05/10/2021
የኢትዮጵያ ገጠር ኢነርጂ ልማትና ማስፋፊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሚካኤል ገሠሠ ማዕከሉን በማቋቋም እና በማደራጀት ያለፋትን ሁለት አመታት ያለመሰልቸት እንዲሁም የግል ሕይወታቸውን በመሰዋት ትልቅ አሻራ አኑረዋል። የማዕከሉ የማኔጅመንት አባላት በደረሰባቸው ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለሁሉም የስራ ባልደረቦቻቸው በመግለፅ ፈጣሪ አምላክ ለነፍሳቸው እረፍትን ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለማዕከሉ ሰራተኞች መጽናናትንና መረጋጋትን ያድለን።