20/02/2025
የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ቢሮውን ለአገልግሎት ምቹ በማድረግና በማዘመን በዛሬው ዕለት ሥራችን በራዕያችን ይመራል በሚል መሪ ቃል ስማርት ፅ/ቤት አስመርቋል::
የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የካ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ቢሮውን ለአገልግሎት ምቹ በማድረግና በማዘመን በዛሬው ዕለት የማስመረቂያ መርኃ-ግብር አካሂዷል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የየካ ክ/ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ፤ የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምስጋነው ህንጂሉ ፣ የም/ቤት መሬት ግንባታ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የወረዳው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ላለፉት 3 ዓመታት በወረዳም ሆነ በክ/ከተማ ስኬታማ የስራ ጊዜዎችን በማሳለፍ ከ 4 ዋንጫዎች በላይ በማምጣት እንዲሁም ሞዴል የነበረውን ቢሮ በቴክኖሎጂ የማዘመን፣ ውብ፣ ማራኪ እና አረንጓዴ በማድረግ እና በቁጥር 12 የሚሆኑ ተሞከሮዎች በመፍጠር ቢሮውን ወደ ስማርት ጽ/ቤት የተሸጋገረበትን ቀን ማስመረቅ ችሏል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የየካ ክ/ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ ተቋሙን ስማርት በማድረግ የተሰራው ስራ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ በ2022 ዓ.ም እንደ ተቋም የተያዘውን ውብ፣ማራኪና አረንጓዴ ስማርት ተቋም እና ከተማን የመፍጠር ራዕይን ቀድሞ ያሳከ ብቻኛ እና ድንቅ ጽ/ቤት መሆኑን የክ/ከተማ እና ወረዳ ተቋማት ልምድ እንዲወስዱ እንደሚደረግ በመግለጽ የከተማ አስተዳደሩ በወረዳው የተሰራውን ስራ ለሌሎች ክ/ከተማ እና ወረዳዎች የማስፋፋት ስራ እንዲሰራ እንደሚደረግ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም በቢሮ ማዘመን ስራ አስተዋጽኦ ላደረጉ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት እና በ2017 በጀት ዓመት የመጀመረያ 6ወር ጥሩ የስራ አፈፃፀም የነበራቸው ባለሞያዎች የእውቅና ሽልማትና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ። የፅ/ቤቱ ሀላፊዎች የሽኝትና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃግብር ተካሂዷል ።