08/09/2026
ለወባ ተጋላጭ ነፍሰ ጡር እናቶችና ሕፃናት የአጎበር ድጋፍ ተደረገ
መዲና – ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም (አርጎባ ኮሙኒኬሽን)
በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ለወባ ተጋላጭ ለሆኑ ነፍሰ ጡር እናቶችና ሕፃናት 1,200 አጎበሮች ድጋፍ ተደረገ።
አጎበሮቹ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሲሆን፣ ድጋፉን ያደረገው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ደሴ ቅርንጫፍ ከደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ነው።
በዕለቱ የወባን ስርጭት በተገቢው መከላከል ላይ ያተኮረ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ትምህርት ተሰጥቷል።
በተለይም አጎበርን በአግባቡ የመጠቀም፣ የመንከባከብና የወባ ትንኝ ንክሻን በመከላከል የሚኖረው ሚና ላይ ትምህርት ተሰጥቷል።
የድጋፍ ሥራው በተለይም ለወባ ተጋላጭ የሆኑ ነፍሰ ጡር እናቶችና ሕፃናትን ከወባ በሽታ ለመከላከል እንዲሁም በማኅበረሰቡ ዘንድ የወባ መከላከያ ግንዛቤን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑ ተገልጿል።
ተጠቃሚዎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ በቀጣይም ተመሳሳይ የጤናና የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል