Bole Woreda 12 Communication

Bole Woreda 12 Communication Bole Sub City Wereda 12 Communication is a 24 hour working public media.

https://www.facebook.com/profile.php?id=100064554647803&mibextid=ZbWKwL

tiktok.com/ ዘመናዊ ፣ ግልፅና ፈጣን ምላሽ መስጠት ባሀሉ ያደረገ የኮሚኒኬሽን ስርአት በመዘርጋትና በዘርፉ መሪ ሚና በመጫወት ብሎም በመንግስትና በህዝብ መካከል ጥራት ያለውን ለሁሉም ነዋሪ ተደራሽ የሆነ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ

የእመርታ ቀንን በማስመልከት የከተማ ግብርና እና የከብት ማድለብ ሥራ ጉብኝት ተካሄደየእመርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በወረዳው የሚከናወኑ የከተማ ግብርና እና የከብት ማድለብ ሥራዎች የመስክ...
06/09/2026

የእመርታ ቀንን በማስመልከት የከተማ ግብርና እና የከብት ማድለብ ሥራ ጉብኝት ተካሄደ

የእመርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በወረዳው የሚከናወኑ የከተማ ግብርና እና የከብት ማድለብ ሥራዎች የመስክ ጉብኝትና የማነቃቂያ ሥራ ተካሄደ።

በጉብኝቱም የከተማ ግብርና ሥራዎች ለምግብ ዋስትና፣ ለገቢ ማስገኛ እና ለኑሮ መሻሻል የሚኖራቸውን አስተዋፅዖ በማጠናከር፣ በተለይም የከብት ማድለብ ሥራን በዘመናዊና በንግድ አስተሳሰብ እንዲመሩ ለሚሳተፉ አካላት የማነቃቂያና የሙያ ድጋፍ ተሰጥቷል።

በመስክ ላይ ያሉ ሥራዎች አፈጻጸም ተመልክቶ ያሉ ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተመክረዋል። የከተማ ግብርናን በማስፋፋት ምርታማነትን ማሳደግ፣ የሥራ ዕድልን መፍጠር እና የነዋሪዎችን ገቢ ማሳደግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

የእመርታ ቀንም የተመዘገቡ ውጤቶችን በመገምገም ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና ተግባራዊ ውጤቶችን ለማስፋት የሚያግዝ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።

በእመርታ ቀን የሥራ ዕድል የተፈጠረባቸው ሼዶች ጉብኝት ተካሄደየእመርታ ቀንን አስመልክቶ በወረዳው የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ሼዶች የመጎብኘትና የሥራ አፈጻጸማቸውን የመገምገም ተግባር ተካሄ...
06/09/2026

በእመርታ ቀን የሥራ ዕድል የተፈጠረባቸው ሼዶች ጉብኝት ተካሄደ

የእመርታ ቀንን አስመልክቶ በወረዳው የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ሼዶች የመጎብኘትና የሥራ አፈጻጸማቸውን የመገምገም ተግባር ተካሄደ።

በጉብኝቱም ሼዶቹ ለወጣቶችና ለሌሎች የሥራ ፈላጊዎች የፈጠሩት የሥራ ዕድል፣ በሥራ ላይ ያስገኙት ውጤት እና የወደፊት የማስፋፊያ አቅማቸው ተመልክቷል።

ጉብኝቱ የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋት፣ የሥራ ፈጣሪነትን በማበረታታትና የዜጎችን ተጠቃሚነት በማሳደግ የተገኙ ተጨባጭ ውጤቶችን ለመለየት ያለመ ነው።

የእመርታ ቀንን አስመልክቶ  የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12  ጠቅላላ የወረዳው አመራር የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎበኘየወረዳው ጠቅላላ አመራር የእመርታ ቀንን አስመልክቶ በወረዳው የተከናወኑ የ...
06/09/2026

የእመርታ ቀንን አስመልክቶ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጠቅላላ የወረዳው አመራር የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎበኘ

የወረዳው ጠቅላላ አመራር የእመርታ ቀንን አስመልክቶ በወረዳው የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በአካባቢው የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን፣ የአካባቢ ውበትና ጽዳትን እንዲሁም የሕዝብ አገልግሎትና የከተማ ገጽታን ለማሻሻል የተወሰዱ ተግባራትን ተመልክተዋል።

የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ውበት ከማስጠበቅ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ የአካባቢ አጠቃቀም ሁኔታን በመፍጠር የከተማ ልማትን የሚያፋጥን መሆኑ ተገልጿል።

አመራሩም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በጥራትና በዘላቂነት እንዲጠናቀቁ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝቧል።

የጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን  በቦሌ /ከተማ ወረዳ 12 በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ::*********************ጳጉሜን 1 - 2018 ዓ.ም "የዛሬ ኢኮኖሚ እምርታችን ለነገው ብሩህ ተስፋ፤...
06/09/2026

የጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን በቦሌ /ከተማ ወረዳ 12 በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ::
*********************
ጳጉሜን 1 - 2018 ዓ.ም

"የዛሬ ኢኮኖሚ እምርታችን ለነገው ብሩህ ተስፋ፤ ዘላቂ የብልፅግና ጉዞ እና ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ በቦሌ ከተማ ወረዳ 12 የጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን በፓናል ውይይት ተከብሯል።

የቦሌ ክ /ከተማ ወረዳ12 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሮሪሶ በተለያዩ የልማት መስኮች የተመዘገቡ ለውጦችን፣ የዕቅድ አፈጻጸሞችንና የተገኘውን ውጤት መመዝገብ ብቻ ሳይሆን፣ የትኞቹ ዘርፎች ትኩረት እንደሚሹና በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍም የፋይናንስ አካታችነትን ማስፋፋት፣ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን ማጠናከርና የኢኮኖሚ ሥርዓቱን የበለጠ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ማድረግ የእመርታ አቅጣጫዎች መሆናቸውን እንዲሁም ባለፉት አምስት አመታት የልማት ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የተከናወኑ ሥራዎች፣ የታዩ ለውጦችና በቀጣይ መጠናከር የሚገባቸው የሥራ አቅጣጫዎች በዝርዝር ተናግረዋል

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ደጋሎ በበኩላቸው በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተከናወኑ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስፋፋትና ተኪ ምርቶችን ማምረት በዘርፉ ትኩረት ከተሰጣቸው ሥራዎች መካከል መሆናቸው ገልፀዋል።

የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የሻነው ግዛቸው ነገሮ በበኩላቸው ከተማ ግብርና ዘርፍ የተከናወኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት፣ የወተት ምርት፣ የዶሮ እርባታ፣ የእንስሳት ማድለብና ሌሎች የከተማ ግብርና ሥራዎችን ምርታማነትን በማስፋፋትና የምግብ ምርትን ከማሳደግ ባለፈ የቤተሰብ ገቢን ለመጨመርና የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልፀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እመርታ የአንድ ቀን በዓል ሳይሆን የየዕለት ተግባር መሆን እንዳለበት እና በታማኝነት፣ በትጋት፣ በተጠያቂነትና በትብብር በመሥራት የተገኘውን ስኬት ማስቀጠል እንዲሁም የበለጠ እመርታ ማምጣት የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ተናግረዋል ።

06/09/2026
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባ...
06/09/2026

እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ! እመርታ ከአሉበት የከፍታ ደረጃ ወደ ላይኛዉ መስፈንጠር ነው፡፡ ከፍታን በአዝጋሚ ሂደትም ዘመናትን ወስዶ ማሻሻል ይቻላል፤ በዚያ አግባብ የሚመጣ መሻሻል ከታለመዉ ግብ ለመድረስ የትውልዶችን ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ግን በቁጭት ለዘመናት ከቆየንበት ኋላ ቀርነት እና ድህነት በአዝጋሚ ጉዞ ለመላቀቅ ስለማይቻል እመርታዊ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርገን ሠርተን ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ያለፉት ጥቂት ዓመታት ጥረቶቻችን ውጤቶች የሚያሳዩትም ይህንኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ጀርባ ያጎበጡ የውጭ ዕዳዎችን ጫና በመቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት ዐቅም በማሻሻል፣ የማዕድን ሀብቶች አጠቃቀምን በማላቅ እመርታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

የመንግሥት አጠቃላይ የማድረግ ዐቅም በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ይህንን እመርታዊ ስኬት ማስመዝገብ የተቻለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፤ የዜጎችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማሳደግ፤ የቢዝነስ ሥርዐቱን ቀልጣፋና ግልጽ በማድረግ፤ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ዐቅም ከዜጋ ተኮር እና ብሔራዊ ጥቅም አንጻር በመግራት የመደመር መንግሥት ባደረገዉ ሰፊ ጥረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶቿን በላቀ የኃላፊነት ስሜት በሕጋዊ አግባብ መጠቀም ጀምራለች፤ ታዳሽ ኃይልን በማምረት ከራስ አልፎ ለቀጠናዉ የኃይል ምንጭ ኾናለች፤ ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን በመተግበር ኹለንተናዊ ዕድገቶችን እያስመዘገበች መጥታለች፤ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳድራ የመሸጥ ዐቅም ፈጥራለች፡፡ የመንግሥት የልማት ዕቅድ ከቁጥ ቁጥ ወጥቶ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ ግብ አስቀምጦ እየተተገበረ ነው፡፡

በ2018 ዓ/ም በሁሉም መስክ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ለውጥ የመሸጋገር ሀገራዊ ራዕይን ማሳካት ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን በ2023 ዓ.ም አፍሪካዊት የብለጽግና ተምሳሌት የማድረግ ግብ ተቀምጦ ርብርብ እየተደረገ የስኬቱ ዋዜማ እየተቃረበ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመደመር መንግሥት በተነደፉ የፖሊሲ ሐሳቦች ኹለንተናዊ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ጀምራለች፡፡ በገቢ አሰባሰብ ላይ የታየዉ እመርታ አንዱ አብነት ነው፡፡ የግብር እና ታክስ መሠረትን በማስፋት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅምን በማሳደግ፤ የግብር ከፋዩን የመንግሥት አገልግሎት እርካታ በመሶብ አንድ ማእከል እና በዲጂታል አገልግሎቶች ከፍ በማድረግ የላቀ አፈጻጸም ማሳየት ተችሏል፡፡ በዚህም የበጀት ጉድለትን በእጅጉ ማጥበብ ተችሏል፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ዐቅም በእጅጉ አድጓል፡፡ ፕሮጀክቶች መቼ እንደሚጀመሩ እና በምን ያህል በጀት እንደሚፈጸሙ ብቻ ሳይኾን መቼ ተጠናቅቀው በትክክል አገልግሎት እንደሚሰጡ ጭምር በከፍተኛ የራስ መተማመን የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ መናገር የሚቻልበት ቁመና ላይ ተደርሷል፡፡

እመርታዊ ስኬቶችን ዕውቅና ለመስጠት፣ በቀጣዮቹም ዓመታት የበለጠ እመርታዊ ስኬቶችን ለማስመዝገብ መዘጋጀት አስፈላጊ በመኾኑ ዛሬ ጳጒሜን 01 ቀንን “የኢትዮጵያ ማንሰራራት!” በሚል መሪ መልእክት እያከበርን ነው፡፡

እንኳን ለእመርታ ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

ጳጉሜን 01 ቀን 2018 ዓ.ም

# የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመጪው የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ገበያ ማረጋጋት ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12   የመጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተከ...
05/09/2026

የመጪው የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ገበያ ማረጋጋት ባዛርና ኤግዚቢሽን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የመጪውን የ2019 አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተከፈተው ሁሉን አቀፍ የንግድ ባዛርና ኤግዚቢሽን በዛሬው እለትም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑ ታውቋል።

ባዛሩ የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል እና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፣ የደላሎችን አላስፈላጊ ጣልቃገብነት በማስወገድ አምራቾችን፣ የአርሶ አደርና የኅብረት ሥራ ማህበራትን ከሸማቹ ሕብረተሰብ ጋር በቀጥታም አገናኝቷል።

በወረዳው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በጋራ የተዘጋጀው ይህ መሰረታዊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡበት የበዓል ገበያ ማረጋጋት ሥራ እስከ በዓሉ ዋዜማ ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

05/09/2026
አዲስ ዓመትን ፅዱና ውብ በሆነ መልኩ እንቀበል!የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ፅ/ቤት “አዲስ ዓመትን ፅዱና ውብ በሆነ ተቋም እንቀበለው!” በሚል መሪ ቃል በወረዳ 12 ቡልቡል አካባቢ ...
05/09/2026

አዲስ ዓመትን ፅዱና ውብ በሆነ መልኩ እንቀበል!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ፅ/ቤት “አዲስ ዓመትን ፅዱና ውብ በሆነ ተቋም እንቀበለው!” በሚል መሪ ቃል በወረዳ 12 ቡልቡል አካባቢ የጽዳት ዘመቻ አካሄደ።

በጽዳት ዘመቻው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙላቱ ተገኝ፣ ጽዳት የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን ገልጸው፣ አዲስ አበባ በጽዳትና በውበት ከአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ለመሆን እየተራመደች መሆኗን ጠቁመዋል።

ይህንንም ለማሳካት መንግስት ያመነጨውን የጽዳት ንቅናቄ በመከተል ህብረተሰቡን በማስተባበር የተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በጽዳት ዘመቻው በትጋት እየተሳተፉ ላሉ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎችና መላው ህብረተሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

በዘመቻው ማጠቃለያ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ታደሰ፣ በዕለቱ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ የተሳተፉ አካላትን አመስግነው፣ በቀጣይ በሚከበሩ በዓላት ዙሪያ በርካታ የጽዳትና ውበት ንቅናቄዎች ስለሚካሄዱ ህብረተሰቡ ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ፅዱ ተቋም፣ ውብ አካባቢ፣ ደማቅ አዲስ ዓመት!
ቦሌ ነሐሴ 30/2018

በሰላም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ሁለንተናዊ ሰላም በእናንተ ቡርቱ ሰላም ወዳድ ጀግኖች ተጠናክሮ ይቀጥላል በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ  12 አስተዳደር በአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጠ...
04/09/2026

በሰላም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ሁለንተናዊ ሰላም በእናንተ ቡርቱ ሰላም ወዳድ ጀግኖች ተጠናክሮ ይቀጥላል

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር በአንድ ማዕከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጠ

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የሰላም ሰራዊት ስምሪት አጠቃላይ ከ6 ቀጠና ሰላም ሰራዊት በተገኙበት ስምሪት ተሰጥቷል ።

በስምሪት ወቅት የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግድ ሮሪሶ በሰላም ሰራዊት ስምሪት አቅጣጫ ላይ እንደተናገሩት አሁን ባለው በወረዳው የሰላም ሰራዊት እንቅስቃሴ በሁሉም መንገዶች ሆነው አከባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ ያሉ እየታዩ ሲሆን በወረዳችን ላይ ያለው ጥንካሬ በሁሉም የሰላም ቀጠናዎች መቀጠል እንዳለበት በተሞክሮነት አንስተዋል። በወረዳው የነበረው የሰላም ሰራዊት ስምሪትና የሰላም ሰራዊቱ አከባቢያቸውን ከፀጉረልውጥ ነቅቶ በመጠበቅ ያደረጉት ቁርጠኝነት የመስቀል ፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር አሁንም በተያዘው ግለት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል።

የወረዳው ብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ደጋሎ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታን ከመጠበቅ አንፃር እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ በጣም የተሻለ ነው ይህ ስራ በሁሉም ብሎኮች ላይ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የወረዳውም የድጋፍ እና ክትትል አግባብ ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት ለጋራ ሰላማችን በጋራ መትጋት የሁሉም ነዋሪ ሀላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል ።

በቀጣይም በጋራ በመሆን ተቋማትንና ግለሰቦችን በማስተባበር ተጨማሪ የሰላም ሰራዊት በሁሉም ቀጠና ሰላም ሰራዊት አባላት መጠናከር እንዳለባቸው ተናግሯል።

Address

Bole Bulbula 93 Mazoriya
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Woreda 12 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share