Mega Projects Construction Office

Mega Projects Construction Office It's All About Mega Projects Construction in the City Government of Addis Ababa

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት መርቀው አገልግሎት ያስጀመሯቸው በአራት ኪሎ ፕላዛዎች :4ኪሎ የገበያ ማእከል እና የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክቶች- በምስል
01/08/2025

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት መርቀው አገልግሎት ያስጀመሯቸው በአራት ኪሎ ፕላዛዎች :4ኪሎ የገበያ ማእከል እና የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክቶች- በምስል

31/07/2025
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነገ ሀምሌ 24 ለተመሳሳይ አለማ በነቂስ ወጥቶ አሻራውን ያኖራል!በነገው ዕለት ከማለዳው አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ሁሉም ኢት...
30/07/2025

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነገ ሀምሌ 24 ለተመሳሳይ አለማ በነቂስ ወጥቶ አሻራውን ያኖራል!

በነገው ዕለት ከማለዳው አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከያለበት በነቂስ ወጥቶ አረንጏዴ አሻራውን ያኖራል::

“በመትከል ማንሰራራት” የሚለውን መሪ ቃል አንግበን ህፃን አዋቂ ሳንል ሁላችንም ኢትዮጵያውያን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተባብረን አሻራችንን እናኑር፡፡

አዲስ አበባ ከተማችንም በነገው እለት የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ቅድመ ዝግጅት አጠናቃለች::

24/07/2025

በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ አንዳንዶች ያልተገባ አስተያየት ሲሰጡ ተሰምቷል፡፡

በትላንትናው ዕለት የተከሰተው ጎርፉ ወቅቱን ጠብቆ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታ ላይ በነበረው ጊዮን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመሙላቱ እና የተሰራለትን ጊዜያዊ ግድብ ጥሶ በመውጣቱ ሆኖ ሳለ አንድንድ ግለሰቦች ግን ወቅቱን ያላገናዘበና ከእውነት የራቀ አስተያየት ሲሰጡት ተሰምቷል፡፡

ይሁን እንጂ መላው ህብረተሰባችን እንደሚረዳው አዲስ አበባ የነበራትን አስቸጋሪ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት እንደ አዲስ በመገንባት የተሰራውን ስራ አስተማማኝ መፍትሔ እና በቀጣይም ተጠናክሮ በመላው ከተማዋ ዳርቻ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ሥራ እና ሙያዊ መፍትሔ ነው። ያም ሆኖ ይህን መያዊ እና መሠረታዊ ሥራ ወደ ጎን በመተው አንዳንዶች ያልተገባ ስ ያሜ ሰጥተውታል፡፡

መላው ህብረተሰብ እና የከተማችን ነዋሪ ወቅቱን እና እንዲሁም አዲስ አበባ አሁንም በበርካታ ግንባታዎች ላይ መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምንጩ ካልታወቀ የተዛበ መረጃ እራሱን በመጠበቅ ትክክለኛውን እና ሚዛናዊ የሆነውን መረጃ እንዲመረምር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሜቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ወቅቱን በማስመልከት የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ እራሱን ከጎርፍ አደጋ እንዲጠብቅ እናሳስባለን ፡፡

በመጨረሻም ማህበረሰባችን እየጣለ ያለውን ዝናብ እና ወቅቱን እንዲሁም በከተማዋ እየተሰራ ያለውን ግንባታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ጎርፍ የመከላከል ስራው አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ከተማው በሚያደርገው የመከላከል ሥራ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን::

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication

21/07/2025
20/07/2025
ከሁሉም በላይ የረዳን ፈጣሪ የተመሰገን ይሁን !በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸዉን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግልሎት ክፍት አድርገናል ።ፕሮ...
18/07/2025

ከሁሉም በላይ የረዳን ፈጣሪ የተመሰገን ይሁን !

በ2017 በጀት አመት በ5 .2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸዉን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግልሎት ክፍት አድርገናል ።

ፕሮጀክቶቹ በጥራትና ደረጃቸዉን ጠብቀዉ የተሰሩ 14 አዳዲስ ትምህርትቤቶች ፤ በ64 ነባር ትምህርትቤቶች ላይ ማስፋፋያ የተገነቡ 1655 የመማሪያ ክፍሎች ፣ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፅሀፍቶች ፣ የስፖርት ሜዳዎች ፣ ምድረጊቢዎችን ፅዱ ፣ ዉብ የማድረግ ፣የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎት ጨምሮ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና መምህራን ምቹ የማድረግ ስራዎችን ያካተተ ነዉ፡፡

ትውልድን ለማነጽ በተሰራው ስራ አብራችሁን የሰራችሁትን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩኝ እነዚህ ትምህርትቤቶች የእናንተ እና የልጆቻችሁ ሀብት በመሆናቸው እንድትንከባከቧቸው አደራ እላለሁ፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቁ የፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የሕዝባችንን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በመንግስትና በህብረተሰብ ተሣትፎ 15‚69ዐ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ የተቻለ ...
11/07/2025

በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቁ የፕሮጀክቶችን አስመልክቶ
የሕዝባችንን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በመንግስትና በህብረተሰብ ተሣትፎ 15‚69ዐ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፤ ካቀድነው በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡
👉 205 በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የተለያዩ ኘሮጀክቶች
👉 8,786 በበጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶች
👉 5,176 በከተማ አስተዳደር የተገነቡ ቤቶች
👉 1064 የመስሪያ ሼዶች
👉 5,563 ሱቆች / ካዛንቺስ፣ ቦሌ፣ ላፍቶ፣ ልደታ፣ አራዳ እና አራት ኪሎ ሽሮሜዳ/ የተገነቡ
👉 1,155 የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች
👉 122 የእስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳዎች
👉 245 የአረንጓዴ ልማት ስራ
👉 153 የመኪና ፓርኪንጎችና ተርሚናሎች
👉ከዚህ ውስጥ 16 ቱ ሜጋ ኘሮጀክቶች ሲሆኑ ወደ 9ሺ ኘሮጀክቶች በህብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ናቸው፡፡

Address

Addis Ababa 4 Kilo Nib Bank Building 6th And 7thFloor
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mega Projects Construction Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mega Projects Construction Office:

Share