05/09/2026
አዋጅ ቁጥር 1425/2018 የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ስለ ኮንትሮባንድ ድረጊት ምን ይላል በሁለት ክፍል እናቀርባለን ተከታተሉን፡፡
ክፍል አንድ
16) የአዋጁ አንቀጽ 147 ኑዑስ አንቀጽ (3) ፊደል ተራ (ሀ) እና (ለ) ተሰርዘው በሚከተለዉ አዲስ ኑዑስ አንቀጽ (3) ፊደል ተራ (ሀ) እና (ለ) ተተክተዋል፡፡ እንዲሁም አዲስ ፊደል ተራ(ሐ) ተጨምሯል ፡፡
ሀ) ዕቃዎቹን ለመደበቅ እንዲያስችል ሆኖ የተሰራ፣የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት ከሆነ፤
ለ) በፊደል ተራ( ሀ) የተመለከተዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ማጓጓዛዉ የኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ የተገኘ ከሆነ ተሽከርካሪዉ ባለቤት የገንዘብ ሚኒስቴር የሚያወጣዉ መመሪያ በሚወሰነዉ መሰረት እንደነገሩ ክብደት እንዲሁም እንደጭነቱ መጠን በገንዘብ መቀጮ ወይም ማጓጓዣዉን እስከ መዉረሰ ሊያደርሰ በሚችል ቅጣት ሊቀጣ ይችላል፤
ሐ) ማጓጓዣዉ ከመወረሱ በፈት ማጓጓዣዉ ባለቤት ይህንኑ እንዲያዉቀዉ ሊደረግ እና ማጓጓዣዉ ጥቅም ላይ ስለዋለበት ሁኔታ ማስረጃ እንዲያቀርብ እድል ሊሰጠዉ ይገባል፡፡
17) የአዋጁ አንቀጽ 155 ኑዑስ አንቀጽ ( 2) ተሰርዞ በሚከተለዉ አዲስ ንዑስ አንቀጽ (2) ተተክቷል፤
2/ ይግባኝ የተባለበት ጉዳይ የቀረጥና ታክስ ክፍያ የሚመለከት ሲሆን የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን 50% (ሃምሳ በመቶ) ክርክር ያስነሳዉ የቀረጥና ታክስ ክፍያ መፈጸሙን ሳያረጋግጥ ይግባኙን አይቀበልም፡፡
18) የአዋጁ አንቀጽ 157 ንዑስ አንቀጽ (3) ተሰርዟል የአንቀጽ 157 ቀሪ ድንጋጌዎች ተሸጋሽገዋል፡፡
19) የአዋጁ አንቀጽ 160 ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ተተክቷል
160. ስለአጓጓዥ ግዴታዎች እና ኮንትሮባንድ በማጓጓዝ ዲርጊት ስለመሳተፍ
1/ማንኛዉም አጓጓዥ፡-
ሀ/ በተወሰነዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ የመንገደኞች ወይም የጭነት መገለጫ ካላቀረበ ፤
ለ/ ከተፈቀደለት ሰዉ በሰተቀር ሌላ ሰዉ ወደ ማጓጓዛዉ እንዲገባ ካደረገ ወይም
ሐ/ ማጓጓዛዉ ከጉምሩክ ወደብ እንዲወጣ ከተወሰነ በኋላ ምክንያቱን ለጉምሩክ ሹም ሳያስረዳና ፍቃድ ሳያገኝ እንዲቆይ ካደረገ ከብር 4,000 ባላነሰ እና ክብር 10,000 (አስር ሺ) በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡
------ ክፍል ሁለት ይቀጥላል