26/08/2026
ማስታወቂያ!
በ “Young Future Energy Leaders” ሥልጠና ፕሮግራም ዕድል መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ታዋቂ የሆነው የካሊፋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በታዳሽ ኃይል፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በዘላቂ ልማት ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርገውን የ2027 Young Future Energy Leaders የአንድ ዓመት ሥልጠና ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያንን በመመልመል ሂደት ድጋፍ እንድናደርግ ጥያቄ አቅርቦልናል፡፡
የፕሮግራሙ ዋና ዋና ጥቅሞች
• የአንድ ዓመት ሙሉ ሥልጠና፦ የምርምር ፕሮጀክቶች፣ የአመራርነት ሥልጠናዎች እና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ የልምድ ልውውጦች።
• ልዩ የሥራ ዕድል፦ ከጥር 12 እስከ 14 ቀን 2027 (እ.ኤ.አ) በአቡዳቢ በሚካሄደው World Future Energy Summit (WFES) ላይ በመገኘት ከዓለም አቀፍ መሪዎች ጋር የመገናኘት ዕድል።
• ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፦ የታዳሽ ኃይል፣ የውኃ ደህንነት፣ የቆሻሻ አወጋገድ፣ ዘላቂ ከተሞች እና የአካባቢ አየር ለውጥ እርምጃዎች።
የአመልካቾች መስፈርት
• ዕድሜ፦ ከ20 እስከ 25 ዓመት
• የትምህርት ውጤት (GPA)፦ 3.50 እና ከዚያ በላይ
• የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ ዲግሪ/ማስተርስ በመከታተል ላይ ያለ፣ በቅርቡ የተመረቀ ወይም በዘርፉ የመጀመሪያ ደረጃ የሥራ ልምድ ያለው
• ሌሎች፦ በታዳሽ ኃይል እና ዘላቂ ልማት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው እና እንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር/መፃፍ የሚችል።
የማመልከቻ ሂደት
ሙሉ መረጃችሁን ማለትም (ሙሉ ስም፣ የትምህርት ማስረጃ እና ሰርቴፊኬቶች ካሉ፣ ስልክ ቁጥር) ከዛሬ ጀምሮ እስከ ኦገስት 29 ቀን 2026 ድረስ በኤምባሲው ኦፊሴላዊ ኢሜይል አድራሻ [email protected] ይላኩ።
ማስታወሻ፦ ኤምባሲው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቁ የሆነ ዕጩዎችን ዝርዝር ለዩኒቨርሲቲው የሚያስተላልፍ ሲሆን የመጨረሻ ተሳታፊዎችን የሚመረጥው ዩኒቨርሲቲው እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡