Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency Serving reliable cadastral services and information

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

ራዕይ

በ2022 በከተማችን የህጋዊ ካዳስተርና አድራሻ ሥርዓት እውን ሆኖ ማየት፣

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ውስጥ የሚገኙ የመሬት ይዞታዎችን በሙሉ በማረጋገጥና በመመዝገብ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በመታገዝ ህጋዊ ካዳስተር፣ የአድራሻና የተቀናጀ የመሬትና መሬት ነክ መረጃ ሥርዓት መገንባት፣

ዕሴቶች

 አገልጋይነት
 ታማኝነት
 ተጠያቂነት
 በዕውቀት መምራት
 ግልጽነትና አሳታፊነት
 የለውጥ ባለቤት መሆን
 የቡድን ሥራ ለስኬታማነት

03/08/2026
የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ----------------------------ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም(የመ/ይ/ም/መ...
03/08/2026

የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ
----------------------------
ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
(የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHRIA
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ማካፈያ በመገኘት የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በዚሁ ህዝባዊና ሀገራዊ መርሃ-ግብር ላይ የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞችን ጨምሮ የወረዳው አስተዳደር አካላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች በነቃ ሁኔታ ተሳትፈዋል።

በዕለቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጥላሁን ለአካባቢው ማህበረሰብና ለሰራተኞች ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ይህን ታላቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ስንፈጽም የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁና ለፍሬ እንዲበቁ ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አክለውም አቶ ተስፋዬ እንደገለፁት፦ "ተቋማችን የተቀበለውን ሀገራዊ ተልዕኮ እንደ ችግኞቹ እንክብካቤ ሁሉ መደበኛ የመንግስት ስራችንንም በተመሳሳይ የላቀ ኃላፊነትና ትጋት ልንሰራ ይገባል ብለዋል። ተገልጋዩን ማህበረሰብ በቅንነት፣ በታማኝነት እና በቅልጥፍና ማገልገል የሁላችንም የወቅቱ ዋነኛ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል።

መርሃ-ግብሩ የተቋሙን ሰራተኞችና አመራሮች አንድነት ያጠናከረ ከመሆኑም ባሻገር፤ ለአካባቢ ጥበቃና ለከተማዋ አረንጓዴ ልማት አስተዋጽኦ ያበረከተ ስኬታማ ሁነት ሆኖ ተጠናቋል።

ተስፋን እንትከል!
የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር 2018

ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉Website; https://addiscadaster.gov.et/
👉Facebook; Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information
👉TikTok; A.Acadaster2016
👉Telegram; https://t.me/lhria
👉you tube; Legal cadaster
👉Customer Call Center: 6577

በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሚመዘገብ የመሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነት------------------------------1/ በመሬት ይዞታ የመጠቀም መብት በሚሰጥበት ወቅት...
29/07/2026

በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሚመዘገብ የመሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነት
------------------------------
1/ በመሬት ይዞታ የመጠቀም መብት በሚሰጥበት ወቅት አግባብ ካለው የመንግሥት አካል
ጋር በነባር፣ በሊዝ፣ በአርሶ አድር ይዞታ እና በንኡስ ሊዝ የመሬት ይዞታዎች ላይ በተገባ የውል ሰነድና በመብት ሰጭ ተቋም በተሰጠ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱ መብቶች፣ ክልከላዎችና ኃላፊነቶች ይመዘገባሉ፤

2/ አዋጅ ቁጥር 1381/2017 አዋጅ፣ አዋጁን ተከትሎ በሚወጣ ደንብና መመሪያ በሚፈቀደው መሠረት በሙሉም ሆነ በከፊል በሽያጭ፣ በስጦታ፣ በውርስ፣ በድርሻ መልቀቅ፣ በዓይነት መዋጮ ወይም በሌላ ሕጋዊ መንገድ የተገኘ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት ይመዘገባል፤

3/ የተዘረዘሩትን መብቶች፣ ክልከላዎች እና ኃላፊነቶች ለማስቀረት፣ ለመቀነስ፣ ለመጨመር፣ ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የሚሰጡ ውሳኔዎች ወይም ትዕዛዞች ወይም ውሎች ይመዘገባሉ፤

4/ መንግስት በሚወስነው መሠረት የመሬት ይዞታ መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነት በንኡስ-ሊዝ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል ይመዘገባል፤

5/ ከመሬት ይዞታው ጋር የተያያዘ ማንኛውም የመያዣ ውል እና በህግ አግባብ ስልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ወይም የፋይናንስ ተቋም አማካኝነት የተሰጠ ዕግድ ትእዛዝ በመዝጋቢው ተቋም ዘንድ መመዝገብ አለበት፤

6/ በመሬት አስተዳደር አገልግሎት ሥርዓት መሠረት የተፈቀዱ መብቶች፣ ክልከላዎችና ኃላፊነቶች በዚህ አዋጅና ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት ይመዘገባሉ፤

7/ የምዝገባው ውጤት በሰነድ የተገኘው የይዞታ ስፋት በልኬት ከተገኘው ጋር ሲነፃፀር ክልሎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች በሚያወጡት መመሪያ መሰረት በማቻቻያ መጠን ውስጥ ከሆነ በልኬት የተገኘው የይዞታ ስፋት ሰርተፊኬት ላይ በማስፈር መሆን አለበት፡፡

ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
(የመ/ይ/ም/መ/ኤ) AA-LHRIA
አዲስ አበባ

ምንጭ፡- የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1381/2017
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇
👉Website; https://addiscadaster.gov.et/
👉Facebook; Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information
👉TikTok; A.Acadaster2016
👉Telegram; https://t.me/lhria
👉you tube; Legal cadaster
👉Customer Call Center: 6577

26/07/2026
25/07/2026
25/07/2026

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሐምሌ 18፣ 2018 ዓ.ም

Address

604 Equatorial Guiene Avenue
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251911409817

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency:

Shortcuts

Share