Addis Ketema Woreda 9 Prosperity

Addis Ketema Woreda 9 Prosperity ይህ የወረዳ 9 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኦፌሴላዊ ገፅ ነው

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

በመደመር መንገድ፣ በቁርጠኛ ትጋት የዜጎቻችን ህይወት ይሻሻላል፤ ዘላቂ ብልፅግናችንም ይረጋገጣል!ሰውን ማዕከል ያደረገው የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካዊ ፍልስፍና፤ የልማት፣ የዴሞክራሲና የሉዓላዊነ...
02/09/2026

በመደመር መንገድ፣ በቁርጠኛ ትጋት የዜጎቻችን ህይወት ይሻሻላል፤ ዘላቂ ብልፅግናችንም ይረጋገጣል!

ሰውን ማዕከል ያደረገው የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካዊ ፍልስፍና፤ የልማት፣ የዴሞክራሲና የሉዓላዊነት ጉዞ ትርጉም የሚኖረው የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ፍላጎት ማርካት ሲችል መሆኑን በፅኑ ያምናል። የብልፅግና ፓርቲ እሴቶችም የሚያጠነጥኑት የሰውን ልጅ ክብር፣ ነፃነትና እኩልነት ላይ ሲሆን፣ ፖሊሲዎቹም የተቀረፁት የዜጎችን ህይወት ማሻሻልን ታሳቢ በማድረግ ነው።

ዜጎች ክብራቸውን በሚመጥን የኑሮ ደረጃ እንዲኖሩ፣ ማኅበራዊ ዋስትናቸው እንዲረጋገጥ ብልፅግና ፓርቲ ዘላቂ ግቦችን ነድፎ እየተረባረበ ይገኛል፡፡
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ማኅበራዊ እንስሳ መሆኑንና ያለ ሌላው ድጋፍ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል ፓርቲያችን የሚመራበት የመደመር ፍልስፍና ያስረዳል። ከዚህ በመነሳትም የህዝባችንን ብዝሀነቶች እና የሀሳብ ልዩነቶች እንደ ጌጥ፣ ጠንካራ አንድነቱ ደግሞ የጋራ እጣፈንታው መሰረት መሆኑን ብልፅግና በፅኑ ያምናል፡፡

አንዱ ለሌላው ብርታት የሚሆንበት፣ በጋራ ጥረት እና ትጋት የጋራ ከፍታን የሚያረጋግጠው ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን የሚሆንበት አካታችና አሳታፊ መንገድ ተፈጥሯል፡፡

የሰው ልጅ ቁሳዊ ፍላጎት እንዳለው ሁሉ መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶችም እንዳሉት የታወቀ ስለሆነ የብልፅግና ጉዟችን የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ፣ የሞራል ልዕልና ያላቸው፣ በዕውቀትና በሥነ-ምግባር የታነጹ ዜጎችን ማፍራት ላይ ያተኩራል። ይህንን የቁስና የመንፈስ ሚዛን መጠበቅ የሰውን ልጅ ሙሉነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የፓርቲያችን የምንጊዜም የርብርብ ማዕከል ነው።

የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር የልማት እሳቤ ለዛሬው ትውልድ ብቻ ሳይሆን ለሚመጣውም ትውልድ ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቅ ነው። ተግባራዊ እየሆኑ የሚገኙት አረንጓዴ አሻራን የመሳሰሉ ኢኒሸቲቮች፣ በፈጠራና በፍጥነት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች፣ የአወንታዊ ሰላም ግንባታ ሥራዎች ሁሉ መዳረሻ ዓላማቸው ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና መሆኑን ልብ ማለት ተገቢ ነው፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

 !የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ተግባራት ስኬት ለማረጋገጥ  ከማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።ለዚህም ይረዳ ...
02/09/2026

!

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ተግባራት ስኬት ለማረጋገጥ ከማህበረሰብ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ "የትምህርት ለትዉልድ " ኘሮግራም ተቀርፆ የትምህርት ተቋማት የማሻሻያ ፣የመማሪያ ቁሳቁስ የማሟላት ተግባራት ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት ይህን መርህ በመከተል በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ ለእሸት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።

  ማግስት :- ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ! በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የአየክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች የ2018 በጀት ...
01/09/2026

ማግስት :- ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የአየክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምን በመገምገም በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የጋራ ተግባቦት ፈጥረዋል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ በአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በአባላት ግንባር ቀደምነት ፣ በህዝባችን ተሳትፎ የብልፅግና ፓርቲን እሳቤዎች ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገው ቅንጅታዊ ርብርብ ክ/ከተማችንን ተምሳሌትነት ያስቀጠሉ፣ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ስኬቶች መመዝገባቸው አስገንዝበዋል።

በዚህም በብልፅግና ፓርቲ አሰራር፣ስርዓት፣ አደረጃጀት እንዲሁም ዕቅዶችና ግቦች በመመሪያው መሰረት እንዲተገበሩ በማድረግ ኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ለጠንካራ ፓርቲ እና ለጠንካራ መንግስት ግንባታ ጉልህ ሚና ማበርከቱንም ገልፀዋል።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ም/ሰብሳቢ እና የአዲስ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚፍታ ወልጫፎ ኮሚሽኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አበረታች ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቅሰው በ2019 በጀት ዓመትም በጠንካራ ኢንስፔክሽን የፓርቲውን የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉሰው ደስታ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ የፓርቲያችንን አሰራርና መመሪያ ለማስጠበቅ ያደረገው ጥረት በከተማ ደረጃ እና በክፍለ ከተማው ለተመዘገቡ ውጤቶች ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከቱን አስገንዝበዋል።
አክለውም የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት ዋና ዓላማ ችግሮችን ቀድሞ መከላከል እንዲሁም ሲከሰቱ ፈጥኖ ማረም መሆኑን አሳስበው፣ ለ2019 በጀት ዓመት ከፍተኛ ስኬት ለማስመዝገብ በሁሉም ደረጃ ያሉ የኮሚሽኑ አመራሮች ቁርጠኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።

በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኮሚሽኑ ተቋማት የምስጋና ሰርተፊኬት የተሰጠ ሲሆን፣
1ኛ ወረዳ 1
2ኛ ወረዳ 13
3ኛ ወረዳ 6
በመውጣታቸው የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል። ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስ...
01/09/2026

ዛሬ 33ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ብሩህ ነገን በዛሬ አዕምሮዎች” በሚል መሪ ቃል አስጀምረናል።

ይህ ጉባኤ በየዓመቱ የምናካሂደው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ጤናማ እና ውጤታማ ለማድረግ፣ በዘርፉ የተሰሩትን ጠንካራ ስራዎች ልምድ የምንቀምርበት፣ የሚታረሙትንም ለይቶ በጋራ መፍትሄ የምንሰጥበትና በጋራ እቅጣጫ የምንይዝበት ጉባኤ ነው ።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደራችን በልዩ ትኩረት ሰርተን የተማሪዎች ውጤት እየተሻሻለ መጥቷል። ዛሬ በከተማችን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ወደ 33 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም ከፍ ያለ ውጤት እንጠብቃለን፤ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

መምህራን፤ ባለድረሻ አካላት በእልህ ሰርተን መፍጠር የሚችሉ፣ ችግር የሚፈቱ፣ በሥነ ምግባር የታነፁ፣ እውቀት የታጠቁ ተማሪዎችን በብዛት ለመፍጠር መረባረብ ይጠበቅብናል።

ከተማ አስተዳደራችን ዋናውን ኢንቨስትመንት ትምህርት ላይ እናውል ብለን፣ ትልቁን በጀት ለትምህርት ዘርፍ እንዲሆን አድርገናል። ትውልድ ላይ ከመሰረቱ መስራት ወሳኝ በመሆኑ፣ ዋና የእዕምሮ እድገት በጨቅላ ህፃንነት ወቅት በመሆኑ ቀዳማይ ልጅነት ላይ እየሰራን እንገኛለን። በዚህ አግባብ ከመሰረቱ ጀምረን እየሰራን በአንደኛ ደረጃ እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት እና በዲሲፕሊን የታነፀ ትውልድ እንጠብቃለን።

እስካሁን በተገኘው ውጤት ሁላችሁንም ከልብ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይም በእውቀት የበለፀጉ፣ በስነምግባር የታነፁ፣ አልቀው የሚሰሩ ተማሪዎች ለመፍጠር ከልብ፣ ዋጋ ከፍለን ተባብረን እንድንሰራ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአረንጓዴ አሻራ ቱሩፋቶች ለትውልድ ተሻጋሪ  ድሎች መሰረት ናቸው!የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያን ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን ለማልማት እና ለቀጣይ ...
01/09/2026

የአረንጓዴ አሻራ ቱሩፋቶች ለትውልድ ተሻጋሪ ድሎች መሰረት ናቸው!

የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያን ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን ለማልማት እና ለቀጣይ ትውልድ ምቹ አካባቢ ለማስረከብ የተጀመረ ህዝባዊ መሰረት ያለው ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።

ይህ ሀገራዊ ፕሮግራም የደን ሽፋንን በማስፋፋት፣ የመሬት መራቆትን በመከላከል፣ የውሃ ሀብቶችን በመጠበቅ እና የብዝሃ ሕይወት ሀብትን በማሳደግ ለሀገራችን ዘላቂ ልማት ጠንካራ መሠረት መሆኑ በተጨባጭ መረጋገጥ ጀምሯል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የልማት ኢኒሸቲቭ ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ምቹ መደላድል እየፈጠረ ይገኛል።

ሁሉም ዜጋ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ለተተከሉ ችግኞች በቂ እንክብካቤ በማድረግ የለመለመች፣ በሁለንተናዊ መልኩ ብልፅግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመገንባት የበኩሉን አሻራ በማሳረፍ ተስፋን መትከል ይገባዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድና የ2019 በጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ውይይት አጠናቀናል።  በውይይታችንም  እቅዶ...
31/08/2026

ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስናካሂድ የነበረውን የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድና የ2019 በጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ውይይት አጠናቀናል።

በውይይታችንም እቅዶቹን ይበልጥ ተጨባጭ በማድረግ በቀጣይ አምስት ዓመታትም አልቀን በመፈፀም፣ የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት ሳንሸራርፍ ለመፈፀም፣ የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ እጅግ ጠቃሚ እና ገንቢ ተግባቦት እና ዝግጁነት ፈጥረናል።

ከሀገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂያችን በመነሳት ህዝባችንም በድጋሚ ሲመርጠን “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር” ብለን የገባነውን ቃል ለመፈፀም እንደ አዲስ አበባ “አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት” ለማድረግ የጀመርነውን ጉዞ ዋና ርዕያችን አድርገናል።

ለእቅዳችን ስኬት መሰረቶች የሆኑት ባለፋት አምስት ዓመታት አቅደን አልቀን ያስመዘገብነው ውጤት፣ የህዝብና መንግሥት ከደህነት የመውጣት ፍላጎት፣ በከተማችን የተፈጠረው የስራ ትጋት፣ በታማኝነት ማገልገል፣ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በፍጥነትና በጥራት የመፈፀም ልምድ፣ በጀትን በመቆጠብ መጠቀም ትልቅ ስንቅ ናቸው።

በቀጣይ ትኩረታችንም ተቋማዊ ብቃትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ የዘመነ ቴክኖሎጂ በሚጠቀም የላቀ አገልግሎት መስጠት፣ የተቀናጀ ጥራት ያለው ሰፊ መሰረት ልማት በፍጥነት መገንባት፣ አዲስ መሰረተ ልማት መገንባት ብቻ ሳይሆን ነባሮቹን በሚገባ ማስተዳደር፣ የንፁህ መጠጥ ውኃና የቤት አቅርቦት ማሳደግ፣ የማህበራዊ ዘርፍ (ጤና፣ ትምህርት …) ተደራሽነትና ጥራት እንዲሁም ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ አልቀን መፈፀም፣ ዓለማቀፍ ስታንዳርድ ያሟላ የጤና አገልግሎት መስጠት፣ የጤና ቱሪዝም ማዕከል መሆን፣ የከተማችንን የቱሪዝም መዳረሻ ከተማነት ማረጋገጥ፣ አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ ማድረግ፣ ለወጣቶች ተጠቃሚነት፣ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲሁም በኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ባህል በማድረግ ማህበራዊ ፍትህን ማንገስ፣ የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማትን ማጠናከር፣ እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህን ማንገስ፣ አምራችነትን ማሳደግ፣ ተረጂነትን መቀነስ፣ የስራ እድልን በሰፊው መፍጠር፣ የከተማ ግብርና፣ የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን፣ ፅዳትና የቆሻሻ አወጋገድን ባህል ማድረግ … ወዘተ፤ በአጠቃላይ ከተማችንን ጽዱ፣ ውብ እና ለሁሉም የምትመች ከተማ ማድረግ የእቅዳችን ትኩረቶች ናቸው።

የእቅዳችን ቅኝትም ስትራቴጂክ እይታ ያለው፤ ራዕያችንን ለማሳካት አቅዶ መተግበር፤ የተለጠጠ፣ አካታች፣ ፍትሃዊ እንዲሁም አሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ይህ የእቅድ ውይይት አመራራችን በዋናነት እቅዱን በተሟላ ሁኔታ የተረዳ፣ ስትራቴጂክ አመራር የሚሰጥ፣ በአስተሳሰብ አንድነት የሚቆም፣ ከተለያየ የጥቅም ትስስር ነፃ የሆነ፣ የይቻላል መንፈስን የተላበሰ፣ በአፈፃፀም ተቀራራቢ የሆነ፣ ትጋት እና የአመራር ዲሲፒሊን ያለው፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት እያሰፈንን ህዝቡ የከተማችንን ራዕይና ግብ የተጋራ እንዲሆን በተለየ መንገድ የሄድንበት የውይይት መድረክ ነው።

ልማትን በመንግስት ብቻ ማሳካት እይቻልም። በመሆኑም መላው የከተማችን ነዋሪዎች፣ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ፣ የግሉን ዘርፍ ማበረታታት፣ በጊዜ የለንም መንፈስ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ አሳድገን በከተማችን ለማሳካት የተወጠነውን ትልቅ ራዕይ ለመፈፀም በላቀ እንተጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለማህበዊ መስተጋብራችን መጎልበት፣ ለጋራ ዕድገታችን መረጋገጥ፣ የበጎነት እሴቶቻችንን እናሳድግ!የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ጥንታዊ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አበረታች ተ...
31/08/2026

ለማህበዊ መስተጋብራችን መጎልበት፣ ለጋራ ዕድገታችን መረጋገጥ፣ የበጎነት እሴቶቻችንን እናሳድግ!

የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ጥንታዊ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጎለብቱ እየተከናወኑ በሚገኙ አበረታች ተግባራት የህዝባችን ብዝሀ አብሮነት ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል።

የህዝባችን በጎ እሳቤዎች በተገቢው መንገድ ወደ ተግባር እንዲለወጡ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራር ስርዓቶች መዘርጋታቸውም ለዕድገታችን መፋጠን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በክረምቱ ወራት ተወስነው የነበሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት፣ በተፈጠረው የአስተሳሰብ ለውጥ፣ እንዲሁም በዳበረው ሁሉንም አቅሞች የማስተባበር ቁርጠኝነት ዓመቱን ሙሉ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ለወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰጠው ልዩ ትኩረትም ወጣቶች፣ ሴቶች እንዲሁም ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሚያከናውኗቸው በገንዘብ የማይተኩ ተግባራት ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን እያጠናክሩ ነው።

የህዝባችን ጥንታዊ እሴቶች በየጊዜው እየተሸረሸሩ ከመምጣታቸው ባሻገር አቀናጅቶ የሚያስተባብር ተቋም ስላልነበር በተለያዩ አግባብ የሚገለፁ የሀብት፣ የጊዜ እንዲሁም የጉልበት ብክነቶች ሲስተዋሉ ቆይተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲን ሰው ተኮር እሳቤዎች አልቆ ለመተግበር የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የተቀናጀና የተደራጀ ለማድረግ ብርቱ ጥረት አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኮሚሽንን በማቋቋም አገልግሎቱን ተቋማዊ ቅርፅ እንዲኖረው ማድረጉ የበጎ ፈቃደኞችን የተደመረ አቅም ፈጥሯል።


በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤትም በተለይም በወጣቶች ክንፍ እና በሴቶች ክንፍ አባላት አስተባባሪነት ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊነት እና ዘላቂነት በልዩ ትኩረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የታመሙትን በመጎብኘት ተስፋና ሞራል የመስጠት የበጎነት በሆስፒታል መልካም ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው።

ለአቅመ ደካሞች ቤት ገንብቶ የማስረከብ የበጎነት ተግባርም የበርካታ የሀገር ባለውለታ ዜጎችን ህይወት ማፍካት ችሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ባለፀጎችን በማስተባበር ያስገነባቸው የበጎነት መንደሮች ለከተማችንም ተጨማሪ ድምቀት ሆነዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በተለይም በበዓላት ወቅት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች የሚያከናውነው ማዕድ የማጋራት ተግባርም በከተማችን በተገነቡ የምገባ ማዕከላት ተቋማዊ መልክ ይዞ በጎ ፈቃደኛ ባለሀብቶችን በማስተባበር ዓመቱን ሙሉ እየተከናወነ መሆኑን ልብ ይሏል።

ደም በመለገስ በደም እጥረት ምክንያት ሊጠፋ የሚችል ህይወትን የመታደግ የበጎነት ተግባርም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መምህራን በማስተማር፣ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ህሙማንን በማከም፣ ሌሎችም በየተሰማሩበት የሚያከናውኗቸው ሙያዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራትም የከተማችንን ዕድገት አፋጥነዋል::

የፓርቲያችንን ሰው ተኮር እሳቤዎች በተግባር ለመተርጎም የሚደረገው ርብርብ ዘላቂ ዕድገትን እያረጋገጠ መሆኑ ተጨባጭ ሲሆን ፤ ማህበራዊ አካታችነትን እንዲሁም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትንም ከፍ ማድረግ አስችሏል።

መልካም የስራ ሳምንት!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

የከንቲባ  አዳነች  አቤቤ  መልዕክት ...!!ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት  መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል...
30/08/2026

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ...!!

ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት መላው የከተማችን አመራሮች በተገኙበት አስጀምረናል።

በስድስተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ህዝባችን የሰጠንን ሃላፊነት መነሻ ያደረገ ስትራቴጂክ እቅድ ነድፈን ቃላችንን በተግባር ቆጥረን ፈፅመን የከተማችንን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ከተማችን ደግሞ ተወዳዳሪ እንድትሆን አድርገናል።

ይህንኑ መነሻ በማድረግ የከተማችን ነዋሪ እምነት አድሮበት ዳግም መርጦን ሀላፊነት ሰጥቶናል።
የዛሬው ውይይትም የከተማችን ነዋሪ የጣለብንን እምነት እና የሰጠንን ሀላፊነት መነሻ ያደረገ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት እና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ዝርዝር ግቦች ላይ ተወያይተን በማዳበር የባለፉት አምስት ዓመታት አፈፃፀምን በእጥፍ ለማሳደግ ዝግጁነታችንን የምናረጋግጥበት መድረክ ነው።

እነዚህን ዝርዝር ውይይቶች ስናደርግ 24/7 የመፈጸም ባህላችንን ይበልጥ በማሳደግ፣ አመራራችን ከፊት ሆኖ የበለጠ እየሮጠ ህዝባችንንና የልማት አጋሮቻችንን በማስተባበርና ተሞክሮዎችን በማስፋት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሀገራዊ ማንሰራራት ውስጥ የአዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌትነት ለማረጋገጥ እንተጋለን።

በተጨማሪም በክረምት የያዝናቸው የ90 ቀን ስራዎች ውስጥ የ60 ቀናት አፈፃፀማችንንም የምንገመግምበት የውይይት መድረክ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

29/08/2026

Address

Autobistera Mesalemiya Square
Addis Ababa

Telephone

+251953139594

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Woreda 9 Prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ketema Woreda 9 Prosperity:

Shortcuts

Share