21/04/2020
የሶማሊ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ሶስተኛው እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ የሚገኝበት ብሔር ነው፣ እና የሶማሊ ክልላዊ መንግስት ከ9 የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ ሁለተኛው ትልቁ እና የምስራቅ መጨረሻ ጫፍ ነው፡፡
በተመሳሳይ የሶማሊ ክልል በትሪሊየን ኪውቢክ ሜትሮች መጠን የሚገመት ከፍተኛ ተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ ሀብት በሰፊው የመሬት ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡ የኦጋዴን ተፋሰስ በሱማሌ ክልል ውስጥ የሚገኝ ቦታ ሲሆን፣ ጉልህ መጠን ያለው የድፍድፍ ነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የያዘ ነው፣ እና ይህ ሸለቆ የተወሰኑ ወይም አብዛኛውን የክልሉን ቦታዎች ይሸፍናል፡፡ በተጨማሪም ከሌሎች በመከላለኛው ምስራቅ የሚገኙ በሃይድሮ ካርቦን ሀብት ከበለጸጉ ሸለቆዎች ጋር ተመሳሳይ የሆነ የጂኦሎጂያዊ ተመሳሳይነት አለው፡፡
በዚህም ምክንያት ክልሉ ለብሔራዊ ኢኮኖሚ እጅግ በጣም ቁልፍ የሆነ ስትራቲጂካዊ ቦታ ነው፡፡ ክልሉ ግዙፍ የሆነ የመሬት ስፋት ያለውነ ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶች እና እንደ የተፈጥሮ ጨው የመሳሰሉ የበለጸጉ ሚኒራሎችን የተትረፈረፈበት ክልል ነው፡፡ በተጨማሪም፣ የኦጋዲን ሸለቆ ባለው ትልቅ አስፈላጊ ሀብቶች ብዛት እና እጅግ በጣም ስትራቴጂካዊ የሆነ ወደ ሀገር ውስጥ የሞገቡ እቃዎች ማጓጓዣ ምክንያት ሱማሊ ክልል በአሁኑ ጊዜ ባለው ብሔራዊ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ውስጥ ግንባር ቀደምሆኖ ይሰለፋል፡፡ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሀገር ብልጽግና አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ያበረክታል ይሁን እንጂ ክልሉ ካለው ግዙፍ የመሬት ስፋት እናሀብቶች መኖር መሁኔታ አንጻር ሲታይ እንዲሁም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ህዝቦች መካከል ሶስተኛው ትልቁ ህዝብ ብዛት ያለው ክልል ቢሆንም፣ የሶማሌ ህዝብ ለዘመናት ያደረገው ፖለቲካ ተሳትፎ ድርሻ በጣም አናሳ ነው፡፡
ለዘመናት ክልሉ በግጭት የተጠቃ ክልል ነበር፣ እና ህዝቡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የውጪ ስደተኞች ፍሰት አጋጥሞታል፡፡ ክልሉ ለበርካታ አመታት የደህንነት ችግር ስጋት ያለበት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህም በነገስታት እና በደርግ አገዛዝ የፖለቲካ ሪኦተ አለም ነበር፡፡ የሶማሌ ክልል ህዝብ አስፈላጊ እንዳልሆነ ሁሉ እጅግ በጣም ተገፍቶ እና በአሉታዊ ሁኔታ ሲታይ ነበር፡፡
ክልል ለዘመናት የወታደራዊ እንቅስቃሴ ቦታ እና የጦርነት ቦታ በመሆኑ እንዲሁም ክልሉ ያልተረጋጋ የፖለቲካ አከባቢ የሰፈነበት ሆኖ በመቆየቱ፣ በመጨረሻ ህዝቡ በክልሉ ላይ ያለውን ጥሩ መንፈስ እንዲጣ አድርጎታል እና የሶማሊ ህዝብ በተደጋጋሚ እና በተከታታይ በተደረጉት ጦርነቶች እና የፖሊቲካ ጭቆና እና የመሪዎች አምባገነነት ምክንያት ተስፋ ቆርጦ ቆይቷል፡፡ ስለዚህ የክልሉ ህዝብ 21ኛውን ክፍለ ዘመን የእረፍት የለሽ እና ሀዘን ምልክት አድርጎ አስቀምጦታል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ከራሳቸው መሬት የተባረሩበት፣ እጅግ በጣም ከባድ በሆነ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ የተፈረደባቸው እና ርህራሄ በሌለው ፊውዳል ፖለቲካ ምክንያት ማንነታቸውን ጠብቀው የመኖር መብት የተከለከሉበት እና ባህላቸውን ተግባራዊ እንዳያደርጉ ወይም እንዳያስፋፉ ተተከለከሉ በመሆኑ ነው፡፡
ይሁን እንጂ እጅግ በጣም ሰፊ የነበረው የፖለቲካ ጫና እና አምባገነኖች እንዲሁም በነበረው አድሎ ምክንያት፣ የሶማሌ ህዝብ ምንም ዓይነት ካሳ ወይም ጉዳት ህክምና አላገኘም፡፡ ይህም ማለት፣ የሶማሌ ህዝብ ካሳ እና ጉዳት ህክምና ለዘመናት ተከልክሎ የነበረውን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ከማግኘት ሌላ ምንም ማለት አይደለም፡፡
ህዝባችንነ ካለበት የአለመግባባት ደረጃ ለማውጣት እና ወደፊት ለመጓዝ ተገቢውን እርምጃ እንዲጀምር ለማድረግ፣ ልዮነቶችን ወደ ጎን በመተው እና በጋራ በመስራት እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም መንግስት ለህዝቡ ጥቅም በማገልገል የሚደረግ እውነተኛ የሶማሌ ህዝብ አንድነት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ስለዚህ፣ ሉዓላዊነቱን ለመጠበቅ፣ ለፖለቲካ መብቶቹ ለመቆም እና የሶማሌ ህዝብን የጋራ ጥቅም ወደ ፊት ለማራመድ፣ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ሃይል የተሞላ እና በክልል ውስጥ ለሶማሌ ህዝብ መብቶች ትግል ለማድረግ የሚቆም የሶማሊ አርበኞች ፓርቲ መመስረት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ ፓርቲ በዴሞክራሲ መርሆች የሚገዛ ሆኖ በፓርቲው ፕሮግራም ውስጥ እንደተጠቀሰው አላማዎቹን ለማሳካት የሚታገል ነው፡፡