13/08/2026
በዓለም ከተማ 03 ቀበሌ በክረምት በጎፍቃድ የተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባና አሻራ አሰጣጥ ተካሄደ።
ነሀሴ 7/2018 ዓ/ም
በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በሚገኘው ኢትዮ ሚሊኒየም ትምህርት ቤት የተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ሥራ ተካሄደ።
የምዝገባና የአሻራ አሰጣጥ ሥራው በዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ተከናውኗል።
በመርሃ ግብሩም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም ከተማ ቅርንጫፍ ሲኒየር ቢዝነስ ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ኤፍሬም ንጉሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢዝነስ ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ፋሲካ አንበርብር ተማሪዎችን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባና አሻራ አሰጣጥ ሥራ አከናውነዋል።
ይህም ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያቸውን በቀላሉ እንዲያገኙና ዲጂታል መረጃቸው በተገቢው መንገድ እንዲመዘገብ የሚያግዝ ነው።