Addis Ketema woreda 5 Communication

Addis Ketema woreda 5 Communication This is woreda 5 communication office .
(1)

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመ...
01/09/2026

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ለዚህም በቂ የበዓል ፍጆታ ምርቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም ከ28/12/18 ዓ ም ጀምሮ በዓሉን በማስመልከት በ11ዱም ክ/ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ ስራ የሚጀምሩ መሆኑን ገልፀው የእሁድ ገበያዎችም ሳምንቱን ሙሉ ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በባዛሮቹ ከበዓል ፍጆታዎች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ ለትምህርት የሚሆኑ ግብዓቶች እና የተለያዩ አልባሳቶች የሚቀርቡ መሆናቸውን ወ/ሮ ሀቢባ አሳውቀዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል የሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቁት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በየደረጃው የሚገኙ የህገ-ወጥ ንግድ መከላከልና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመግለጫቸው የበዓል ፍጆታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው፣ ህገ-ወጥ የሆነ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥም የከተማችን ነዋሪ በ8588 ነፃ የስልክ ጥሪ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈ...
01/09/2026

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ አምስት ዓመትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ በምርጫ ለሕዝብ የገባነውን ቃል ለመፈጸም 24/7 በትጋት በመስራት አዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የመዲናዋ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከሀገራዊ ርዕይ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ አንጻር የተቃኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ የተቀናጀ ጥራት ያለውና ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ 11 የመሶብ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ በ2019 በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማዕከላት እንደሚከፈቱ ተናግረዋል፡፡

ማዕከላቱ የሚከፈቱት ወረዳዎችን በክላስተር በማደራጀት እንደሆነና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 66 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ለመክፈት መታቀዱን አመልክተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተሳለጠ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
01/09/2026

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ::*****************ነሐሴ 24-2018ዓምበአዲስ ከተማ ክ/ከተማ  "የአካል ብ...
30/08/2026

በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ::
*****************
ነሐሴ 24-2018ዓም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ "የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናችንን እንጠብቅ" በሚል መሪ ሐሳብ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉት ደማቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል::

በእድሜ መግፋት ምክንያት ከሚከሰቱ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እራስን ከመጠበቅ ባሻገር ስፖርት ለአብሮነትና ለፍቅር ከፍተኛ ሚና ስላለው ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነዉ ተብሏል::

የክፍለ ከተማው ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል ማድረግ ይገባል ያሉት የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ታደሰ ወርቁ ሁሉም ሰው የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የየእለት ከእለት ተግባሩ ሊያደርገው ይገባል ብለዋል::



የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው በእድሜ መግፋት ምክንያት ከሚከሰቱ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እራስን ለመጠበቅ ስፖርትን ባህል ማድረግ ተገቢ በመሆኑ በየአካባቢው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በጤናና በአካል ጉዳት ምክንያት ቢሮ ድረስ መምጣት ለማይችሉ ነዋሪዎች የቤት ለቤት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ። ***************** ነሐሴ 23-20...
29/08/2026

የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በጤናና በአካል ጉዳት ምክንያት ቢሮ ድረስ መምጣት ለማይችሉ ነዋሪዎች የቤት ለቤት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ።
*****************
ነሐሴ 23-2018 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በህመም፣ በአካል ጉዳት እና መሰል ጉዳዮች ምክንያት በአካል መጥተው የመንግስት ቤት ውል እድሳት ማድረግ ለማይችሉ ነዋሪዎች የቤት ለቤት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል::

የክፍለ ከተማው የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዲሳለም እንቻለው እንዳሉት ጽ/ቤቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልፀው ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በጤና፣ በአካል ጉዳትና በእርጅና ምክንያት ቢሮ ድረስ መምጣት ለማይችሉ ነዋሪዎች ሰራተኞችን ወደ መኖሪያ ቤት በመላክ ውል የማደስ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ አዲሳለም አክለውም በተለያየ ጊዜ ሃገራቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ ዜጎች በእድሜ መግፋትና በህመም ምክንያት ቢሮ መጥተው ማደስ ባለመቻላቸው እኛ ቤታቸው ድረስ ሒደን አገልግሎቱን በመስጠት ሰብዓዊ ሃላፊነታችንን በተገቢው መንገድ በመወጣት ላይ እንገኛለን ብለዋል::

አገልግሎቱን ያገኙ ነዋሪዎች በበኩላቸው በጤና እክል ምክንያት የአልጋ ቁራኛ በመሆናችን የቤት ውድ እድሳት አለፈን አላለፈን እያልን በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነበርን፣ አሁን ግን የቤቶች አስተዳደር አመራሮችና ሰራተኞች ቤታችን ድረስ መጥተው ውላችንን እንድናድስ ስላደረጉልን ከፍተኛ እፎይታ ተሰምቶናል ሲሉ ተናግረዋል::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

የቅዳሜና እሁድ ገበያ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ሚናቸው የላቀ መሆኑ ተገለፀ።በአዲስ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የንግድ ጽ/ቤት እና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የኑሮ ውድነትን ለማረጋ...
29/08/2026

የቅዳሜና እሁድ ገበያ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ሚናቸው የላቀ መሆኑ ተገለፀ።

በአዲስ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የንግድ ጽ/ቤት እና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በመዳኒያለም እና ፓስተር አደባባይ የግብርና ምርቶች እና የእንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪው እየቀረበ ይገኛል።

ሸቀጣ ሸቀጦችንና ፍራፍሬዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በቅዳሜና በእሁድ ገበያ ለሕብረተሰቡ በማቅረብ በወረዳው አካባቢ ለሕዝቡ ተደራሽነት የማስፋት ስራዎች እየተሠሩ ሲሆን በቀጣይም የተሻሉ ምርቶችንና ፍራፍሬዎችን የኑሮ ውድነቱን ባገናዘበ መልኩ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም

«ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ ስጋት መንስኤ ሊሆን አይገባም» በሚል መሪ ቃል በወረዳ 5 የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደበአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽሕፈ...
29/08/2026

«ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ ስጋት መንስኤ ሊሆን አይገባም» በሚል መሪ ቃል በወረዳ 5 የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት «ደረቅ ቆሻሻ የሀብት ምንጭ እንጂ የጎርፍ ስጋት መንስኤ ሊሆን አይገባም» በሚል መሪ ቃል ሰፊ የህዝብ ንቅናቄና የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ። ንቅናቄው በአካባቢው የሚገኙ የፍሳሽ ማለፊያዎችንና ቦዮችን በማፅዳት ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል ያለመ ነው።

ንቅናቄውን ያስጀመሩት የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የፅዳት ፕሮግራም የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በንቃት የተሳተፉ ሲሆን፤ የፍሳሽ መስመሮችን በማፅዳትና ደረቅ ቆሻሻዎችን በማንሳት ለወረዳው ውበትና ጽዳት ያላቸውን ዝግጁነት አሳይተዋል።

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር መሆኑን የተረዱ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰራተኞችና አመራሮች በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡********************ነሐሴ...
28/08/2026

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር መሆኑን የተረዱ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰራተኞችና አመራሮች በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡
********************
ነሐሴ 22-2018ዓም

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በአገልግሎት ቀን ሁሉም ሰራተኛ እና አመራር በቢሮው ተገኝቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል::

በተቀናጀ አገልግሎት ባለጉዳዮችን እያስተናገዱ ያሉ ሰራተኞች ህዝባችንን ዝቅ ብለን በማገልገል በአገልግሎታችን የረካ ማህበረሰብ ለመፍጠር በመትጋት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ህዝብን ማገልገል ከክብርም በላይ ክብር በመሆኑ በባለጉዳይ ቀን ህብረተሰቡን እያገለገሉ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

"ዓድዋ ናይት ፋይት"  በአዲስ አበባ ሰማይ ስር የተጻፈ አዲስ የስፖርት ታሪክ! ​በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም የተደረገው ታላቁ "ዓድዋ ናይት ፋይት" (Adwa Night Fight) የሚክስድ...
28/08/2026

"ዓድዋ ናይት ፋይት" በአዲስ አበባ ሰማይ ስር የተጻፈ አዲስ የስፖርት ታሪክ!

​በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም የተደረገው ታላቁ "ዓድዋ ናይት ፋይት" (Adwa Night Fight) የሚክስድ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በታላቅ ስኬት፣ በደመቀ ድባብ እና በሰላም ተጠናቋል!

​ይህ ታሪካዊ ምሽት የከተማችንን ሁለገብ አቅም፣ የስፖርታዊ ውድድሮች አዲስ እይታን፣ እንዲሁም መዲናችን አዲስ አበባ አለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ታላላቅ የስፖርት ዝግጅቶች የማስተናገድ ብቃቷ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ዳግም ያረጋገጠበት ነበር። ዋና ዋና የስኬት ኩነቶች፦
1. ​ስማርት እና ዘመናዊ አዲስ አበባ :-የኢትዮጵያዊነት እና የፅናት ምልክት በሆነው በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደው ይህ ውድድር፤ የከተማችንን ዘመናዊነት (Smart City) እና ለትላልቅ አለም አቀፍ ኹነቶች ያላትን ዝግጁነት በግልጽ እና በተግባር አሳይቷል።
2. ​የተወዳዳሪዎች ድንቅ ብቃት:-ተወዳዳሪዎቻችን ያሳዩት ከፍተኛ የቴክኒክ፣ የፅናት እና የስፖርታዊ ጨዋነት ብቃት የምሽቱን ሳቢነት እና አዛኝነቱን በእጅጉ ጨምሮታል።
3. ​የስፖርቱ አዲስ ምዕራፍ:- እንደ Mixed Martial Arts (MMA) ያሉ አዳዲስ እና አሳታፊ የስፖርት አይነቶች በሀገራችን እያደጉ መምጣታቸውን እና የወጣቶቻችንን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆናቸውን ማሳያ ነው።
4. ​የህዝቡ ደማቅ አቀባበል፦ የስፖርት አፍቃሪው ህዝባችን ያሳየው ደማቅ ድጋፍ እና ፍቅር ውድድሩ ልዩ ቀለም እንዲላበስ አድርጎታል።

​ይህ ታላቅ ዝግጅት በስኬት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተወዳዳሪዎች፣ አዘጋጆች፣ የስፖርት አፍቃሪዎች እና ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

​አዲስ አበባ፣ የአለም አቀፍ ስፖርታዊ ኹነቶች እና የታላላቅ ህልሞች መድረክ!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Telephone

+251925470613

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema woreda 5 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ketema woreda 5 Communication:

Shortcuts

Share