National ID Ethiopia

National ID Ethiopia መታወቅ ለመተማመን! Identity is the new collateral!
(9)

04/09/2026

የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥራችሁን (Fayda FAN) በመጠቀም፤ ወደ ትምህርት ቤት በአካል መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በቀላሉ መምረጥ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

ለመምረጥ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ፡ https://student.ethernet.edu.et/

Foreign nationals residing in Ethiopia are required to present documents proving their legal residency in the country to...
04/09/2026

Foreign nationals residing in Ethiopia are required to present documents proving their legal residency in the country to register for the Fayda Digital ID.

1. Foreign Nationals of Ethiopian Origin
• Valid Ethiopian Origin ID
• Valid Passport
2. Foreign Nationals
• Valid Residence Permit or Work Permit
• Valid Passport
3. Valid Refugee ID
4. Diplomats or foreign national employees of intergovernmental organizations, or international organizations with diplomatic privileges residing in Ethiopia: Valid Diplomatic ID issued by the Ministry of Foreign Affairs.
5. New Foreign Investors in the process of obtaining an investment license:
• Valid Passport
• Investment Visa
• Support letter issued by the Ethiopian Investment Commission
6. Foreign investors licensed to invest in Ethiopia as a Sole Proprietor or a One-Member Private Limited Company (PLC):
• Valid Passport
• Investment License
7. Foreign investors who have invested in a Share Company:
• Valid Passport
• Investment License
• Shareholder Certificate
8. Foreign investors who have invested in a Private Limited Company (PLC):
• Valid Passport
• Investment License
• Memorandum of Association (Founding Document)

Please Note:
1. All documents listed under each investment category above must be submitted together. Presenting only one document individually is not sufficient for the registration process.
2. The applicant must appear in person to provide biometric data (fingerprints, iris scan, and facial photo).

***************************

በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ በሀገሪቱ ሕጋዊ ነዋሪነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
እነዚህም፥
1. የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጲያውያን
• የፀና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታውቂያ (Ethiopian Origin ID)
• የፀና ፓስፖርት
2. ለውጭ አገር ዜጎች
• የፀና ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሕጋዊ የስራ ፈቃድ
• የፀና ፖስፖርት
3. የፀና ስደተኞች መታወቂያ
4. በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ የውጭ አገራት፣ የበይነ መንግስታት ድርጅቶች ወይም የዲፕሎማቲክ ልዩ መብት ያላቸው የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዲፕሎማቶች ወይም ሠራተኞች ከውጭ ጉዳይ የሚሰጥ የፀና የዲፕሎማቲክ መታወቂያ።
5. የኢንሸስትመንት ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ ላሉ አዲስ የውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች (New Foreign Investors)
• የፀና ፓስፖርት ፣
• የኢንቨስትመንት ቪዛ፣ እና
• ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ
6. የኢንሸስትመንት ፈቃድ ላለው የግል ኢንቨስተር / Sole Proprietor / ወይም በአንድ አባል የተመሰረተ የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (One-Member Company) ደረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃድ ያገኘ የውጭ ባለሀብት ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሰነዶች:
• የፀና ፓስፖርት (ህጋዊና ጸንቶ የሚገኝ)
• የኢንቨስትመንት ፈቃድ
7. የአክሲዮን ማህበር (Share Company) ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ባለሀብት ለመመዝገብ የሚያሰፈልጉ ሰነዶች:
• የፀና ፓስፖርት፣
• የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ እና
• የባለአክስዮንነት ማረጋገጫ
8. ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ የውጭ ባለሀብት ለመመዝገብ የሚያሰፈልጉ ሰነዶች:
• ፓስፖርት (ህጋዊና ጸንቶ የሚገኝ)፣
• የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ እና
• የመመስረቻ ሰነድ

ያስተውሉ
1. በእያንዳንዱ ከላይ በተጠቀሱት የኢንቨስትመንት አይነቶች ስር የተዘረዘሩት ሰነዶች በሙሉ (በአንድነት) መቅረብ አለባቸው። አንዱን ሰነድ ብቻ ነጥሎ ማቅረብ ለምዝገባው ሂደት በቂ አይደለም።
2. የባዮሜትሪክ መረጃ (የጣት አሻራ፣ የዓይን አሻራ እና የፊት ፎቶ) ለመስጠት ተመዝጋቢው በአካል መገኘት ይኖርበታል።

የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ በኦሮሚያ ክልል፤ ነገሌ ቦረና ከተማ እናት ልጆቿን ለፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማገዝ ላይ  #ፋይዳቨርስ  #ፋይዳለሁሉም
29/08/2026

የፋይዳ የሳምንቱ ፎቶ፡ በኦሮሚያ ክልል፤ ነገሌ ቦረና ከተማ እናት ልጆቿን ለፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማገዝ ላይ

#ፋይዳቨርስ #ፋይዳለሁሉም

Fayda, has been shortlisted as a finalist in the Digital Government category at the Digital@UNGA Awards, alongside leadi...
27/08/2026

Fayda, has been shortlisted as a finalist in the Digital Government category at the Digital@UNGA Awards, alongside leading international peers.

A great testament to the remarkable impact of and in building an inclusive, trusted, and digitally empowered future for the nation.

United Nations Development Programme - UNDP ITU

“Fayda ID gives me an identity in society. I am no longer just a refugee, and now even my two sons who have just graduat...
25/08/2026

“Fayda ID gives me an identity in society. I am no longer just a refugee, and now even my two sons who have just graduated are looking for jobs.” Said Zahra Abdi, a Somalian refugee

See how is opening doors to basic services and economic opportunities for refugees across .

The Ethiopian government, partnered with UNHCR, is integrating refu...

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል (ልደት) በሰላም አደረስዎ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንልዎ እንመኛለን! #ፋይዳቨርስ   #ዲጂታልኢትዮጵያ203...
25/08/2026

እንኳን ለ1501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል (ልደት) በሰላም አደረስዎ።
በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንልዎ እንመኛለን!

#ፋይዳቨርስ #ዲጂታልኢትዮጵያ2030 #መውሊድ

Digital transformation in the Global South is changing. We’re moving toward technical sovereignty through peer-to-peer c...
24/08/2026

Digital transformation in the Global South is changing. We’re moving toward technical sovereignty through peer-to-peer collaboration. Our latest article dives into how Ethiopia is inspiring this shift, using open-source tools and local talent to build scalable, secure digital public infrastructure.

Read full article here

By Abiy Solomon and Eyob Alemu Buba For many years, the global playbook for digital transformation followed a familiar script across the Global South where inv…

ቀላል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የማንነት ማረጋገጥ ስርዓት በፋይዳቨርስ! ላለፉት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሥር ተቋቁሞ በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ ነዋሪዎችን የፋይዳ ...
22/08/2026

ቀላል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የማንነት ማረጋገጥ ስርዓት በፋይዳቨርስ!

ላለፉት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሥር ተቋቁሞ በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ ነዋሪዎችን የፋይዳ መታወቂያ ሲመዘግብና ለተለያዩ ተቋማት የማረጋገጥ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ፕሮጀክት፣ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ይህንኑ ሥራ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማዳረስ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። በቅርቡ ደግሞ ይበልጥ ዘመናዊ ወደሆነ አዲስ ምዕራፍ በመሸጋገር "ፋይዳቨርስ" (FaydaVerse) በመባል በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥር የልማት ድርጅት ሆኖ በመቋቋም ለሀገር ውስጥና ለአፍሪካ ሀገራት ለሚገኙ ተቋማት ዘመናዊ፣ አስተማማኝ እና ፈጣን የዲጂታል ማንነት ማረጋገጫ አገልግሎትን እያቀረበ ይገኛል።

ይህን የማረጋገጥ አገልግሎት ሲሰጥ ወደ ተጠቃሚ ኪስ የማይደርስ ክፍያ እንዲሁም ለባንኮች፣ ለቴሌኮም እና ለሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት (Service Providers) ከዚህ ቀደም ከሚያወጡት የኤሌክትሮኒክ ደንበኛህን እወቅ (eKYC) ወጪ ከ95% በላይ ቅናሽ ያደረገ እጅግ አነስተኛ የሆነ ዋጋን ይዞ ቀርቧል። ክፍያው ተቋማት ባከናወኑት የማረጋገጥ አገልግሎት (Authentication Transactions) መጠን (Pricing Tier) መሠረት የሚወሰን ይሆናል።

በፋይዳቨርስ የማረጋገጥ አገልግሎት የምንሰጥባቸው መንገዶች ምን ምን ናቸው?

* OTP (የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል) ፡ በደንበኛው ስልክ ቁጥር ወይም ኢሜይል አድራሻ የሚላክ፣ ፈጣንና ቀጥተኛ የማንነት ማረጋገጫ መንገድ ነው

* TOTP (Time Based One Time Password ወይም በጊዜ የተገደበ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል)፡ የፋይዳፓስ የሞባይል መተግበሪያን ተጠቅሞ በየ30 ሰከንዱ በክሪፕቶግራፊ* የሚቀያየር ኮድ በማግኘት እንደ አንድ ጊዜ የይለፍ ቃል መጠቀም የሚያስችል መንገድ ነው

* ባዮሜትሪክስ (የፊት ወይም የጣት አሻራ)፡ የደንበኛን "የፊት ገጽታ" ወይም "የጣት አሻራ" በመጠቀም የግለሰቡን ትክክለኛ ማንነት በማረጋገጥ አገልግሎትን በቅጽበት መስጠት የሚያስችል መንገድ ነው

እነዚህን የማረጋገጥ አገልግሎች መንገዶች በመጠቀም የሚሰጡ አገልግሎቶችስ ምንድናቸው?

1. የ (Yes/No) ማረጋገጥ አገልግሎት፡ ደንበኞች ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሰጡት መረጃ ከብሔራዊ የመረጃ ቋት ጋር መዛመዱን ብቻ በማረጋገጥ "አዎ፣ ይዛመዳል" ወይም "አይ፣ አይዛመድም" (Yes/No) ምላሽ በመስጠት ብቻ የደንበኛውን መረጃ ደህንነት በመጠበቅ ቀላል ማረጋገጫ ነው

2. የኤሌክትሮኒክ ደንበኛህን እወቅ (eKYC) አገልግሎት ሲሆን ደንበኛው እንደከዚህ ቀደም ፎርም መሙላት ሳይጠበቅበት መረጃውን ከመረጃ ቋት በማግኘት የሚያደርገው ማረጋገጫ ነው

ያስተውሉ፡ ሁሉም የማረጋገጥ አገልግሎትች በደንበኛው ጥያቄ እና ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ብቻ ነው።

20/08/2026

አዲስ ነገር ይዘን መጥተናል!

የፋይዳ መተግበሪያ (Fayda App) ከዚህ ቀደም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ አዳዲስ አማራጮችን አካትቶ መጥቷል።

ከፋይዳ ጋር ተያይዘው የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡንን ማስረጃዎች በወረቀት መያዝ ለመጥፋት፣ ለመቀደድ እና ለማረጋገጥ መዘግየት ይዳርጋል። ፋይዳፓስ (FaydaPass) ግን እነዚህን ችግሮች በጥራት ይቀርፋል! መረጃዎን በአስተማማኝ እና በዘመናዊ መንገድ ለማጋራት እንዲሁም ለማረጋገጥ ያስችልዎታል።

መተግበሪያውን ያውርዱ፤ ከዚህ ቀደም ካወረዱት ደግሞ ያዘምኑት (Update ያድርጉ)!

ፕሌይስቶር፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp
አፕስቶር፡ https://apps.apple.com/app/id6740314990

19/08/2026

የፋይዳ መታወቂያ ተጠቅማችሁ እንዴት የቴሌብር አካውንታችሁን ደረጃ ማሳደግ እንደምትችሉ በዚህ ቪዲዮ ተመልከቱ።

Address

Bole, Wolosefer, Ethio-China Street. ቦሌ ወሎ ሰፈር ኢትዮ-ቻይና መንገድ
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 18:00
Tuesday 08:30 - 18:00
Wednesday 08:30 - 18:00
Thursday 08:30 - 18:00
Friday 08:30 - 18:00

Telephone

+251912210790

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when National ID Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to National ID Ethiopia:

Shortcuts

Share