Prosperity Party Kolfe Woreda 07 Branch - ብልፅግና

Prosperity Party Kolfe Woreda 07 Branch - ብልፅግና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚከናወኑ ስራዎችን በዚህ የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ!!

25/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Hordoftoota amantaa Islaamaa hundaaf Baga Ayyaana Mawliidaa Nabiyyii Mahaammad (S.A.W) 1, 501ffaaf nagaan geessan!

Ayyaanicha wayita kabajnu akkuma kanaan duraa lammiilee keenya rakkatan gargaaraa, warra hin qabneef qoodaa, warra daaran uffisuun, warra dhukkubsatan gaafachuun akka ta'un hawwa.

Irra deebiin baga geessan - Iid Mubaarak!

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁየነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላ...
24/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ

የነቢዩ መሐመድ ታሪክ ትውልድን ለበጎ ከሚቀርጹ ታሪኮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የተጠሩበትን ዓላማ ማክበር፤ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ መክፈል፤ የተጠሩበትን ለሌሎች ማካፈል፤ የተጠሩበትን አክብሮ መኖር - እነዚህ ሁሉ ሺ መጻሕፍት የሚወጧቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

ነቢዩ የተጠሩበትን ዓላማ በሚገባ ስለተገነዘቡ አክብረው ኖረዋል፡፡ የተጠሩት ለተራና ርካሽ ነገር እንዳልሆነ ተገንዝበዋል፡፡ የተጠሩት ትውልድን ለመቅረጽና ታሪክን ለመቀየር መሆኑን አምነዋል፡፡ ያንንም በቃላቸው፣ በሥራቸውና በኑሯቸው አክብረውት ነኖረዋል፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ተጠርተናል ብለን የምናምን ከሆነ ይህ የነቢዩ ሕይወት ታላቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡ የተጠራንበትን ዓላማ በንግግራችን፣ በሥራችንና በሕይወታችን እንግለጠው፡፡

ነቢዩ ለተጠሩበት ዓላማ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ከቦታቸው ተሰደዋል፤ ምግብና መጠለያ ተነፍገዋል፤ ከቤተሰቦቻቸው ተለይተዋል፡፡ ለሞት በሚያበቁ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ ጦርነት ተከፍቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉንም በአላህ ኃይል አሸንፈዋል፡፡ ክብር ያለ መከራ አይገኝምና፡፡ እውነተኛ ሰው ለዓላማው እንደ ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ)ዋጋ ይከፍላል፡፡ ዓላማው የሚያስገኘውን ክብርና ጥቅም ብቻ ሳይሆን ዓላማው የሚያስከፍለውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ይሆናል፡፡

ነቢዩ መሐመድ(ሰዐወ) ከአላህ የደረሳቸውን መልእክት ለራሳቸው ብቻ አላስቀሩም፡፡ የተጠሩበትን ለሌሎች ለማካፈል ተግተዋል፡፡ መጀመሪያ በጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች፣ በኋላም ለቅርብ ሱሐባዎች፣ በመጨረሻም ለዓለም መልእክቱን አዳርሰዋል ፡፡ እሳቸው የዘሩት ዘር እያፈራና እየጎመራ ተጉዟል፡፡ ዓላማችንን እኛ ማወቃችንና ማመናችን ብቻ ጥቅም የለውም፡፡ ሌሎች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ልክ እንደነቢዩ ተገትተን መድከም አለብን፡፡

የነቢዩን መውሊድ ስናከብር ከሕይወታቸው እየተማርን፤ የተማርነውንም ለሀገረ መንግሥት ግንባታችን እየተጠቀምን እንዲሆን አደራ እላለሁ፡፡

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


woreda 07_prosperity

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።  እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም  ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የ...
24/08/2026

ዛሬ የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስን መርቀን ሥራ አስጀምረናል።

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
ከተማችን አዲስ አበባ የጤና ቱሪዝም ማዕከል እናደርጋታለን ስንል በመንግስት ብቻ የምናሳካው ሳይሆን በግሉ ዘርፍ የሚገነቡትንም ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ፣ ዛሬ ያስመረቅነው የኒው ሊፍ ሜዲካል ሆስፒታልም የዚህ አንዱ ማሳያ ነው ።

ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ በሃገራችን ከላፍቶ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀጥሎ ሁለተኛው PET-CT SCAN CAT LAB እና ሌሎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ትልቅ የጤና ማዕከል ነው። በጤናው ዘርፍ የምናደርገው ኢንቨስትመንት ክፍያው ከሁሉ የላቀ ስለሆነ እንደዚህ አይነት በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ የጤና ተቋማት እና ሆስፒታሎች ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

የኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ መስራችና ስራአስኪያጅ ዶ/ር ኢማን አብዱልራህማን እና ባለቤታቸው አቡበከር መሃመድ ሳላህን በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም በጣም እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Har'a Kompileeksii Meedikaalaa Niiw Liif eebbisnee hojii jalqabsiisneerra.

Baga gammaddan! Baga gammanne!

Magaalaa keenya Finfinnee giddugala turizimii fayyaa taasifna yoo jennu waan mootummaadhaan qofa milkeessinu osoo hin taane, dameen dhuunfaa kan itti ijaaraman yaada keessa galchuudhaan waan ta'eef, Hospitaalli Meedikaalaa Niiw Liif har'a eebbisiisnes isa kanaaf agarsiistuu tokkodha.

Kompileeksiin Meedikaalaa Niiw Liif biyya keenya Hospitaala Ispeshaalaayizdii Laftootti aanuudhaan lammaffaa kan ta'e PET-CT SCAN, CAT LAB fi teeknooloojiiwwan ammayyaa biroo kan guuttameef giddugala fayyaa guddaadha. Investimantiin damee fayyaan taasifnu kaffaltiin isaa hundumaa caalaa waan ta'eef, dhaabbilee fayyaa fi Hospitaalota damee akkasiin hojjataniif deeggarsa keenya cimsinee itti fufna.

Hundessituu fi Hoji gaggeessituu olaanaa Kompileeksii Meedikaalaa Niiw Liif kan ta'an Dr. Imaan Abdulrahimaan fi abbaa warraa isaanii Abuubakar Mahaammad Saalaahiin maqaa koo fi maqaa bulchiinsa magaalichaan baay'ee galateeffanna.

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!
AA.Prosperity
Kolfe.prosperity
Kolfe.woreda 07 prosperity

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የሰራነዉ ልማት በተጨባጭ አዳዲስ የአኗኗር ባህል እየገነባ  ማህበራዊ መስተጋብሩን ይበልጥ እያጠናከረ ነዉ።በዉቧ ካዛንችስ የገንባነዉ ስፖርት ፓርክ  ለከተማ...
23/08/2026

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የሰራነዉ ልማት በተጨባጭ አዳዲስ የአኗኗር ባህል እየገነባ ማህበራዊ መስተጋብሩን ይበልጥ እያጠናከረ ነዉ።

በዉቧ ካዛንችስ የገንባነዉ ስፖርት ፓርክ ለከተማችን ነዋሪዎች የጤንነት መጠበቂያ ፣ የአካልና አእምሮ ማጐልበቻ ፣ የህፃናት መቦረቂያ፣ የብሄራዊ ጀግኖች አትሌቶቻችን ዉለታ መታሰቢያ አከታች ልማት በመሆኑ ለሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጠ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Misoomni nuti fayyadamummaa jiraattota Finfinneetiif hojjanne qabatamaan aadaa jireenyaa haaraa ijaaraa hariiroo hawaasummaa caalmaatti cimsaa jira.

Paarkiin Ispoortii Kaazaanchiis miidhagduutti ijaarrre jiraattota magaalaa keenyaaf eegumsa fayyaa, gabbisa qaamaa fi sammuu, bohaartii daa'immanii fi oolmaa yaadannoo gootota atileetota keenya biyyaalessaa misooma of keessa qabu ta'uu isaatiin kutaa hawaasaa hundumaaf tajaajila kennaa jira.

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!
woreda 7 prosperity party

21/08/2026

@

ማህበራዊ ስብራቶቻችንን በመጠገን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!አካታቹ የብልፅግና የልማት ፖሊሲ በተግባር እየተተረጎመ በመሆኑ የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጎልብቷል፡፡  ሁለንተናዊ ብልፅግ...
19/08/2026

ማህበራዊ ስብራቶቻችንን በመጠገን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን!

አካታቹ የብልፅግና የልማት ፖሊሲ በተግባር እየተተረጎመ በመሆኑ የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጎልብቷል፡፡ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞአችን የሁሉንም ዜጋ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

የፓርቲያችን ሰው ተኮር እሳቤዎች ሁሉም ዜጋ እኩል ተሳታፊና ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆን አስችለዋል።

ባዶ የምሳ እቃ በመያዝ ምሳቸውን ሳይመገቡ የሚውሉ በርካታ ተማሪዎች የነበሩባት አዲስ አበባ በጀመረችው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ፍትሀዊ የትምህርት ተደራሽነትን አሳድጋለች፡፡

በተለይም የአቅመ ደካማ ወላጆችን ሸክም በእጅጉ ማቃለል ያስቻለው ይህ ፕሮግራም ከትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ባሻገር የኑሮ ውድነቱን ጫናም እያቃለለ ነው፡፡

በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች የከተማችንን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ችግሮች ከመቅረፍ አንፃር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ጧሪ የሌላቸውን፣ የሀገር ባለውለታዎችንና አቅመ ደካሞችን ፍትሀዊ ተጠቃሚ ለማድረግም ባለሀብቶችን እና የከተማችንን ነዋሪዎች በማስተባበር የከተማ አስተዳደሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በመገንባት የብዙዎችን እምባ አብሷል፡፡ በከተማችን እየተበራከቱ የሚገኙት የበጎነት መንደሮች የከተማችንን የለውጥ ግስጋሴም አፋጥነዋል፡፡

የምግብ ሉዓላዊነትን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብርቱ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን፤ ቢያንስ በቀን አንዴ መመገብ የማይችሉ ዜጎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በአቅራቢያቸው የምገባ ማዕከላት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚያሻሽሉ ሰው ተኮር ልማቶችን በማጠናከር ፣ ማህበራዊ ስብራቶችን በመጠገን፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጣችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡



11/08/2026
በሁላችንም የሀሳብ እና የተግባር አሻራ ኢትዮጵያ ወደ ላቀ ከፍታ ትሸጋገራለች!ኢትዮጵያ የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር ብዙዎች ሲመኙት የኖረ፣ ግን ደግሞ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ያልተተገበረ፣...
10/08/2026

በሁላችንም የሀሳብ እና የተግባር አሻራ ኢትዮጵያ ወደ ላቀ ከፍታ ትሸጋገራለች!

ኢትዮጵያ የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር ብዙዎች ሲመኙት የኖረ፣ ግን ደግሞ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ያልተተገበረ፣ ኢትዮጵያ ካሁን በፊት ያልሞከረችው አዲስ መንገድ ነው፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ የመደመር ትውልድ ተሻጋሪ ቅርስ ነው፡፡ ዘመን የሚታወስበት፣ ትውልድ የሚወደስበት፣ ታሪክ የሚዘከርበት ይህ መልካም ዕድል ድንገት የተገኘ አጋጣሚ አይደለም፡፡

በሆደ ሰፊነት ታላላቅ ችግሮችን በመሻገር፣ መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር እውን የሆነው ሀገራዊ ምክክሩ የእኛ ትውልድ ከሚጠራባቸው አስደማሚ ድሎች መካከል በግንባር ቀደምትነት እንደሚጠቀስ በልበ ሙሉነት መግለፅ ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያ የውስጥ ብዝሀ አንድነቷን ካፀናች ከሚመጥናት ከፍታ ላይ እንደምትደርስ ጠንቅቀው የተረዱ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሁሉ ኢትዮጵያውያን የሚጠፋፉበትን ጠብመንጃ ለማቀበል ባለ በሌለ አቅማቸው ሲፍጨረጨሩ ይስተዋላል፡፡

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የከፍታ ጉዞ ካረጋገጠች የማትደፈር ብቻ ሳትሆን የምትፈራ እና የምትከበር ታላቅ ሀገር እንደምትሆን በመረዳት ታሪካዊ ጠላቶቿ እንዲሁም የውስጥ ባንዳዎች ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞዋን ለማደናቀፍ ለእኩይ ዓላማቸው ይደክማሉ፡፡

ከየአቅጣጫው የሚወረወሩ ጠጠሮችን ጭምር ለሀገር ግንባታዋ በማዋል ኢትዮጵያ ለእኩይ ሀይሎች ጆሮ ሳትሰጥ ውስጧን እያዳመጠች ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያውያን በመደማመጥ እና በመግባባት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማረጋገጥ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ፍላጎታቸው ሰላም ነው፣ ፍላጎታቸው አብሮ ማደግ ነው፤ ከዚህ የሚፃረር አፍራሽ እንቅስቃሴ በህዝባችን ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ህዝባችን በምርጫ ብቻ በማለት ከሌሊት እስከ ሌሊት ድምፁን በመስጠት 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ስኬታማ አድርጓል፡፡

ለሀገራዊ ምክክሩም ቢሆን ህዝባችን ታሪካዊ አሻራውን አሳርፏል፡፡ ይህ ታላቅ ሀገራዊ የውይይት ማዕድ አሁን ከሚገኝበት ደረጃ የደረሰው ውስን አባላት ባሉት በብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ብቻ እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ ኮሚሽኑ የማስተባበር ሚናውን በአግባቡ በመወጣት እየፃፈ የሚገኘው ደማቅ ታሪክ ለሁሉም ግልፅ ቢሆንም ያስመዘገባቸው ስኬቶች ሁሉ በህዝባችን ያልተቋረጠ ድጋፍ ነው እውን መሆን የቻሉት፡፡

የህዝባችን ችግሮች እና ጥያቄዎች ለማሰባሰብ ባለፉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑ ከጫፍ እስከ ጫፍ በመዞር ባካሄዳቸው አድካሚ ጉዞዎች ሁሉ ህዝባችን ከጎኑ በመቆም ያልተቋረጠ ድጋፉን አድርጓል፡፡


ፅንፍ እና ፅንፍ በቆሙ የጥፋት ሀይሎች የሚደርስበትን ዛቻና ማስፈራሪያ ጆሮ ሳይሰጥ፣ የኮሚሽኑ ዕቅድ እንዲሳካ ብርቱ ጥረት ሲያደርግ የቆየው ህዝባችን ለውይይት ባህል መገንባት ቁርጠኛ አቋሙን አፅንቷል፡፡

ከሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በመሰባሰብ በመዲናችን አዲስ አበባ እየመከሩ የሚገኙት 4 ሺህ አካባቢ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎችም ህዝባችን የጣለባቸውን ታሪካዊ አደራ ለመወጣት በሀላፊነት ስሜት እየመከሩ ይገኛሉ፡፡

የሀገራችንን የመገዳደል እና የመጠፋፋት ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል በሰለጠነ የውይይት ባህል የተካው ሀገራዊ ምክክሩ ለዴሞክራሲያዊ ባህል ግንባታችንም ላቅ ያለ አበርክቶ ይኖረዋል።
መልካም የስራ ሳምንት!



08/08/2026
በወረዳዉ አስተዳደር የሚገኙት የእሁድ ገበያ ተጠናክሮ ቀጥሏል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል እና የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት በቤተል ሆስፒታል ጀ...
08/08/2026

በወረዳዉ አስተዳደር የሚገኙት የእሁድ ገበያ ተጠናክሮ ቀጥሏል

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል እና የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት በቤተል ሆስፒታል ጀርባ እና አንፎ 75 በሚገኙት የእሁድ ገበያ ማዕከላት ከዋናው ገበያ በተሻለ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ሸማቹ ማህበረሰብም ከእሁድ ገበያዎቹ እየተገበያየ እና እየሸመተ ይገኛል፡፡



Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity Party Kolfe Woreda 07 Branch - ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Prosperity Party Kolfe Woreda 07 Branch - ብልፅግና:

Shortcuts

Share