21/04/2026
አራቱ የዓለም ወሳኝ የባሕር ሠርጦች (Straits):
1ኛ/ የሆርሙዝ ሠርጥ (Hormuz):
በኢራን እና ኦማን መካከል የሚገኝ የዓለም የነዳጅ ማዕከል። ኢራን ይህንን ሠርጥ በመዝጋትና "የባሕር ላይ ክፍያ" (Tolls) በመጠየቅ ዓለምን እያስጨነቀች ትገኛለች።
2ኛ/ ባብ ኤል-ማንደብ (Bab-el-Mandeb):
በኤርትራ፣ በየመን እና በጅቡቲ መካከል የሚገኝ። ለኢትዮጵያ እጅግ ቅርብ እና ወሳኝ የሆነው ይህ ሠርጥ ከተዘጋ፣ ወደ አውሮፓ የሚሄደው የንግድ መስመር ሙሉ በሙሉ ይቆማል።
3ኛ/ የማላካ ሠርጥ (Malacca):
በደቡብ ምስራቅ እስያ የሚገኝ የዓለም ትልቁ የንግድ መስመር። ቻይናን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ የኢኮኖሚ ዋስትና ነው።
4ኝ/ የጊብራልታር ሠርጥ (Gibraltar):
አትላንቲክ ውቅያኖስን ከሜዲትራኒያን ባሕር ጋር የሚያገናኝ የአውሮፓ እና አፍሪካ መገናኛ በር።
⚖️ የአሰብ እና የኢትዮጵያ የባሕር በር መብት!!
ኢራን የሆርሙዝን ሠርጥ ተጠቅማ በዓለም ላይ ተጽዕኖ ስትፈጥር ስናይ፣ እኛም አንድ ትልቅ እውነት እናስታውሳለን።
የባሕር በር የሌለው አገር ህልውናው አደጋ ላይ ነው የሚለው የትውልድ ጥያቄ ነው።
ኢትዮጵያ በታሪካዊ እና በሕግ አግባብ የአሰብ ወደብ ባለቤት መሆን አለባት።
#አሰብ ከባብ ኤል-ማንደብ ሠርጥ 50 ኪ.ሜ ብቻ የምትርቅ "የቀይ ባሕር በር ጠባቂ" ናት። 130 ሚሊዮን ሕዝብ ያለው አገር ያለ ባሕር በር መቅረቱ ታሪካዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሃዊነት የጎደለው የዓለም አቀፍ ሕግ ውጤት ነው።
የኢትዮጵያ ትንሣኤ መልእክት!
ኢትዮጵያ በሕግ አግባብ የራሷን በር (አሰብን) የማግኘት መብቷ ሊከበር ይገባል የሚለው የብልህ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው።
የባሕር በር የቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚ ነፃነት እና የብሔራዊ ደህንነት ዋስትና ነው የሚባለው ለሀቀኛ ኢትዮጵያውያን የትንሣኤ ናፋቂ መልዕክት ነው!