Addis Ketema Woreda12 Communication

Addis Ketema Woreda12 Communication በዚህ ወሳኝ ወቅት ከመንግስት ተቋማት የሚተላለፉትን መረጃዎ�

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለመጪው የአዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ ሁሉም አይነት የፍጆታ ምርቶች በበቂ ሁኔታ መቅረባቸው  ተገለፀ::*******************ነሐሴ 27-2018 ዓ.ም በክፍለ ከ...
02/09/2026

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለመጪው የአዲስ ዓመት በዓል የሚሆኑ ሁሉም አይነት የፍጆታ ምርቶች በበቂ ሁኔታ መቅረባቸው ተገለፀ::
*******************
ነሐሴ 27-2018 ዓ.ም

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም የህብረት ስራ ማህበራት መጭውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ የፍጆታ ምርቶች በበቂ ሁኔታ ለሸማቹ ህብረተሰብ እየቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል::

ለበዓል የሚሆኑ የፍጆታ ግብዓቶችን በሸማች ማህበራት እንዲሁም በእሁድ ገበያዎች አማካኝነት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት እየቀረቡ መሆናቸውን እንዲሁም ከምርት አቅርቦት አንፃር ሸማች ማህበራት አማካኝነት መቅረባቸው ተገልጿል::

የአዲስ ዓመት በዓልን ተከትሎ ሊከሰት የሚችል የምርት እጥረትና የገበያ ጫና ለመቀነስ የአቅርቦት ሂደቱ በስፋትና በጥራትና የቀረበ ሲሆን በበዓሉ ሰሞን የሚጨምረውን የሸማቾች ፍላጎት ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በበቂ መጠን መቅረባቸው ተገልጧል::

በሸማች ማህበራቱ ከቀረቡ ምርቶች መካከል እንቁላል፣ ቂቤ፣ በርበሬ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፓስታ፣ መኮረኒ እና የመሳሰሉት ተጠቃሾች ናቸው::

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው በሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ በመሆናቸው የሚፈልጉትን ምርት እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል::


# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

የአገልግሎት ቀን ምክንያት በማድረግ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ምልከታ ተደረገ ።***በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ምክር ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤ...
02/09/2026

የአገልግሎት ቀን ምክንያት በማድረግ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ምልከታ ተደረገ ።
***

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ምክር ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት እና ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተቋማት ላይ ምልከታ የማድረግ ስራ ተሰራ።

የአገልግሎት ቀንን ለህዝብ ብቻ በማዋል የህብተሰባችንን የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አስተዳደር ችግር አመራሩ እና ፈፃሚው የአገልግሎት ቀን ለህዝብ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እና የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

(27/12/2018ዓ.ም
(ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት) )

01/09/2026
የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕ...
01/09/2026

የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አጥጋቢ ውጤት አምጥተዋል – ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው 33ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ፣ በመዲናዋ ያለፉትን የትምህርት ስትራቴጂዎችን በማሻሻል በአዲስ ስትራቴጂ የሚመራበት ዓመት መሆኑ የዘንድሮውን ጉባኤ ለየት ያደርገዋል ብለዋል።

ባለፉት ጊዜያት ተረባርበን በሰራንባቸው የትምህርት ዘርፎች ላይ ውጤት ተመዝግቧል ያሉት የቢሮ ኃላፊው ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) ፣ በዚህም የተማሪዎች ውጤት ላይ ፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እና የአመራሩና የትምህርት ባለሙያው የጋራ ውህደት የተረጋገጠበት ሆኗል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረጉን ገልጸው ፣ በዚህም በትምህርት ዘርፍ ውጤት እየመጣ ይገኛል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመዲናዋ ቀደም ሲል በደረጃ 4 ምንም የመንግስት ትምህርት ቤት ባልነበረባቸው አካባቢዎች ጭምር አሁን ላይ 23 ትምህርት ቤቶች መድረሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከቀዳማይ ልጅነት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ድረስ የሰጠው ትኩረትና እያከናወነው ያለው ተግባር ለዘርፉ ሰፊ የቤት ስራ የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ፤ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የበለጠ ከፍ ለማድረግ የሁሉም አካል ርብርብ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።

ይህ ጉባኤ በቀጣይ በትምህርቱ ዘርፍ ለሚከናወኑ ተግባራት በርካታ መሰረት የሚጥል ስለመሆኑም ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር)
አብራርተዋል።

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመ...
01/09/2026

የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የበዓል ፍጆታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በአገር ውስጥ ለሚገኙ ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ለዚህም በቂ የበዓል ፍጆታ ምርቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ አክለውም ከ28/12/18 ዓ ም ጀምሮ በዓሉን በማስመልከት በ11ዱም ክ/ከተሞች የበዓል ባዛሮች በይፋ ስራ የሚጀምሩ መሆኑን ገልፀው የእሁድ ገበያዎችም ሳምንቱን ሙሉ ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በባዛሮቹ ከበዓል ፍጆታዎች በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ምርቶች፣ ለትምህርት የሚሆኑ ግብዓቶች እና የተለያዩ አልባሳቶች የሚቀርቡ መሆናቸውን ወ/ሮ ሀቢባ አሳውቀዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ አርቴፊሻል የሆነ የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቁት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በየደረጃው የሚገኙ የህገ-ወጥ ንግድ መከላከልና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመግለጫቸው የበዓል ፍጆታ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው፣ ህገ-ወጥ የሆነ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ሲያጋጥም የከተማችን ነዋሪ በ8588 ነፃ የስልክ ጥሪ በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈ...
01/09/2026

በመዲናዋ 20 ተጨማሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ - ከንቲባ አዳነች

በተያዘው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ 20 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላት ይከፈታሉ አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ አምስት ዓመትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ በምርጫ ለሕዝብ የገባነውን ቃል ለመፈጸም 24/7 በትጋት በመስራት አዲስ አበባን ተምሳሌታዊ ከተማ እናደርጋታለን ብለዋል።

ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የመዲናዋ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከሀገራዊ ርዕይ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ አንጻር የተቃኘ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ የተቀናጀ ጥራት ያለውና ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ አይበገሬ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መፍጠር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ በከተማ አስተዳደሩ 11 የመሶብ ማዕከላት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ በ2019 በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማዕከላት እንደሚከፈቱ ተናግረዋል፡፡

ማዕከላቱ የሚከፈቱት ወረዳዎችን በክላስተር በማደራጀት እንደሆነና በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 66 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ለመክፈት መታቀዱን አመልክተዋል።

በሁሉም ዘርፍ የተሳለጠ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡

Address

Addis Ketema
Addis Ababa

Telephone

+251925694929

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Woreda12 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share