06/05/2025
የአዲስ ከተማ እግር ኳስ ቡድን በ3ኛ ዙር የውድድር መርሐ ግብር 1ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋገጠ::
*****************
ሚያዚያ 28-2017ዓም
በኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ እየተሳፈ የሚገኘዉ የአዲስ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በ1ኛ እና በ2ኛዉ ዙር ዉድድር 2ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመቀላቀል የ3ኛ ዙር የውድድር መርሃ-ግብር 1ኛ ደረጃ በመያዝ ወደ ቀጣዬ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም እንዳሉት በ1ኛ ሊግ ዉድድር መርሀ ግብር ተሳታፊ ከነበሩ ክለቦች አዲስ ከተማ ከአቃቂ ቃሊቲ ጋር ለዋንጫ በማለፉ የተደለደለ መሆኑን እና ለዋንጫ ወይም ለደረጃ ከደረሰ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚቀላቀል ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ዮናስ አክለውም መርኬዎቹ እያስመዘገቡት ያለው ውጤት የሚገባቸውና የልፋታቸው ውጤት መሆኑን ጠቅሰው ባስመዘገቡት ውጤት ሳይኩራሩ ለበለጠ ውጤት መትጋትና መረባረብ እንደሚገባቸውና የስፖርቱ ማህበረሰብ በየጫወታው በመገኘት የተለመደውን ሞራላዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል::