Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን

Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን, Government Organization, Addis Ababa.

03/09/2026
መጪውን የአዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፈተነሐሴ 28/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽንበየካ ክፍለ ከተማ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመል...
03/09/2026

መጪውን የአዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ተከፈተ

ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽን

በየካ ክፍለ ከተማ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል አስመልክቶ "መሠረታዊ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰባችን በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ የበዓል ባዛር ተከፍቷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ግዛው ባዛሩ ሻጮችንና ሸማቾችን በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ የግብይት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ውጤታማና አጥጋቢ የግብይት ሥርዓት እንዲሰፍን የሁሉም አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ዶ/ር ኤፍሬም ባዛሩ በሰላማዊና ሥርዓት በተሞላበት መልኩ እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት በበኩላቸው፣ ባዛሩ ለነዋሪዎችና ለአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት የሚያግዝ፣ የግብይት ሥርዓቱን የሚያሻሽልና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል።

የባዛሩ ዓላማ በሸማቾች እና በአምራቾች መካከል ቀጥተኛ የግብይት ሥርዓትን በማጠናከር የምርት አቅርቦትን ማሳደግና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰቡ ማቅረብ መሆኑን ያመለከቱት አቶ እንዳልካቸው፣ ለባዛሩ ስኬታማ አፈጻጸም የተረባረቡ አካላትን በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

ባዛሩ በቀጣይም በቅንጅትና በተቀናጀ አሠራር እንዲጠናከር አስፈላጊው ሥራ በየደረጃው መከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የተከፈተው የበዓል ባዛር እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ የክፍለ ከተማው ንግድ፣ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ህብረት ሥራ፣ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና እንዲሁም ሥራና ክህሎት ተቋማት በጋራ በመሆን የባዛሩን አገልግሎት እያስተባበሩ ይገኛሉ።

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው**********************የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ አክት...
03/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው
**********************

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ አክት ፎር ኤርሊ ይርስ ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

እውቅናው የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደ ፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት እንደሚሠራ ተመላክቷል።

እውቅናው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን፣ ዩኒሴፍ እና ዩኔስኮን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

ለከንቲባዋ የተሰጠው እውቅና አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክር መታመኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

02/09/2026

በየካ ክፍለ ከተማ ባሉ የሸማች ሱቆች እና የሰንበት ገበያ ማዕከላት ለመጭው ዓዲስ ዓመት የበዓል የፍጆታ ዕቃዎች በብዛትና በጥራት ቀርበዋል።

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎችጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”
02/09/2026

የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች

ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”

ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”

ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”

ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”

ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላ...
02/09/2026

እየተጠናቀቀ ያለው ዓመት ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ።

እየተጠናቀቀ በሚገኘዉ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ እንደምትገኝ የሚያመላክቱ ስኬቶችን እንዳስመዘገበች የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ አገልግሎቱ የዘንድሮ የጳጒሜን ቀናት የሚከበሩበትን ዓውድ፣ የቀናቱን ስያሜ እና መሪ መልእክት ይፋ ያደረገበትን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫዉን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጳጒሜን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ወር ብሎ ለማክበር የሚያስችሉ ስኬቶች እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መመዝገባቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ቴክኖሎጂ ነክ ዓመታዊ ስኬቶችን በመግለጫቸዉ ያነሡት ሚኒስትር ድኤታዉ የጳጒሜን ቀናት በልዩ ልዩ ስያሜዎች እና ኹነቶች ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡ አካታች፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተሳተፉበት ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተካሄደበት፣ ኅብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ አካታች እና የነበሩ ልዩነቶችን በመፍታት የጋራ ትልሞች ላይ እንዲተኮር የሚያስችል ሀገራዊ ምክክር በስኬት የተጠናቀቀበት፣ የውስጥ አንድነቷ የተጠናከረ እና የዲፕሎማሲ ዐቅሟ ያደገች ኢትዮጵያ የታየችበት ዓመት እንደነበር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንጻር የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በወቅታዊ ዓለማቀፋዊ ቀውሶች ጭምር ታልፎ ስኬት የተመዘገበበት፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር የተቻለበት፣ የዕዳ ጫና በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰበት፣ ገቢ የመሰብሰብ ዐቅም ከ1.5 ትሪሊዮን ብር የተሻገረበት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና የውጭ ምንዛሪ ግኝት ታሪካዊ ዕድገት ያስመዘገበበት፣ የወጪ ንግድ ገቢ ከ10.2 ቢሊዮን ዶላር የተሻገረበት፣ በአንድ ዓለማቀፍ የኢንቨስትመንት ፎረም ብቻ ከ13.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመበት እና በአብዛኛዉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ማውጣት ደረጃ የተሸጋገሩበት፣ የግብርና ምርት እና ምርታማነት በጋ ከክረምት በግብዓት አቅርቦት ታግዞ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበት ስኬታማ ዓመት ነበር፡፡

የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ ከ100 በላይ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎቶች የተስፋፉበት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን በፅኑ መሠረት የሚያስቀምጥ እና ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጎለብት ስኬታማ ምክክር የተደረገበት፣ የሕዝቡን የማኅበራዊ መሻቶች ለማሳካት ሰፋፊ የበጎ አድራጎት እና የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የተከወኑበት በውጤቱም ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበት ዕድገት ማሸጋገር የተቻለበት ዓመት እንደነበር ክቡር አቶ ከበደ በመግለጫቸዉ አመላክተዋል፡፡

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ ግዙፍ መሠረታዊ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት እና ዐዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ወደ ግንባታ በማስገባት የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶችንም ዳስሰዋል፡፡ የዐፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የቢሾፍቱ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጀመር ከሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በክቡር ሚኒስትር ድኤታዉ በአብነት ተነሥተዋል፡፡ እነዚህን ስኬቶች፣ ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና በዕቅድ ከተያዙ ሀገራዊ ትልሞች ጋር በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በማንሰራራት ላይ መኾኗንም አመላክተዋል፡፡
የጳጒሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል የጋራ መሪ መልእክት ይከበራሉ፡፡
ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፣
ጳጉሜን 2 - የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜን 3 - የጽናት ቀን፣
ጳጉሜን 4- የኅብር ቀን እና
ጳጉሜን 5 - የነገ ቀን በሚሉ ስያሜዎች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከበሩ ያስታወቁት ሚኒስትር ድኤታዉ ለዚህም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በዐዲስ ዓመት ለግል ስኬቶቻቸዉ እንደሚያቅዱት ኹሉ ለኹለንተናዊ ሀገራዊ ብልጽግናም የሚጫወቱትን ሚና ታሳቢ እንዲያደርጉ፣ የመንግሥትን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም ዕቅድ ተገንዝበዉ ተሳትፏቸዉን እንዲያሳድጉ ለማነሣሣት ቀናቱ እንደሚከበሩም ገልጸዋል፡፡ የጳጒሜን ቀናቱን ስያሜ መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች፣ የበጎ አድራጎት እና ማዕድ ማጋራት ተግባራት፣ ነፃ ጤና ምርመራ፣ የደም ልገሳ፣ የፓናል ውይይት እና መሰል መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩም አስታውቀዋል፡፡

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን:

Shortcuts

Share