Jimma University

  • Home
  • Jimma University
Call Website Contact the organization

Jimma University Official fb of JU, Ethiopia's leading institution known for its Community Based Education philosophy.
(6)

እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አደረሰን ፡፡በዚህ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን፣ ሁላችንም ልዩነቶቻችንን በማክበር፣ የጋራ እሴቶቻችንን በማጠናከርና በትብብር በመሥራት ለሀገራችን...
12/10/2026

እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አደረሰን ፡፡

በዚህ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን፣ ሁላችንም ልዩነቶቻችንን በማክበር፣ የጋራ እሴቶቻችንን በማጠናከርና በትብብር በመሥራት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ልማት ያለንን አስተዋፅኦ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድናጎለብት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በማህበረሰብ ውስጥ ነን
ጅማ ዩኒቨርሲቲ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ያስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክትውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎቻችን፣የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን ወስዳችሁ የከፍተኛ ትምህርት ...
12/10/2026

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ያስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት

ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎቻችን፣

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን ወስዳችሁ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ በማምጣት፣ ተቋማችንን ጅማ ዩኒቨርሲቲን ምርጫችሁ በማድረግ የተመደባችሁ፣ የነገ አገር ተረካቢ የሆናችሁ ውድና ጠንካራ የኢትዮጵያ ልጆች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት በተሰጠኝ ኃላፊነት፣ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም፣ በማህበረሰብ ተኮር የትምህርት ፍልስፍና ፋና ወጊ ወደሆነው፣ አንጋፋው ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማዕከል ወደሆነችው፣ የሰላምና የልማት ተምሳሌት ወደሆነችው ጅማ ከተማ በሰላም መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ውድ ተማሪዎቻችን፣

እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በዚህ ዓመትም እናንተን የምንቀበለው በከፍተኛ ደስታና በኃላፊነት ስሜት ነው። የተቋማችን ሕልውና በተማሪዎቻችን ላይ የተመሰረተ መሆኑን ስለምንገነዘብ፣ ከማንኛውም ጊዜ በላይ ለትምህርታችሁ፣ ለፍላጎቶቻችሁ፣ ለምታገኟቸው አገልግሎቶች እና በአጠቃላይ ለሁለንተናዊ ዕድገታችሁና ስኬቶቻችሁ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገን እየጠበቅናችሁ መሆናችንን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።

በተለይ በዚህ ዓመት ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን በሂደት ላይ በመሆናችን፣ በዚህ ሂደት ውስጥ የእናንተም ሚና ጉልህ እንዲሆን ሁኔታዎችን እናመቻችላችኋለን።

የነገ ስኬታችሁ በእጅጉ የሚወሰነው በዛሬው ጥረታችሁ እንደመሆኑ፣ በቀጣዮቹ ዓመታት በምታደርጉት ጥረት ሁሉ የተቋማችን መምህራን፣ ሠራተኞች፣ የሥራ ኃላፊዎችና ነባር ተማሪዎች ከጎናችሁ በመቆም ድጋፍ እንደምናደርግላችሁ እንገልጻለን።

የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ የተመደበላችሁን የትምህርት ሰዓት በአግባቡ እንድትጠቀሙ፣ ትምህርታችሁን በአግባቡ እንድትከታተሉ የሚያስፈልገውን ምሁራዊ ድጋፍ በማድረግ የእውቀት አባትነት ሚናቸውን ለመወጣት ዝግጁ ናቸው።

የአስተዳደር ሠራተኞቻችንም አቅማቸው በፈቀደው መጠን የምታገኙት አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን፣ ምቹና ሰላማዊ የትምህርት አካባቢ እንዲኖራችሁ፣ ከዚህም በተጨማሪ አካላዊና አእምሮአዊ ጤናችሁ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን እንገልጻለን።

የእናንተ ታላላቅ ወንድሞቻችሁ ነባር ተማሪዎችም ባለፉት ዓመታት ያካበቱትን ልምድና የሕይወት ተሞክሮ በማካፈል፣ በትምህርታችሁና በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ውጤታማ እንድትሆኑ እንደ ሁልጊዜውም ከጎናችሁ ለመቆም ዝግጁ ናቸው።

ውድ ተማሪዎቻችን፣

ከምንም በላይ እንግዳ ተቀባይ የሆነው፣ ሰላማዊው የጅማ ሕዝብ እናንተን እንደ ልጆቹ ተቀብሎ ለማስተናገድ፣ ቆይታችሁም ያማረና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ልክ እንደ ሁልጊዜው ዛሬም መምጫችሁን በጉጉት እየጠበቀ መሆኑን ስንገልጽላችሁ በደስታ ነው።

በመሆኑም በጅማ ቆይታችሁ በዩኒቨርሲቲያችን ብቸኛውና ልዩ በሆነው በማህበረሰብ ተኮር የትምህርት ፕሮግራም በመሳተፍ፣ በክፍል ውስጥ የምትማሩትን የንድፈ ሐሳብ ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር ተግባራዊ ልምድ የመቅሰም እድል ከማግኘታችሁም በላይ፣ በእንግዳ አክባሪነቱ የሚታወቀውን የጅማ አባ ጅፋር ሕዝብ በቅርበት የማወቅ እድል ይኖራችኋል።

ውድ ተማሪዎቻችን፣

ዛሬም እንደ ትናንት “ሁልጊዜም ውዶቻችን ናችሁ! ለዚህም የመምህራኖቻችን፣ የሠራተኞቻችንና የሥራ ኃላፊዎቻችን ሁሉ ዋነኛ ትኩረት እናንተ ተማሪዎችና የእናንተ ትምህርት ነው” እንላለን። የተቋማዊ ስኬታችን መለኪያም ግብም የእናንተ ስኬት ነው።

በመሆኑም በቆይታችሁ በትምህርታችሁ ላይ በማተኮርና በትጋት በመማር፣ ያልታወቀውን የነገውን ዓለም ለማሸነፍና የዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችላችሁን እውቀትና ክህሎት ከስብዕና ጋር እንድትላበሱ አደራ እላለሁ። ምሉዕ ስብዕና ያላቸውና ለሰው ልጅ ችግር ፈቺ እና አዳዲስ ፈጠራ የምትፈጥሩ ዓለም አቀፍ ዜጎች ሆናችሁ እንድትወጡ፣ መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና የጅማ ህዝብ ከጎናችሁ መሆኑን በድጋሚ እያረጋገጥኩላችሁ ፣ ቆይታችሁ ያማረና ውጤታማ እንዲሆን ጥልቅ ምኞቴን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።

መልካም የትምህርት ዘመን
ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር)
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

As we prepare to welcome our freshman students in the coming week, we are featuring some special places with our beloved...
11/10/2026

As we prepare to welcome our freshman students in the coming week, we are featuring some special places with our beloved alumni.

Kolo Ber (ቆሎ በር) — the gate many of you passed through, where memories begin and never end. On the road from Koche to Agip, students, teachers, and the city meet at one gate. Cafes, laughter, lecture halls, and a thousand stories all pass through here. Some call it a neighborhood. We call it home.

Please share your story, picture, and memories of Kolo Ber. What does this gate mean to you? Drop them in the comments and tag a friend who walked through it with you.

Congratulations, Professor Tsige Ketema! Jimma University is proud to congratulate Professor Tsige Ketema on being selec...
10/10/2026

Congratulations, Professor Tsige Ketema!

Jimma University is proud to congratulate Professor Tsige Ketema on being selected as a Winner of the prestigious BRICS+ Women in Science and Technology Award 2026 in the category of Medicine and Biotechnology.

Your outstanding commitment, tireless hard work, and deep scientific curiosity stand as a powerful testament to excellence in research. You continue to serve as a living model of inspiration for young and female researchers across Ethiopia and beyond.

This well-deserved recognition elevates both your remarkable contributions and the name of Jimma University on the global stage. We celebrate your achievement and the path you continue to pave for the next generation of scientists.

Congratulations, Professor!

Heartfelt Congratulations! On behalf of Jimma University, we extend our warmest congratulations to Drs. Tilahun Habte, W...
10/10/2026

Heartfelt Congratulations!

On behalf of Jimma University, we extend our warmest congratulations to Drs. Tilahun Habte, Wongel Tena, and Lidya Gemechu on their prestigious induction as Fellows of the American College of Surgeons (FACS) .

This remarkable professional achievement is a great honor for our institution. It stands as a testament to our continued commitment to staff development, excellence in clinical care, education, and academic leadership.

This milestone significantly strengthens our vision of building Jimma University Medical Center as a true center of excellence.

Congratulations once again, and we wish you continued success in your professional journey!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
10/10/2026

ጅማ ዩኒቨርሲቲ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

Hussein stands still, but his story moves through every corner of Jimma University—clean, green, and rooted in community...
10/10/2026

Hussein stands still, but his story moves through every corner of Jimma University—clean, green, and rooted in community-based education.

Dear alumni, friends, and students, share your picture with this iconic monument in the comments.

Like and follow our page.
Jimma University

Happy weekend!

‎በቴክኖሎጂ ፣ ኢኖቬሽንና  ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት ተካሄደ ።‎መስከረም 30/2019‎ጅማ ዩኒቨርሲቲ ‎****************‎የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከኢኖ...
10/10/2026

‎በቴክኖሎጂ ፣ ኢኖቬሽንና ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት ተካሄደ ።
‎መስከረም 30/2019
‎ጅማ ዩኒቨርሲቲ
‎****************
‎የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ ፣ ኢኖቬሽንና ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ለማሳካት ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ ጥናት ተካሄደ።
‎
‎በመርሃ ግብሩ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ታደሰ ሀብታሙ (ዶ/ር) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ሀላፊዎች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ ተማሪዎች ፣መምህራን እና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።
‎
‎የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ታደሰ ሀብታሙ (ዶ/ር) አለማችን ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በፍጥነት እየተለወጠች መሆኗን ጠቅሰው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ከመማር ማስተማር ባሻገር ዕውቀትን ወደ ቴክኖሎጂ ፤ ቴክኖሎጂን ወደ ፈጠራ ፤ ፈጠራን ወደ ማኅበረሰብ መቀየር እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
‎
‎የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታ ለማበልፀግ በዩኒቨርሲቲው በሰፊው እየተሰራ ነው ያሉት ታደሰ ሀብታሙ(ዶ/ር) መርሀግብሩ ሀገራችን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂን በማሳካት ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እና ዲጂታል ማኅበረሰብ ለመሸጋገር አስፈላጊ ነው ብለዋል።
‎
‎​ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የመጡት ዶ/ር አበበ ሞላ በብሔራዊ የሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ዙሪያ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን በአቶ ታደሰ አምበሴና በዶ/ር በኩረጽዮን ዓለማየሁ በተከታታይ በኢትዮጵያ የስታርት አፕ አዋጅና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዙሪያ ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል።
‎
‎ዲጂታል ሉዓላዊነቷን የጠበቀች፣ በፈጠራና ቴክኖሎጂ የተመሠረተች ኢትዮጵያን ለመፍጠር «ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ስትራቴጂ ሁለንተናዊ መንገድ መሆኑን በእለቱ ተመላክቷል።
‎
‎የ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ስትራቴጂ የሀገሪቱን የልማት አቅጣጫ በቴክኖሎጂ መሠረት ለመቀየር የታለመ ትልቅ ሀገራዊ እቅድ መሆኑን የገለጹት ባለሙያዎቹ፣ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በተለይ የዩኒቨርሲቲ ሙህራን እና ተመራማሪዎች በንቃት ማሳተፍ የስትራቴጂው ዋነኛ መርህ መሆኑን ጠቁመዋል።
‎
‎የስታርታፕ አዋጁ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የስታርታፕ ማዕከል ለማድረግ፣ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታትና የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ያለው መሆኑን አንስተዋል።
‎
‎በመጨረሻም ከተሰታፊዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
‎
‎በማህበረሰብ ውስጥ ነን!
‎Facebook: https://www.facebook.com/JimmaUniv/
‎Twitter: https://twitter.com/JimmaUniv
‎Telegram: https://t.me/JimmaUniversityOfficial
‎LinkedIn: https://www.linkedin.com/school/jimma-university/
‎YouTube: https://www.youtube.com/
‎TikTok : https://vm.tiktok.com/ZS9DxvJVnbHtq-khtKl/
‎Instagram : https://www.instagram.com/jimma_universityofficial?stkn=MWowMWszcHlhNWwybg==
‎E-mail: [email protected]
‎

Congratulations to Jimma University Researchers Recognized in the Stanford/Elsevier Top 2% Scientists List for 2026Dear ...
10/10/2026

Congratulations to Jimma University Researchers Recognized in the Stanford/Elsevier Top 2% Scientists List for 2026

Dear Esteemed Researchers,

On behalf of Jimma University, we extend our warmest congratulations to the researchers from Jimma University who have been listed in the much-anticipated Stanford/Elsevier Top 2% Scientists List for 2026. This prestigious list recognizes the world’s leading scientists who have made a substantial impact in their respective fields through citation influence.

Your inclusion in this ranking is a testament to your dedication, scholarly excellence, and the global influence of your research. Jimma University is proud of your achievement and deeply values your contributions to science, innovation, and the advancement of knowledge.

We celebrate you and wish you continued success in your research and academic journey. Your recognition brings honor to Jimma University and inspires our entire academic community.

Congratulations once again!

Sincerely,
Jimma University

08/10/2026

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jimma University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Jimma University:

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed government service?

Share