Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office

Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office Government Organization

በ13 ዓመት ህጻን ላይ  የግብረ-ሰዶም  ወንጀል የፈጸመው  ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ #ሣውላ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (ሣውላ ከተማ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ) በሣውላ ከተማ መብራት ኃይል ...
04/09/2026

በ13 ዓመት ህጻን ላይ የግብረ-ሰዶም ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

#ሣውላ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (ሣውላ ከተማ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን )

በሣውላ ከተማ መብራት ኃይል ከተማ ቀበሌ በ13 ዓመት ሕጻን ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ8 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የሣውላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል ።

የ52 ዓመቱ አቶ አልቤኔ ካልፃዬ ወንጀሉን የፈፀመው በመብራት ኃይል ከተማ ቀበሌ ዲሞ ቀጠና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ አቶ አልቤኔ ለአካለ መጠን ያልደረሰና ዕድሜው 13 ዓመት የሆነውን ህፃን ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1: 00 ሰዓት ገደማ ህፃናት ተሰብስበው ከሚጫወቱበት የግል ተበዳይን የማን ልጅ ነህ በማለት ኃይል እና ማስገደድ በተሞላበት አኳኃን የግብረ ሰዶም ጥቃት ያደረሰበት በመሆኑ በፈፀመው ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሹ የተከሰሰበት ክስ በችሎት ተነቦለት የክስ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ቃሉን የሰጠ ሲሆን ዐቃቤ ህግም ተከሳሽ ክሱን ክዶ የተከራከረ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ የሚያስረዱ የህግ ምስክሮች ይሰሙልኝ በማለት ባቀረበው የሰውና የህክምና ማስረጃ መሰረት ተገቢውን ብይን ይሰጥልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

በኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 631 ንዑስ 1 ( ሀ ) መሠረት በአቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ መሠረት ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ በሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጣራት ነሐሴ 29/2018 ዓ. ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ያስተምረዋል በማለት በ8 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል ።

የኮሪደር መሠረተ ልማት አሰራርና አጠቃቀምን ለመቆጣጠር በቀረበ ረቀቅ ደንብ ዙሪያ ውይይት ተደረገ ፦ #ሣውላ  ነሐሴ 29/2019 ዓ.ም (ሣውላ ከተማ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን )የሣውላ ከተማ አ...
04/09/2026

የኮሪደር መሠረተ ልማት አሰራርና አጠቃቀምን ለመቆጣጠር በቀረበ ረቀቅ ደንብ ዙሪያ ውይይት ተደረገ ፦

#ሣውላ ነሐሴ 29/2019 ዓ.ም (ሣውላ ከተማ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን )

የሣውላ ከተማ አስተዳር ምክር ቤት የኮሪደር መሠረተ ልማት አሰራርና አጠቃቀምን ለመቆጣጠር በቀረበ ረቀቅ ደንብ ዙሪያ ውይይት አድርጓል ።

የከተማው ፍትህ ጽህፈት ቤት የህግ ጥናት ማርቀቅና ማስረጽ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ለማ አሸናፊ በረቂቅ ደንቡ ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በዋናነት የኮሪደር ልማት ሥራው የእግረኛ መንገዶችን፣ የመንገድ ዳር መብራቶችንና አረንጓዴ ስፍራዎችን ካልተገባ አጠቃቀም ለመከላከልና የሚስተዋሉ የፅዳት ጉድለቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን በቀረበው ረቂቅ ድንብ ላይ አመላክተዋል

ረቂቅ ደንቡ በከተማዋ በሚለሙ የኮሪደር መሠረተ ልማቶች የአሰራርና አጠቃቀም ተፈጻሚነት በግልጽ መቀመጥ እንዳለበት በመጠቆም የደንቡን አስፈላጊነትና በረቂቅ ደንቡ ግልጽነት ሊፈጠር ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች ለምክር ቤቱ አንስተዋል ።

ለአብነትም የንግድ ድርጅቶች መገኛን በተመለከተ ፣ በኮሪደር መሠረተ ልማቶች አከባቢ ጎሚስታ ፣ የተለያዩ መጋዘኖች ፣ ወፍጮ ቤቶችና ጊዜያዊ ሼዶችን ጨምሮ መሰል ግንባታዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባ መሆኑን በመጥቀስ ቅጣት ያልተጣለባቸው የተከለከሉ የደንብ ጥሰቶችን በተመለከተ የከተማው ህዝብ ምክር ቤት ዝርዝር አሰራር ሲያጸድቅ ተፈፃሚ ይሆናል የሚል ተጠቅሷል ።

የሣውላ ከተማ ከንቲባ አቶ በላይነህ ባህሩ የደንቡን አስፈላጊነት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በከተማዋ የሚከናወኑ የኮሪደር መሠረተ ልማት ሥራዎች በዋናነት ለከተማዋ ነዋሪዎች ምቹ ፣ ጽዱ ፣ ውብና ዘመናዊነትን በማላበስ ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን አንስተዋል ።

አክለውም በተለያዩ ከተሞች ከሚስተዋሉ የኮሪደር ልማት አጠቃቀም ልምድ አኳያ ደንቡ በአሰራርና አጠቃቀም ዙሪያ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት ራሱን የቻለ ልዩ ስነ-ስርአት እንዲኖረውና ህግን ታሳቢ አድርጎ የከተማዋን ደረጃ በሚመጥን መልኩ የህግ ማዕቀፍ መኖሩ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም በረቂቅ ደንቡ ሊካተቱ እና ሊስተካከሉ ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት በመወያየት ለከተማው ህዝብ ምክር ቤት ቀርቦ እንዲጸድቅ በሙሉ ድምጽ ወስነዋል ።

እንኳን ደስ አላችሁ!ሣውላ፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ምውድ የሣውላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና መላው የሣውላ ከተማ ነዋሪዎች፤በጎፋ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አጠ...
04/09/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!

ሣውላ፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

ውድ የሣውላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና መላው የሣውላ ከተማ ነዋሪዎች፤

በጎፋ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አጠቃላይ አፈጻጸም ምዘና ላይ ሣውላ ከተማ አንደኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኗ ከፍተኛ ደስታና ኩራት የሚሰጥ ዜና ነው። ለዚህ የላቀ ውጤት ያበቃችሁ የሣውላ ከተማ አመራሮች፣ አባላትና መላው ነዋሪ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ!

ይህ ውጤት በ2018 በጀት ዓመት በከተማችን የተከናወኑ የፓርቲ ሥራዎች፣ የአመራር አፈጻጸም፣ የአባላት ተሳትፎ፣ የሕዝብ ተሳትፎና ተቋማዊ አፈጻጸም በአጠቃላይ ተመዝነው የተገኘ ውጤት ነው።

በዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎችን በትጋት መፈጸም፣ የአመራር ተሳትፎን ማጠናከር፣ የአባላትን ንቁ ተሳትፎ ማሳደግ እና ሕዝቡን በተለያዩ የሥራ እንቅስቃሴዎች ማሳተፍ ለተገኘው ውጤት ወሳኝ ሚና አበርክቷል። ስለሆነም ለዚህ ስኬት በትጋት የሠራችሁ፣ የተሳተፋችሁና ኃላፊነታችሁን በተገቢው የተወጣችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናና አድናቆት ይገባችኋል።

በተለይም የሣውላ ከተማ አመራር የተመደቡ ሥራዎችን በዕቅድ በመምራት፣ የሥራ አፈጻጸሙን በመከታተልና አባላትን በማስተባበር ያደረገው ጥረት የሚደነቅ ነው። የፓርቲ አባላትም በተሰጣችሁ ኃላፊነት ላይ በትጋት በመሥራትና በተለያዩ የፓርቲ ሥራዎች በንቃት በመሳተፍ የበኩላችሁን አበርክታችኋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሣውላ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ በተለያዩ የሥራ መስኮች ያሳየው ትብብር፣ ተሳትፎና ድጋፍ ለተገኘው ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። በመሆኑም ለመላው የሣውላ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የተገኘው ውጤት የበለጠ ለመሥራት የሚያነሳሳን ነው

የተገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ትልቅ የሥራ ውጤት ቢሆንም፣ በዚህ ብቻ መርካት አይገባንም። የዛሬው ስኬት ከትናንት የበለጠ ለመሥራት፣ ከዛሬ የበለጠ ለመትጋትና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጠይቅ ኃላፊነት ነው።

ስለሆነም በቀጣይ ዓመት የተገኘውን ውጤት ለማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚህ በላይ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ከፍ ያለ ትጋትና ቁርጠኝነት ያስፈልገናል። የታዩ ክፍተቶችን በጋራ ማረም፣ የተገኙ ጥንካሬዎችን ማጠናከር፣ የአባላትን ተሳትፎ ይበልጥ ማሳደግና ከሕዝብ ጋር ያለንን ቅርበት ማጠናከር ይኖርብናል።

ይህንን ዋንጫ እንደ የሥራ ፍጻሜ ሳይሆን እንደ አዲስ የላቀ ስኬት መነሻ በመውሰድ፣ በቀጣይ ዓመት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ ሁላችንም በአንድነት እንሥራ።

በመጨረሻም ለዚህ የላቀ ውጤት ያበቃችሁ የሣውላ ከተማ አመራሮች፣ አባላትና መላው ነዋሪ ሕዝብ በድጋሚ ከፍ ያለ ምስጋናዬንና አድናቆቴን አቀርባለሁ።

እንኳን ደስ አላችሁ!
እንኳን ደስ አለን!

የዛሬውን ድል የነገ የበለጠ ስኬት መነሻ እናድርገው!

አቶ ከተማ ከበደ
የሣውላ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት ኃላፊ

በጎፋ ዞን አምስቱ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ መርሐ ግብሮች በድምቀት ይከበራሉ:-የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት!ሣውላ፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ምወደ አዲስ ዓመት የምንሸጋገርበት የጳጉሜ...
04/09/2026

በጎፋ ዞን አምስቱ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ መርሐ ግብሮች በድምቀት ይከበራሉ:-የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት!

ሣውላ፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

ወደ አዲስ ዓመት የምንሸጋገርበት የጳጉሜን ወር፣ ያለፈውን ዓመት ስኬት የምንገመግምበት፣ ያጋጠሙንን ክፍተቶች የምንለይበትና ለነገው የከፍታ ጉዞ አዲስ ተስፋና ብርታት የምንሰንቅበት ልዩ የዘመን መሸጋገሪያ ወቅት ነው።

በዚሁ መነሻ፣ በጎፋ ዞን የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን አምስቱ ቀናት በተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ልማታዊ፣ የሰላም፣ የኅብረትና የቴክኖሎጂ መርሐ ግብሮች በንቅናቄና በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ።

የጎፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ አቶ የትምጌታ ተስፋዬ የጳጉሜን ቀናትን አከባበር አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን በፅናት በመሻገር በማኅበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች ጉልህ ድሎችን እያስመዘገበች ወደ ከፍታ የማንሠራራት ምዕራፍ መሸጋገሯን ገልጸዋል።

የጎፋ ዞንም የሀገራችን የለውጥና የማንሠራራት ጉዞ አካል በመሆን፣ ባለፉት ዓመታት በልማት፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት፣ በማኅበራዊ አገልግሎቶችና በሕዝብ ተሳትፎ ዘርፎች ሁለንተናዊ ለውጦችን በማስመዝገብ የከፍታው ጉዞ ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ ሆኖ መቀጠሉን አመልክተዋል።

የጳጉሜን ወር በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ውስጥ ያለፈውን ዓመት በስኬት የምናጠቃልልበትና ወደ አዲሱ ዓመት በአዲስ ራዕይ የምንሻገርበት የተስፋ ድልድይ መሆኑን አቶ የትምጌታ ጠቅሰው፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አንኳር ስኬቶች በማስታወስና የቀሩ ተግባራትን በማረም ለቀጣዩ ዓመት የተሻለ አፈጻጸም መሠረት የሚጣልበት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል።

የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት አከባበርም ለሀገራችን ልዩ ታሪካዊ ወቅት ላይ በመዋሉ ልዩ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ይሁንታ የተመረጠው ፓርቲ መንግሥት በሚመሠርትበትና የሕዝብን አደራ ለመወጣት ዝግጅት በሚደረግበት እንዲሁም የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ውጤቶችን ወደ ተግባር ለመለወጥ ጠንካራ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት መከበሩ በዓሉን ይበልጥ ታሪካዊና ትርጉም ያለው እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።

የጳጉሜን ቀናትን በዞኑ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለማክበርም በዞን ደረጃ ዐቢይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅተው ወደ ሙሉ የተግባር ምዕራፍ መግባቱን አቶ የትምጌታ ገልጸዋል። ኮሚቴዎቹም ከዞን እስከ ወረዳና ከተማ መዋቅር ድረስ በተዋረድ በመደራጀት በዕቅድ የተያዙ መርሐ ግብሮች በአንድነትና በተቀናጀ መልኩ እንዲፈጸሙ እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጳጉሜን 1 – “የእምርታ ቀን”

የጳጉሜን የመጀመሪያ ቀን “የእምርታ ቀን” በሚል መሪ መልእክት ይከበራል።

በዚህ ዕለት በሀገርና በዞን ደረጃ የተመዘገቡ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ የተመዘገቡ ስኬቶች በትኩረት ይጎላሉ።

ከተረጂነት ወደ አምራችነት፣ ከፍጆታ ወደ ምርት፣ ከጥገኝነት ወደ ራስ በራስ መቻል የሚደረገውን የመዋቅር ሽግግር የሚያሳዩ ተግባራት በተለይ ትኩረት ያገኛሉ። የጎፋ ዞን የልማት አቅሞችን በማስፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ለሕዝቡ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር እያደረገው ያለው ጥረትም ይቀርባል።

ጳጉሜን 2 – “የማንሠራራት ቀን”

ሁለተኛው የጳጉሜን ቀን “የማንሠራራት ቀን” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።

በዚህ ዕለት በየደረጃው የተመዘገቡ የልማትና የመሠረተ ልማት ውጤቶች በዜጎች ዕለታዊ ሕይወት ላይ ያመጡት ተጨባጭ ለውጥ በልዩ ልዩ ይዘቶችና ሁነቶች ይቀርባል።

የልማት ሥራዎች የመንገድ፣ የውሃ፣ የትምህርት፣ የጤናና የሌሎች መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት በሕዝቡ ሕይወት ላይ ያሳረፉትን አዎንታዊ አሻራ በማሳየት፣ የበለጠ ከፍታ ለማምጣት የሚጠይቁ ቀጣይ ተግባራትም ይታወሳሉ።

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

“የጽናት ቀን” የሆነው ጳጉሜን 3 የሀገርና የሕዝብ ሰላም፣ የሀገረ-መንግሥት ቀጣይነትና የሕዝብ ደኅንነት የሚጎላበት ቀን ይሆናል።

በዚህ ዕለት የፀጥታ መዋቅሮች ዘመናዊ ቁመና፣ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የተገነባው አቅም እንዲሁም ለሀገር ሰላምና ለሕዝብ ደኅንነት በመስዋዕትነት ያገለገሉ ጀግኖች በክብር ይዘከራሉ።

ሰላም የልማት መሠረት፣ ጽናት የድል ምንጭ መሆኑን በማስገንዘብ፣ መላው ሕዝብ የሰላም ግንባታ ላይ ያለውን ሚና በማጠናከር ቀኑ ይከበራል።

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

አራተኛው የጳጉሜን ቀን “የኅብር ቀን” በሚል መሪ መልእክት ይከበራል።

በዚህ ዕለት በለውጡ ዓመታት በተደረጉ ሪፎርሞች የተገኙ የብዙኃን አካታችነት ውጤቶች፣ ሀገር በቀል እሴቶች፣ የወል ትርክት ግንባታ ሂደቶች እና በጎፋ ዞን የሚገኘው የሕዝቦች አብሮነትና መተባበር በልዩ ትኩረት ይቀርባሉ።

የባህል እሴቶችን ማጎልበት፣ የአብሮነት መንፈስን ማጠናከር፣ የመረዳዳትና የበጎ አድራጎት ባህልን ማስፋፋት የዕለቱ ዋና መልእክቶች ይሆናሉ።

ጳጉሜን 5 – “የነገው ቀን”

የጳጉሜን የመጨረሻው ቀን “የነገው ቀን” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።

ቀኑ የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ፣ የሳይበር ሉዓላዊነትን እና በ“5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ” መርሐ ግብር የተገኙ ውጤቶችን በማጉላት ይከበራል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ የዛሬን ሥራ ቀላል ከማድረግ ባሻገር የነገዋን ኢኮኖሚ፣ የትምህርት ሥርዓት፣ የሥራ ዕድልና የሀገር ተወዳዳሪነት የሚወስን ቁልፍ አቅም መሆኑ በተለያዩ የንቃተ ህሊና መርሐ ግብሮች ይገለጻል። በተለይ ወጣቱ ትውልድ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በዲጂታል ክህሎት ራሱን አብቅቶ የነገዋን ኢትዮጵያ በእውቀትና በፈጠራ የሚገነባበት ራዕይ ይጎላል።

በመሆኑም መላው የጎፋ ዞን ሕዝብ፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ማኅበረሰብ አደረጃጀቶችና ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች በጳጉሜን ቀናት አከባበር በንቃት እንዲሳተፉ አቶ የትምጌታ ተስፋዬ ጥሪ አቅርበዋል።

የጳጉሜን ቀናት ያለፉትን ድሎች በማስታወስ ብቻ የሚገደቡ ሳይሆኑ፣ ከስኬቶቻችን ብርታትን በመውሰድ፣ ከክፍተቶቻችን በመማርና ለቀጣዩ ዓመት በአንድ ራዕይ በመሰለፍ የበለጠ ከፍታ የምንቀይስበት የኅብረትና የተስፋ ቀናት መሆናቸው ተጠቅሷል።

“ያለፈውን በስኬት እንዘክር፤ ክፍተቶቻችንን በቁርጠኝነት እናርም፤ ለነገው ከፍታ በአንድነት እንቁም!”

በዚህም መላው የጎፋ ዞን ሕዝብ የተቀደሱ እሴቶቻችንን በማጎልበት፣ አብሮነታችንን በማጠናከር፣ ሰላምን በመጠበቅና ለነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ በጋራ በመቆም የጳጉሜን አምስቱን ቀናት በደማቅ ሁኔታ እንዲያከብር ጥሪ ተላልፏል።

መልካም የጳጉሜን ቀናት!
መልካም የአዲሱ ዓመት የመሸጋገር ወቅት!

“ሣውላን እንደገና እንሰራለን!” በሚል መሪ ቃል ለተጀመረው የከተማዋ ኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር  ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ 12,000 ...
04/09/2026

“ሣውላን እንደገና እንሰራለን!” በሚል መሪ ቃል ለተጀመረው የከተማዋ ኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ 12,000 (አሥራ ሁለት ሺህ) ብር ድጋፍ አድርገዋል።

እርስዎም የዚህ ታሪካዊ የከተማ ልማት አካል ለመሆን፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000787967829 ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በጎፋ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ሣውላ ከተማን አንደኛ ደረጃ አሸናፊ አደረጋትሣውላ፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም — በጎፋ ዞን በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አ...
03/09/2026

በጎፋ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ሣውላ ከተማን አንደኛ ደረጃ አሸናፊ አደረጋት

ሣውላ፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም — በጎፋ ዞን በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አጠቃላይ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማምጣት ሣውላ ከተማ አንደኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

የደረጃ ምዘናው በ2018 በጀት ዓመት በከተማዋ የተከናወኑ የፓርቲ ሥራዎችን፣ የአመራር አፈጻጸምን፣ የአባላት ተሳትፎን፣ የሕዝብ ተሳትፎና ተቋማዊ አፈጻጸምን በማጠቃለል የተካሄደ ሲሆን፣ ሣውላ ከተማ በአጠቃላይ አፈጻጸሟ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆናለች።

ይህ ውጤት በከተማዋ የፓርቲ አመራርና አባላት በጋራ የተደረገውን ብርቱ ጥረት፣ ተግባራዊ ቁርጠኝነትና የተቀናጀ የሥራ አመራር ያሳያል። የተገኘው የመጀመሪያ ደረጃም ለቀጣይ ሥራዎች ተጨማሪ ተነሳሽነትና ኃላፊነት የሚጨምር መሆኑ ተገልጿል።

የሣውላ ከተማ የፓርቲ አመራር ለተገኘው ስኬት የአመራሩንና የአባላትን የጋራ ጥረት በማድነቅ፣ የተገኘውን ውጤት እንደ መነሻ በመውሰድ በቀጣይም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በተጠናከረ መንፈስ እንደሚሠራ ገልጿል።

የተገኘው ሽልማት በአመራርና በአባላት የጋራ ተሳትፎ ትጋትና ቁርጠኝነት የተገኘ ውጤት መሆኑን በማመላከት ሣውላ ከተማ ይህንን የላቀ ውጤት በቀጣይ ዓመትም በማስጠበቅ ከፍ ያለ የሥራ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ተጨማሪ ጥረት ታደርጋለች።

የርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መልዕክትየሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ወደ ተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ለመሸጋገር የተያዘው ሀገራዊ እና ክልላዊ ግብ፤ የሉዓላዊነት ጥያቄ ብቻ ...
03/09/2026

የርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መልዕክት

የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ወደ ተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ለመሸጋገር የተያዘው ሀገራዊ እና ክልላዊ ግብ፤ የሉዓላዊነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋር የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ፤ በየደረጃው ያለው አመራር በክልሉ ለዚሁ ግብ ስኬት በመከናወን ላይ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከተለምዷዊ አሰራሮች ወጣ ባለ መልኩ ብዝኃ ታታሪነትንና የተሟላ የአመራር ብቃትን ተላብሶ፤ በከፍተኛ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት በመምራት እና ሕዝባዊ ተሳትፎን ባረጋገጠ መልኩ በማስፈፀም በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ከግብ ለማድረስ ከምን ጊዜውም በላይ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ይገባዋል፡፡

ለዚህ የሕዝባችንን ድንቅ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እሴቶች በአግባቡ ተጠቅሞ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች፡- መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፤ የልማት ማህበራትና ድርጅቶች፤ የኃይማኖት ተቋማት፤ መንግስት ሠራተኛውንና የንግዱን ህብረተሰብ፤ አርሶና አርብቶ አደሩን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በንቅናቄ በማሳተፍ ተግባራትን በጠንካራ ተቋማዊ ማዕቀፍ አልቆ በመፈፀምና በማስፈፀም ለውጤት ማብቃት ያስፈልጋል፡፡

ለተሻለ ነገ ዛሬን በኅብረት እንትጋ!!

ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

የጎፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።ሣውላ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ  የጎፋ ዞን ብልፅ...
03/09/2026

የጎፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።

ሣውላ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የጎፋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የወረዳ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችንና የዘርፍ አመራሮችን ባሳተፈ መልኩ በሣውላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በጥልቀት እየተገመገመ ሲሆን፣ በዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከር እና በየዘርፉ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ የሥራ ዘመን ስንቅ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለመውሰድ ያለመ ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል።

በግምገማው የተለዩ የሥራ ክፍተቶች በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውስጥ በማካተት ወደ ተግባር እንዲቀየሩ እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

በመድረኩ በተሰጠው ገለጻ፣ 2018 በጀት ዓመት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆናም ትልልቅ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና በማስመረቅ ለዓለም ተምሳሌት የሆኑ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት ዓመት መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም 7ኛውን አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ በስኬት በማጠናቀቅ ሀገሪቱ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል የፖለቲካ ሂደት በማስቀጠል ታሪካዊ ምዕራፍ የተመዘገበበት ዓመት መሆኑም ተነስቷል።

ከዚህ ባሻገር፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ አፍራሽ ኃይሎች ያቀዱት ዕቅድ ሳይሳካ በቅንጅትና በትብብር በመመከት ውጤታማ ሥራ መሠራቱ ተጠቁሟል።

የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ለተሳታፊዎች ቀርቦ በጥልቀት እንደሚመከርበትና በቀጣይም የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ኦሬንቴሽንና ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

መድረኩ የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከር፣ የተለዩ ድክመቶችን በማረምና በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሚያስችል ይጠበቃል።

በሳውላ ከተማ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋልነሐሴ 27/2018 ዓ.ም  በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኙ ትም...
02/09/2026

በሳውላ ከተማ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አዲሱን የትምህርት ዘመን በላቀ ዝግጅት ለመቀበልና የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ ሁለገብ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉ ተመላክቷል።

በከተማዋ በተደረገው ምልከታ ትምህርት ቤቶች ከተማሪዎች ምዝገባ ጎን ለጎን የመማሪያ ክፍሎችን የመጠገን፣ የመቀመጫ ዴስኮችን የማዘጋጀት፣ ጥቁር ሰሌዳዎችን የማደስ እና የትምህርት መጻሕፍትን የማሟላት ሥራዎችን በስፋት እያከናወኑ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

የትምህርት ቤቶቹን ዝግጅት አስመልክተው አስተያየታቸውን የሰጡት የቦትሬ መጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አለምቱ አረጋ፣ የቲባቴ መጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ንጉሴ ጩንፋላ እና የሳውላ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አያለው ቦላዶ፤ ተማሪዎች ሳቢና ምቹ በሆነ የመማርያ አካባቢ እንዲጀምሩ የጽዳትና የውበት ሥራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የትምህርቱ ሂደት ፍሬያማ ይሆን ዘንድ የወላጆች አብሮነት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት የተማሪ ወላጆች፤ ከትምህርት ቤቶች ጎን በመቆም የልጆቻቸውን የትምህርት አቀባበልና ውሎ በቅርበት ለመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ተማሪዎች ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ ከማባከን ተቆጥበው፣ በትምህርታቸው ላይ በማሳለፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የሳውላ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያዕቆብ በተላ በሰጡት ማብራሪያ፤ በተያዘው የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ለማሳደግና የትምህርት ጥራትን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማስጠበቅ የተማሪዎች፣ የወላጆች፣ የመምህራንና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረትና በቅንጅት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ይህም አዲሱን የትምህርት ዘመን በተሻለ ዝግጅት በመጀመር የመማር-ማስተማሩን ሂደት ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

#ደሬቴድ

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

Adresse

Democratic Republic Of The

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Raccourcis

Partager