Habtamu Taye

Habtamu Taye Donate Blood save life! Pledge cornea, don't burry it; it will restore sight of person in darkness!

28/05/2026
ለ1447ኛው ኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል እንኳን አደረሳችሁ!ለእስልምና እምነት ተከታይ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ሰራተኞች፣ ለደም ለጋሾች፣ እንዲሁም አይን ብሌናችሁን ለመለ...
26/05/2026

ለ1447ኛው ኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል እንኳን አደረሳችሁ!

ለእስልምና እምነት ተከታይ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ሰራተኞች፣ ለደም ለጋሾች፣ እንዲሁም አይን ብሌናችሁን ለመለገስ ቃል ለገባችሁ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች በሙሉ፤

ለ1447ኛው ኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል እንኳን አደረሳችሁ!

በዚህ የተባረከ የአረፋ ቀን፣ ሕይወት ለመታደግ እና ብርሃን ለመመለስ ላደረጋችሁት ክቡር አስተዋጽኦ ከልብ የመነጨ ምስጋናና ክብር አቀርባለሁ።

አረፋ የምህረት፣ የፍቅር፣ የመስዋዕትነት፣ የይቅርታ እና የሰብአዊነት ታላቅ ቀን ነው። እናንተም በምታደርጉት የደም እና የዓይን ባንክ አገልግሎት፣ በደም ልገሳ፣ በዓይን ብሌን ልገሳ እና በሕይወት ማዳን ሥራችሁ የብዙ ወገኖች ተስፋ ሆናችኋል።

በእናንተ ሰብአዊ አስተዋጽኦ፤
ታካሚዎች ሕይወታቸውን አራዝመዋል፣
ቤተሰቦች ተስፋ አግኝተዋል፣
ዓይነ ስውራንም ብርሃን አግኝተዋል።

አንድ ጠብታ ደም ሕይወትን ያድናል፤
አንድ የዓይን ብሌን ልገሳ ደግሞ ብርሃንን ይመልሳል።

በዚህ የተቀደሰ የአረፋ ቀን፣
ፈጣሪ መልካም ሥራችሁን ይቀበል፣
ዱዓችሁን ያሳካ፣
ለእናንተና ለቤተሰቦቻችሁ ጤና፣ ሰላም፣ ረህማ እና በረከት ያድርግላችሁ።

🌸 መልካም የአረፋ በዓል! 🌸

🩸 ደም ይለግሱ — ሕይወት ያድኑ!
👁️ የዓይን ብሌን ይለግሱ — ብርሃን ይመልሱ!

ለዓይን ባንካችን እንኳን ደስ አለን!በ“ዓለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ ብቃት” ዘርፍ የ“የሰብዓዊነት ዘውድ” (Crown of Humanity Award) ሽልማት በማግኘታችን ከፍተኛ ክብር ይሰማና...
23/05/2026

ለዓይን ባንካችን እንኳን ደስ አለን!

በ“ዓለም አቀፍ የጤና እንክብካቤ ብቃት” ዘርፍ የ“የሰብዓዊነት ዘውድ” (Crown of Humanity Award) ሽልማት በማግኘታችን ከፍተኛ ክብር ይሰማናል። ይህ እውቅና በአይን ብሌን ልገሳና በቀዶ ሕክምና አማካኝነት ተስፋን ለመመለስ፣ ሕይወትን ለመቀየር እና ብርሃንን ለማብራት ያለንን ቁርጠኝነት ያበረታታል።

ብሌን ይለግሱ፤ ብርሃንን ይመልሱ!!

Congratulations to our Eye Bank team!

We are honored to receive the Crown of Humanity Award under the theme of Global Healthcare Excellence. This recognition inspires us to continue restoring hope, transforming lives, and bringing light to those living in darkness through cornea donation and transplantation.

Pledge Cornea, Restore Sight.

12/05/2026


Adama city!!
10/05/2026

Adama city!!

Planted in October this year  city on 110 hectar!
08/05/2026

Planted in October this year city on 110 hectar!

ወንድሜ ሙሳ አህመድ ጋር የስራ አጋጣሚ አገናኘንና ምስራቅ ሸዋ ዞን አዳአ ወረዳ አስተዳደር በስጦታ አባ ገዳ አስመሰለን! ኢትዮጵያ የህብረብሄራዊ አንድነት ማሳያ!!
29/04/2026

ወንድሜ ሙሳ አህመድ ጋር የስራ አጋጣሚ አገናኘንና ምስራቅ ሸዋ ዞን አዳአ ወረዳ አስተዳደር በስጦታ አባ ገዳ አስመሰለን!

ኢትዮጵያ የህብረብሄራዊ አንድነት ማሳያ!!

እናመሰግናለን!
27/04/2026

እናመሰግናለን!

ክንዳችሁን ዘርግታችሁ ደማችሁን ለግሳችሁ ህይዎት የታደጋችሁ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች፣ ብሌናችሁን ለመለገስ እና ብርሃን ለመሂን ቃል የገባችሁ ቅን ልቦች፣ መላው የደም እና ህብረህዋስ ባንክ ...
12/04/2026

ክንዳችሁን ዘርግታችሁ ደማችሁን ለግሳችሁ ህይዎት የታደጋችሁ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች፣ ብሌናችሁን ለመለገስ እና ብርሃን ለመሂን ቃል የገባችሁ ቅን ልቦች፣ መላው የደም እና ህብረህዋስ ባንክ ቤተሰቦች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ አደረሰንፕ!

ዛሬ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል የነሳበት ታላቅ ቀን ነው።
ክርስቲስ በመስቀል የተሸነፈ ቢመስልም፤ ነገር ግን በትንሳኤ ሞትን አሸንፎ ለዓለም ሕይወት አመጣ!
“እርሱ እዚህ የለም፤ ተነስቶአል!” (ሉቃስ 24፡6) ትንሳኤ የፍቅር፣ የመስጠትና የሕይወት መልእክት ነው። ይህን በውል በመገንዘብ ደም በመለገስ ህይዎት ለታደጋችሁ እና ብሌን በመለገስ ብርሃን ለመለሳችሁ ወገኖች በዚህ በተከበረ ቀን ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ:: የደም እና አይን ብሌን ማሰባሰብ ስራ ቁርጠኛ እና ርሁሩህ ሰራተኛን ይፈልጋል፣ ከዚህ አንፃር የደም እና ህብረህዋስ ባንክ ሰራተኞች በማይመች ይስራ ከባቢ ሳይቀር ለወገናቸው በህይዎት መኖር ከፍተኛ ትጋት አድርገዋል፣ እያደረጉም ነው፣ ምስጋና ይድረሳችሁ!!
🩸 ደም መስጠት ሕይወት ማዳን ነው
👁️ የአይን ብሌን (ኮርኒያ) መስጠት ብርሃን መመለስ ነው
ትንሳኤን በፍቅር እና በመስጠት እናክብር
የእኛ ትንሽ ስጦታ ለሌሎች ታላቅ ሕይወት ሊሆን ይችላል

ትንሳኤው ሰላም፣ ጤናና ደስታ ወደ ቤታችሁ ያመጣ!
መልካም ፋሲካ!

እንኳን ለጌታ ስቅለት መታሰቢያ ቀን አደረሰን!የጌታ ስቅለት  የመከራ ታሪክ ብቻ አይደለም፤ የፍቅር፣ የመስዋዕትነት እና የቤዛነት መግለጫም ነው። ኃይል በክፉዎች እጅ ሲሆን፣ እውነት ግን በመ...
09/04/2026

እንኳን ለጌታ ስቅለት መታሰቢያ ቀን አደረሰን!

የጌታ ስቅለት የመከራ ታሪክ ብቻ አይደለም፤ የፍቅር፣ የመስዋዕትነት እና የቤዛነት መግለጫም ነው። ኃይል በክፉዎች እጅ ሲሆን፣ እውነት ግን በመስቀል ላይ እንኳን አይሸነፍም። በዚያ ቀን የተላለፈው መልእክት ግልፅ ነው—ኢፍትሀዊ ግፍ ጊዜያዊ ነው፣ እውነት ግን ዘላለማዊ ነው። ትንሳኤ ደግሞ የመጨረሻ መልስ ነው—ጨለማ ለጊዜው ያሸነፈ ሊመስለው ይችላል ግን ብርሃን መምጣቱ አይቀሬ ነው፤ ሞት መስሎ የታየው ለአዲስ ሕይወት መወለድ ምክኒያት ይሆናል።

Happy crucifixion commemoration day/Happy Good Friday!!

The crucifixion of Christ is not just a story of suffering—it is the ultimate expression of love, sacrifice, and redemption. When power falls into the hands of the unjust, truth may seem defeated—even nailed to a cross—but it is never destroyed. The message of that day is clear: injustice is temporary, but truth is eternal. And then comes the resurrection—the final answer. Darkness may prevail for a moment, but light will rise again. What seems like death gives birth to new life.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habtamu Taye posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Habtamu Taye:

Share