Bole 12 trade office

Bole 12 trade office Office

Boolee Aanaa 12
29/09/2023

Boolee Aanaa 12

የክፍለ ከተማ ንግድ ፅ/ቤት ኢሬቻን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በመግቢያ በሮች ላይ ተገቢውን አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀቱን አሳወቀ፡፡
=====================
አዲስ አበባ፣ መስከርም 18 ቀን 2016ዓም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ፅ/ቤት መስከርም 26 እና 27 ኢሬቻ በዓልን ለማክበር በክፍለ ከተማው መግቢያ በሮች ወደ አዲስ አበባ ለሚመጡ እንግዶች ተገቢውን አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀቱን አሳወቀ፡፡
በክፍለ ከተማው የንግድ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዷለም ክብረት ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለፁት ክፍለ ከተማው በቡራዩና በሱሉልታ አቅጣቻዎች ለሚገቡ እንግዶች ቆሎ፣ ዳቦና ውሃ በማቅረብ ለማስተናገድ እየተዘጋጀ መሆኑን አስረድተውናል፡፡
አክለውም ፅ/ቤታቸው በአዲስ አበባ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን በጠበቀ ደረጃ በሰላም እንዲከበር ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከወጣቶችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መድረክ ለማዘጋጀት አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ነግረውናል፡፡
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ መከበሩ በተለይ ለንግድና ግብይት እንቅስቃሴው መነቃቃት የሚፈጥር ነው ያሉት አቶ አንዷለም የንግዱ ማህበረሰብም ይህንን በመረዳት አጋጣሚውን በኢትዮጲያዊ ጨዋነት እና በመተሳሰብ ማክበር እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡

Keessummoota Irreecha kabajuuf dhufaniif karra seensaa irratti simannaa sirrii qopheessuusaa Waajjirri daldala aanaa gulaalee beeksise.
================================
Finfinnee, Fulbaana 18, 2016

Bulchiinsa magaalaa Finfinneetti waajjirri daldala aanaa Guleelee keessummoota gara Finfinnee dhufan karra seensa magaalaa guddichaatti simachuun Ayyaana Irreechaa 26 fi 27 kabajuuf qophaa'uu beeksise.

Gaaffii fi deebii kutaa qophii keenya waliin taasisaniin itti gaafatamaan waajjira daldalaa Aanaa gulaalee obbo Andualem kibireti akka ibsanitti, magaalattiin keessummoota Buraayyuu fi Sulultaa irraa dhufaniif daabboo, akkayii fi bishaan dhiyeessuun daawwattoota keessummeessuuf qophaa’aa jiraachuu ibsaniiru.

Ayyaanni Irreecha Finfinneeti kabajamu haala qabiyyee aadaa isaatiin nagaan akka kabajamuuf waajjirri isaanii hawaasa, daldalaa, dargaggootaa fi qooda fudhattoota dhimmi ilaallatu waliin waltajjii marii qopheessuuf karoorfachuu isaa nuuf ibsaniiru.

Obbo Andualem akka jedhanitti, Ayyaanni Irreechaa magaalaa Finfinneeti kabajamu keessumaa hojii daldalaa fi gabaaf kaka’umsa kan qabu ta’uu ibsaniiru.

02/02/2023

የነጋዴ ግዴታዎች

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 5 እንደተገለጸው የሙያ ሥራቸው አድርገው ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ስራዎች ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ሥራዎችን የሚሠሩ ሰዎች ነጋዴዎች ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት እነዚህ አካላት ምን ግዴታ እንደሚኖርባቸው ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተከታዩን ጽሁፍ አዘጋጅተናል፡፡

መልካም ንባብ

ማንኛውም ነጋዴ የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ከማቅረቡ በፊት ግዴታውንና መብቱን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል፡፡

አንድ ነጋዴ መብቱንና ግዴታውን በማወቅ ባግባቡ ስራውን ካልፈፀመ የህግ ተጠያቂነትን ሊያስከትልበት ይችላል፡፡

በመሆኑም የነጋዴ ግዴታን በተመለከተ በአዋጁ ላይ በርካታ አንቀፆች ተደንግገዋል፡፡ በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ከአንቀፅ 15 ጀምሮ የነጋዴ ግዴታዎች በሚመለከት በሰፊው ተዘርዝሯል፡፡

7.1 መግለጫ የመለጠፍ ግዴታ

ይህ ግዴታ ነጋዴው የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን የዋጋ ዝርዝር በንግድ ቤቱ በግልፅ ወይም በሚታይ ቦታ ማመልከት ወይም በንግድ ዕቃዎች ላይ መለጠፍ እንዳለበት በአንቀፅ 15 (1) ላይ ይደነግጋል፡፡የዕቃዎች ወይም የአገልግሎቶች ዋጋ ህጋዊ ክፍያዎችን ያካተተ መሆን እንዳለበትም ተግልጿል፡፡ ይህ መግለጫ መለጠፍ ወይም ደግሞ በተለየ ወረቀት ተፅፎ ለሸማቹ መስጠት እንዳለበት ይናገራል (አንቀፅ 16 (1) ፡፡ መግለጫውም እንደአግባብነቱ የሚከተሉትን ዝርዝር ነገሮችን አካቶ መያዝ ይኖርበታል፡፡ እነርሱም፡-

የንግድ ዕቃውን ስም፣ ዕቃው የመጣበትን ወይም የተሰራበትን ሃገር፣ የዕቃው ክብደት፣ መጠንና በብዛት፣ የዕቃው ጥራት፣ ዕቃዉ ከምን እንደተሰራ የሚገልፅ ዝርዝር፣ የዕቃውን የአጠቃቀም ሁኔታ፣በአወሳሰዱ ላይ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፣ ነጋዴው ለዕቃዉ የሚሰጠው ዋስትና፣ የአስመጪው ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የአምራቹንና የአሻጊውን አድራሻ፣ የዕቃዉ የአገልግሎት ዘመኑ የሚያበቃበት ጊዜ /expired date/ የተመረተው ዕቃ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ድርጅት የተረጋገጠ መሆኑና እንደአስፈላጊነቱ ሚኒስቴሩ በህዝብ ማስታወቂያ የሚያወጣቸውን ሌሎች ዝርዝር ነገሮችን ያካትታል፡፡

7.2 ራስን የመግለፅ ግዴታ

ራስን መግለፅ ሲባል አንድ ነጋዴ የንግድ ስሙን በግልፅ በሚታይበት ቦታ መለጠፍ ወይም ማመልከት ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ነጋዴ የንግድ ስሙን (trade name) ግልፅና በሚታይ ቦታ መለጠፍ አለበት፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ነጋዴው ከሚሸጠው የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት አንፃር ሸማቹ በሚያቀርብለት ጥያቄ መሰረት ራሱን መግለፅና ሸማቹ የሚፈልገውን መረጃ እንዲወስድ የመፍቀድ ግዴታ አለበት አንቀፅ 18 (1) እና (2) ይመልከቱ፡፡

7.3 ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ

በአዋጁ ላይ ከተቀመጡት ግዴታዎች አንዱ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ሲሆን ይህ ግዴታ ነጋዴው ለሸጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ነጋዴው ለሸማቹ (consumer) የሚሰጠውን ደረሰኝ ይመለከታል፡፡ ይህም አሰራር ነጋዴው ለመንግስት በአግባቡ ግብር መክፈሉን ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 በአንቀፅ 17 (1) እና (2) ነጋዴው ለሸጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ወዲያውኑ ለሸማቹ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት መሆኑንና የሰጣቸውን ደረሰኝ ቀሪዎችን ለአስር ዓመታት ያህል ይዞ ማቆየት እንዳለበት ጭምር ይገልፃል፡፡ ይህ ብቻ ሣይሆን ሸማቹ ደረሰኝ መያዙ ዕቃውን ከማንና መቼ እንደገዛ በግልጽ የሚያስረዳ ሲሆን ነጋዴው አልሸጥኩም ብሎ ቢክድ እንኳን እንደ ማስረጃ ሊቀርብ እና በህግ ፊትም ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

7.4 አሳሳችና ሀሰተኛ ያልሆኑ ማስታዎቂያዎችን የማስተካከልና የማረም ግዴታ

በነጋዴው የሚወጡ የንግድ ማስታወቂያዎች ግልፅ የማያሻማና በቀላሉ መረዳት የሚያስችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የሚወጣውም ማስታወቂያም የዕቃዉን ባህሪይ፣ ከምን እንደተሰራና ብዛቱን የሚገልፅ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተመረተበትን ቀን፣ አግልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን፣ የአጠቃቀም መመሪያዎችንና የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን አቅራቢ ያካተተ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡

ማስታወቂያው የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ የግዢ ሁኔታና ከግዢ በኋላ ስለሚሰጠው አገልግሎት፣ ዋስትና፣ ዋጋና የክፍያ ሁኔታ፣ የጥራት ምልክቶች፣ የንግድ ምልክቶችንና አርማን እንዲሁም ዕቃዉን ወይም አገልግሎቱን በመጠቀም የሚጠበቅ ውጤት ጭምር እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡

12/11/2022

የተቋምን ስራ ለማስተዋቅና ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ጠንካራ የኮሙኑኬሽን ስርዓት ያስፈልጋል
===========================================

አዲስ አበባ 3/3/2015(ንቀትሚ) የእንድን ተቋም ስራ ስኬታማ ለማድረግ፣ ለማስተዋወቅና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት ያስፈልጋል፡፡

የእንድን ተቋም ስራ ለማሳለጥ ከምንም በላይ ወጥ የሆነ የመረጃ ፍሰት መኖር እንዳለበትና ለዚህም ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የጥራት መሰረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ገልጸዋል፡፡

ሚኒቴር መ/ቤቱ የተሰጡትን በርካታ ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው ኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤቱ የሰራቸውን እና የሚሰራቸውን ስራዎች በማስተዋወቅ እና በህዝብና በመንግስት በኩል እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም በቀጣይ ወጥ የሆነ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ሚኒስቴር መ/ቤቱ አበክሮ አንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

ለሚኒቴር መ/ቤቱ አመራሮች፣ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች በተቋማዊ የመረጃ ልውውጥና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨባጫ መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

14/10/2022

የንግድ አሰራርን ስርዓት ለማስያዝና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ንግድ ቢሮ አስታወቀ!!

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የ2015 በጀት ዓመት የሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደተገለጸው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል፤እየተያ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመግታት በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ከቢሮው ጋር በላቀ ተነሳሽነት እየሰሩ መሆኑም ተጠቅሶዋል ፡፡
አቶ ፋንታሁን እያዩ የንግድ ቢሮ እቅድና በጀት ዳይሬክተር የሩብ ዓመቱን የአፈጻጸም ሪፖርተ ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ቢሮው ባለፉት ሶስት ወራት በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግልት፤በንግድ ቁጥጥርና ክትትል፤በገበያ መሰረተ-ልማት ግንባታ እንጻርና የንግድ አሰራርን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ለማቆራኘት የታዩ አበረታች ጥረቶች፤እንዲሁም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደገ በመጣው የሰንበት ገበያ የታዩ አበረታች ለውጦችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም የተገኙ አበረታች ለውጦች ማጠናከር እንደሚነባ ባቀረቡት ሪፖርት ዳሶዋል፡፡
ወ/ት ቅድስት ስጦታው የንግድ ቢሮ ም/ሃላፊ በበኩላቸው እንዳሉት በላፈው ሩብ ዓመት አፈጻጸም የተገኙ አበረታች ለውጦችን በላቀ አገልግሎት አሰጣጥ መጠናከር እንዳለባቸው ጠቅሰው፤የንግድ አሰራርን ስርዓት ለማስያዝ እየተደረገ ያለው ቁጥጥርና ክትትል ተግባር ከመቼውም ጊዜ መጠናከር እንዳለበት፤የሰንበት ገበያ ምርት አቅርቦትና ስርጭት ከፍ በማድረግ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት በቅንጅት ፈር ማስያዝ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
ሰረተኞችም በቀረበው የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የተለያዩ ሃሳቦችን የሰጡ ሲሆን በላቀ አገልግሎት አሰጣጥ የንግዱን ማህበረሰብ ለማገልገልም ቃል በመግባት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

14/10/2022

የኦን-ላይን ምዝገባና ፍቃድ አሰጣጥን ለማሳለጥ የቴሌ ብር መተግበሪያ ስርዓት ተግባራዊ ተደረገ፡፡
===============================

አዲስ አበባ 4/2/2015 (ንቀትሚ)መንግስት የንግድ ስርዓቱን በማዘመን በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ተግባራት መካከል የኦንላይን ምዝገባና ፍቃድ አሰጣጥ አንዱ መሆኑን የሚናገሩት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የላይሰንሲንግ እና ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ናቸው፡፡

ይህ ስርዓት በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝና በዚሁም ካሁን ቀደም በተገልጋዮች ዘንድ ሲስተዋሉ ለነበሩ እንግልቶች እና አላስፈላጊ ወጪዎች ሁነኛ መፍትሄ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ይህንኑ አሰራር ይበልጥ ዘመናዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ካሁን ቀደም ከነበረው የንግድ ባንክ የክፍያ ስርዓት በተጨማሪ የቴሌ ብር መተግበሪያ ስርዓት ተግባራዊ እንዲሆን በሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ስርዓቱ ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም መሪ ስራ አስፋጻሚው አስረድተዋል፡፡

ዘርፍን በይበልጥ ለማዘመን ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የሚናገሩት ዋና መሪ ስራ አስፈጻሚው ከቴሌ ብር መተግበሪያ በተጓዳኝ የጥሪ ማዕከል ለማደራጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ እና አሁን በቅርቡም ወደ ትግበራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡

ይህ አሰራር በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ እና በስርዓቱ ትግበራ የአማራ ክልል የተሻለ አፈጻጸም እንዳለው የተናገሩት አቶ ጅራታ በቀጣይም ይህንን አሰራር በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎች በማውረድ ካሁን ቀደም ሲሰራበት የነበረውን አሰራር ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ዕቅድ መያዙንም ጠቅሰዋል፡፡

አሁን በዘመነ ሉላዊነት ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ወቅት ከምንም በላይ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት መስጠት ተገቢ መሆኑን እና ለዚህ ስርዓት ተግባራዊነት ሁሉም የንግዱ ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

08/10/2022

በመንግስት ተቋማት የሰራተኞች ቅጥርና እድገት በእውቀት፣ በክህሎት እና በአስተሳሰብ ብቃት ላይ እንዲመሰረት የማስቻል ስርዓት መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
================================
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 26/2015ዓ.ም
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚካሄድ የሰራተኞች ቅጥርና ዕድገት አሰራር ስርዓት በዋናነት እውቀት (Knowledge) ፣ ክህሎት (Skill ) የአስተሳሰብ ደረጃ (Emotional intelligence) ብቃቶች ላይ ተመስርቶ ሊተገበር እንደሚገባ ገለፀ፡፡
የኮምሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በቢሮው ተገኝተው እንደ ሀገር በቀጣይ የሚካሄዱ የሰራተኞች የቅጥርና የዕድገት ስርዓት የማስተግበሪያ የጥናት ሰነድ ላይ ገልፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በገለፃውም በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ተግባሪያዊ ሆኖ የሚገኘው የቅጥርና የዕድገት ስርዓት ከዚህ በኃላ በዋናነት እውቀትን፣ ክህሎትንና አስተሳሰብን መሰረት ባደረገ የምዘና ስርዓት በብቃት ላይ ብቻ እንዲመሰረት የሚደረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አክለውም በመንግስት ተቋማት ከዝቅተኛ የስራ መደብ ደረጃዎች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የስራ መደቦች ድረስ ብቃት ላይ የተመሰረተ የቅጥርና የዕድገት ስርዓትን ተግባሪያዊ ማድረግ የመንግስት ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን በማስቻል የዜጎች እርካታ ለማሳደግ ወሳኝ ከመሆኑም በላይ እንደ ሀገርም ሆነ ከተማ የልማትና የዕድገት ግቦች ስኬታማ በሆነ ደረጃ ለመተግበርና ለማስተግበር የማይተካ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

በገለፃውም በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ተግባሪያዊ ሆኖ የሚገኘው የቅጥርና የዕድገት ስርዓት ከዚህ በኃላ በዋናነት እውቀትን፣ ክህሎትንና አስተሳሰብን መሰረት ባደረገ የምዘና ስርዓት በብቃት ላይ ብቻ እንዲመሰረት የሚደረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አክለውም በመንግስት ተቋማት ከዝቅተኛ የስራ መደብ ደረጃዎች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የስራ መደቦች ድረስ ብቃት ላይ የተመሰረተ የቅጥርና የዕድገት ስርዓትን ተግባሪያዊ ማድረግ

በመንግስት ተቋማት የሰራተኞች ቅጥርና እድገት በእውቀት፣ በክህሎት እና በአስተሳሰብ ብቃት ላይ እንዲመሰረት የማስቻል ስርዓት መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
============================================
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 26/2015ዓ.ም
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮምሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚካሄድ የሰራተኞች ቅጥርና ዕድገት አሰራር ስርዓት በዋናነት እውቀት (Knowledge) ፣ ክህሎት (Skill ) የአስተሳሰብ ደረጃ (Emotional intelligence) ብቃቶች ላይ ተመስርቶ ሊተገበር እንደሚገባ ገለፀ፡፡
የኮምሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በቢሮው ተገኝተው እንደ ሀገር በቀጣይ የሚካሄዱ የሰራተኞች የቅጥርና የዕድገት ስርዓት የማስተግበሪያ የጥናት ሰነድ ላይ ገልፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በገለፃውም በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ተግባሪያዊ ሆኖ የሚገኘው የቅጥርና የዕድገት ስርዓት ከዚህ በኃላ በዋናነት እውቀትን፣ ክህሎትንና አስተሳሰብን መሰረት ባደረገ የምዘና ስርዓት በብቃት ላይ ብቻ እንዲመሰረት የሚደረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አክለውም በመንግስት ተቋማት ከዝቅተኛ የስራ መደብ ደረጃዎች ጀምሮ እስ

09/07/2022
09/07/2022

ንግድ ቢሮ የንግድና ገበያ መረጃ ስርዓት ሲስተምን በኤልኢዲ አስክሪን ስራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡
ንግድ ቢሮ የንግዱንና ሸማቹን ማህበረሰብ በዘመናዊ የመረጃ ዘዴ በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ ይረዳው ዘንድ ግልጽና ተአማኒነት ያለው እለታዊ የገበያ መረጃ ለህዝቡ በየጊዜው ተደራሽ እንዲሆን፤ እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበረው የንግድና ገበያ መረጃ ስርዓት የራሱ የሆነ ክፍተቶች የነበረው ሲሆን በተለይ የሚዘጋጀው የገበያ መረጃ ሪፖርት በወረቀት በመሆኑ፣ ከዝግጅት እስከሚፈለግበት ቦታ ድረስ አድካሚ፣ ወጪ የሚጠይቅ፣ ጊዜ የሚወስድ፣ ታዓማኒነት የጎደለው፣ በተፈለገው መጠን፣ ጊዜና ጥራት የማይደርስ በመሆኑ፣ ይህን አዲስ የእለት ገበያ መረጃ ስርዓት በኤልኢዲ አስክሪን በአራዳ ክፍለ ከተማ ጊዮሪጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት፤በየካ ፤በአቃቂና ኮልፌ ክፍለከተሞች ስራ ላይ ለማዋል መገደዱን የቢሮው የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ገልጾዋል፡፡
አቶ ገመቺስ መንግስቱ የንግድ ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዛሬው እለት ለኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በሰጡት ማብራሪያ ከዚህ በፊት የነበረው የመረጃ ስርዓት መረጃውን የሚፈልጉ ተቋማት በቀላሉ ሊያገኙ የማይችሉበት እና ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ያልነበረ በመሆኑ የእለት የገበያ ዋጋ መረጃ ምን እንደሚመስል ለማወቅ የሚችልበት ሁኔታ የራሱ ውስንነት የነበረው መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ ተጠቃሚው ህብረተሰብ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የፋብሪካ ምርቶችን የገበያ ዋጋ መረጃን ካለማግኘት የተነሳ የሚፈለጉትን ምርት የት ማግኘት እንደሚችሉና በዋጋ አማርጦ ለመሸመት ይቸገር እንደነበረ ገልጸው፤እነዚህን ክፍተቶች ለሟሟላት ቢሮው ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ዘመናዊ የንግድና የእለት ገበያ መረጃ ስርዓት ሲስተምን በኤልኢዲ አስክሪን በአራት ክፍለከተሞች ስራ ላይ ማዋሉን፤ ወደፊት ደግሞ በቀሩት ክፍለ ከተሞች ተደራሽ እንደሚደረግ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ንግድ ቢሮ የንግድ ቁጥጥርና ክትትል ስርዓትን በዘመናዊ ሲስተም ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም መደበኛ ያልሆነ የንግድ ስርዓት ለማስያዝ የሚያስችሉ ዘመናዊ ሲሲተሞችን በቅርቡ ስራ ላይ እንደሚያውል ከአቶ ገመቺስ መንግስቱ ገለጻ ለማወቅ ተችሎዋል፡፡

09/07/2022

የሲሚንቶ ግብይትና ሥርጭት መመሪያን በሚጥሱ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል
=================================
አዲስ አበባ ሐምሌ 01/2014 (ንቀትሚ) የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎት ባለመመጣጠኑ ምክንያት ዋጋው እየናረ ሥርጭቱም ባልተገባ መንገድ እየተከወነ የግንባታውን ዘርፍ ሲፈትነው ቆይቷል፡፡ የፋብሪካዎች ከአቅም በታች ማምረት፣ የግንባታው ዘርፍ ማደጉን ተከትሎ የሲሚንቶ ፍላጎት መጨመር ለአቅርቦትና ፍላጎቱ አለመጣጣም ምክንያቶች ናቸው፡፡

በሌላ መልኩ ከፍላጎቱ መጨመር ጋር ተያይዞ ደላላዎች፣ አምራቾችና አከፋፋች በፈጠሩት የግብይት አሻጥር ያለው ጥቂት የሲሚንቶ ምርትም በትክክለኛው የግብይት ሂደት እንዳያልፍ በመደረጉ ምክንያት የሚፈጠረውን የዋጋ ንረት ማስተካከልና ግብይቱን ሥርዓት ማሲያዝ መንግስትን ሲፈትነው ቆይቷል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የሲሚንቶ ጨምሮ ግብይቱ በትክክለኛው የነፃ ገበያ እስከሚመራ ድረስ የተመረተው ሲሚንቶ በአግባቡ ለተጠቃሚው እንዲደርስ የሚያስችል መመሪያ አዘጋጅቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ከሰኔ 17/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባር ላይ የዋለው የሲሚንቶ ግብይትና ሥርጭት መመሪያ ቁጥር 908/2014 የመንግስት ግንባታ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሲሚንቶ እንዲያገኙ ይፈቅዳል፡፡ ይህ መመሪያ የሲሚንቶ አምራቾች፣ የሲሚንቶ አምራቾች ማህበር፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስተር እንዲሁም የክልልና ከተማ አስተዳደሮችን ተግባርና ኃላፊነቶች ያካተተ ሲሆን መመሪያው ከሚፈቅደው ውጪ የሲሚንቶ ግብይት ሲፈጽሙ በተገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ደንግጓል፡፡

09/07/2022

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ 8 የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከህግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ
8 የነዳጅ ካምፓኒዎች ቦቴዎችን በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ በውረስ በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቀዋል ።
አቶ መስፍን አሰፋ የንግድ ቢሮ ም/ሃላፊ ይህንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ 8የነዳጅ ቦቴዎች ተደብቀው የተያዙት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ትብብር መሆኑን ገልጸው፥ህግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው ገልፀዋል።

Address

Bole
Addis Ababa

Telephone

+251947246775

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole 12 trade office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share