Waayyuu Promotion

Waayyuu Promotion promotion

ከምገባ እስከ ሰብአዊ ከብር — የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታሪካዊ የምገባ ፕሮግራምበአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ መፋዘዝና በኑሮ ውድነት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖ...
06/08/2026

ከምገባ እስከ ሰብአዊ ከብር — የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታሪካዊ የምገባ ፕሮግራም

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢኮኖሚ መፋዘዝና በኑሮ ውድነት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖች ለረሃብና ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሳሳቢ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDG Goal 2 - Zero Hunger) ለማሳካት አገራት ዘርፈ ብዙ ጥረት እያደረጉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስጀመረው አጠቃላይ የምገባ ፕሮግራም ለሌሎች ከተሞች ጭምር ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ሰብአዊ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።

ከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ለማረጋገጥ ባስቀመጠው ግልጽ ግብ መሰረት፣ በተለይም አቅመ-ደካሞችንና ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ ሰፊ ስራ ሰርቶ በተግባር እየፈፀመ ይገኛል። ፕሮግራሙ በቀን አንድ ጊዜ እንኳ በቂ ምግብ ማግኘት የማይችሉ ዜጎችን ለመደገፍ በመላው ከተማዋ ከ30 በላይ ዘመናዊና የተቀናጁ የምገባ ማዕከላትን አቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

👉 የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ማሳደግ፡ በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታ የሚቀሩና ትኩረት የሚያጡ ተማሪዎችን በመደገፍ፣ ትምህርታቸውን በትክክል እንዲከታተሉና የነገዋን ኢትዮጵያ በዕውቀት እንዲገነቡ መንገድ ከፍቷል።

👉 ሰብአዊ ክብርን ማረጋገጥ፡ ማንኛውም ዜጋ በራሱ ከተማ ውስጥ የመኖር፣ የመብላትና የመጠበቅ ሰብአዊ መብቱን የሚያረጋግጥ የአመራር ቁርጠኝነት ማሳያ ነው።

✅ ዓለም አቀፍ ደረጃን ያገናዘበ እይታ፡ ፕሮግራሙ ከተማዋ ዓለም አቀፍ የልማትና የሰብአዊነት መስፈርቶችን እንድታሟላ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ፣ በከተሞች ደረጃ የሚደረግ ማህበራዊ ዋስትና (Social Protection) እንዴት ውጤታማ መሆን እንደሚችል ያሳያል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን በጎ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል፣ ረሃብና ድህነት የተሸነፉባት፣ የዜጎቿ ሰብአዊ ክብር የተጠበቀባትና ለአፍሪካ አህጉር አርአያ የምትሆን ከተማ የመገንባት ግቡን አሳክቶ ለማሳየት በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

05/07/2026

Finfinnee!

19/05/2026
የሕወሓት ጭንብል ሲቀደድ!የ50 ዓመቱ "እኔ ከሌለሁ ሕዝቡ ይጠፋል" የሚለው የፍርሃት ፖለቲካ ዛሬ አብቅቶለታል። ሕወሓት ላለፉት አምስት አስርተ ዓመታት የትግራይን ሕዝብ እንደ "ፖለቲካዊ ጋሻ...
28/12/2025

የሕወሓት ጭንብል ሲቀደድ!

የ50 ዓመቱ "እኔ ከሌለሁ ሕዝቡ ይጠፋል" የሚለው የፍርሃት ፖለቲካ ዛሬ አብቅቶለታል። ሕወሓት ላለፉት አምስት አስርተ ዓመታት የትግራይን ሕዝብ እንደ "ፖለቲካዊ ጋሻ" ሲጠቀምበትና በስነ ልቦናው ካለኔ የሚል ቁማር ሲቆምርበት ቆይቷል።

በአገር ላይ በየግዜው ቅርፁንና አጀንዳ እየቀያየረ የሚበጠብጠው ሕወሓት የፖለቲካ ድርጅት ነበር፤ የትግራይ ሕዝብ ግን የሥልጣኔ መሠረት የሆነ ቋሚ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ማንነት ነው።

ድርጅት የነበረው ህውሃት ይሞታል፤ ሕዝብ ግን በመሬቱ ለዘላለም ይኖራል!

የትግራይ ህዝብ አሁናዊ የመከራ ውስጥ ዝምታው የሽማግሌዎች ተስፋና ፍቅር ሳይሆን የጠመንጃና የሞት ፍርሃት ውጤት ነው።

ለዚህ ደግሞ የሕፃፅ ረሃብና በሽታ ምስክሮች ናቸው። ድርጅቱ ለሕዝቡ ሳይሆን ሕዝቡ ለድርጅቱ እንዲገብር ተፈርዶበታል።

እርዳታን ለፖለቲካ ታማኝነት መለኪያ ማድረግ የተራ ሽፍታ ግንኙነት እንጂ የህዝብ ውክልና አይደለም።

እኛ የምንፈልገው የትግራይ ሕዝብ ከሥልጣን ጥመኞች እና ከደም ጠጪዎች ቁማር ወጥቶ ሰላም፣ ዳቦና መድኃኒት በማግኘት፣ወልዶ መሳም፣ዘርቶ ማጨድ፣ለምቶ ማደግ፣ተምሮ መጥቀምና ሰብአዊ መብቱ እንዲከበርለት ይፈልጋል።

ወገኖቼ ይሄን የደም ጠጪና የጨካኞች ስብስብ ቡድን መተቸት፣ ሕዝቡን መጥላት አይደለም፤ ሕዝቡን በስነ ልቦና ከታሰረበት ፍርሃትና ከተጋረደበት ጭንብል ነፃ ማውጣት እንጂ!

🛑 አጋልጥይህ ዜና ፈፅሞ ከእዉነት የራቀ ነዉ።በአዲሰ አበባ የተጨመረም የተቀነሰም አመራር የለም።በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች "ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ሆነው ...
18/12/2025

🛑 አጋልጥ
ይህ ዜና ፈፅሞ ከእዉነት የራቀ ነዉ።በአዲሰ አበባ የተጨመረም የተቀነሰም አመራር የለም።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች "ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ" ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስና ከእውነት የራቀ ነው።
ሊታወቁ የሚገቡ ነጥቦች፦

* ምንም ዓይነት አዲስ ሹመት የለም፦ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ አመራር ደረጃ የተደረገ ምንም ዓይነት አዲስ ሹመትም ሆነ ለውጥ የለም።

> ማሳሰቢያ፦ ህዝቡ መሰል ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠብና ትክክለኛ መረጃዎችን ከከተማ አስተዳደሩ ይፋዊ ገጾች ብቻ እንዲከታተል እናሳስባለን።

16/12/2025
11/12/2025

Address

Adama

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waayyuu Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share