የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን - Addis Ababa Cooperative Commission

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን - Addis Ababa Cooperative Commission

የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን - Addis Ababa Cooperative Commission Addis Ababa Cooperatives Commission manages, aids, controls, and organizes cooperatives. Addis Ababa Cooperative Agency organizes cooperatives in Addis Ababa.
(1)

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡***ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪ...
17/08/2026

በማህበራዊ ሚዲያ አንዲት ታዳጊ ስትደበደብ የሚያሳይ ቪዲዮን በተመለከተ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ ማጣራቱን አስታወቀ፡፡
***
ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አካባቢ ጓደኛቸውን ሲደበድቧት የሚያሳይ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ ህብረተሰቡ አስተያየት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከመሰራጨቱ ከወራት በፊት ወንጀሉን የፈፀሙትን ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማጣራቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡
በወንጀሉ የተጠረጠሩት ሦስት ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በጊዜ ቀጠሮ ታስረው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ልጅቷ ስትደበደብ የሚያሳየው ቪዲዩ መለቀቁ በልጅቷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ቪዲዮውን የለቀቀውን አካል ለማረጋገጥ ፖሊስ ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ ድርጊቱን በማውገዝ ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ያሳየውን መቆርቆር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አድንቋል፡፡

16/08/2026

ለነዋሪዎቻችን ተጠቃሚነት በተከታታይነት ያልተቋረጠና አዳዲስ ብስራት ማብሰር ያስቻለን ፈጠሪ አምላክ የተመሰገ ይሁን !!

የንፁህ መጠጥ ዉሃ እና የዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ምርቃት ላይ በመገኘት ያስተላለፍኩት መልዕክት

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ደስ አለን!!ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ  ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት  እና በቀን 20 ሺህ  ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክ...
16/08/2026

እንኳን ደስ አለን!!

ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት እና በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን አስመርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በቱሉ ጉዶ፣ ለገዳዲ ክፍል 2፣ በረከት የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳና ሌሎችም በርካታ ጉድጓዶችን አልምተን በከተማችን ከአምስት ዓመት በፊት የነበረው 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ዛሬ ላይ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ አድርሰናል፡፡

በተመሳሳይ ለረጅም ዘመን በከተማችን የሚገኙ ወንዞች በፍሳሽም፤ በደረቅ ቆሻሻም ሲበከሉ ቆይተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የፍሳሽ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የማጣራት አቅምን ለማሳደግ ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በሰጠነው ከፍተኛ ትኩረት በ2009 ዓ .ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ማሳደግ ችለናል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎቻችንን ጤናና ንጽህና የሚጠብቁ፣ የወንዞቻችንን ብክለት የሚቀንሱ፣ የአካባቢ ጥበቃችንን የሚያጠናክሩ ናቸው። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ውብ፣ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ፣ ዘመናዊና ለትውልድ የምትመች ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት እውን ላደረጋችሁ፤ በተለይ ደግሞ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የብድር አገልግሎት እየሰጠን ያለውን የዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የውሃው መገኛ አካባቢዎችን በትብብር እንድናለማ ላገዘን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ከሁሉ በላይ ዘላቂ ኑሯቸውን ሲመሩበት የነበረውን መሬት ለዚህ ታላቅ ልማት የለቀቁ አርሶ አደሮች እና ለፕሮጀክቱ ስኬት ሌት ተቀን ያለእረፍት የተጉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አመራሮች እና ባለሙያዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ኢትዮጵያ የዘመናት ስብራቶቿን ለመጠገን እየመከረች ነዉ!የአንዲት ሀገር የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ጉዞ አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው በህዝቦች የጋራ መግባባትና በጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ላይ...
16/08/2026

ኢትዮጵያ የዘመናት ስብራቶቿን ለመጠገን እየመከረች ነዉ!

የአንዲት ሀገር የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ጉዞ አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው በህዝቦች የጋራ መግባባትና በጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ላይ ሲገነባ ብቻ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በገለልተኛ ተቋም የጀመረችው ሀገራዊ ምክክር የቆዩና የተወሳሰቡ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ፈትተን፣ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የተከፈተ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነዉ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልተኛ ሆነ ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። አሁን ላይ ሂደቱ እጅግ ተስፋ ሰጪና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ኮሚሽኑ በመላው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መዋቅሩን ዘርግቶ፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግብዓቶችንና አንገብጋቢ ሀገራዊ አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ስራን በስኬት አጠናቋል።

አሁን ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ ከ4,000 በላይ ተወያዮቹ ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ከትጥቅ ትግል ወደ ሳላም አማራጭ የተመለሱ ሃይሎች ፣ የዲያስፖራ አባለት፣ ምሁራንና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገናኝተው ታሪካዊ ምክክሩን እያሳለጡ ነዉ።

ሀገራዊ ምክክር የጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ የወደፊት እጣ-ፈንታ የሚወሰንበት ብሄራዊ መድረክ ነው። ሀገራዊ ምክክርን በአግባቡ በመጠቀም ከተወሳሰበ ቀውስና ከእርስ በርስ ጦርነት ወጥተው ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት የተሻገሩ በርካታ ሀገራትን ማንሳት ይቻላል።

ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት ካደረሰባት ጥልቅ ማህበራዊ ቁስልና የርስ በርስ ጦርነት ስጋት የወጣችው በሀገራዊ ምክክር (CODESA) አማካኝነት ነው። የፖለቲካ ሃይሎች በጥላቻ ፈንታ ይቅርታንና እርቅን በማስቀደማቸው ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ጠንካራ ዲሞክራሲ መገንባት ችላለች።

ቱኒዚያ እ.ኤ.አ በ2011 ከነበረው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ፣ የሀገር መፍረስ ስጋትና አለመረጋጋት ህዝቧን የታደገችው በሲቪል ማህበራት መሪነት በተደረገ ብሄራዊ ምክክር ነው። ይህ ምክክር ሀገሪቱን አዲስና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ለማርቀቅ አብቅቷታል።

የእነዚህ ሀገራት ተሞክሮዎች የሚያሳየን በቅንነትና በቁርጠኝነት በጠረጴዛ ዙሪያ ከተቀመጥን የማይፈታ የትኛውም ውስብስብ የፖለቲካ ቀውስ እንደሌለ ነዉ።

ስለዚህ የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግና ከልቡ የሚሻ ሁሉ ዜጋ ሀገራዊ ምክክሩ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ የሚወስን ስለሆነ በሃሳብ፣ በዕውቀት፣ በንቁ ተሳትፎና በጸሎት መደገፍ የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው።

prosperity

ተመራቂ የፖሊስ  መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ! ዛሬ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ  በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ  መኮንኖችን መርቀናል።  ተመራቂዎቹ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር  በጠ...
15/08/2026

ተመራቂ የፖሊስ መኮንኖች እንኳን ደስ አላችሁ!

ዛሬ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ መኮንኖችን መርቀናል።

ተመራቂዎቹ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር በጠንካራ ዲሲፕሊን ስልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ፤ በአካልና በመንፈስ ጠንክረው የወጡ በመሆናቸው በፖሊስ መኮንንነት ማዕረግ ተመርቀዋል።
ተመራቂዎች በቆይታችሁ ያገኛችሁት እውቀት ለላቀ ፖሊሳዊ ስብዕና የሚያበቃችሁ እንደመሆኑ ወደ ስራ ስትሰማሩም ያለአድልዎና ልዩነት በታማኝነት፣ በጀግንነት፣ በሰብዓዊነትና በክብር፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንደምታገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሰንበት ገበያ የኑሮ ውድነትን በማቃለልና ገበያን በማረጋጋት ያለውን ሚና አጠናክሮ ቀጥሏልነሀሴ 9/2018 ዐ.ምየሸማቾችን የግዢ አቅም ለማጠናከር፣ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የገበያ መረጋጋ...
15/08/2026

የሰንበት ገበያ የኑሮ ውድነትን በማቃለልና ገበያን በማረጋጋት ያለውን ሚና አጠናክሮ ቀጥሏል

ነሀሴ 9/2018 ዐ.ም
የሸማቾችን የግዢ አቅም ለማጠናከር፣ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የገበያ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የሚካሄደው የሰንበት ገበያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ።

የሰንበት ገበያ የሸማች ኀብረት ሥራ ማኅበራት ከአምራቾችና ከአቅራቢዎች በቀጥታ የሚያገኟቸውን የተለያዩ የምግብና የፍጆታ ምርቶች ለሸማቾች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ የሚያስችል የገበያ አማራጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

በተለይም ምርትን ከአምራች ወደ ሸማች በቀጥታ ለማድረስ የሚያስችለው አሰራር፣ በመካከለኛ የገበያ ደረጃዎች የሚጨመረውን የዋጋ ልዩነት በመቀነስ ሸማቾች በተሻለ ዋጋ ምርቶችን እንዲገዙ ዕድል ይፈጥራል። ይህም በተለይ የዕለት ተዕለት የፍጆታ ምርቶች ዋጋ በሚከታተልበት ወቅት የሰንበት ገበያ ያለውን አስተዋጽኦ የሚያጎላ ነው።

የሰንበት ገበያ በሸማቾች በኩል ተመጣጣኝ ዋጋ ያለውን ምርት የመምረጥ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ የኀብረት ሥራ ማኅበራት የገበያ አቅርቦትን በማሳደግ የዋጋ መረጋጋት ላይ ያላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ ያደርጋል። በዚህም የገበያ ተወዳዳሪነት እንዲጨምርና ሸማቾች የተሻለ የግዢ አማራጭ እንዲያገኙ ያግዛል።

ከዚህ ባለፈ የሰንበት ገበያ የአምራቾችን ምርት ወደ ገበያ ለማስገባት አስተማማኝ የገበያ መዳረሻ በመፍጠር የአምራችና የሸማች ትስስርን ያጠናክራል። ይህ አሰራር በአንድ በኩል ለአምራቾች የገበያ ዕድል ሲፈጥር፣ በሌላ በኩል ለሸማቾች ተመጣጣኝ ዋጋና የምርት አማራጭ ያቀርባል።

የገበያው እንቅስቃሴ በየሳምንቱ እየተጠናከረ መምጣቱም የሸማቾች ፍላጎትና በኀብረት ሥራ ማኅበራት የሚቀርበው የምርት አቅርቦት እየጨመረ መሆኑን ያመላክታል። በመሆኑም ገበያውን በቀጣይነት ማስፋት፣ የምርት ዓይነትና መጠን ማሳደግ እና ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲያገኙት የማድረግ ሥራ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።

በአጠቃላይ፣ የሰንበት ገበያ ለሸማቾች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ምርት ከማቅረብ ባለፈ፣ የአምራችና የሸማች ትስስርን በማጠናከር፣ የገበያ አቅርቦትን በማሳደግና የዋጋ መረጋጋትን በመደገፍ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ያለውን ሚና እያጠናከረ ይገኛል።

“ሰንበት ገበያ፤ ለተመጣጣኝ ዋጋ፣ ለተረጋጋ ገበያ!” ፣ የሚገለጸው ይህ የገበያ አማራጭ በቀጣይም በስፋት ተጠናክሮ መቀጠሉ ለከተማዋ የገበያ መረጋጋትና ለሸማቾች ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ምርት የሚኖረውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል።
https://linktr.ee/addis_cooperative

15/08/2026

አዲስ ፤ የመሻት ከትላንት ተሻግራ ዛሬን ለትውልድ ፣ለነዋሪዎች ምቹ የአለምአቀፉዊ የስበት ማዕከል

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚገጥሙ የአሰራር ግድፈቶችን መታገልና ማረም ይቻል ዘንድ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች በኮሚሽኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምላሽ ያገኛሉ፦ ኮሚሽነር ሽታዬ መሃመ...
14/08/2026

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚገጥሙ የአሰራር ግድፈቶችን መታገልና ማረም ይቻል ዘንድ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች በኮሚሽኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምላሽ ያገኛሉ፦ ኮሚሽነር ሽታዬ መሃመድ፡፡

ኮሚሽኑ የዕለተ አርብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አካሄደ፡፡
ነሀሴ 08/2018 ዓ.ም
ዘወትር ረዕቡና አርብ በሚካሄደው የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚቀርቡ ቅሬታና ጥያቄዎች እንዲሁም ጥቆማዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚፈጠሩ የአሰራር ግድፈቶችን ተከታትሎ ፍትሃዊ ውሳኔ ለማስጠት ያስችላል ያሉት ኮሚሽነር ሽታዬ መሃመድ የችግሮቹን መሰረታዊነት በማጣራት ደንብና መመሪያን ተከትለን ውሳኔ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ይህንኑ አሰራር በመከተል መስራት በመቻሉ የሚታዩ ለውጦች መምጣታቸውንም ኮሚሽነሯ ጠቁመዋል፡፡
https://linktr.ee/addis_cooperative

14/08/2026

የህብረት ስራ ማህበራት ምርቶችን እሴት በመጨመር ለገበያ በማቅረብና ገበያን በማረጋጋት ማህበረሰቡን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

Address

5 Kilo Near Kidiste Mariam Church
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 12:30
13:30 - 17:30
Friday 08:30 - 11:30
13:30 - 17:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን - Addis Ababa Cooperative Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን - Addis Ababa Cooperative Commission:

Shortcuts

Share