ሁለቱ ተቋማት የህግ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት ያካሄዱት የትብብር ስምምነት በተጀመሩ የለውጥና የማሻሻያ ስራዎች ላይ እንደ ክልል እና እንደ ሀገር የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።

ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ከፊርማ ስነስርዓቱ በኋላ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤቱ ለክልሉ የዳኝነት እና የፍትህ አካላት የሚሰጠውን ስልጠና በይፋ አስጀምረዋል።

የኢ.ፌ.ዴ. ሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፣ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሌ ሃሰን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳ...
04/05/2026

የኢ.ፌ.ዴ. ሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፣ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሌ ሃሰን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት: ከቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ዮሴፍ ረታ ፣ ከአገር ሽማግሌዎች ፣ ከሃይማኖት አባቶች ፣ ከአባ ገዳዎች ፣ ከአደ ስንቄዎች ፣ ከባለሃብቶች እና ከሌሎች የክልል እና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤትን ጎብኝተዋል።

ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በየጊዜው እና ያለማቋረጥ እያደረገ ያለውን የለውጥ ሥራ አድንቀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ሌሎች ጎብኝዎች ባዩት የለውጥ ሥራ በጣም መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጎበኙባህርዳር ፣ ሚያዚያ 23/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል...
01/05/2026

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጎበኙ

ባህርዳር ፣ ሚያዚያ 23/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ሎሜ በዶ፣ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሀረላ አብዱላሂ ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር ) እና ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት ለተገልጋዩ ለማቅረብ እያደረገ ያለውን የለውጥ ስራ፣ ምቹ የስራ ቦታ ፈጠራ እና በአጠቃላይ በክልሉ የዳኝነት እና የፍትሕ ሁሉ አቀፍ የለውጥ ስራዎች የተጀመሩ የመሰረተ ልማትና የአሰራር ማሻሻያ ለውጦችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩ የዳኝነት እና የፍትሕ አገልግሎት የለውጥና የማሻሻያ ስራዎችን በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በበላይነት የሚያስተባብሩ ሲሆን፣ ምክትል አፈ ጉባኤዋ እና ሌሎች ከፍተኛ ሀላፊዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለመመልከት በመጡበት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየተገበራቸው ያሉ አጠቃላይ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የለውጥና የማሻሻያ ስራዎችን ተመልክተዋል።

የባለጉዳዮችን ወጭ፣ እንግልት፣ ጊዜ እና ጉልበት በመቀነስ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ፣ ተገማች እና ተደራሽ የዳኝነት አገልግሎት ለመዘርጋት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያከናወናቸውን፣ የመሰረተ ልማት፣ ምቹ የስራ ከባቢ እና ሌሎች የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎችን በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ገለጻ እና ማብራሪያ የተደረገላቸው ሀላፊዎቹ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባጭር ጊዜ ውስጥ ባከናወናቸው የማሻሻያ ስራዎች መደነቃቸውን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የለውጥ እና የማሻሻያ ስራዎች ለሌሎች የዳኝነት እና የፍትሕ ተቋማት አርአያ የሚሆኑ ናቸው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ፣ የተጀመሩ ስራዎች የባለጉዳዮችን እንግልት የሚቀንሱ እንዲሁም የዳኞችን እና የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት የሚጨምሩ ናቸው ብለው፣ እስካሁን የተመዘገቡ መሰረታዊ የለውጥ ስራዎችን በላቀ ደረጃ አስቀጥሎ መሄድ እንደሚገባ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት አስተያይት ተናግረዋል።

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉብኝት ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

30/04/2026

“የጠበቆች ማህበር ለህብረተሰቡ የፍትሕ አገልግሎት ተጠቃሚነት ሊሰራ ይገባል” ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው-የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት| Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

29/04/2026

“የባሕል ፍርድ ቤቶችን በየአካባቢው በማጠናከር ዜጎች አማራጭ ፍትሕ እንዲያገኙ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል” ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው-የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት| Amhara Media Corporation/ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

የፍርድ ቤት ቀጠሮዎን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!ባህርዳር፣ሚያዚያ 21/2018(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት)የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሕን በታማኝነት ለማረጋገጥ የጀመረውን ጉዞ በቴክ...
29/04/2026

የፍርድ ቤት ቀጠሮዎን ባሉበት ሆነው ይከታተሉ!

ባህርዳር፣ሚያዚያ 21/2018(የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሕን በታማኝነት ለማረጋገጥ የጀመረውን ጉዞ በቴክኖሎጅ ይበልጥ ለአገልግሎት ፈላጊው ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤታችን ለባለጉዳዮቻችን ተደራሽ እየሆነባቸው ካሉ የቴክኖሎጅ አማራጮች አንዱ ደግሞ የሞባልይ መተግበሪያችን ነው።

አዲሱ የሞባይል መተግበሪያ የተገልጋዮችን እንግልት ለመቀነስ እና ግልጽነትን ለማስፈን ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

የሞባይል መተግበሪያው 👇

ቀጠሮ ፍለጋ፦ በመዝገብ ቁጥር፣ በአመልካች ወይም በተጠሪ ስም መፈለግ ያስችላል።

ቀጠሮዎችን ማየት፦ የዕለቱን የችሎት ውሎዎች በቀላሉ ለማየት ያስችላል።

ቀላል አጠቃቀም፦ ለማንኛውም ሰው ግልጽ በሆነ አማርኛ የተዘጋጀ ነው።

የመዝገብ ቁጥርዎን በማስገባት ብቻ የቀጠሮ መረጃ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ነው።

ወደ ፍርድ ቤት በአካል መሄድ ሳያስፈልግዎት መረጃዎችን ባሉበት የሚያገኙበት ነው።

የሞባይል መተግበሪያው አሁን ላይ የባህር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት መረጃዎችን የያዘ ሲሆን፣ በቀጣይ የሁሉም ከፍተኛና ወረዳ ፍርድ ቤቶች መረጃ የሚካተትበት ይሆናል።

አሁኑኑ መተግበሪያውን በመጫን ጊዜዎን እና ጉልበትዎን ይቆጥቡ!

መተግበሪያውን ለማውረድ 👇

1. በድረ-ገጽ (Web): https://amhsc.gov.et/ ላይ በመግባት ማንኛውንም መረጃ ይፈልጉ።
የዕለቱን መዝገቦች ለማየት https://amhsc.gov.et/?page_id=1929
ዌብሳይቱ ላይ በመዝገብ ቁጥር በአመልካች ስም እና በተጠሪ ስም ለመፈለግ https://amhsc.gov.et/?page_id=1815
2. በሞባይል መተግበሪያ (App): መተግበሪያውን ለማውረድ
እዚህ ይጫኑ፦ https://amhsc.gov.et/?page_id=1957

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት - ፍትህን በታማኝነት!

"የባህል ፍርድ ቤቶችን በሙሉ አቅም ስራ ለማስጀመር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ያስፈልጋል"  ክቡር አቶ አለም አንተ አግደው- የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትባህር ...
28/04/2026

"የባህል ፍርድ ቤቶችን በሙሉ አቅም ስራ ለማስጀመር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ያስፈልጋል" ክቡር አቶ አለም አንተ አግደው- የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት

ባህር ዳር፣ ሚያዚያ 20/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ የባህል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 298/2017 መሰረት እዉቅና የተሰጣቸው የባህል ፍርድ ቤቶች ስራ በማስጀመር ላይ ይገኛል።

በዛሬው እለትም ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ከፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያበረከታቸውን እና ለባህል ፍርድ ቤቶች ስራ ማስኬጃ የሚያግዙ ቁሳቁሶችን የተረከበው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ በባህርዳር ከተማ ሞዴል የባህል ፍርድ ቤቶችን በይፋ ከፍቶ ስራ አስጀምሯል።

በርክክብ ስነ- ስርዓቱ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ፣ ከፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለባህል ፍርድ ቤቶች ስራ ማስጀመሪያ የሚሆኑ ኮንፒውተሮች እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች አበርክቷል።

በርክክብ ስነ- ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለም አንተ አግደው ፣ የባህል ፍርድ ቤቶችን በሙሉ አቅም ስራ ለማስጀመር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር የሚያስፈልግ መሆኑን ገልጸው፣ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እና የፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሀን (ዶ/ር)፣ የባህል ፍርድ ቤቶች ስራ መጀመር ህብረተሰቡ ሳይንገላታ፣ ሩቅ ሳይሄድ፣ ወጭ ሳያወጣ፣ በሚያውቀው እና በሚቀበለው ባህል እንዲዳኝ ያስችለዋል ብለው፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የባህል ፍርድ ቤቶችን ሙሉ ለሙሉ ስራ ለማስጀመር እያደረገ ያለውን ስራ አድንቀው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በቀጣይም ድጋፎችን ለማድረግ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ከክልሉ ጠበቆች ማህበር አመራሮች ጋር ተወያዩባህር ዳር፣ ሚያዚያ 20/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)የአ...
28/04/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው ከክልሉ ጠበቆች ማህበር አመራሮች ጋር ተወያዩ

ባህር ዳር፣ ሚያዚያ 20/2018 (የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ተደራሽ፣ ፈጣን እና ወጪ ቆጣቢ የሆነ ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን በመተግበር ላይ ይገኛል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነጻነቱን ባከበረ መንገድ የፍትህ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ በፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ ሚና ካላቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል። በዛሬው እለትም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ አለምአንተ አግደው በህግ ከተቋቋመው የክልሉ የጠበቆች ማህበር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ፣ ጠበቆች የፍትሕ አካሉ አጋር እና በፍትሕ አገልግሎት ውጤታማነት ላይ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ናቸው ያሉት ክቡር ፕሬዘዳንቱ፣ ጠበቆች የፍትህ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና የወከሏቸውን ዜጎች መብት ማስከበር ዋና ስራቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ጠበቆች በፍትሕ ተቋማት የሪፎርም ስራዎች፣ በዳኝነት እና የፍትሕ አካላት የትብብር መድረክ፣ እንዲሁም በነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ትልቅ አስተዋጾ የሚኖራቸው መሆኑን አንስተዋል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በህግ አስገዳጅ ሆኖ እና እራሱን እንዲያስተዳድር ተደርጎ የተቋቋመው የጠበቆች ማህበር ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራቸው ከሚገባቸው ጉዳዮች ውስጥ የጠበቆችን የሙያ ብቃት እና ስነ ምግባር ማሳደግ ግንባር ቀደሙ መሆኑን ክቡር አቶ አለምአንተ አንስተዋል። ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሆነው የክልሉ የፍትሕ እና የህግ ምርምር ኢንስቲቲዩት እና በክልሉ ከሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የማህበሩ አመራሮችም ማህበሩ አዲስ እንደመሆኑ ብዙ ኃላፊነቶች የሚኖሩባቸው ቢሆንም የተሰጣቸውን ስልጣን እና ኃላፊነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የሆነ ተቋም እንዲሆን ለማስቻል መስራት የሚገባ ስለመሆኑ ክቡር አቶ አለም አንተ አግደው አሳስበዋል።

በዉይይቱ የተሳተፋት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ጎሽም በበኩላቸው፣ የጠበቆችን አዋጅ በ2017 ዓ/ም ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመሆን ማውጣት የተቻለ መሆኑን አውስተው፣ የጠበቆች ማህበር ከፍርድ ቤት እና ከፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር የፍትሕ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ሊሰራ የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል።

የጠበቆች ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ሰለሞን ጎራው በበኩላቸው፣ የጠበቆች ማህበር በህግ በአስገዳጅ ሁኔታ እንዲቋቋም መደረጉ መልካም መሆኑን ገልጸው፣ የሙያ ስታንዳርድ እና ስነ-ምግባር በዋነኝነት የሚሰሩበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠበቆች የፍርድ ቤቶችን የዘመናዊ ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የለውጥ ሂደቶች ተከትለው እንዲሄዱ ማድረግ የሚገባ መሆኑን አንስተው፣ አዋጅ እንዲወጣ በማድረግም ሆነ የአመራር ምርጫ ሲካሄድ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

በውይይቱ የክልሉ የፍትሕ እና ህግ ኢንስቲቲዩት ፕሬዘዳንት ዶክተር ደሴ ጥላሁን፣የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች እና የጠበቆች ማህበር አመራሮች ተሳትፈዋል።

Address

Bahir Dar
Kebele 13
P.BOX901

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት/ Supreme Court of Amhara Region posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share