Addis Ababa City Administration Bureau of Finance

Addis Ababa City Administration Bureau of Finance Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa City Administration Bureau of Finance, Government Organization, ደጃች ውቤ ከአዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊትለፊት 1888 ህንፃ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ፎቅ ( Dejach Wube, in front of Addis Ababa Restaurant, 1888 Building, 4th to 6th Floor), Addis Ababa.

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል።ኢትዮጵያ ...
03/08/2026

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው።

መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል።

ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው።

ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል።

ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል ።

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

03/08/2026
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል...
03/08/2026

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሐ ግብር አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።

በዚህም ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል፡፡

በዚህ ደማቅ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ 26.2 ሚሊዮን ዜጎች በነቂስ ወጥተው እጅግ ከፍተኛ እና የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ የአንድ ጀምበር ተሳትፎ 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት የአረንጓዴ ዐሻራ መልበስ መቻሉን አስታውቀዋል፡:

03/08/2026

ከመረጃ ማዕከል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማጠቃለያ መልዕክት

03/08/2026

ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ላብ ደማቅ ታሪክ አስመዝግበዋል - የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ

እንበርታ!! ከተማችንን በአብሮነት እናልብስ!በዛሬው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር፣ ከተማችን አዲስ አበባ 1 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ ማልዳ የተነሳች ሲሆን፣ የከተማችን ...
03/08/2026

እንበርታ!! ከተማችንን በአብሮነት እናልብስ!

በዛሬው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር፣ ከተማችን አዲስ አበባ 1 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ ማልዳ የተነሳች ሲሆን፣ የከተማችን ነዋሪ “ተስፋን መትከል የሁላችን ዋነኛ ሀላፊነት ነው!” በሚል ስሜት ባሳየው ጠንካራ ርብርብ እስካሁን ከዕቅዳችን በላይ 1.4 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ባለቤትነቱን በተግባር አሳይቷል።

አሁንም ቢሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች ይህንን የጀመርነውን እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ርብርባችንን በማስቀጠል፤ የከተማችንን ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ አሻራ ማኖራችንን ጠንክረን እንቀጥል፣ እንበርታ እላለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ 700 ሚሊዮን ቸግኞች ተተክለዋል፡- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ***************ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ...
03/08/2026

እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ 700 ሚሊዮን ቸግኞች ተተክለዋል፡- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ
***************

ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በያዙት ታሪካዊ ሀገራዊ ዕቅድ መሠረት ከማለዳው ጀምሮ በከፍተኛ ንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ የዕለቱን የችግኝ ተከላ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ 700 ሚሊዮን ቸግኞች መተከላቸውን አስታውቀዋል።

ቢሮዉ “ተስፋን እንትከል “በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡ # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #ፋይናንስ ቢሮ ሐምሌ ...
03/08/2026

ቢሮዉ “ተስፋን እንትከል “በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
ፋይናንስ ቢሮ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ፋይናንስ ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ አመራርና ሰራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘውን በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አካሄደ፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን !!
ዌብሳይት:- aabof.com.et
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP
ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA
ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu

03/08/2026

በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እስከ ቀኑ 8 ሰዓት ድረስ 650 ሚሊዮን ችግኝ ተተክሏል”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Address

ደጃች ውቤ ከአዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊትለፊት 1888 ህንፃ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ፎቅ ( Dejach Wube, In Front Of Addis Ababa Restaurant, 1888 Building, 4th To 6th Floor)
Addis Ababa
2PMW+RWADDISABABA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa City Administration Bureau of Finance posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share