የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council

የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council The official representative voice of more than 41 million young people in Ethiopia.

28/07/2026
09/07/2026
08/07/2026
07/07/2026
18/06/2026

‎የክረምት በጎ ፈቃድ መርኃ ግብር ወጣቶች በሀገር ልማት ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ እያደረገ ነው
‎****************
‎ወጣቶች በሀገር ልማትና ዘላቂ እድገት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ በማስቻል ረገድ የክረምት በጎ ፈቃድ መርኃ ግብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ ገለፁ።

‎የዘንድሮ 2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፊቃድ መርኃ ግብርም በተደመረ አቅም ለመከወን የሚያስችል ዝግጅት መደረጉንም አመልክተዋል፡

‎የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ ግብር፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በማሳተፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸውን በርካታ ተግባራት የሚያከናውንበት ትልቅ መድረክ ነው።

‎መርኃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶች ዝግ በሚሆኑበት የክረምት ወቅት ወጣቶች ጊዜያቸውን፣ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለሀገር ጠቃሚ በሆኑ ስራዎች ላይ እንዲያውሉ ለማድረግ ያለመ ነው።

‎ባለፉት አመታት በአገራችን እየተተገበረ በሚገኘው በዚህ አገር አቀፍ ንቅናቄ ውስጥ ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ፣ ነጻ ህክምና አገልግሎት፣ ደም ልገሳ፣ ትራፊክ አገልግሎት፣ ትምህርት፣ የአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና በሌሎችም በጥቅሉ14 የስምርት መስኮች ላይ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አሕመድ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ እየተተገበረ ያለው የክረምት በጎ ፈቃድ መርኃ ግብር ወጣቶች ዕውቀታቸውና ጉልበታቸው ለሕዝባቸው በሚጠቅም ተግባር ላይ እንዲያውሉ እያስቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ይህም የበጎነት ባህል በሀገራችን እንዲዳብር በማስቻል ረገድ ባለፉት ዓመታት በትኩረት መሰራቱንና ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን አንስተዋል።

‎በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሰጡት ትኩረትና ያሳዩት አርአያነት ለበርካቶች መነሳሳት መፍጠሩን ስታውቀዋል፡፡

‎ባጠቃላይ ከለውጡ ወዲህ የበጎ ፈቃድ ተሳታፊዎች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩን አረጋግጠዋል።

‎ለአብነትም በ2010 ዓ.ም 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን የነበረው የወጣቶች ተሳትፎ በ2017 ዓ.ም ወደ 25 ሚሊዮን ማደጉን እንዲሁም 13 ነጥብ 6 ሚሊዮን የነበረው የኅብረተሰብ ተጠቃሚነት ወደ 53 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል።

‎ይህም በዘርፉ ከፍተኛ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የተቻለበት መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

‎በተያዘው የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርኃ ግብር 14ቱ የስምርት መስኮች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በተለይም በአረንጓዴ አሻራ፣ በሰላም ግንባታ፣ በአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እንዲሁም በትውልድ ግንባታ ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ሚኒስትር ዴኤታዋ አስገንዝበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተጽኖ ፈጣሪነት ለማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን ገቢራዊ ማድረግ ይገባል፤ፕሬዚደንት ፉአድ ገና የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚ...
11/06/2026

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተጽኖ ፈጣሪነት ለማጠናከር ቅንጅታዊ አሰራርን ገቢራዊ ማድረግ ይገባል፤ፕሬዚደንት ፉአድ ገና

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ፉአድ ገና በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጎበኙ።

ፕሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው በሩሲያ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ገነት ተሾመ ጋር ተወያይተዋል።

ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት እያካሄዳቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል። ከAll-Russian public-state movement of children and youth, "Movemeng of the first" ጋር የተደረሰውን የትብብር ስምምነት አስመልክቶም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን የወጣቶች ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣቶች በወጣቶች መሪነት ልማት፣ በትምህርት፣ በባህላዊ ልውውጥ፣ በስራ ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት እና በዓለም አቀፍ የወጣቶች አጋርነት መስኮች እድሎችን ለማስፋፋት ተግባራዊ መንገዶችን በመፈለግ ላይ ያተኮረ ነበር።

ውይይቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተሳትፎ፣ተደማጭነትና ተጽኖ ፈጣሪነት ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

በተጨማሪ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተቋማት የወጣቶች ግንኙነትን ለማራመድ፣ ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማጠናከር እና ወጣት መሪዎችን ለማበረታታትና ለማብቃት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ምክክር ተደርጓል።

ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና በኤምባሲው ለተደረገላቸው አቀባበልና ለነበራቸው ፍሬያማ የውይይት ጊዜ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢ/ወ/ም/ቤት

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት በሩሲያ ፌዴሬሽን ከሚገኘው All-Russian public-state movement of children and youth, "Movement of the first" ጋር ...
10/06/2026

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት በሩሲያ ፌዴሬሽን ከሚገኘው All-Russian public-state movement of children and youth, "Movement of the first" ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ትብብርን ለማስፋፋት ትልቅ ምዕራፍ እንደሚከፍት ታምኖበታል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገናና የAll-Russian public-state movement of children and youth, "Movement of the first" የቦርድ ሊቀመንበር አርተር ኦርሎቭ በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ገነት ተሾመ በተገኙበት ተፈራርመዋል።

ይህ አጋርነት ኢትዮጵያና ሩሲያ በወጣቶች መሪነት ልማት፣ በትምህርትና በባህል ልውውጥ፣ በስራ ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት፣ በሰላም ግንባታ፣ በቱሪዝም ልውውጥ፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና በጋራ የወጣት ፕሮግራሞች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው ስለመሆኑ ተመላክቷል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና ባደረጉት ንግግር የወጣቶች ዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ትብብር ወጣቶችን ለማበረታታትና መጪው ትውልድ ለዓለም አቀፍ ልማት ንቁ አስተዋፅዖ እንዲያደርግ ለማዘጋጀት አበርክቶው የጎላ ነው ብለዋል።

ዓለም ከምንጊዜውም በላይ እየተቆራኘ ባለበት በዚህ ወቅት፤ በወጣቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን መፍጠር ዘላቂ አጋርነትና የተሻለ ነገን ለመገንባት ያግዛል ሲሉም ተናግረዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የወጣቶች ግንኙነት ለማስፋፋትና በሁለቱ ሀገራት ለሚገኙ ወጣቶች ዘላቂ እድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል በመድረኩ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ግንኙነቱን በማስፋትና በማጠናከርና የኢትዮጵያ ወጣቶች በዓለም መድረክ ላይ ተወክለው በሁለንተናዊ መልኩ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

የኢ/ወ/ም/ቤት

Address

Bambis Area
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council:

Shortcuts

Share