Ethiopian Statistical Service-ESS

Ethiopian Statistical Service-ESS Ethiopian Statistical Service collects, processes, and disseminates official statistical data.
(3)

ለተቋሙ ባለሙያዎች በሜታ ዳታ ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ነሐሴ 22/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በመተባበር ከተቋሙ የተለያ...
28/08/2026

ለተቋሙ ባለሙያዎች በሜታ ዳታ ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
ነሐሴ 22/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በመተባበር ከተቋሙ የተለያዩ ስራ ክፍል ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በሜታ ዳታ አስፈላጊነትና አዘገጃጀት ላይ በተቋሙ የስልጠና ማዕከል ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
የስልጠናው መጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ግንዛቤ ወደ ተግባር እንዲለወጡ የስራ መመሪያ ሰጥተው ፤ለተደረገው ድጋፍ የኖርዌይ ስታቲስቲክስንና ስልጠናውን ሲሰጡ ለቆዩትን የኖርዌይ ስታቲስቲክስ ከፍተኛ ባለሙያ ሚስተር አላን ሔብሪሰንን(Allan Hebrysson) አመስግነዋል።

27/08/2026
ኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት የጓሮ ማሳ ላይ ለከተማ ግብርና ማሳያ ግንቦት 26 /2016 ዓ.ም ተተክሎ የለማ የቡና ተክል ዕድገት በፎቶ
26/08/2026

ኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት የጓሮ ማሳ ላይ ለከተማ ግብርና ማሳያ ግንቦት 26 /2016 ዓ.ም ተተክሎ የለማ የቡና ተክል ዕድገት በፎቶ

ተቋሙ የክረምት በጎ አድራጎት ስራ አስጀመረ  ነሐሴ 16/2018ዓ.ም፤ ጅማ ከተማየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በጅማ ከተማ ጉዳታ ቡላ ቀበሌ በመገኘት የ201...
22/08/2026

ተቋሙ የክረምት በጎ አድራጎት ስራ አስጀመረ
ነሐሴ 16/2018ዓ.ም፤ ጅማ ከተማ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በጅማ ከተማ ጉዳታ ቡላ ቀበሌ በመገኘት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራ አስጀመሩ።
ቀበሌው ተገኝተው የክረምት በጎ አድራጎት ስራውን ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የዚህ ዓመት የበጎ አድራጎት ስራ ለማስጀማር ከአዲስ አበባ 150 የተቋሙ ሰራተኞች ይዘን ወደ ጅማ ከተማ ስንመጣ ፣ችግኝን በመትከል በህዝቦች ውስጥ የመልማት ተስፋን ለመትከል፣ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት በመገንባት የነጌውን ትውልድ በዕውቀት ለመገንባት ፣ህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለመጠናከርና ከለን ላይ ሰባአዊ ድጋፍ የመድረግ አራት ግቦች ለመሳከት ተሳቢ በመድረግ እንደሆና አስረድተው በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመርና ጉዳታ ቡላ ቀበሌ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ ሁሉንም ግቦች መሳካት መቻሉ ገልጾው ተቋማቸው በጉዳታ ቡላ ቀበሌ የሚገነባውን ኡርጅ ጅማ ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ግንባታ በአጠረ ጊዜ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ቃል ገብቷው ስራውን ለማስጀመር ወደ ከተማው ሲመጡና በነበራቸው ቆይታ በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር ፣ በከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት አመረሮችና ጉዳታ ቡላ ቀበሌ ነዋሪዎች ለተደረገላቸው ደማቅና ቤተሰባዊ አቀባበል በተቋማቸው ስም የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በከተማቸው ጉዳታ ቡላ ቀበሌ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራ ለማከናወን ወስኖ በመካከላቸው በመገኘታቸው ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና በማቅረብ የተጀመረው ኡርጅ ጅማ ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ግንባታበአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለሚፈለገው አገለግሎት እንዲውል ክትትልና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራው በከተማው ጉዳታ ቡላ ቀበሌ አንድ ኡርጅ ጅማ ቡኡራ ቦሩ ቅድማ አንደኛ ደረጀ ት/ቤት ግንባታ የማስጀመርና 200 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የመድረግ ተግባራት ተከናውኗል።
ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከጅማ ቅ/ጽ/ቤት የተውጣጡ 200 ሠራተኞች ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኛች የችግኝ  ተከላ አካሄዱነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ጅማለ2018 ዓ.ም ለክረምት በጎ አድራጎት ስራ ጅማ ከተማ የሚገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመ...
22/08/2026

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኛች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ጅማ
ለ2018 ዓ.ም ለክረምት በጎ አድራጎት ስራ ጅማ ከተማ የሚገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ከከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር ጋር በመሆን በከተማው ወንዝ ዳርቻ በሚገኝ የሸንኮሬ ፓርክ የችግኝ ተከላ አካሄዱ። በችግኝ ተከላው ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከጅማ ቅ/ጽ/ቤት የተውጣጡ 200 ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን 2000 ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ችግኞች ተክለዋል።

ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደረገነሐሴ15/2018 ዓ.ም ጅማየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነሐሴ16 /2018 ዓ.ም በክረምት በጎ አድራጎት ስራ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ...
21/08/2026

ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደረገ
ነሐሴ15/2018 ዓ.ም ጅማ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነሐሴ16 /2018 ዓ.ም በክረምት በጎ አድራጎት ስራ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ከተማ ኢፋቡላ ቀበሌ የሚያስገነባው የቡአራ ቦሩ ት/ቤት ግንባታ ለማስጀመሪና ለ200 አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለመድረግ ጅማ ከተማ ለገቡት የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በጅማ ኤርፖርት በከተማው ከንቲባ ክቡር አቶ ጣሃ ቀመር አቀባበል ተደረገላቸው።

በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ አተኩሮ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀነሐሴ 6/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ለኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤትና ለ26ቱ ቅ/ጽ/ቤቶች ሰራተኞች ...
12/08/2026

በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ አተኩሮ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
ለኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤትና ለ26ቱ ቅ/ጽ/ቤቶች ሰራተኞች ዕምርታ በስታቲስቲክስ ልማት በሚል ርዕስ ከነሐሴ4_6/2018 ዓ.ም በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ አተኩሮ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው መዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በስልጠናው ያገኘነውን ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲሁም ባለፉት ሶስት አመታት ባከናወናቸው ታላላቅ ተግባራት የተገኙት የአመራር ጥበብ ልምድ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራትና ሌሎች ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋትና ስኬቶቻችንን ይበልጥ በማላቅ በስታቲስቲክስ ዘርፍ በአህጉሪቱ መሪ ፤በአለም አቀፍ ስመ-ጥር፣ተወዳዳሪና የልህቀት ማዕከል የሆነ ተቋም ግንባታ እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ ለማሳካት መላው የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነትና በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

Address

Piassa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Statistical Service-ESS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Statistical Service-ESS:

Shortcuts

Share